TIKVAH-ETHIOPIA
" ወደ አዲስ አበባ አትገቡም ተብለን እየተንገላታን ነው ፤ ወደ መጣችሁበትም ተመለሱ ተብለናል " - መንገደኞች መነሻቸዉን ከአማራ ክልል አድርገዉ ወደ አዲስ አበባ የሚሄዱ መንገደኞች በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኀይሎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከላቸዉን ገለፁ። በዚህ ምክንያትን እንግልት እየደረሰባቸው መሆን ጠቁመዋል። ከኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸኖ ከተማ ጀምሮ ወደ አ/አ ለመግባት የሞከሩ…
" አሁንም እዛው ነን " - መንገደኞች
" ወደ አዲስ አበባ መግባት አይቻልም " ተብለናል ያሉ መነሻቸውን ከአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ያደረጉ መንገደኞች አሁንም በዛው ባሉበት እንደሉ ጠቁመዋል።
ከመንገደኞቹ መካከል የባህር ዳር እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ይገኙበታል።
እኚህ ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች ከግቢ እንዲወጡ የተቀመጠው የመጨረሻው ቀን ዛሬ መሆኑን በመግለፅ በርካታ ተማሪዎች ወደ ቤተሰባቸው እየተመለሱ ሳሉ ወደ አዲስ አበባ መግባት አይቻልም በሚል እየተንገላቱ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ ሳቢያ ቤተሰብም መጨነቁን ጠቁመዋል።
መልዕክታቸውን የላኩት የቤተሰባችን አባላት ፤ " በርካታ ባሶች ቆመው ነው የሚገኙት እነዚህ ባሶች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ አቅመ ደካማ አረጋውያንን ይዘዋል ሁላችንም እየተጉላላን ነውና መፍትሄ ይፈለግልን " ብለዋል።
ሌሎች የቤተሰባችን አባላት የሆኑ ተማሪዎችም በተመሳሳይ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ወደ ፊቼ እንዲመለሱ መደረጉን ጠቁመው፤ " ስንት ቀን እንደምንቆይ አናውቅም፤ በጣም ነው የተጨነቅነው ቤተሰብም ተጨንቋል፤ እኛ ተማሪዎች ነን ለምን እንሰቃያለን ? " ብለዋል።
ያነጋገርናቸው ተማሪዎቹና ሌሎችም መንገደኞች በወቅታዊነት ያለውን ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ አስፈላጊው አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርበዋል።
ዛሬ ከሰዓት የኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ቢሮ ምክትል ኀላፊ የሆኑ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ከመገደኞች መንገላታት ጋር በተያያዘ ለአሚኮ በሰጡት ቃል " እኛ ኢሬቻ በዓል ላይ ችግር እንዳይፈጠር ጥብቅ ፍተሻ እያደረግን እንጅ መንገደኞችን አልመለስንም። " ብለዋል።
ም/ቢሮ ኀላፊዉ መንገደኞቹ ስለመመለሳቸዉና መንገዱ ስለመዘጋቱ የሚያውቁት ነገር እንደሌለም ነው የተናግሩት።
@tikvahethiopia

#Irreecha2015
ለ " ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል " ወደ አዲስ አበባ የመጡ እንግዶችን ከተማዋ እያስተናገደች ነው።
በአዲስ አበባ የበዓሉን ድባብ ለመቃኘት በተለያዩ ስፍራዎች ተዘዋውረን እንደተመለከትነው የተለያዩ እንግዳ መቀበያዎች ተዘጋጅተው እንግዶችን እያስተናገዱ ነው።
በየመንገዱም የተለያዩ የባህል አልባሳት ፤ በዓሉን ማድመቂያ ቁሳቁሶች እየተሸጡ ይገኛሉ።
ለዚሁ ለኢሬቻ በዓል የጎረቤት ኬንያ ልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ እየመጣ የሚገኝ ሲሆን ልኡካን ቡድኑ አርቲስቶችንና ሌሎች ታዳሚያንን ያካተተ ነው።
Photo Credit : Vist Oromia , Mayor Office of AA , OBN

Photo
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት በዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ተቋማቱን ለቀው እንዲወጡ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።
ይሁን እንጂ ጦርነትና የፀጥታ ችግር ካለባቸው የትግራይ፣ አማራ እና ኦሮሚያ አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች ወደ ቤተሰብ ለመሄድ እንደማይችሉ እና ውጪ ለመቆየት አቅም እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ገልጿል።
ፈተና እስከሚጠናቀቅ ተማሪዎቹ የሚቀመጡበት ቦታ እንዲመቻችላቸው ህብረቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረቡን የህብረቱ ፕሬዝዳንት ሚካኤል ያቦነሽ ለቲክቫህ ተናግሯል።
ህብረቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ተማሪዎቹ ብሔራዊ አደጋና ስጋት ኮሚሽን ማዕከላት እንዲቆዩ ጥያቄ ቢያቀርቡም ኮሚሽኑ እንደማይችል ገልጿል።
በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲዎች የቴሌቪዥን ማሳያ ክፍሎችና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ተማሪዎቹ የሚቆዩበት መመሪያ እንዲሰጥ ህብረቱ ጠይቋል።
ተማሪዎቹ ለፈተና አሰጣጡ ስጋት እንዳይሆኑ ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት ከማደሪያቸው እንዳይወጡና ምግብም ከተፈታኞቹ በኋላ እንዲመገቡ በማድረግ ችግር እንዳይፈጠር ህብረቱ እንደሚሰራ የህብረቱ ፕሬዜዳንት ለቲክቫህ ገልጿል።
ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17/2015 ዓ.ም በሁሉም የዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምንም አይነት መደበኛ ተማሪ እንዳይገኝ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።
More : @tikvahuniversity

ሆራ ፊንፊኔ - #ማስታወሻ
(በዓሉን ለምታከብሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት)
1. በዓሉ በሚከበርበት #ዙሪያ እና #በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው።
2. ፕሮግራሙ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚዘጉትን መንገዶች በዚህ ይመልከቱ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/73985?single
3. በዓሉን ለማክበር ለሚመጡ ከለሊቱ 11፡00 ጀምሮ ፦ የአንበሳ ፣ የሸገር የድጋፍ ሰጪ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ አውቶብስ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣሉ። ከአባኪሮስ አደባባይ፣ ከአያት አደባባይ፣ ከቱሉዲምቱ አደባባይ፣ ጎሮ አደባባይ፣ አዲሱ ገበያ፣ ከቁስቋም፣ ከሳንሱሲ፣ ከአየር ጤና አደባባይ፣ ከጀሞ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።
4. በዓሉን ስታከብሩ ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሳችሁን ስልክ ፣ አይፓድ ፣ የፎቶ እና ቪድዮ ካሜራችሁን ሌላም የምትይዟቸው ንብረቶቻችሁን ሳትዘናጉ በአግባቡ ጠብቁ።
5. የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት / ማንኛውም አይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ መረጃ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እንዲሁም 0111110111፣ 0111264359፣ 0111010297 መጠቀም ይቻላል።
#የኮቪድ19_መከላከያዎችን_ይተግብሩ!
#TikvahFamily🫶
#HappyIrreecha 🇪🇹 🖤❤️🤍

ፕሬዝዳንት ካቦሬ በወታደሮች ታስረዋል። የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት በሀገሪቱ ወታደሮች መታሰራቸው ተነግሯል። ፕሬዝዳንት ሮች ካቦሬ የታሰሩት በአማጺ ወታደሮች ሲሆን፤ በሀገሪቱ መዲና ኡጋዱጉ ባለ አንድ ወታደራዊ ማዘዣ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል። የቡርኪና ፋሶ መንግስት በትናንትናው ዕለት የወታደሮቹ እንቅስቃሴ መፈንቅለ መንግስት አለመሆኑን ገልጾ ነበር። በቡርኪና ፋሶ ወታደሮች ውስጥ ጥያቄ እንዳነሱ የሚነገርላቸው…
መፈንቅለ መንግስት - በቡርኪናፋሶ !
" መፈንቅለ መንግሥት " በማደረግ ስልጣን የያዙት የቡርኪናፋሶ መሪ መፈንቅለ መንግሥት ተደረገባቸው።
የቡርኪናፋሶ የጦር መኮንኖች ትላንት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ሌተናል ኮሎኔል ፖል ሄንሪ ዳምቢባ ከሥልጣን መወገዳቸውን አስታውቀዋል።
የቡድኑ መሪ ሻምበል ኢብራሂም ትራኦሬ የሚባሉ ሲሆን ባሰሙት ንግግር የወታደራዊ መሪ ሌትናል ኮሎኔል ዳምቢባ ከመሪነት የተወገዱት፣ በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱትን አማጺያንን በአግባቡ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ነው። ላልተወሰነ ጊዜ ሁሉም ድንበሮች ዝግ እንደሚሆኑና የትኛውም አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መከልከሉን አሳውቀዋል።
አሁን ከሥልጣን መወገዳቸው የተገለጸው ዳምቢባ የሚመሩት ቡድን ባለፈው ዓመት ጥር ላይ ነበር በሕዝብ የተመረጠውን አስተዳደር በመፈንቅለ መንግሥት ገልብጦ ወደ ሥልጣን የመጣው። በወቅቱ ወታደራዊ ቡድኑ መንግሥት የአማፂያንን ጥቃት ማስቆም አልቻለም በሚል ነበር መፈንቅለ መንግሥት ያደረገው።
ትናንት ምሽት ላይ ከ20 በላይ የሚሆኑ አብዛኞቹ ፊታቸው የተሸፈነ የታጠቁ ወታደሮች በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የቡድኑ መሪ ናቸው በተባሉት ትራኦሬ የተፈረመ መግለጫ አቅርበዋል።
መግለጫው ፤ " እየተባባሰ የሚሄድ ችግር በገጠመን ጊዜ ዳምቢባ በደኅንነት ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ በተደጋጋሚ ሞክረናል፤ ነገር ግን የዳምቢባ ተግባር ለማድረግ ካቀድነው ውጪ በመሆኑ አሁን ከሥልጣን እንዲወገድ ወስነናል " ብሏል።
ከዚህ በኋላም በመላዋ አገሪቱ ከምሽት 3 ሰዓት እስከ ንጋት 11 የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ የተጣለ ሲሆን፣ ሌተናል ኮሎኔል ዳምቢባ የት እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።