#JIGJIGA
”ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተበረከተው ሽልማት #ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰጠ ትልቅ ክብር ነው” ሲሉ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ዑመር ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ሽልማት በማግኘታቸው ”የእንኳን ደስ አልዎ!” ሰልፍ በጅግጅጋ ስታዲዬም ዛሬ ተካሂዷል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት “ሰዎች 50 ዓመታት ስልጣን ላይ ቆይተው የማያገኙትን ዓለም አቀፍ ሽልማት ክብር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በማግኘታቸው እጅግ ተደስቻለሁ” ብለዋል።
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

በሶማሌ ክልል ህጋዊ እውቅና ይዘው የሚንቀሳቀሱ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው ውይይት አደረጉ። ድርጅቶቹ ትናንት በሶማሌ ክልል ር/መስተዳደር ጽህፈት ቤት ባደረጉት ውይይት በቀጣይ በጋራ የሚሰሩባቸው ጉዳዮች በጹሁፍ የሚያዘጋጁ አምስት አባላት መሰየማቸውን የሶማሌ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ ተወካይ አቶ መሀመድ ኡመር ገልጸዋል፡፡ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተመረጡ አምስቱ አባላት የሚያዘጋጁትን ሰነድ በጋራ ውይይት ዳብሮ ሁሉም ከተቀበሉት በኋላ ወደ ቀጣዩ የስምምነት ምእራፍ ይሸጋገራሉ ተብሏል።
(ኢዜአ)

#UPDATE
ትላንትና ዛሬ በተለያዩ ከተሞች በሞጣ ከተማ የተፈፀመውን ድርጊት የሚያወግዙ ሰልፎች ተደርገዋል። ትላንት በሀረር ከተማ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው አደባባይ በመውጣት ድርጊቱን አውግዟል፤ መንግስት ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ለእምነት ተቋማትም አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ አሳስበዋል። በአሳሳ እና አርሲ ነጌሌ ተመሳሳይ ሰልፍ ተደርጓል። ዛሬ ደግሞ በጅጅጋ፣ ወራቤ፣ ዶደላ፣ ጪናቀሰን፣ ዱብቲ፣ባሌ ሮቤ ድርጊቱን የሚያወግዙ ሰልፎች ተካሂደዋል። በተደረጉት ሰልፎች ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሰው አደባባይ ወጥቶ ድርጊቱን አውግዟል።
#Jigjiga
https://telegra.ph/DW-12-24
PHOTO: YeyaseineWodaj
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Jigjiga : የሶማሊላንድ ም/ ፕሬዝዳንት እና ልዑካቸው ጅግጅጋ ገብቷል።
በሶማሊላንድ ም/ፕሬዝዳንት አብዱረህማን አብዱላሂ ሰይሊኢ የተመራው ልዑክ ዛሬ ከሰዓት ጅግጅጋ መግባቱን የሱማሊ ክልል ማስ ሚዲያ ዘግቧል።
ለም/ፕሬዝዳንቱና ልዑካቸው በቶግወጃሌ ከተማ የሶማሊ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች አቀባበል እንዳደሩጉለቸው ተገልጿል።
የሶማሊላንድ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱረህማን አብዱላሂ ሰይሊኢ እና ልዑካቸው በነገው ዕለት በጅግጅጋ ከተማ የሚመሠረተው አዲሱ የሶማሊ ክልል የመንግሥት ምስረታ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል።
@tikvahethiopia

ዛሬ ከሰዓት በጅግጅጋ ፤ " ጋራድ ዊልዋል ኤርፖርት " በተከፈተ ተኩስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ 3 ሰዎች መቁሰላቸውን ለመስማት ችለናል።
የኤርፖርቱ የፀጥታ ኃይል አባል የሆነው ግለሰብ በከፈተው ተኩስ የክልሉ ፓርላማ አባል ጁዋሪያ ሱብዕስ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ሌሎች ሶስት ሰዎች ቆስለዋል።
በኤርፖርቱ በተከፈተ ተኩስ ሰለባ የሆኑት ተጓዦች እንደሆኑ ተመላክቷል።
የነበረው ሁኔታ ላይ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ሲሆን ምርመራው እንደተጠናቀቀም ውጤቱን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
በጁዌሪያ ህልፈት ሀዘን እንደተሰማው የሶማሊ ክልል ፖሊስ አመልክቷል።
የድርጊቱ ተሳታፊ የሆነው የፀጥታ ኃይል አባል በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል ከተደረገ በኃላ በኤርፖርቱ የነበረው እንቅስቃሴ ወደ መደበኛነት የተመለሰ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ መረጃ ያሳያል።