TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ጥያቄ ምንድነው ? ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ምላሽስ ? • " እንደዚህ ዓይት ውሳኔ ላይ የተደረሰው አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ኃላፊዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው " - የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ፍቅረስላሴ አካሉ (ለአዲስ ስታንዳርድ) • " ማህበራችን የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አላቀረበም " - ዶ/ር በፍቃዱ ዘለቀ (ለዶቼ…
" የተሰራጨውን የአቋም መግለጫ አላውቀውም " - የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፤ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች ስም የተሰራጨውን አቋም አላውቀውም ብሏል።

ማህበሩ ይህን ያለው #ለኢዜአ በላከው መግለጫ ነው።

ማህበሩ ፤ ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምሀርት ድረስ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎችን በማደራጀት በአምስት ዓላማዎች እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጿል።

ከአምስቱ ዓላማዎች መካከል አንዱ የመምህራን መብትና ጥቅም ማስከበር ነው ያለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲ መምራን ያነሱትን ጥያቄዎች ለትምህርት ሚኒስቴርና ለሚመለክታቸው የፌዴራል መንግስት አካላት እያቀረበ ለመፍትሄው እየሰራ መሆኑን አመልክቷል።

" አንዳንድ ጥያቄዎች በፍጥነት ምላሽ ማግኘት የሚገባቸው መሆኑን " እናምናለን ያለው ማህበሩ " አንዳንዶቹ ደግሞ ጊዜ የሚፈልጉ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል " ብሏል።

ማህበሩ ከሰሞኑን " የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች የአቋም መግለጫ "  በሚል ርዕስ  " ከህዳር 26/2015 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሥራ ማቆም አድማ እናደርጋለን " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ አላውቀውም ብሏል።

እውቅና ያለው የማህበሩ መዋቅር ስም  " የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር "  መሆኑን የገለፀው ማህበሩ ፤ መምህራን ማህበራቸው ጉዳዩን በጥብቅ ይዞ እየሰራ መሆኑን አውቀው የተለመደውን የማስተማር የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት በሙያዊ ኃላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ጥሪውን አቅርቧል።

#ኢዜአ

ማስታወሻ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/74911

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በየትኞቹ አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎት ጀመረ ? ኢትዮ ቴሌኮም ፤ የቴሌኮም አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩና ዳግም ያስጀመረባቸውን አካባቢዎችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል። የቴሌኮም አገልግሎት የጀመረባቸው አካባቢዎች ፦ - አላማጣ፣ - ኮረም፣ - ዓዲ አርቃይ፣ - ጸለምት፣ - ጪሮ ለና፣ - ጎብዬ ቆቦ፣ - ቆቦ ሮቢጥ፣ - ዞብል - ዋጃ ናቸው። #በሌሎችም የቴሌኮም አገልግሎት በተቋረጠባቸው…
#Tigray #EthioTelecom

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ፦

" ሽረ የሚገኘውን ኮር ሳይት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚያስችል ቅኝት ተደርጓል። ሳይቱ ለሁለት ዓመት አግልግሎት ሳይሰጥ እንደመቆየቱ የጎደሉ እቃዎችን ማሟላትን ጨምሮ ሌሎች ስራዎች ሲሰሩ ቆይቷል።

በርብርብ በተከናወነ ስራ 266 ኪሎ ሜትር የፋይበር ጥገና ማከናወን ተችሏል። ጥገናውን ለማጠናቀቅ 6 ኪሎ ሜትር ይቀረናል።

የጥገና ስራው ሲጠናቀቅ ከአስቸኳይ (Emergency) የቴሌኮም አገልግሎት በዘለለ ሰፊው ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲያገኝ ያስችላል።

ከሽረ ቀጥሎ አክሱም እና አድዋም አገልግሎት እንዲያገኙ የማስተላለፊያ መስመር ፍተሻ ጀምረናል። #በቅርቡ በርካታ ከተሞች (ትግራይ ክልል ውስጥ) የቴሌኮም አገልግሎት ያገኛሉ። "

Credit : ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DigitalLottery አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ጥቅምት 22/205 ዓ/ም በብሄራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል። 1.5 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 004159786369 ሆኖ ወጥቷል። 👉 1.5 ሚሊዮን ብር - 004159786369 👉 800 ሺህ ብር - 004412460260 👉 350 ሺህ ብር - 004223166354 👉 200 ሺህ ብር - 004429482613…
#DigitalLottery

አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ህዳር 23 /2015 ዓ/ም በብሄራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል።

1.5 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 005187503482 ሆኖ ወጥቷል።

👉 1.5 ሚሊዮን ብር - 005187503482
👉 800 ሺህ ብር - 005304384029
👉 350 ሺህ ብር - 005255580874
👉 200 ሺህ ብር - 005230182809
👉 160 ሺህ ብር - 005294089297
👉 120 ሺህ ብር - 005114526375

(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል)

@tikvahethiopia
#ኤርትራ #ኦርቶዶክስ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ፓትርያርክ ዘሀገረ ኤርትራ አረፉ።

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 5ኛ ፓትርያርክ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዘጠና ስድስት (96) ዓመታቸው ማረፋቸውን ተሰምቷል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ከሰኔ 6 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ቤተክርስቲያኒቱን በፓትርያሪክነት ሲያገለግሉ ነበር።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
#DashenBank

ዳሽን ባንክ እ.ኤ.አ በ2022  " ዘ ባንከር " በተሰኘውና በፋይናንሺያል ታይምስ ጋዜጣ ስር በሚታተመው መፅሄት በኢትየጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ቀዳሚ ሆኖ በመመረጥ ሽልማት ተቀብሏል።

ባንኩ ይህንን ሽልማት ሲቀበል ለ12ኛ ጊዜ ሲሆን ሽልማቱን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በእንግሊዝ ተገኝተው ተቀብለዋል፡፡

በዲጂታል የባንክ አገልግሎት ዘርፍ በተለይ ባለፈው ዓመት ያሳየው እመርታ ለሽልማት እንዳበቃው ተነግሯል።

ከኢትዮ ቴሌኮምና በፋይንንስ አገልግሎት ዙሪያ ከሚሰሩ ሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር የመስራት አቅም ከመፈጠሩ በላይ አነስተኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎቱን ለማስፋት አስችሎታል፡፡

በባንክ ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚስተዋለው ዕድገት፣ የውጭ ባንኮች እንዲገቡ መፈቀዱና የካፒታል ገበያ መቋቋም እንዲሁም የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭዎች በባንክ አገልግሎት ዘርፍ መሰማራት የሚፈጥሯቻን እድሎች በማጤን ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማምጣት እየሰራ መሆኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ባደረጉት ንግግር አመልክተዋል፡፡

ዳሸን ባንክ ባለፈው ዓመት ፍላተርዌቭ ፣ ቱንስና ኤምኤፍኤስ ከተሰኙ በአፍሪካ በፋይናንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከሚሰሩ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራርሟል። በግል የባንክ ኢንዱስትሪ ዘርፍም የመጀመሪያው የሆነውን ደረጃ 3 ግዙፍ የዳታ ማዕከል ያስገነባው ባለፈው በጀት ዓመት ነበር፡፡

ከ700 ባለይ ቅርንጫፎችን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመክፈት መደበኛና ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለደንበኞቹ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Peace

የሰላም ስምምነቱን በተመለከተ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከሃይማኖት ተቋማት እና ሲቪክ ማህበራት ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በዚህ ውይይት ላይ ምን አሉ ?

- የሰላም ስምምነቱ #የህዝብ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።

- የሰላም ስምምነቱ ፤ ከፍተኛ የሆነ ችግር ላይ ያለውን ህዝብ ለማዳንና ህዝቡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲጠቀም ሰላም እንዲያገኝ ለማድረግ የተደረሰ መሆኑን ገልፀው ሌሎች ጉዳዮች በህገመንግስት መሰረት ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚፈለግላቸው መሆኑን ገልፀዋል። ስምምነቱ ከምንም በላይ ተኩስ የማቆም ጉዳይ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

- የተደረሰው  የሰላም  ስምምነት  ተግባራዊ እንዲሆን እየተሰራ ባለበት በዚህ ወቅት ላይ አሁንም የኤርትራው ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ ኃይል በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ግፍ እየፈፀመ፣ ንብረት እየዘረፈ ፣ እያወደመ መሆኑና ስምምነቱ እንዲደናቀፍ እየሰራ እንደሆነ ገልፀው የፌዴራል መንግስት የህዝቡን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነበት ስላለበት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

- በስምምነቱ መሰረት ሰብዓዊ እርዳታ እና መድሃኒት እየገባ መሆኑን ተናግረዋል። " ስምምነቱ ላይ ድጋፍ በአቸኳይ እንዲገባ የሚል ነገር ነበር በወቅቱ ወዲያው የገባ ድጋፍ አልነበረም አሁን ግን ቀስ በቀስ የሚገባው ሰብዓዊ ድጋፍ እየጨመረ ነው " ብለዋል። እህል እና መድሃኒት ይዘው የሚገቡ ተሽከርካሪዎች እየጨመሩ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ደብረፅዮን ፤ ዓለም አቀፍ እርዳታ አቅራቢዎች በሙሉ ወደ እንቅስቃሴ ገብተዋል ብለዋል።

- ወደ ክልሉ ከሚገባው የሰብዓዊ እርዳታ ጋር በተያያዘ በስምምነቱ መጀመሪያ ሰሞን ላይ አስፈላጊው ስራ በጊዜ ስላላለቀ እና ባለመዘጋጀቱ ወደ ትግበራ እንዳልተገባ አሁን ላይ ግን ሁሉም ዝግጁ መሆኑን ፣ የሚያደናቅፍ ነገር እንደሌለው ፣ በመንገድ ላይ የነበረው በርካታ ፍተሻና የቁጥጥር ጣቢያዎች አሁን መስተካከሉን ተናግረዋል።

- ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ፤ " የተቋረጡት መሰረታዊ አገልግሎቶች መልሰው አልተከፈቱም " ያሉ ሲሆን " በኛ በኩል ሙሉ ዝግጅት አድርገናል #ባንክ#ቴሌኮም እንዲጀምር ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል ባለን አነስተኛ አቅም እየተጠቀምን ብንቆይም መስተካከል ያለባቸው ነገሮች መስተካከል አለባቸው። በፌዴራል አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ እያንዳንዳቸው ተፈትሸው ስራ ለመጀመር ምን ያስፈልጋቸዋል  ?  የሚለው ተጠንቷል። አገልግሎት ወደ ነበረበት ለመመለስ ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል ፤ አሁን የሚቀረው ስርዓት አስይዞ ከፌዴራል አገልግሎት ሰጪ አካላት ጋር በመነጋገር በቅደም ተከተል ማስፈፀም ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኦሮሚያ #ትኩረት በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች አሁንም በቀጠለው የፀጥታ ችግር በርካቶች ህይወታቸው እያለፈ ፣ አካላቸው እየጎደለ፣ ንብረታቸው እየወደመ እንደሚገኝ ቤተሰቦቻችን ጠቁመዋል። ባለፉት ዓመት ህዝቡ በሰላም እጦት ብዙ ቢሰቃይም መፍትሄ ሳይገኝ አሁንም እየተባባሰ በመቀጠሉ ንፁሃን ክፉኛ እየተጎዱ እና ስቃያቸውም እየተባባሰ እንደሚገኝ ነው ቤተሰቦቻችን የገለፁት። ከጥቂት ቀን በፊት…
" የሰው ደም ከፈሰሰ በኃላ የመግለጫ ጋጋታና ሰበር ዜና ለኛ ትካዜ እና ሀዘን እንጂ ጥቅም የለውም " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል

በምስራቅ ወለጋ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሁንም የዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ፤ በርካቶችም ሰላምን ፍለጋ ከቄያቸው እንዲፈናቀሉ እያደረገ ቀጥሏል።

ከጥቂት ቀናት በፊት በአካባቢው ስላለው የፀጥታ ችግር እና እየደረሰ ስላለው ጉዳት ቤተስቦቻቸው በዛው የሚኖሩ የቲክቫህ አባላት በተደጋጋሚ ማሳወቃቸው ይታወሳል።

አሁንም ችግሩ መቀጠሉን የገለፁልን ቤተሰቦቻችን በተለይም በአንገር ጉትን ከፍተኛ ችግር መኖሩን ገልፀው አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል ዛሬ በምስራቅ ወለጋ ፤ በአንገር ጉተን ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ገልፆ የሚመለከተው አካል እንዲደርስ ጥሪ አቅርቧል።

ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ " ወለጋ ላይ ባለው ችግር ወገኖቻችን እየረገፉ ነው " ሲል የከዚህ ቀደሙን አስታውሶ ዛሬም በጉትን ከተማ ዙሪያ ላይ ከፍተኛ ችግር መኖሩን አመልክቷል።

ይህንን ጉዳይ የሚመለከተው አካል እንዲያውቅ ድምፁን ያሰማው የቤተሰባችን አባል ፤ " ህዝብ ረግፎ ከማለቁ በፊት ቢያንስ መከላከያ ገብቶ ያረጋጋልን ፤ የሰው ደም ከፈሰሰ በኃላ የመግለጫ ጋጋታና ሰበር ዜና ለኛ ትካዜ እና ሀዘን እንጂ ጥቅም የለውም " ሲል አስገንዝቧል።

በተጨማሪ ሌላው የቤተሰባችን አባል ፤ በአንገር ጉተን ከፍተኛ ችግር መኖሩንና የህዝቡም ደህንነት አደጋ ላይ በመውደቁ ቶሎ መፍትሄ እንዲፈለግ ፤ ሀገር መከላከያም እንዲገባ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት በአዲስ አበባ ከ4 ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረዉ የመታወቂያ #እድሳት አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል። @tikvahethiopia
#መታወቂያ

የአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ፤ የተፈቀዱ አዲስ የነዋሪነት ምዝገባ እና የመታወቂያ አገልግሎቶችን አሳውቋል።

በከተማ አስተዳደሩ ተቋርጦ የነበረዉ የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ከህዳር 1/2015ዓ.ም ጀምሮ የተፈቀደ መሆኑ ያስታወሰው ኤጀንሲው አሁን ደግሞ ፦

👉 በቤተሰብ ማህደር ተመዝግበው 18 ዓመት የሞላቸው ነዋሪዎች፤

👉 ለህክምና ክትትል የሚፈልጉ እና ህጋዊ የህክምና ማስረጃ የሚያቀርቡ ዜጎች፤

👉 በከተማዉ ፍ/ቤት መብት ለማስከበር የሚያበቃቸዉ የመብት ጉዳይ ኖሯቸዉ #የነዋሪነት_መታወቂያ ለሚያስፈልጋቸዉ ነዋሪዎች አሰራርን በመከተል አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች ሲያሟሉ አገልግሎት እንዲያገኙ መፈቀደኑን ገልጿል።

ይህ የተፈቀደው ከትላንት ዓርብ ህዳር 23/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን ተገልጋዮች ሊኖር የሚችለውን ጫና ከግምት በማስገባት በተረጋጋ ሁኔታ ቀርባድ አገልግሎት እንዲያገኙ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ፤ የአዲስ አበባ ከተማ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 24 #ሙሉ_ቀን በሁሉም የወረዳ ፅ/ቤቶች አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለፀ ሲሆን ነገ እሁድ ህዳር 25 አገልግሎት ዝግ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ሰው አግተው ከፍተኛ ገንዘብ ሊቀበሉ የነበሩ አጋቾች #ተገደሉ

እንደ መተማ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት መረጃ ፦

1ኛ. አጋች ጥጌ አበበ አለሙ
2ኛ. አጋች ባበይ አበባው የተባሉ ግለሰቦች አድራሻቸው መተማ ወረዳ መቃ ቀበሌ ሲሆን ሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ በመሄድ " በመተማ ወረዳ ገንዳውሃ ከተማ #ሱቅ ብትሰሩ ቶሎ መቀየር እና ሀብታም ትሆናላችው " በማለት  የላሊበላ ከተማ ነዋሪ እና በአነስተኛ ጥቃቅን የሚሰሩ ግለሰቦችን ፦

1ኛ. አፀደ መኮነን
2ኛ. እመቤት መለሰ
የተባሉ ግለሰቦችን ተሰፋ በመስጠት በቀላሉ እንደሚከብሩ በመግለፅና ደውሉልን በማለት ስልክ ሰጠው ይሄዳሉ።

በኃላን እነዚህ ግለሰቦች ይህን ተሰፋ በማድረግ ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ በመነሳት ማዕከላዊ ጎንደር ዞን አይከል ከተማ ካደሩ በኃላ በነበራቸው የስልክ ልውውጥ በሁለተኛው ቀን ከአይከል ከተማ  በመነሳት ወደ #ገንዳውሃ _ከተማ ይመጣሉ።

1ኛ.አጋች ጥጌ አበበ አለሙ
2ኛ. አጋች ባበይ አበባው የተባሉት ግለሰቦች ህዳር 21ቀን 2015 ዓ.ም መተማ ወረዳ መቃ ቀበሌ ዝንጀሮ በር ከተባለው ልዩ ቦታ ፦
1ኛ አፀደ መኮነን ከ2 ዓመት ልጇ ጋር ፤ 2ኛ እመቤት መለሰ ከ3 ዓመት ልጇ ጋር ከተቀበሏቸው በኃላ ወደ መቃ ቀበሌ ባርኩርኩር ጎጥ ጫካ ውሰጥ በመውሰድ እያንዳንዳችው ታግታችሁዋል  ብር ካልከፈላችው አትለቀቁም ይሏቸዋል።

አጋቾቹ በአጠቃላይ " 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) ብር ክፈሉ ካልከፈላችው ህይወታችሁን ታጣላችው " በማለት ለቤተሰቦቻቸው የደወሉ ሲሆን ቤተሰቦችም " እኛ ትንሸ ብር ነው ያለን ይህን መክፈል አንችልም " ሲሉ ይመልሳሉ።

አጋቾቹ፤ " ላሊበላ ከተማ ላይ ብር በልመና ስለሚገኝ  የቤተክርሰቲያን ሄዳችሁ ጥላ ይዛችው ለምኑ  ያለዚያ ህይወታቸውን ታጣላችው " በማለት በማስለመን 600,000 ብር ከብዙ ክርክር ካደረሱ በኃላ ሊከፍሉ ሲሉ የመተማ ወረዳ ፓሊስ ከማህበረሰቡ ጥቆማ ይደርሰዋል።

የወረዳው ፖሊስም ፤ ከአማራ ክልል ፓሊሰ ልዩ ሃይል " ኮከብ ክፍለጦር " ጋር በመቀናጀት በደረሰው ጥቆማ መሰረት ታጋቾችን ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ላይ መቃ ቀበሌ ባርኩርኩር ላይ የተኩሰ ልውውጥ በማድረግ ታጋቾችን አስለቅቋል።

አጋቾቹ በፀጥታ ሀይሉ የተገደሉ ሲሆን አምስት ቦንብ መያዙ ተገልጿል።

መገጃው ከምዕራብ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ከተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሰው ደም ከፈሰሰ በኃላ የመግለጫ ጋጋታና ሰበር ዜና ለኛ ትካዜ እና ሀዘን እንጂ ጥቅም የለውም " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በምስራቅ ወለጋ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሁንም የዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ፤ በርካቶችም ሰላምን ፍለጋ ከቄያቸው እንዲፈናቀሉ እያደረገ ቀጥሏል። ከጥቂት ቀናት በፊት በአካባቢው ስላለው የፀጥታ ችግር እና እየደረሰ ስላለው ጉዳት ቤተስቦቻቸው በዛው የሚኖሩ የቲክቫህ አባላት በተደጋጋሚ…
" እዛ እየሆነ ያለው ድርጊት ይሄ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም። " - ተፈናቃይ

በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ባለው የፀጥታ ሁኔታ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቄያቸው ተፈናቅለዋል ፤ ህይወታቸውን ለማትረፍ ሸሽተዋል።

እንደ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ዘገባ ተፈናቃይ ወገኖች / ህይወታቸውን ለማትረፍ የሸሹ ወገኖች ሰላምን ፍለጋ 40 ኪሎ ሜትር ድረስ በእግር ታጉዘው ጊዳአያና ወረዳ መግባት ችለዋል።

በወረዳው በ19 ቀበሌዎች ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ነቀምቴ እና ጊዳ አያና ወደሚገኙ አካባቢዎች ለመሸሽ ተገደዋል።

ባለፈው ሀሙስ ኪረሙ ላይ ከፍተኛ ውድመት የደረሰ መሆኑ ተመላክቷል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ፥ " እዛ እየሆነ ያለው ድርጊት ይሄ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም። " ያሉ ሲሆን ብዙ ህዝብ መፈናቀሉን ፣ ተፈናቃዮች ሰላምን ፍለጋ በሸሹበት ወቅት እየራባቸው ፤ እየደከማቸው በእግር ለመጓዝ መገደዳቸውን ገልፀዋል።

ከተፈናቃዮች መካከል ፤ አንድ አዛውንትም በመንገድ ላይ ደክሟቸው ህይወታቸው እንዳለፈ ያጠቆሙት እኚሁ ነዋሪ " ባለፉት ሳምንታት በነበረው ግጭት ኪረሙ ላይ በአንድ ጉድጓድ ሃያ (20) እና አርባ (40) ሰው ስንቀብር ነበር " ሲሉ የሁኔታውን አስከፊነት ተናግረዋል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት እንዳሳወቁት ፤ ከሰሞኑን በነበረው ሁኔታ የሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን እናቶች ልጆቻቸውን ተሸክመው ጫካ ለጫካ እንዲንከራረቱ፣ እንዲሰቃዩ ሆነዋል።

በኦሮሚያ ክልል መንግስት በተለያዩ ዞኖች አካባቢዎች በተለይም ደግሞ በወለጋ ላለፉት ዓመታት የነበረው የፀጥታ ችግር፣ ጥቃት፣ መፈናቀል፣ ሞት ፣ መፍትሄ ሳያገኝ ዛሬም ድረስ የቀጠለ ሲሆን ችግሩ እልባት ከማግኘት ይልቅ ይበልጥ እየተባባሰ እና እየተወሳሰበ መጥቷል።

የአካባቢው ህዝብ ዘርቶ ማጨድ ፣ ሰርቶ መብላት ፣ እንደልቡ ወጥቶ መግባት፣ ልጆቹን በሰላም ያለስጋት ማሳደግ አልቻለም።

- በተደጋጋሚ ጊዜ ፤ የፀጥታ ችግር ያለባቸው ቦታዎች በግልፅ ተለይተው እየታወቁ ችግርም ሲኖር የድረሱልን ጥሪ እየቀረበ በፍጥነት መፍትሄ መስጠት ለምን አልተቻለም ?

ሁሌም ክቡር የሆነው የሰዎች ህይወት ከረገፈ በኃላ የአንድ ሰሞን ትኩረት ተሰጥቶ ፤ ሰሞነኛ ጩኸት ተጩሆ ከዛ ችግሩ ለምን ይቀጥላል ?

- ስንት ሰው ሲያልቅ ነው ዘላቂ መፍትሄ የሚበጀው ? አሁን እየሆነ ላለው እና ለነበረው ነገር ሁሉ ማነው ተጠያቂ ?

-  ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ ፤ እንመራዋለን የሚሉትን ህዝብ ሰላሙንና ደህንነቱን ማስጠበቅ ያልቻሉ የመንግስት አካላት መቼ ነው በህግ ፊት ተጠያቂ የሚሆኑት ?

-  የተሰቃዩ ፣ የተበደሉ ፣ የሚወዱትን የተነጠቁ እንዴት ነው ፍትህ የሚያገኙ ? የሚሉ ጥያቄዎች መልስ ሊሰጣቸው ይገባል።

@tikvahethiopia