TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ቅሬታ ! የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ደርሷቸው እንደሆነ ለማወቅ የሚጠባበቁ ነዋሪዎች የስም ዝርዝር ይፋ ባለመደረጉ ቅሬታ እንዳላቸው ገለፁ። የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ዓርብ ቢወጣም እስካሁን የቤት ዕጣ የደረሳቸው ሰዎች ስም ዝርዝር በይፋ አልተገለፀም። ይህም የቤት ዕጣ ደርሷቸው እንደሆን ለማወቅ እየተጠባበቁ ባሉ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት…
#ማብራሪያ የ20/80 እና 40/60 ጉዳይ 👆

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፦

" ... ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ስንጀምር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች ተግኝተዋል።

በመሆኑም በእስካሁኑ የማጠራት ስራ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል፡፡

ከዚህ በመነሳትም የቤት ማስተላለፉን ሂደት ግልፅነት ለማስፈን ሲባል እና ውጤቱን የሚያዛባ ተግባር ሲያጋጥም መልሰን ኦዲት እንዲደረግ በገባነው ቃል መሰረት የተፈጠረውን ችግር ከጉዳዩ ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር #በቁጥጥር_ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል።

ስለሆነም ሂደቱን በአጭር ጊዜ አጠናቀን ለቤት ተመዝጋቢዎችና ለመላው የከተማችን ነዋሪ የምናሳውቅ መሆኑን ስንገለጽ ተመዝጋቢዎች እንደተለመደው በከፍተኛ ትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን፡፡

ለተፈጠረው ስህተት የከተማ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ ይጠይቃል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት📣 ነዋሪዎችን ከፍተኛ ስጋት ላይ የጣለው የፀጥታ ችግር ! ከቲክቫህ ቤተሰብ አባል ከአጣዬ አካባቢ ፦ " እንደ ሁል ጊዜው ሁሉ አጣዬ ከተማ ዳግም ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት ውስጥ ገብታለች። ይሄም የሆነው በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ ቦታዎች ዳግም ግጭት በመቀስቀሱ ነው። ትላንት ማለትም በ02/11/2014 " የቤት እንሰሶች የተዘራ ሰብልን በሉብን " በማለት ልዩ ቦታው…
#Update

" የፀጥታ አካላት እና ንፁሃን አርሶአደሮች ህይወታቸው አልፏል "

በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ እና በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ አዋሳኝ አከባቢዎች መካከል በተከሰተው ግጭት በፀጥታ አካላት እንዲሁም በንፁሃን አርሶአደሮች ላይ የሕይወት መጥፋት እና የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በንፁሃን ዜጎች እና በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ በሚኖሩ ሰላማዊ ዜጎች ላይ አለመረጋጋት ተከስቷል፡፡

ይህን ተከትሎ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በኩል የተለያዩ ክልከላዎች ተጥለዋል ፦

- ማንኛውም በወረዳው እና በከተማው ውስጥ የሚገኙ የሶስት እግር ተሽከርካሪዎችን (ባጃጆችን) ላልተወሰነ ጊዜያት በቀንም ሆነ በማታ ማሽከርከር አይችልም።

- ከመንግሥት የፀጥታ መዋቅር ውጭ ማንኛውንም አካል የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ አይችልም።

- ከተፈቀደለት የፀጥታ አስከባሪ መዋቅር ውጭ ማንኛውም ግለሰብ ከቀበሌ ወደ ቀበሌ መንቀሳቀስ አይችልም።

- በህብረተሰቡ ውስጥ እና በማህበራዊ ሚዲያ ተጨባጭ ያልሆኑ መረጃዎችን የሚያናፍሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

(የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማብራሪያ የ20/80 እና 40/60 ጉዳይ 👆 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፦ " ... ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ስንጀምር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች ተግኝተዋል። በመሆኑም በእስካሁኑ የማጠራት ስራ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል፡፡ ከዚህ በመነሳትም…
" ዕጣው ሙሉ ለሙሉ ተሰርዟል ብሎ መናገር አይቻልም " - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ተሰርዟል ብሎ መናገር አይቻልም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገለፀ።

የኮርፖሬሽኑ የሥራ ሀላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት " ዳታው ገብቶ ዕጣው ከወጣ በኋላ ያሉ ስህተቶች መኖራቸው ይታያል በተባለው መሰረት የተወሰኑ ክፍተቶች አሉ " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት የከተማ አስተዳደሩ ምን ሊወስን እንደሚችል አልታወቀም ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ሽመልስ ጉዳዩና ውሳኔው ዛሬ ሊታወቅ ይችላል ሲሉም ጠቁመዋል።

ባለፈው ሳምንት ዓርብ 25,491 ሰው ዕጣ ወጥቶለታል ያሉት አቶ ሽመልስ ፤ ስህተት የፈጠረው ሰው እንደተለየው ሁሉ በስህተቱ እድሉ የተፈጠረለት ማነው የሚለው ተለይቶ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ የሚያሻግረው አማራጭ ይታያል ተብሎ እንደሚታመን አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበረው የተዝረከረከ አሰራር እንዳይኖር ቀድሞ ማጣራት ተደርጓል ያለው የቤቶች ኮርፖሬሽን ዳታው ከገባ እና ዕጣው ከወጣ በኋላ ያሉ ስህተቶች መኖራቸውን ገልጿል፤ ጉዳዩ እልባት ለማግኘት ተቃርቧል ሲልም አሳውቋል።

መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነው።

@tikvahethiopia
#ደሴ

" 11 ሰዎች ቆስለዋል ፤ በእንሰሳት ላይ ሞትና ከፍተኛ ቁስለት ደርሷል " - የደሴ ከተማ አስተዳደር

በደሴ ከተማ ፤ በሰኞ ገበያ ሳላይሽ ቀበሌ አካባቢ ቆራሊዮ የሚያከማቹ ሰዎች ቆራሊዮ ከመኪና ሲያራግፉ ቦንብ ፈንድቶ 11 ሰዎች ቆስለዋል።

በእንስሳት ላይም ሞትና ከፍተኛ ቁስለት ደርሷል።

ፍንዳታው ያጋጠመው ዛሬ 5:30 ላይ ሲሆን በቆራሊዮ መጋዘን ከመኪና ላይ ወርዶ ሚዛን ሲመዘን ከነበረ ኬሻ ውስጥ የፈነዳ ቦንብ 11 ሰዎች ላይ ጉዳት ሲያደርስ 3 በጎችን እና 1 ፍየልን ገድሎ 15 በጎችን ለጉዳት ዳርጓል።

በቦታው ላይ የበኣል የፍየል እና የበግ ግብይት ስለነበር ብዙ ሰዎችና እንስሳት እንዲጎዱ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

በፍንዳታው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በግ ሲገዙ የነበሩ እና የቀን ሰራተኞች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ተጎጂዎች ወደ ሆሰፒታል ተወስደዋል።

መረጃው ከደሴ ከተማ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
የትግራይ መልሶ ግንባታ !

የኢትዮጵያ መንግሥት በዓለም ባንክ የሚደገፈውን የትግራይ መልሶ ግንባታ ፕሮግራም የተመድ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ቢሮ (UNOPS) በበላይነት እንዲመራው ስምምነት መፈረሙን ገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል።

ዓለም ባንክ ለትግራይ ክልል መልሶ ግንባታ የመደበው 300 ሚሊዮን ዶላር ነው (ይህ መጠን በተያያዘው የገንዘብ ሚኒስቴር ደብዳቤ ላይ አልተጠቀሰም)።

የትግራይ መልሶ ግንባታ ፕሮግራም በአገሪቱ በግጭት የወደሙ አካባቢዎችን በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ መልሶ ለመገንባት መንግሥት የቀረጸው አገር ዓቀፍ ፕሮግራም አካል ነው።

የፕሮግራም ሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች መሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ መገንባት እና በወሲብ ጥቃት ተጎጅ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለተለያዩ አገልግሎቶች ያላቸውን ተደራሽነት ማስፋት ናቸው።

ስምምነቱን የፈረሙት የገንዘብ ሚንስትር አሕመድ ሽዴ እና የተመድ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ቢሮ የኢትዮጵያ ተወካይ ወርቅነሽ መኮንን ናቸው።

በስምምነቱ መሠረት የትግራይ መሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ግንባታ የተመድ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ቢሮ በቀጥታ የሚተገብር ሲሆን፣ የወሲብ ጥቃት ተጎጅዎችን የሚመለከተውን የፕሮግራሙን ዓላማ ደሞ ሌሎች ሦስተኛ አካላት ይተገብሩታል።

የተመድ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ቢሮ ፕሮግራሙን በሃላፊነት ተረክቦ በትግራይ ክልል ተፈጻሚ የሚያደርገው፣ በትግራይ ክልል እና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ያለው ችግር ተቀርፎ መንግሥት ፕሮግራሙን እስኪረከብ ድረስ እንደሆነ ተገልጿል።

Credit : www.wazemaradio.com

@tikvahethiopia
የሰኔ ወር የዋጋ ግሽበት !

የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ አገልግሎት (CSA) በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ መሰረት ፦

- የሰኔ ወር 2014 አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 34 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

- የሰኔ ወር 2014 የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ38 ነጥብ 1 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ፤

- በእህሎችና አትክልት ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ ታይቷል። የሚቀዳ የምግብ ዘይት፣ ዘይትና ቅቤ፣ ቡናና ለስለሳ መጠጦችም ጭማሪ ያሳዩ ቢሆንም ከውጭ የሚመጣው የምግብ ዘይት ላይ መጠነኛ ቅናሽ ተመዝግቧል።

- ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት የሰኔ ወር 2014 ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ28 ነጥብ 4 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

- ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ምክንያቶች ፦ አልኮልና ትምባሆ፣ ልብስና ጫማ፣ አነቃቂዎች (ጫት) ፣ የቤት እንክብካቤና ኢነርጅ (ማገዶና ከሰል) ፣ የቤት መስሪያ እቃዎች (የቤት ኪራይ፣ ሲሚንቶ፣ የቤት ኪዳን ቆርቆሮ) ፣ የቤት ዕቃዎችና የቤት ማሰገጫዎች ፣ ነዳጅ ፣ ህክምናና እና ጌጣጌጥ (ወርቅ) ናቸው።

- የሰኔ ወር 2014 ዓ/ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ግንቦት ወር 2014 ጋር ሲነፃፀር በ4 ነጥብ 5 ከመቶ እና፤ የምግብ የኢንዴክሱ ክፍሎች በ3 ነጥብ 9 ከመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን የምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት በ5 ነጥብ 5 ከመቶ አሳይቷል፡፡

Credit : www.addismaleda.com

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የሥራ ፈጠራ ውድድር !

የ2ኛ ዙር " አሁን/Ahun " የዲጂታል አንተርፕነሮች የሀሳብ ማበልፀጊያ ፕሮግራም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (#UNDP) አጋዥነት ጀምሯል።

በመጀመሪያ ዙር ተካሂዶ በነበረው ውድድር አሸናፊዎችን ለሥራ ያበቃው ይኸው መርሃግብር #አሁን ሁለተኛ ዙር የሥራ ፈጠራ ውድድር በይፋ መጀመሩን ተነግሯል።

ፕሮግራሙ የ4 ወር የሀሳብ ማበልፀጊያ ድጋፍና የሥራ ማስጀመሪያ ሽልማት ያካትታል፡፡

አዳዲስ እና ችግር ፈቺ የሆኑ የዲጂታል የሥራ ሃሳብ ያላችሁ አመልካቾች በውድድሩ መሳተፍ ትችላላችሁ ተብሏል።

የማመልከቻ ቅጹን ለማግኘት ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ : https://enkopa.org/high-growth/ አለያም በመልዕክት ሳጥን ቁጥር 25534 ቅፁን ሞልቶ መላክ እንደሚቻል ተገልዬ።

ምዝገባው የሚጠናቀቀው ሐምሌ 24, 2014 ዓ/ም ነው።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲሰራጭ የዋለው ሀሰተኛ ፎቶ !

ከላይ ፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው ሸይኽ ዶክተር ማህር አል-ሙአይቂሊ ይባላሉ እጅግ የተከበሩ ኢማም እና የእስልምና ሃይማኖት መምህር ናቸው።

ትውልዳቸው እኤአ 1969 ሳዑዲ አረቢያ በመዲና ሲሆን በተለያዩ መስጅዶች መካ እና መዲና ውስጥ በረመዳንና በተለያዩ ወቅቶች ፀሎትና ሶላት በመምራት በእጅጉ ይታወቃሉ።

በመዲና እጅግ ታዋቂ ከሆኑ በኃላ የልዑል አብዱል መጂድ አማካሪ ሆነውም ነበር። በኃላም የማማከር ስራውን በመተው በንጉስ አብዱላህ ሳዑድ ዩኒቨርሲቲ በአስተማሪነት አገልግለዋል።

ሸይኽ ዶክተር ማህር አል-ሙአይቂሊ በጣም ባለብሩህ አእምሮ ባለቤት ሲሆኑ በተለይ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኃላ የሂሳብ መምህር በመሆንም አገልግለዋል።

ስለእሳቸው ባለን መረጃ የተራዊህ ሶላትን በሳዑዲ እንዲሁም ከሳዑዲ ውጭ በተለይ በፓሪስ በመምራት ይታወቃሉ።

ዛሬ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ከአንድ ዜና ጋር በተያያዘ በሀሰት ፎቷቸው ሲለጠፍ ውሏል።

ዜናው ፤ የአሜሪካ መንግስት በሶሪያ የሚገኝን የአይኤስ መሪ ማሃር አል-አግአል በድሮን ጥቃት መግደሏን የሚገልፅ ሲሆን ዜናውን ያወጡት የአሜሪካ ሚዲያዎች ፎቶ ሲያጋሩ አልያተየም።

ነገር ግን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ጨምሮ የማሃር አል-አግአል ፎቶ ተብሎ ሲሰራጭ የነበረው ፎቶ ፍፁም ሀሰተኛ ነው። ሲሰራጭ የነበረውም የዶ/ር ሸይኽ ዶክተር ማህር አል-ሙአይቂሊ ነው።

የማህበራዊ ሚዲያዎች ከኢንተርኔት ላይ የሚገኙ መረጃዎችን ከመቀባበላቸው በፊት ደጋግሞ ማረጋገጥ ይገባል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማብራሪያ የ20/80 እና 40/60 ጉዳይ 👆 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፦ " ... ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ስንጀምር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች ተግኝተዋል። በመሆኑም በእስካሁኑ የማጠራት ስራ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል፡፡ ከዚህ በመነሳትም…
#AddisAbaba

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአዲስ አበባ ካቢኔ አባል የሆኑት ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ አልታሰሩም።

ከ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ችግር የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የአ/አ አስተዳደር መግለፁ ይታወቃል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ " ወ/ሮ ያስሚን ወሃቢረቢ በቁጥጥር ስር ዉለዋል " ተብሎ መረጃ ሲሰራጭ ነበር።

ነገር ግን ፤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ያስሚን ወሃቢረቢ በቁጥጥር ስር ውለዋል ተከባሉት ግለሰቦች መካከል እንዳልሆኑ #ኢትዮጵያ_ቼክ መረጃ ማጣሪያ ድረገፅ ከራሳቸው ከወ/ሮ ያስሚን እንዲሁም ከከተማ አስተዳደሩ ማረጋገጡን አሳውቋል።

ወ/ሮ ያስሚን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ አባል እንዲሁም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሲሆኑ የምክር ቤቱ አባል መሆናቸው በግልፅ ሂደት ካልተነሳ በቀር ያለመከሰስ መብት አላቸው።

@tikvahethiopia