TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ከግንቦት 15 እስከ 20/2014 ዓ.ም በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙ ሰመራ እና አጋቲና ካምፖች በመባል በሚታወቁ ቦታዎች ውስጥ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያይዞ " ለደኅንነታቸው ጥበቃ እና በወንጀል ጥርጣሬ የሚፈለጉ ሰዎችን ለመለየት " በሚል ምክንያት ከትግራይ ክልል አዋሳኝ ከሆኑ 3 የአፋር ክልል ወረዳዎች ፦ - ከአባላ - ከኮነባ - ከበረሃሌ…
#Afar

በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ በሚገኝ የማቆያ ካምፕ ውስጥ #ያለፈቃዳቸው ተይዘው ከነበሩት የትግራይ ተወላጆች መካከል የተወሰኑት በአውቶብሶች እና የደረቅ ጭነት መኪኖች ተሳፍረው ወደ ቀደመ መኖሪያቸው እየተወሰዱ እንደሆነ መግለፃቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

በሺዎች የሚቆጠሩት የትግራይ ተወላጆች ከአፋሯ አብኣላ ተይዘው ወደ ሰመራ ተዘዋውረው የነበረ ሲሆን  ከ8 ወራት እስር በኋላ ወደ አብኣላ እየተመሰሉ መሆኑን ተናግረዋል።

በሰመራ ተይዘው የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን "በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ ሕገ ወጥ እና የዘፈቀደ እስር በመሆኑ በአፋጣኝ ሊለቀቁ ይገባል ብሎ ነበር።

https://t.iss.one/tikvahethiopia/71528?single

የትግራይ ተወላጆቹ ቀደሞ ወደሚኖሩበት የመኖሪያ ስፍራቸው እንዲመለሱ እያመቻች የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት (OCHA Ethiopia) መሆኑ የተነገረ ሲሆን ድርጅቱ ሰዎቹን " የአገር ውስጥ ተፈናቃይ (IDP) " ሲል ገልጿቸዋል።

ዜጎችን ወደነበሩበት ቦታ የመመለሱ ስራ በሚቀጥሉት ሳምንታት እንደሚቀጥልም ገልጿል።

ነገር ግን ተመድ ባሰራጨው መረጃ ላይ በርካቶች በቃል አጠቃቀሙ ላይ ያለቸውን ተቃውሞ የገለፁ ሲሆን እነዚህ ተይዘው የነበሩት ዜጎች " ያለአንዳች ፍላጎታቸው በመውሰድ ነው " እንጂ የውሥጥ ተፈናቃይ አይደሉም ብለዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩት እዚህ ዜጎች ለወራት ተይዘው በቆዩበት ካምፕ ውስጥ የምግብ እና ሌሎች አገልግሎቶች ችግሮች እንደነበሩባቸው የተናገሩ ሲሆን ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋልጠው መቆየታቸውን እንደገለፁለት ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ለሰሜን ኢትዮጵያ ችግር ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ለመፈለግ እና ችግሩን በሰላማዊ ድርድር ለመቋጨት በፌዴራሉ መንግስት የተቋቋመው " የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ " ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በመግለጫው ላይ ከተጠቀሱ #ወሳኝ ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል ፦

• ኮሚቴው ባደረገው ውይይት የትግራይ፣ የአፋር፣ የአማራ ክልል አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑ ዜጎች በእለት ተእለት ኑሮዋችው ላይ እየገጠማቸው ያለውን ችግር መቀረፍ እንደሚገባ ፤ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተማማኝ እና ዘላቂ በሆነ መንገድ ለማድረስ ይቻል ዘንድ ፣ እንዲሁም የመሰረተ ልማት እና የመሰረታዊ አገልግሎቶችን ዳግም ስራ ለማስጀመር አስቻይ የሆነ ሁኔታ በፍጠነት ለመፍጠር ፤ #የተኩስ_አቁም_ስምምነት ላይ በአጭር ጊዜ ላይ መድረስ እንደሚገባ አጽኖት ሰጥቷል።

• ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት ሊያደርስ የሚችል እና ለቀጣይ የፖለቲካ ውይይቶች መሰረት የሚጥል የሰላም ምክረ ሃሳብ ላይ ውይይት በማድረግ የምክረ ሃሳብ ሰነድ አጽድቆዋል።

• የሰላም ምክረ ሃሳቡ በተቻለ ፍጥነት ለአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ወኪል እንዲቀርብ ወስኗል።

• ወደተኩስ አቁም ስምምነት ሲገባ በሚፈጠረው አስቻይ ሁኔታ፣ መሰረታዊ አገልግሎቶችን #በተቻለ_ፍጥነት መልሶ ማቅረብ ይቻል ዘንድ፣ አስፈላጊ ቅደም ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልጿል።

• የአፍሪካ ህብረትም የሰላም ንግግሩ በአስቸኳይ ተጀምሮ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ይቻል ዘንድ፣ የሰላም ንግግሩ የሚካሄድበትን ቦታ እና ጊዜ በፍጠነት ወሰኖ ንግግሩ እንዲጀመር፣ ይህን ማድረግ ይቻል ዘንድ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሆነ ገምግሟል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Egypt

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በደረሰው ጉዳት የተሰማትን ሐዘን ገለፀች።

በዛሬው ዕለት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ቀናት በምእመናን እና በሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰው ጉዳት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ሐዘን ላይ እንደጣለ ገልጸዋል።

የደረሰውን ጉዳትም "ልብ ሰባሪ ነው" ሲሉ ገልፀዋል።

"የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ሐዘን ላይ ስለሆነች የሀዘናቸው ተካፋይ መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን" ብለዋል።

ሰሞኑን በግብፅ ቤተክርስቲያን በደረሰ እሳት አደጋ 41 ምዕመናን ህይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።

በሌላ በኩል በዛሬው መግለጫቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርስትያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን የህክምና ጉዳይ አንስተዋል።

"ቅዱስነታቸው በውጭ ሀገር የሚያደርጉትን ህክምና አጠናቀው በሰላም ወደ ክቡር መንበራቸው በመመለስ የተለመደ ቡራኬያቸውን ይሰጡናል ብለን እናምናለን፤  እንጸልያለን" ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ቤተክርስቲያኗ 3ኛው የሕዳሴ ግድብ የውሃ መሙላት በመገለጹ ታላቅ ደስታ እንደተሰማት ገልፃ፤ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አላችሁ ብላለች።

ሃሳቡ ከተጠነሰሰበት ጊዜ ጀምሮ ተግባር ላይ እስኪውልና 3ተኛ የውሃ ሙሌት እስከሚከናወን ድረስ ሥራውን ለመሩ ፣በሥራው ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናዋን አቅርባለች።

ለወደፊቱም ከጸሎት ጀምሮ የሚጠበቅባትን እንደምታደርግ ገልፃለች።

@tikvahethiopia
የልጁን ህይወት አትርፎ ህይወቱ ያለፈው አባት !

የልጁን ሕይወት ለማዳን ከጀልባ ላይ የዘለለው እንግሊዛዊ አስክሬኑ ጣልያን ተገኘ።

ዛሬ ጥዋት ቢቢሲ በደረገፁ አንድ አሳዛኝ ክስተት አጋርቷል።

አረን ቻዳ የተባለ እንግሊዛዊ ልጁን ለመታደግ ከጀልባ ከዘለለ በኋላ ለሳምንታት ጠፍቶ አስክሬኑ ጣልያን ውስጥ ተገኝቷል።

አረን ባለፈው ወር " ጋርዳ " የተባለ ባሕር አካባቢ ከትዳር አጋሩና ከሁለት ልጆቹ ጋር እየተንሸራሸረ ነበር። ሽርሽሩ ተዘጋጅቶ የነበረው የአረንን 52ኛ ዓመት ልደት ለማክበር ነበር።

ቤተሰቡ ጀልባ ተከራይቶ በባሕር እየተጓዘ ሳለ  የአረን ልጅ " ሊሞን " የተባለ ሪዞርት አካባቢ ችግር ገጠመው። አባትም ልጁን ለማዳን ከጀልባው ከዘለለ በኋላ አስክሬኑ ከሊሞን በ800 ሜትር ርቀት፣ በ316 ሜትር ጥልቀት እንደተገኘ የነፍስ አድን ሰራተኞች ገልጸዋል።

#ልጁን_ካዳነ በኋላ ውሃ ውስጥ መስመጡት የተገለፀው አረን  " የሰመጠው አንዳች ሕመም ስላለበት ይመስለኛል " ሲል አንድ ነፍስ አዳን ሰራተኛ ገልጿል።

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የደቡብ ክልል ዕጣፋንታ ምን ይሆን ? መንግስት ክልሉ በክላስተር ተከፍሎ በአጎራባች ያሉ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች አንድ ላይ በመሆን ሁለት አዲስ ክልል እንዲመሰርቱ አቅጣጫ አስቀምጧል። ይህን አቅጣጫ ከተትሎም የዞን እና ልዩ ወረዳ ም/ቤቶች በየም/ቤቶቻቸው በመሰባሰብ በቀረቡላቸው የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ውሳኔ አሳልፈዋል፤ ውሳኔያቸውንም ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት አስገብተዋል። አዎ! በመንግስት አቅጣጫ መሰረት…
* ዛሬ

የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባውን ያካሂዳል።

አስቸኳይ ስብሰባውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ነው የሚካሄደው።

በዚህም የአስቸኳይ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

ከዛሬው አስቸኳይ ስብሰባ ቀደም ብሎ ትላንት ነሐሴ 11 የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ከአስቸኳይ ስብሰባው አጀንዳዎች ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ቋሚ ኮሚቴዎቹ ፦
- የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ፣ 
- የመንግሥታት ግንኙነት ፣ የዲሞክራሲያዊ አንድነትና የሕገ መንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ፣
- የድጎማና የጋራ ገቢዎች ድልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ እና
- የሕገ መንግሥት ትርጉምና ውሳኔ አፈጻጸም ክትትል ቋሚ ኮሚቴ ሲሆኑ የተወያዩባቸውን አጀንዳዎች ተከትሎ ለም/ቤቱ የውሳኔ ሃሳቦችን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የዛሬውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ተከታትለን እናሳውቃለን።

ፎቶ ፦ የፌዴሬሽን ም/ቤት

@tikvahethiopia
#ኮማንድ_ፖስት

በጉራጌ ዞን በማንኛውም ቦታ ማንኛውም አይነት መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆነ ስብሰባ፣ ውይይት ማካሄድ ተከለከለ።

በተጨማሪ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጥሏል።

ውሳኔው የተላለፈው በዞኑ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አስቸኳይ ስብሰባውን ካካሄደ በኃላ መሆኑን ከወልቂጤ ከተማ ኮሚኒኬሽን ያወጣው መረጃ ያሳያል።

በዚህም ኮማንድ ፖስቱ ፦

- ከዛሬ ነሀሴ 12 ጀምጎ በዞኑ በማንኛውም ቦታ ማንኛውም አይነት መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆነ ስብሰባ፣ ውይይት ማካሄድ ከልክሏል።

- በመንግሥት የስራ ሰአት የቢሮ ሀላፊም ይሁን ባለሙያ በቢሮ አለመገኘት እንደማይችል አሳስቧል።

- የንግድ ሱቆችና ተቋማትን ያለምንም ምክንያት መዝጋትም ከልክሏል።

- ማንኛውም ሰልፍና መሰል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ከልክሏል።

- የሞተር ሳይክል እንቅክቃሴ እስከ ምሽት 1 ሰአት ብቻ እንዲሁም የባጃጅ እንቅስቃሴ እስከ ምሽት 2 ሰአት ድረስ ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ አዟል።

ኮማንድ ፖስቱ የተላለፉትን ትእዛዛት በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቁን በወልቂጤ ከተማ ኮሚኒኬሽን ገፅ ላይ የሰፈረው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* ዛሬ የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባውን ያካሂዳል። አስቸኳይ ስብሰባውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ነው የሚካሄደው። በዚህም የአስቸኳይ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል። ከዛሬው አስቸኳይ ስብሰባ ቀደም ብሎ ትላንት ነሐሴ 11 የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ከአስቸኳይ ስብሰባው አጀንዳዎች…
#Update

ፌዴሬሽን ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጧል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን አንደኛ ዓመት የስራ ጊዜ 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡

ም/ቤቱ በስብሰባው ከሚወያይባቸው አጀንዳዎች መካከል በዋነኝነት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ስር ያሉ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች #በጋራ_ክልል_ለመመስረት ያቀረቡት ጥያቄ ላይ ሲሆን ጥያቄውን መርምሮ #ያፀድቃል ተብሏል።

ምክር ቤቱ በሌሎች ጉዳዮችም ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ በሚገኝ የማቆያ ካምፕ ውስጥ #ያለፈቃዳቸው ተይዘው ከነበሩት የትግራይ ተወላጆች መካከል የተወሰኑት በአውቶብሶች እና የደረቅ ጭነት መኪኖች ተሳፍረው ወደ ቀደመ መኖሪያቸው እየተወሰዱ እንደሆነ መግለፃቸውን ቢቢሲ አስነብቧል። በሺዎች የሚቆጠሩት የትግራይ ተወላጆች ከአፋሯ አብኣላ ተይዘው ወደ ሰመራ ተዘዋውረው የነበረ ሲሆን  ከ8 ወራት እስር በኋላ ወደ አብኣላ እየተመሰሉ…
" ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ መጀመሩን በበጎ እቀበለዋለሁ " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙት አጋቲና እና ሰመራ ካምፖች የነበሩ ሰዎች ወደ ቀዬአቸው መመለስ መጀመር እንዲሁም የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱን በበጎ እንደሚቀበለው ገልጿል።

ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በአፋር ክልል፣ ሰመራ ከተማ የሚገኙትን አጋቲና እና ሰመራ ካምፖች በተመለከተ ያካሄደውን ክትትል እና ያወጣውን ሪፖርት አስታውሰዋል።

ይህንኑ ተከትሎ በካምፖቹ የነበሩ ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው የመመለሱ ተግባር መጀመር እና የባንክ አገልግሎት ማግኘትን ጨምሮ ሌሎች እየተደረጉ ያሉ ሰብአዊ ድጋፎችን ኮሚሽኑ በበጎ እንደሚመለከተው ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ በአማራ ክልል፣ ወሎ ይገኛሉ ያላቸውን የጃራ እና የጃሬ ካምፖች በተመለከተ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ ፤ ከአስተዳደራዊ እና የፀጥታ አካላትም እያሰባሰበ ያለውን መረጃ የሚያካትት ሪፖርት በቅርቡ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ዶ/ር ዳንኤል ገልፀዋል።

ማስታወሻ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/71528?single

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ፌዴሬሽን ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጧል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን አንደኛ ዓመት የስራ ጊዜ 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡ ም/ቤቱ በስብሰባው ከሚወያይባቸው አጀንዳዎች መካከል በዋነኝነት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ስር ያሉ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች #በጋራ_ክልል_ለመመስረት ያቀረቡት ጥያቄ ላይ ሲሆን ጥያቄውን መርምሮ…
#Update

12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 12ኛ ክልል እንዲቋቋም የሚያስችል ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወስኗል።

ምክር ቤቱ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስር የነበሩ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል እንዲደራጁ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወስኗል።

ሕዝበ ውሳኔ የሚያካሂዱት ፦
- የወላይታ ዞን፣
- የጋሞ ዞን፣
- የጎፋ ዞን፣
- የደቡብ ኦሞ ዞን፣
- የጌዴኦ ዞን፣
- የኮንሶ ዞን፣ እንዲሁም
- የደራሼ ልዩ ወረዳ፣
- የአማሮ ልዩ ወረዳ፣
- የቡርጂ ልዩ ወረዳ፣
- የኧሌ ልዩ ወረዳ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ናቸው።

ቀሪዎቹ የሀድያ ዞን ፣ ሀላባ ዞን ፣ ከምባታ ጠንባሮ ዞን፣ ጉራጌ ዞን ፣ ስልጤ ዞን እና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ይቀጥላሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia