TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጾመ_ፍልሰታ

የ2014 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታን በተመለከተ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትከዋሽንግተን ዲሲ፤ ሰሜን አሜሪካ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦

" ሁላችንም እንደምንገነዘበው በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት ፍጹም ሰላም ያላት ሀገር እንድትኖረው ነው፤ ይህ ትክክለኛ ፍላጎት ነው፡፡ ይሁንና ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም ነገር ስለማይሆን ፍጹም ሰላም በሀገር ሰፍኖ ሕዝባችን እግዚአብሔር በሰጠው ምድር በፍቅር፣ በአንድነት በነጻነትና በእኩልነት እንዲኖር ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ በዚህ ወቅት የቅድስት ድንግል ማርያምን ጸሎትና ስእለት ተማኅፅኖና አስተበቊዖት አጋዥ አድርገን በልዩ ሱባዔ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ በንሥሐ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ ነዳያንን በመርዳትና ቅዱስ ቊርባንን በመቀበል እሱን መማፀን ይኖርብናል፡፡

... በሀገራችን የተከሠቱት ያላስፈላጊ ግጭቶችን በድርድር ለመፍታት እየተሞከሩ ያሉ አንዳንድ የሰላምና የውይይት ድምፆች ተስፋ ሰጪ ስለሆኑ ሥር ሰደው፣ በተግባር ተተርጉመው፣ ለተጐዳው ሕዝባችን መጠገኛ ይሆኑ ዘንድ፣ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ በዚህ ዙርያ በሱባዔው ወቅት ወደ እግዚአብሔር አቤት በማለትና ሂደቱን በመደገፍ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ፣ መንግሥትም ሆነ የዓለም አቀፉ ማኅበረ ሰብ በዚህ በጎ ሐሳብ እንዲገፉበትና ሕዝባችንንና ሀገራችንን ከጥፋት እንዲታደጉ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን የሰላም፣ የሥርየት፣የፍቅር፣ የአንድነት ጾም ያድርግልን።

ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
👍802296🙏99🥰29😢11👏5👎2