TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Irreecha2015

የ2015 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል መስከረም 21 " ሆራ ፊንፊኔ " ፤ መስከረም 22 በቢሾፍቱ " ሆራ ሃርሰዴ " እንደሚከበር የኦሮሞ አባ ገዳዎች በዛሬው ዕለት አስታውቀዋል፡፡

@tikvahethiopia
#Irreecha2015 #እንድታውቁት

ነገ መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚከበረውን የ2015 የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ተከትሎ በዓሉን ለማክበር የሚመጡ ከለሊቱ 11፡00 ጀምሮ ፦
- የአንበሳ
- የሸገር
- የድጋፍ ሰጪ
- የፐብሊክ ሰርቪስ አውቶብስ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

እንደ ቢሮው መረጃ ፦

👉 ከአባኪሮስ አደባባይ፣
👉 ከአያት አደባባይ፣
👉 ከቱሉዲምቱ አደባባይ፣
👉 ጎሮ አደባባይ፣
👉 አዲሱ ገበያ፣
👉 ከቁስቋም፣
👉 ከሳንሱሲ፣
👉 ከአየር ጤና አደባባይ
👉 ከጀሞ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።

@tikvahethiopia
#Irreecha2015

ለ " ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል " ወደ አዲስ አበባ የመጡ እንግዶችን ከተማዋ እያስተናገደች ነው።

በአዲስ አበባ የበዓሉን ድባብ ለመቃኘት በተለያዩ ስፍራዎች ተዘዋውረን እንደተመለከትነው የተለያዩ እንግዳ መቀበያዎች ተዘጋጅተው እንግዶችን እያስተናገዱ ነው።

በየመንገዱም የተለያዩ የባህል አልባሳት ፤ በዓሉን ማድመቂያ ቁሳቁሶች እየተሸጡ ይገኛሉ።

ለዚሁ ለኢሬቻ በዓል የጎረቤት ኬንያ ልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ እየመጣ የሚገኝ ሲሆን ልኡካን ቡድኑ አርቲስቶችንና ሌሎች ታዳሚያንን ያካተተ ነው።

Photo Credit : Vist Oromia , Mayor Office of AA , OBN

@tikvahethiopia