TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update ብርጋዴር ጀነራል #ክንፈ_ዳኘው በቁጥጥር ስር የዋሉት #በትግራይ ክልል ልዩ ፖሊስ ነው።

via-etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም🔝

የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር #በትግራይ_ክልል ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አክሱም ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክሱም ሲደርሱ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር እና ከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር አብረሃም ተከስተን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል ቆይታቸው በዓየርላንድ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ይጎበኛሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው። በተጨማሪም በሽረ እንደስላሴ የሚገኝ የስደተኛ ጣቢያንም ይጎበኛሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሰመኮ

EHRC / ኢሰመኮ #በትግራይ_ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር ተያይዞ በሲቪል ሰዎች ላይ እንግልት እና እስር ፣ የንግድ ቤት መዘጋት ፣ ብሎም በሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መከሰቱንና ሕይወት መጥፋቱን፣ እንዲሁም በታሳሪዎችና በምርኮኞች ላይ የሚደርስ ኢሰብአዊ አያያዝ፣ በስደተኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ሕጻናትን ለውትድርና መጠቀም የሚያመላክቱ መረጃዎች እጅግ የሚያሳስበው መሆኑን ገልጿል።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia