በርካታ ወላጆችን ያስጨነቀው የ " ፍራንስ ሌይ " የህፃናት ወተት ጉዳይ ምንድነው ?
ፍራንስ ሌይ ላብራቶሪ የፈረንሳይ ኩባንያ ሲሆን " ፍራንስ ሌይ " የተባለ የህፃናት ወተቶች አምራች ነው።
ይህንን ወተት ወደ " #ኢትዮጵያ " እያስመጣሁ አሰራጫለሁ ያለው " ዶክ ቶክ " የተባለ አስመጪና ላኪ ከሰሞኑን ከህፃናት ወተቱ ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ ሀሰተኛ መረጃ ወላጆች እየተረበሹ መሆኑንና ስራውንም ላይ እክል እንደገጠመው ገልጿል።
የህፃናት ወተቶቹ አለም አቀፍ ደረጃቸዉን የጠበቁ በአውሮፓ ስታንዳርድ የተመረቱ የ CODEX SASO, FDA መስፈርቶችን ያሟሉ ናቸው ያለው ይኸው አስመጪ ድርጅት እነዚህ ምርቶች በአምራች ኩባንያዉ የአሰራር ሂደት መሰረት ለምርቶቹ መለያ ይሆን ዘንድ የማይቀየርና ወጥ የሆነ መለያ ቁጥር (Bar Code) የሚጠቀሙ ናቸው ብሏል።
ይህ ባር ኮድ የምርቱን ትክክለኛነትና የምርቱን አይነት (type of product and type of Sku) ለመግለፅ ይጠቅማል ፤ እንዲሁም እነዚህ የዱቄት ጣሳዎች እንደማንኛዉም ምርቶች የባች ቁጥር (Batch Number) ያላቸዉ ናቸው ይህም የምርቱን ሁኔታ ለመከታተል (Product traceability, production date and time, expire date) ይረዳል ሲል አስረድቷል።
በዚህም ባር ኮድና የምርቱ መጠቀሚያ ጊዜ መካከል ምንም አይነት ግንኙነት የለም ሁለቱም የተለያዩ መረጃዎችን ጥቅሞችን ይይዛሉ፤ አንድ ባር ኮድ የተለያዩ የባች ቁጥር እና የመጠቀሚያ ጊዜን ይይዛል ብሏል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/France-Lait-12-07
@tikvahethiopia

ቄስ በሊና ሳርካ አረፉ።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል " ለቤተክርስቲያንና ለሀገራችን ኢትዮጵያ በረከት የነበሩት ቄስ በሊና ሳርካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ። " ያለ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸው፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም በአጠቃላይ ለወንጌል አማኙ ማህበረሰብ መፅናናት ተመኝቷል።
ቄስ በሊና ሳርካ ከ60 ዓመታት በላይ በወንጌል አማኞች ዘንድ በማገልገል " የወንጌል አርበኛ " የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።
ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተገነግሯል።

በኦሮሚያ_ክልል_የተለያዩ_አካባቢዎች_በየጊዜው_በሲቪል_ሰ_ላይ_በሚፈጸሙ_ጥቃቶች_ምክንያት_የተከሰቱ_መጠነ.pdf
219.6 KB
#OROMIA : በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በየጊዜው በሲቪል ሰዎች ላይ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ምክንያት የተከሰቱ መጠነ ሰፊ ሰብአዊ ቀውሶችን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ።
@tikvahethiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኦሮሚያ_ክልል_የተለያዩ_አካባቢዎች_በየጊዜው_በሲቪል_ሰ_ላይ_በሚፈጸሙ_ጥቃቶች_ምክንያት_የተከሰቱ_መጠነ.pdf
ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጫ ፦
"
- በምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ፣ መነ ሲቡ ወረዳ (ነጆ መንዲ ከተማ)፣ ለታ ሲቡ፣ ቦጂ ድርመጂ (ቢላ ከተማ)፣ ነጆ ከተማ፣ ቆንዳላ ወረዳ፣ ቤጊ ወረዳ፣ ቅልጡ ካራ ወረዳ፤
- በምሥራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ ዴጋ ወረዳ፣ ሳሲጋ ወረዳ፣ ጊዳ አያና ወረዳ፣ ኪረሙ ወረዳ፣ ጉትን ወረዳ፣ ሊሙ ወረዳ፣ ጅማ አርጆ፤
- በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ውስጥ ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ (አሊቦ፣ ጃርደጋ እና ጃርቴ ከተሞች)፣ አሙሩ ወረዳ (አሙሩ ከተማ፣ አገምሳ ከተማ እና ከ10 በላይ ቀበሌዎች)፣ ሆሮ ቡልቅ ወረዳ፣ ጉዱሩ ወረዳ፤
- ወለጋ ዞን ውስጥ ሀዋ ገላን ወረዳ (መንደር 20 እና 21)፤
- በምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ ሜታ ወልቂጤ ወረዳ፣ አደዓ በርጋ ወረዳ፣ ጮቢ ወረዳ፣ ጀልዱ ወረዳ፣ አቡና ግንደበረት ወረዳ፣ ግንደበረት ወረዳ፣
- በምሥራቅ ሸዋ ዞን ውስጥ ቦሰት ወረዳ፣ ዱግዳ ወረዳ፣ ፈንታሌ ወረዳ፤
- በአርሲ ዞን ውስጥ ጀጁ ወረዳ፣ መርቲ ወረዳ፤
- በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ኩዩ ወረዳ ወረጃርሶ ወረዳ፣ ደራ ወረዳ፤
- በኢሉ አባ ቦር ዞን ውስጥ ደርሙ ወረዳ፣ አሊጌ ሰቺ ወረዳ፤
- በደሌ ዞን ውስጥ ጨዋቃ ወረዳ፣ ዳቦ ሃና ወረዳ፣ መኮ ወረዳ፣ ዴጋ ወረዳ
በነዚህ በተዘረዘሩ አካባቢዎች ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ የደረሱ ግጭቶችና ጥቃቶች ያስከተሉት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በሰብአዊ መብቶች መርሆችና ድንጋጌዎች መሰረት እጅግ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት (#grave_violation_of_human_rights) ተብሎ ሊመደብ የሚችል ስለመሆኑ በርካታ አመላካቾች በመኖራቸው፤ የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥቱ ተቀናጅተው በአፋጣኝና በሙሉ ትኩረት በመሥራት ዘላቂ ምላሽ መስጠት የሚሻ ነው። "
(ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#Tigray
መቐለን ጨምሮ የተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች ከ18 ወራት በኋላ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የኃይል ቋት ማግኘት እንደጀመሩ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በመቐለ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰሜን ሪጅን ሠራተኞችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ሰራተኞቹ ከትናንት ማክሰኞ ምሽት ጀምሮ መቐለን ጨምሮ ፦
- መኾኒ ፣
- ውቅሮ፣
- ዓዲግራት፣
- ዓብይዓዲ እና ሌሎች በአካባቢው ያሉ ከተሞች ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የኃይል ቋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት ጀምረዋል ሲሉ ተናግረዋል።
ክልሉ ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የኃይል ቋት ያገኝ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት በጦርነቱ ምክንያት ከሰኔ ወር 2013 ዓ/ም ወዲህ ተቋርጦ ቆይቶ ነበር።
ነገር ግን በዚህ መሃል በትግራይ ክልል ከሚገኝ የኃይል ምንጭ፣ በክልሉ አስተዳደር አስተባባሪነት በውስን መጠን እና መቆራረጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ለሕዝቡ ይቀርብ እንደነበር ተጠቁሟል።
ከ18 ወራት በኋላ የኤሌክትሪክ ኃይል የተመለሰው ትናንት ማክሰኞ አመሻሽ ከ11 ሰዓት ጀምሮ ሲሆን የኤልክትሪክ አገልግሎት በመቐለ እና በተለያዩ የክልሉ ከተሞች መቅረብ መጀመሩ ለነበረው የኃይል ፍላጎት መልስ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል ሲል ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

" እዛ እየሆነ ያለው ድርጊት ይሄ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም። " - ተፈናቃይ በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ባለው የፀጥታ ሁኔታ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቄያቸው ተፈናቅለዋል ፤ ህይወታቸውን ለማትረፍ ሸሽተዋል። እንደ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ዘገባ ተፈናቃይ ወገኖች / ህይወታቸውን ለማትረፍ የሸሹ ወገኖች ሰላምን ፍለጋ 40 ኪሎ ሜትር ድረስ በእግር ታጉዘው ጊዳአያና ወረዳ መግባት ችለዋል። በወረዳው…
" ለሌላው ሰሞነኛ ወሬ ሆኖ ቢያልፍም ለእኛ ለቤተሰቦች ግን ዘውትር ሀዘን እና ጭንቀት ነው " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል
በኦሮሚያ ውስጥ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ፣ ብዙሃንን ከቄያቸው እያፈናቀለ፣ እያስራበ ሰርተው እንዳይበሉ ወጥተድ እንዳይገቡ እያደረገ ያለው ሁኔታ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግለት መልዕክታቸውን የላኩ የቤተሰብ አባላቶቻችን ጠይቀዋል።
በነቀምቴ ከተማ ተወልዶ ያደገና ቤተሰቦቹ ምስራቅ ወለጋ የሚገኙ አንድ የቤተሰባችን አባል፤ " ምንም እንኳን የንፁሃን ግድያ፣ መፈናቀል፣ መንገላታት ለሌላው የአንድና የሁለት ቀን ወሬ/አጀንዳ ሆኖ ቢያልፍም እኛ ቤተሰቦቻችን በችግር ውስጥ ያሉ ግን በየዕለቱ ሀዘን፣ ሰቆቃ፣ ጭንቀት እንደተደራረበብን ነው፤ ይህ ደግሞ ዓመታትን አስቆጥሯል " ብሏል።
" የዜጎች ሞትና ስቃይ በማንነታቸው መጠቃት መንገላታት መዋከብ ከቀናት ዜና እና ከመግለጫ አያልፍም ስቃዩ የደረሰበት፣ ልጁን ያጣ ወላጆቹን ያጣ በብዙ ሀዘን ውስጥ ነው እየኖረ ያለው አሁንም ካለው ሌላ ችግር ሳይደረብ መፍትሄ ይፈለግ " ብሏል።
በቀጣናው ያለው ችግር እየተወሳሰበ ተዋናይ ወገኖችም እየበዙ ተጎጂዎችም ቁጥራቸው እያየለ መምጣቱን ጠቁሟል።
አንድ በአዲስ አበባ ነዋሪነቱን ያደረገ የቤተሰባንች አባል ፤ በወለጋ ባለው ሁኔታ ከዚህ ቀደም ቤተሰቦቹን እንዳጣ ገልጾ፤ ፍትህ እንዳለገኘ፤ ዛሬም የቀሩት ቤተሰቦቹ በችግር ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጿል።
" በጣም የሚያስገርመው ይሄን ሁሉ ጊዜ ያለውን ችግር መፍታት እንዴት አይቻልም መንግስት ዋናው ስራ ይሄ አይደለም ወይ? በመንግስት ውስጥ ሆነው ይሄ ችግር እንዲቀጥል የሚያደርጉ፤ ስልጣን ላይ ያሉ ለጥፋው ጥፋት የሚጠየቁትስ መቼ ነው? " ሲል ጠይቋል።
አሁንም ያለው ችግር እንዲፈታ ንፁሃን ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ድምፁን አሰምቷል።

Photo
" አሁን ላይ ቅድሚያ የተሰጠው ለድምፅ አገልግሎት ነው " - ኢትዮ ቴሌኮም
የኢትዮ ቴሌኮም ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሳይ ውብሸት ፤ ትላንት ምሽት ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል በዚህ ሳምንት በሽረ ከተማ ሙሉ የስልክ አገልግሎት መጀመሩን ተናግረዋል።
አቶ መሳይ ፤ " ሽሬ ሙሉ በሙሉ ጀምሯል። ሰው በደንብ እየተጠቀመ ነው። ባገኘናቸው የኃይል አማራጮች ተጠቅመን አሁን ሙሉ ማህበረሰቡ አገልግሎት ማግኘት ጅምሯል በተለይ ደግሞ ከእሁድ ጀምሮ። በዋናነት ኦፕቲካል ፋይበር መሬት ስር ትራንስሚሽን የምንጠቀምበትን ፋይበር ጥገና ነው ያከናወነው 270 ኪ/ሜ በላይ የሆነ ጥገና ተሰርቶ ኮር ሳይቱን የማገናኘት ስራ ነው የተጠናቀቀው መልሶ ደግሞ ኃይል የመስጠትና ያሉ ጄነሬተሮቻችን ጠግነን ከነዳጅ ኃይል እንዲያገኙ የማድረግ ስራ ነው የተሰራው " ብለዋል።
ለሬድዮ ጣቢያው ቃላቸውን የሰጡ ቤተሰቦቻቸው ሽረ የሚገኙ ነዋሪዎች የስልክ አገልግሎት ከጀመረ ሳምንት እንዳሆነው ገልፀው የጥራት ችግር ግን እንዳለ አመላክተዋል። አንድ በአክሱም ቤተሰቦቹ ያሉ የአክሱም ተወላጅ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጠው ቃል፤ በሙከራ ላይ ባለው ኔትዎርክ በአክሱም ያሉ ቤተሰቦቹን እንዳገኘ ገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም በአድዋ እንዲሁም በአክሱም አገልግሎት ለማስጀመር እየሰራ መሆኑን የገለፁት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ መሳይ ውብሸት ፤ መላውን ትግራይ የስልክ አገልግሎት ለማስጀመር ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
አሁን ላይ ቅድሚያ የተሰጠው ለድምፅ አገልግሎት ሲሆን በቀጣይ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አስተማማኝ ሲሆን የኢንተርኔት አገልግሎት ይታያል ሲሉ ለሬድዮ ጣባያው ተናግረዋል።

#Tigray መቐለን ጨምሮ የተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች ከ18 ወራት በኋላ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የኃይል ቋት ማግኘት እንደጀመሩ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በመቐለ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰሜን ሪጅን ሠራተኞችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ሰራተኞቹ ከትናንት ማክሰኞ ምሽት ጀምሮ መቐለን ጨምሮ ፦ - መኾኒ ፣ - ውቅሮ፣ - ዓዲግራት፣ - ዓብይዓዲ እና ሌሎች በአካባቢው…
ከረጅም ጊዜ በኃላ ሽረ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘቷ ተገለፀ።
ሽረ ከተማ ከረጅም ጊዜ በኋላ ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ማስታወቃቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
@tikvahethiopia
ሽረ ከተማ ከረጅም ጊዜ በኋላ ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ማስታወቃቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
@tikvahethiopia
የሰቆጣ ከተማ ጤና ጣቢያ "ብፁዕ አቡነ በርናባስ ጤና ጣቢያ " ተብሎ እንዲጠራ የከተማው ም/ቤት አጸደቀ።
የሰቆጣ ከተማ ም/ቤት ባካሔደው አስቸኳይ ጉባኤ ነው የሰቆጣ ከተማ ጤና ጣቢያን " በብፁዕ አቡነ በርናባስ ጤና ጣቢያ" በሚል ስያሜ እንዲፀድቅ ያደረገው።
ጤና ጣቢያው በብፁዕ አቡነ በርናባስ የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ስም እንዲሰየም የተደረገበትን ዋነኛ ዓላማ ለም/ቤቱ የተብራራ ሲሆን በዚህም፦
- ብፁዕነታቸው ባለፈው ዓመት ማኅበረሰቡ በጦርነት ምክኒያት ተፈናቅሎ በነበረበት ወቅት ያበረከቱት አስተዋጽኦና መልካም ሥራቸው ሕያው ሆኖ እንዲቀጥል፤
- ብፁነታቸው ሙስሊም፣ ክርስቲያን ዘርና ቋንቋ ሳይለዩ ሁሉም እናቶች፣ ሕጻናት፣ አረጋዊያንና ማኅበረሰብ የሚበሉትና የሚጠጡት አጥተው ሲቸገሩ ካለው ለምነው የሌለው በመስጠት፣ መንግስት ሠራተኞች ለዐራት ወራት ያህል ደሞዝ በመቋረጡ ምክኒያት ሲቸገሩ ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ከባለሃብቱና ከበጎ አድራጊዎች ገንዘብ አፈላልገው በመስጠት ታሪክ የማይረሳው ሥራ በመሥራታቸው፤
- ከሕዝባቸውና ማኅበረሰባቸው ጋር ችግሩን ሁሉ ተጋፍጠው በየቦታው ገንዘብ እያሰባሰቡ፣ ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ላይ ለምዕመናን ትምህርት በመስጠትና በማጽናናታቸው፤
- የጤና ተቋማት እንዳይዘነጉ እና አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ከ160 በላይ እናቶች በጤና ተቋም እንዲወልዱ በማድረጋቸው፤ ያበረከቱትን ሕያው ሥራ እውቅና ለመስጠትና ትውልዱ ከመልካምና ከማይሞት ሥራቸው እንዲማርና የእሳቸውን ፈለግ እንዲከተል፣ በጤና ተቋም አገልግሎት የሚያገኙ አካላት እንዲዘክሩ የሰቆጣ ከተማ ጤና ጣቢያ የሚለው ስም" ብፁዕ አቡነ በርናባስ ጤና ጣቢያ" ተብሎ እንዲሰየም ተደርጓል።
መረጃው የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ነው።

#እንድታውቁት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም የቋሚ ንብረት ሥም ዝውውር አገልግሎት፤ ከትናንት ኀዳር 29 ቀን 2015 ጀምሮ በጊዜያዊነት መታገዱ ተገልጿል።
አገልግሎቱ የታገደው በከተማዋ ህገ ወጥነትን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ሒደት ውጤታማ ለማድረግ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።
ለሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ለሚመለከታቸው አካላትም የተላለፋው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ትዕዛዝ መሰጠቱንም የከተማ አስተዳደሩን ዋቢ አድርጎ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።