#Tigray
በናይሮቢው የሰላም ስምምነት ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት የትግራይ ኃይሎች አዛዥ ጄነራል ታደሰ ወረደ በናይሮቢው ስምምነት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ባለፉት ቀናት ለኃይሎቻቸው ኦረንቴሽን ሲሰጥ እንደነበር እና ይኸው ኦረንቴሽን በቀጣይ ሁለት ቀን እንቀሚያልቅ ገልፀዋል።
ይህን የገለፁት በክልሉ ለሚገኙት የመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ነው።
ጄኔራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ?
" በናይሮቢው ሰላም ስምምነት ጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመጀመሪያው ከሰራዊቱ ጋር መግባባት ነው ስለ ሰላሙ ጉዳይ አጠቃላይ መግባባት መፍጠር ነው (orientation phase) ። ህዝቡ ጋርም ማለት ነው ፤ ምክንያቱም ህዝቡም ማወቅ አለበት ፤ ሰራዊቱም ማወቅ አለበት።
ቀጥታ ከእኛ ከስራችን ጋር በተያያዘ ፤ ከሰራዊቱ ጋር እየጨረስን ነው ፤ ከሰራዊት አዛዦች እስከታች ድረስ ስለሰላሙ የመግባባት ሁኔታ (ኦረንቴሽን) እየጨረስን ነው ያለነው ፤ ምነልባትም በዚህ ሁለት (2) ቀን ሙሉ በሙሉ እንጨርሳለን እስከታች ድረስ።
ከዛም ቀጥሎ ወደ ሰራዊቱ Disengage አድርጎ / ተላቆ ካለበት ቦታ የውጊያ ግንባሮች የማፍረስ ሰራዊቱ ወደ ተቀመጠለት ቦታ አለ እሱን ጨርሰናል ማን የት ይንቀሳቀሳል የሚለው ወደዛ የማጓጓዝ ጉዳይ ነው ይሄ ደግሞ ተከታትሎ የሚጀምር ነው የሚሆነው ፤ የሎጅስቲክስ አቅማችን ወይም የማጓጓዝ አቅማችን እስከፈቀደ ድረስ በአንድ ጊዜም ልናነሳው እንችላለን ምናልባት የተወሰኑ ቀናት ሊወስድ ይችላል ማጓጓዝ፤ ይሄ ይጀመራል፤ Already #ጀምረነዋል።
የመጀመሪያው ስራ የመግባባት ( #orientation ) ፣ የማሳመን ፣ የመተማመን ሁኔታውን ከጀመርን ጀምረናል ማለት ነው፤ በዛ ነው የጀመርነው፤ ይሄ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በኩልም እንደተጀመረ እየሰማሁ ነው።
ከእኛ በኩል እየጨረስን ነው ያለነው፤ አንድ ከፍተኛ ስራ ይሄ ነው፤ ስምምነቱን ከማድረግ አንፃር፤ why የሚሉ ነገሮችን መመለስ ነው ፤ ሰራዊቱን አንድ አስተሳሰብ አንድ ዕዝ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ በቆየበት ማድረግ ነው ስለዚህ አንዱ ትልቅ ስራ ይሄ ይመስለኛል፤ ጀምረናል ብቻ ሳይሆን እየጨረስን ነው ያለነው። ከዚህ በኃላ የሚቀጥሉት ስራዎች ቀላል ናቸው።
ከእኛ በኩል ፤ #ማንኛውም በትግራይ ውስጥ ያለው የትግራይ ኃይል ከአንድ የኮማንድ ስርዓት ውስጥ ሆኖ የሚንቀሳቀስ ፣ ግዳጅ የሚፈፅም ነው ከዚህ ውጭ የሆነ ኃይል #የለንም ፤ ከዚህ ውጭ የሆነ የታጠቀ የሚባልም ኃይል የለም ፤ ትግራይ ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ ኃይል ተመሳሳይ ነገር ነው ያለው ስለዚህ ከቁጥጥር ውጭ የሚሆን ነገር የሚኖር አይመስለኝም።
የስነምግባር ደንብ ሊሆን ሚችል ሰላሙን ለማስከበር ስምምነቱንም ተግባራዊ ለማድረግ (code of conduct) አውጥተናል እያንዳንዱ ይሄኛውን code of conduct እንዲያውቀው አድርገናል አመራሩም አባሉም ሁለተኛው ስራ ይሄ ነው ከኦረንቴሽን ጋር የተያያዘ ነው።
ኃይል ማንቀሳቀሱ ቀላል ነው የሚሆነው ፤ አቅም ነው የሚወስነው ይሄ የሎጅስቲክስ ጉዳይ ነው ፤ ስለዚህ ትግበራው ተጀምሯል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንዶቹ በሁለቱም ዶክመንቶች ግልፅ ያልሆኑ ነገሮች አሉ more የፖለቲካው ስራ ፈጥኖ ተጀምሮ መፍታት ያለበት/ ሊፈታቸው የሚገባ። በስምምነቱ መሰረት በክልሉ ውስጥ ያለ መስተዳደር አለ ስለዛ ትንሽ የተባለ አለ local መስተዳዳሮች በየዞኑ በየወረዳው በየቀበሌው ያሉ መስተዳደሮች አሉ ስርዓት ያለው ህዝብ የራሱ የአስተዳደር ማዋቅር ያለው ህዝብ ነው ከምስራቅ ይሁን ከደቡብ ከየትኛውም እነዚህ እንደሚቀጥሉ ነው ተስፋ የማደረገው እንጂ እኚህ እንዲፈርሱ አይደለም።
ሰራዊቱ ነው እንጂ disengage የሚያደርገው እንጂ ሲቪል መስተዳደሩን disengage የሚያደርገው የለም ይቀጥላል። የእነዚህን ደህንነት በሚመለከት መሰራት ያለበት ነገር አለ ፤ የቆየ ፖሊስ አለ እንደ አደረጃጀት ፖሊስ አለ እሱ በቀጣይ የpolitical dialogue መፍታት ያለበት ነገር አለ።
አሁን ላይ disengage ከምናደርግባቸው ግንባሮች ዓዲግራት ፣ ማይጨው ... ወዘተ የመሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች ፤ የዞን የመስተዳደር ማዕከሎች ይቅርና እነሱ ጋርም ያሉት አክሱም ፣ ሽረ አይነትም አዲስ መስተዳደር ይቆማል ይፈርሳል ምናም የሚባል ነገር አይደለም ፤ እነዛም reset መደረግ አለበት የሲቪል መስተዳደሩ ፤ የ Poltical Dialogue ይሄን መፍታት አለበት መፍጠን ያለበት ይሆናል ፤ ይሄ በዘገየ ቁጥር ለ Conflict መነሻ ሊሆን ይችላል፤ እነዚህ ዝርዝር ነገሮች አሉ ንፁሁ የ Security Agreement መተግበር ግን ጀምረናል በጣም ጥሩ ሆኖ እንዲተገበር የ Political Dialogue ፈጥኖ መጀመር ያለበት ይሆናል። "
@tikvahethiopia