TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኮንሶ_ዞን፣_በሦስት_ልዩ_ወረዳዎች_የሚገኙ_የሀገር_ውስጥ_ተፈናቃዮች_የሰብአዊ_መብቶች_አያያዝ_ላይ_የተከናወነ.pdf
987.6 KB
#EHRC : የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርት ፦

ኢሰማኮ በደቡብ ክልል ፤ በኮንሶ ዞን እና በአጎራባች 3 ልዩ ወረዳዎች ማለትም በአሌ ልዩ ወረዳ፣ በዲራሼ ልዩ ወረዳ እና በአማሮ ልዩ ወረዳ ለሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በቂ፣ ወቅቱን የጠበቀ እና ተደራሽ የሰብአዊ ድጋፍ ሊቀርብ ይገባል ብሏል።
 
መንግሥት በኮንሶ ዞን እና በአጎራባች ልዩ ወረዳዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተደራጀ የምዝገባ ሥርዓት ማከናወን፣ የወሳኝ ኩነት አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች ሰነዶችን ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ፣ እንዲሁም በክልሉ ለተደጋጋሚ መፈናቀል መንስዔ ለሆኑ ጉዳዮች ዘላቂ መፍትሔ ሊያፈላልግ እንደሚገባ አስገንዝቧል።

(የኢሰመኮ ሙሉ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ሰላም

"ለስምምነቱ ለተግባራዊነት ጠንክረን እንሰራለን"

ትግራይ ክልል ያሉ የሃይማኖት ተቋማት በፕሪቶሪያ የተፈፀመውን የሰላም ስምምነት እንደሚደግፉና ለተግባራዊነቱ እንደሚሰሩ አሳውቀዋል።

ይህን ያሳወቁት በሃይማኖት ተቋማቱ ጉባኤ በኩል በሰጡት መግለጫ ነው።

የሃይማኖት ተቋማቱ፤ ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው ያሉ ሲሆን፥ በባለፈው ጊዜ በጦርነት በደረሰው ጥፋት/ጉዳት፣ በወደመው መሰረተ ልማት እንደሚያዝኑ ገልፀው በደቡብ አፍሪካ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

ስምምነቱንም እንደሚደግፉ እና ለተፈፃሚነቱም ጠንክረው እንደሚሰሩ አሳውቀዋል።

የሃይማኖት ተቋማቱ ጦርነት የጭንቅ እንጂ የመጀመሪያ ሆነ የመጨረሻ አማራጭ ሊሆን እንደማይገባው አስገንዝበው " ጦርነት የማይተካውን የሰው ህይወት የሚበላ፣ ሀብት እና ንብረትን አውዳሚ እንደሆነ ሁሉም ቢገነዘበው አይደለም ጦርነት ወዳዛ የሚገፋፋና ከአንዳንድ ግለሰቦች የሚወጣው መርዛማ ቃላት አስፈላጊ አልነበሩም " ብለዋል።

እስካሁን በጦርነት የጠፋውን በጀት ለሰላም እና ለልማት ቢውል በሀገሪቱ ምን ያህል ለውጥ ሊያመጣ ይችል ነበር ? ብለን ማሰብ አለብን ያሉት የሃይማኖት ተቋማቱ ወደፊትም ችግሮች ቢያጋጥሙ በጦርነት ሳይሆን በሰላማዊ ውይይት፣ በትዕግስት፣ በመቀራረብ፣ በህግ ብቻ ሊፈቱ ይገባል ብለዋል።

የሃይማኖት ተቋማቱ ከአሁን በኃላ ጦርነት እና ወደጦርነት የሚገፋፉ ነገሮች ሊኖሩ እንደማይገባና ሁሉም ያለአንዳች እንቅፋት ለሰላም ለልማት፣ ለሀገር እድገት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበው ከአሁን ሰዓት ጀምሮ የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ መሬት እንዲወጣ ሲሉ አሳስበዋል።

የሃይማኖት ተቋማቱ በመግለጫቸው ከአሁን በኃላ ከሁሉም አጎራባች ክልሎች እንዲሁም ከሀገራት ጋር ስለ #ሰላም እንደሚወያዩ አመልክተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ምናልባትም በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ወይም በሚቀጥለው ሳምንት አጋማሽ ላይ የሰብአዊ እርዳታ እንዲገባ ሊደረግ እንደሚችል የኢትዮጵያ መንግስት ተደራዳሪ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለጋዜጠኞች መናገራቸውን ኤፒ አስነብቧል። የህወሓት ተደራዳሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው የዕርዳታ አቅርቦት መቀላጠፍ በሰላም ንግግሩ እና ስምምነቱ ላይ እምነት እንዲጨምር…
" ... መገናኛ ብዙሃን ጦርነትን ማራገብን ትተው ሰላምን እና መረጋጋትን መዘገብ ይገባቸዋል " - አምባሳደር መለስ አለም

የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሃት ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች በናይሮቢ እያደረጉ የሚገኙት ምክክር አሁንም መቀጠሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ፤ የተለያዩ ሀገራት በሰላም ስምምነቱ ላይ ያላቸውን ደስታ እየገለፁ መሆኑን ገልፀው ወዳጅ ሀገራት የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ ንበረቶችን ወደ አገልግሎት ለመመለስ  ፍላጎታቸውን እያሳዩ ነው ብለዋል።

ቃል አቀባዩ ፤ በስምምነቱ ላይ እንደተገለፀው መገናኛ ብዙኃን ስም ማጥፋትን እና ጦርነትን ማራገብን ትተው ሰላምን እና መረጋጋትን መዘገብ ይገባቸዋል ያሉ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ሁሉም አስተዋፅኦ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

Credit : AMC
Photo : Citizen TV Kenya

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#የፀጥታ_ችግር ሰሞኑን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ አሶሳ ከተማ 96 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ማና ሲቡ ፤ መንዲ ከተማ (ምዕራብ ወለጋ) እና አካባቢው ላይ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መኖሩና ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል። አንድ በአካባቢው ላይ ቤተሰቦቹ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል፤ ከትላንት ወዲያ ሰኞ  ታጣቂዎች ከማለዳ ጀምሮ ቶክስ በመክፈት ወደመንዲ…
#Oromia

በኦሮሚያ ክልል፣ በምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ቤተሰቦቻቸው ያሉ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በግጭት ቀጠናዎች ሰዎች ህይወታቸው እያለፈ መሆኑን፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም መንገድ በማጣታቸው ባሉበት ለመሆን መገደዳቸውን፣ በአንዳንድ ከተሞችም መሰረታዊ አገልግሎት ሰጪዎች መመዘጋታቸውን በመግለፅ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርበዋል።

አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል፤ እናት እና አባቱ በምዕራብ ወለጋ ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጾ በፀጥታው ችግር ሳቢያ ሊያገኛቸው እንዳልቻለ አመልክቷል።

ከታጣቂዎች ጋር ያለው ግጭት የአየር ጥቃትንም ያካተተ እንደሆነ በመግለፅ በግጭቱ ንፁሃን ሰለባ እየሆኑ እንዳለ አመልክቷል።

ባለው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ መናሩንና ዜጎች ሰላም ፍለጋ ቄያቸውን ለቀው እንዳይወጡ እንኳን መንገድ መዘጋቱን ትራንስፖርትም ማግኘት አዳጋች መሆኑን ገልጿል።

ላለፉት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል ያለው የፀጥታ ችግር ይህ ነው የሚባል ዘላቂ መፍትሄ ሳያገኝ ቆይቷል፣ ህዝቡ ሰለምን ተርቧል ፣ ገበሬው ማረስ፣ መላው የወለጋ ህዝብ እድገትን ይሻል፣ ሁሌ የግጭት ቀጠና ሆኖ መቀጠል ለህዝቡ አይገባም አስቸኳይ መፍትሄ ይፈለግ ሲል ይኸው የቤተሰባችን አባል ጥሪ አቅርቧል።

ከጥቂት ቀናት በፊት በምዕራብ ወለጋ በተለይ መንዲና አካባቢው ላይ የፀጥታ ችግር መኖሩን በዚህም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ እንደሆኑና ከአሶሳ - መንዲ የህዝብ ትራንስፖርት እንደተቋረጠ በክስተቱ ንፁሃን ሰለባ እየሆኑ እንዳለ ቤተሰቦቻችን መግለፃቸው ይታወሳል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው የወለጋ አካባቢዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እና የህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ብሎ የፈረጀው " ሸኔ " እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ በሚጠራው የታጠቀ ቡድን መካከል ግጭቶች መሆናቸውን ለማውቅ ችለናል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከ4 ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረዉ የመታወቂያ #እድሳት አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Oromia

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ም/ ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ በኦሮሚያ ያለው ጦርነት በዜጎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል አሉ።

አቶ ጃዋር ፤ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በጮቢ እና በሜታ ወልቂጤ (ምዕራብ ሸዋ)፣ በነቀምቴ (ምስራቅ ወላጋ)፣ ቢላ፣ ናጆ፣ ማንዲ (ምዕራብ ወለጋ) በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል ብለዋል።

ንፁሃን በሚደረገው የተኩስ ልውውጥ ከሚደርስባቸው ጉዳት በተጨማሪ ያለ ልዩነት በሚፈፀመው የአየር ጥቃት የንፁሃንን ጉዳት በከፋ ሁኔታ እየጨመረው ነው ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ጃዋር ካለንበት የፖላቲካ ቀውስ ልንወጣ የምንችለው በኃይል አይደለም ያሉ ሲሆን ይህ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ አልሰራም፤ ዛሬ ወይም ነገ አይሰራም ይልቅ ነገሩን የበለጠ ያባብሰዋል ብለዋል።

በኦሮሚያ የእርስ በርስ ጦርነት መንስኤው የፖለቲካ ልዩነት ነው ሲሉ የገለፁት ምክትል ሊቀመንበሩ የሚፈታው መሪዎች በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው ለመወያየት እና በጋራ ተቀባይነት ያለው ስምምነት ላይ ሲደርሱ ብቻ ነው ብለዋል።

በአንድ የሀገሪቱ ክፍል ሰላም አምጥቶ ሌላው ጥግ እየደማ ዘላቂ ሰላም ሊመጣ ይችላል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው ብለው ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ሰላም ያስፈልጋታል ሲሉ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia