TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ሁለቱም ወገኖች ሰላም፣ ጸጥታና የኢትዮጵያ መረጋጋት ምኞታቸው መሆኑን ገልፀውልኛል " - ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ

በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የመንግስትን እና የህወሃትን አመራሮችን ማነጋገራቸውን ካስታወቁ በኋላ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ኦባሳንጆ ሁሉም ወገኖች ወታደራዊ ፍልሚያውን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል፡፡

ከመንግስትም ሆነ ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀው ህወሃት በኩል የሰላም ፍላጎቶች መኖራቸውን የገለጹት ከፍተኛ ተወካዩ ‘የሰላም መንገዱ ምን ይሁን’ የሚለው ግን ልዩነታቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የአፍሪካ መሪዎችና ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ሕብረቱ የጀመረውን የማሸማገል ጥረት እንዲደፉ እና ግጭቱን ሊያባብሱ ከሚችሉ ነገሮች እንዲቆጠብም ኦባሳንጆ ጥሪ አቅርበዋል።

ኦባሳንጆ፥ "ሆን ተብሎም ይሁን ባለማወቅ ግጭቱን የሚባብሱና ወደከፋ ደረጃ ከሚያደርሱ ንግግሮች መቆጠብ ያስፈልጋል" ብለዋል ።

ኦባሳንጆ፤ ውጊያው ከቆመ የንግግር ዕድል እንደሚኖር የገለጹ ሲሆን አሁን ባለው ሁኔታ ውጊያ እየተደረገ ግን ለመነጋጋር የሚመች እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ኦባሳንጆ ፥ የኦሮሚያ እና አማራ ክልል አመራሮችን ማግኘታቸውን በመግለጫቸው ላይ የገለፁ ሲሆን በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የአፋር ክልል አመራሮችን እንደሚያገኙ አሳውቀዋል።

ኦባሳንጂ ይህ የማሸማገል ስራ እንዲሳካ ቁርጠኛ እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን ፦
- #የኬንያ
- #ኡጋንዳ
- #ጅቡቲ
- #ደቡብ_ሱዳን
- #ሶማሊያ እና ሱዳን መሪዎችን ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አስማሚ ሁኔታ ይፈጠራል ብዬ አስባለሁ ያሉት ኦባሳንጆ ሁለቱም ወገኖች ሰላም፣ ጸጥታና የኢትዮጵያ መረጋጋት ምኞታቸው መሆኑን እንደገለጹላቸው አሳውቀዋል።

Credit : #Al_AIN
Pic : AU

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በጎረቤታችን ሶማሊያ እየተካሄደ በሚገኘው ምርጫ የ2ኛው ዙር ድምፅ አሰጣጥ ሂደት አብቅቷል ፤ ይህን ተከትሎ የድምጽ ቆጠራው ይካሄዳል። #ማስታወሻ ፦ የመጀመሪያው ዙር ውጤት ፦ 👉 ሰዒድ አብዱላሂ ዴኒ ➡️ 65 👉 ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 59 👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 52 👉 ሀሰን አሊ ኻይሬ ➡️ 47 @tikvahethiopia
#ሶማሊያ

እጅግ ከባድ ፉክክር እየታየበት በሚገኘው የሶማሊያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ የሁለተኛው ዙር ድምፅ አሰጣጥ ተጠናቆ የድምፅ ቆጠራው እየተካሄደ ይገኛል።

የ2ኛው ዙር የምርጫ ውጤትን እንዲሁም አጠቃላይ የምርጫውን ሂደት ከሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እየተከታተል እንልክላችኃለን።

ቀጣዩ የጎረቤታችን ሶማሊያ ፕሬዜዳንት ማን ይሆን ? አብረን የምናየው ይሆናል።

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ 🌍

➡️ #ሶማሊያ ፦ በሶማሊያ እየተባባሰ ያለው የድርቅ ሁኔታ ለምግብ እጦት እና ለውሃ እጥረት የተጋለጠው ህዝብ ቁጥር 8 ሚሊየን ሊደርስ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል። አሁን ላይ በሀገሪቱ ያለው ድርቅ በገጠር 66 ወረዳዎችና ሰፊ አካባቢዎች ክፉኛ መቷል።

➡️ #ዩክሬን ፦ ዩክሬን በጦርነቱ ምክንያት 243 ህጻናት መሞታቸውን እና 444 ህፃናት መቁሰላቸውን አረጋግጫለሁ ስትል አስታውቃለች።

➡️ #ግብፅ ፦ የግብፅ ፍርድ ቤት በቀድሞው የፕሬዚዳንት እጩ አብደል ሞኒም አቡል ፎቱህ እና በሙስሊም ወንድማማች ቡድን ውስጥ ያሉ ታዋቂ ግለሰቦችን " የሀሰት ዜና በማሰራጨት " እና መንግስትን ለመገልበጥ አሲረዋል በሚል በእስራት እንዲቀጡ ወስኗል። አቡል ፎቱህ 70 ዓመታቸው ሲሆን የ15 አመት እስራት ተፈርዶባቸዋል፣ መሐመድ አል-ካሳስ የአቡል ፎቱህ " Strong Egypt Party " ምክትል ኃላፊ የ10 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል፣ እንዲሁም የ15 አመት እስራት የተፈረደባቸው የወንድማማችነት የቀድሞ የበላይ መሪ ማህሙድ ኢዛት ሲሆኑ እሳቸው ቀደም ሲልም በሌሎች ክሶች የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ነበር።

➡️ #ሱዳን ፦ የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ጥቅምት 25 የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ተጥሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳቱን አሳውቀዋል። ቡርሃን " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአገር አቀፍ ደረጃ ተነስቷል " ብለዋል።

➡️ #ሩስያ ፦ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የዩክሬን #ዶንባስ ግዛትን ነፃ ማውጣት ለሞስኮ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገልፀው ሌሎች ግዛቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን ለራሳቸው መወሰን አለባቸው ብለዋል።

#ቲአርቲ #AJ #ኤፒ #SNTV

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ ፦

#ካናዳ ፦ የካናዳው ጠ/ሚ ጀስቲን ትሩዶ አነስተኛ የእጅ ሽጉጥ መግዛትም ሆነ መታጠቅ እንዲከለከል ጠይቀዋል። የትሩዶ መንግሥት በጠቅላላው የእጅ ሽጉጥ መግዛት ሆነ ቤት ማስቀመጥ በሕግ እንዲያስቀጣ ረቂቅ እያወጣ ነው። ረቂቁ እንደሚለው ካናዳዊያን የእጅ ሽጉጦቻቸውን ባይነጠቁም ከዚህ በኋላ አዲስ መግዛት ግን አይችሉም። ትሩዶ ይህን ሐሳብ ያፈለቁት በአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት አንድ አፍላ ታጣቂ 19 ሕፃናትን ተኩሶ ከገደለ በኋላ ነው።

➡️ #እስራኤል #UAE ፦ እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የነፃ ንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል ፤ ይህ እስራኤል ከአረብ ሀገር ጋር ያደረገችው የመጀመሪው ትልቅ ስምምነት ነው።

➡️ #ሴኔጋል ፦ የሴኔጋል ፖሊስ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰው እና የ11 ህጻናት ህይወት ከቀጠፈው የእሳት አደጋ ጋር በተያያዘ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል።

➡️ #ሩስያ ፦ በያዝነው ዓመት 70ኛ ዓመታቸውን የሚደፍኑት የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጤና እክል ምናልባትም በካንሰር ህመም እየተሰቃዩ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ያልተረጋገጡ የመገናኛ ብዙኃን ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ግን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታመዋል መባሉን ሀሰት ሲሉ አስተባበሉ። ላቭሮቭ ፕሬዚዳንት ፑቲን በየቀኑ በአደባባይ እንደሚታዩ እና እንደማኛውም ጤነኛ ሰው የህመም ምልክት አያታይባቸውም ብለዋል።

➡️ #ሶማሊያ ፦ የሶማሊያ ባይዶዋ ከተማ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ነች። ከተማዋ ፕሬዝዳንቱ ፈርማጆን አሸንፈው ዳግም የፕሬዜዳንትነት መንበሩን ከተረከቡ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጎበኟት ከተማ ትሆናለች።

#ቢቢሲ #ቲአርቲ #ሲጂቲኤን #SNTV

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ 📣

➡️ #ካሜሮን፦ በካሜሩን መገንጠልን አላማቸው አድርገው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ ታጣቂዎች ናይጄሪያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ መንደር በፈጸሙት ጥቃት በትንሹ 20 ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል። ጥቃቱ ባሳለፍነው እሁድ በደ/ምዕራብ የካሜሩን ክፍል ኦቦኒ ሁለት በተሰኘ መንደር የተፈፀመ ሲሆን ከሞቱ ሰዎች ባሻገር ከ60 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ታጣቂዎቹ ነዋሪዎቹ በየወሩ ገንዘብ እንዲከፍሏቸው ይፈልጋሉ፤ ነዋሪዎቹ ደግሞ ፍቃደኛ አልሆኑም። ለዚህም ነው ጥቃት ያደረሱባቸው ተብሏል።

➡️ #ሜክሲኮ ፦ በደቡባዊ ሜክሲኮ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ በትንሹ 10 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች የገቡበትን ማወቅ እንዳልተቻለ ተሰምቷል።

➡️ #ቻይና ፦ የሻንጋይ ነዋሪዎች ከሁለት ወር በኃላ የኮቪድ-19 የእንቅስቃሴ ገደብ መነሳቱን ተከትሎ ነፃ ሆነዋል። ነዋሪዎች ባለፉት 2 ወር ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል በተጣለ የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ከእንቅስቃሴ ርቀው ቆይተዋል።

➡️ #ዩክሬን ፦ የየክሬን ኬርሰን ግዛት በሩስያ ቁጥጥር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ሁሉንም የግንኙነት መስመሮች እንዲዘጉ ማድረጋቸው ተነግሯል።

➡️ #አሜሪካ ፦ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ሀገራቸው ለዩክሬን 'ቁልፍ ኢላማዎችን' ለመምታት የሚያስችላትን እጅግ የዘመኑ ሮኬቶችን እንደምትልክ አሳውቀዋል።

➡️ #ሶማሊያ ፦ ወደ ባይዶዋ እንደሚሄዱ የተነገረላቸው አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ፕሬዝዳንት ከሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ግዛት መሪ አብዲአዚዝ ሀሰን ሞሀመድ እና ከባህላዊ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። ፕሬዜዳንቱ ወደ ባይዶዋ ያደረጉት ጉዞ ዳግም ፕሬዜዳንት ሆነው ከተመረጡ በኃላ የመጀመሪያቸው ነው።

#ቲአርቲ #ቢቢሲ #ፍራንስ24 #ሲጂቲኤን

@tikvahethiopia