TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ በ3ኛው ዙር የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ 24 ሺህ 491 ቤቶች ነገ ዕጣ ይወጣባቸዋል ተብሏል።

በዕጣ አወጣጥ ሥነ ስርአት ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ላይ " በዕጣ አወጣጥ ሥነ ስርአቱ 79 ሺህ 794 ተመዝጋቢዎች በዕጣ አወጣጥ ውድድሩ ውስጥ ይካተታሉ " ብለዋል።

#ከ1997 ዓ.ም የ20/80 ተመዝጋቢዎች መካከልም 60 ወራት ሳያቋርጡ የቆጠቡ ቅድሚያ እንደሚሰጣቸውም ገልፀዋል።

ነገ ጠዋት ሁለት ሰአት ላይ በሚካሄደው የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ላይ ከንቲባ አዳነች አበቤን ጨምሮ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮችና ታዛቢዎች ይገኛሉ መባሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#HoPR

ነገ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ህ/ተ/ምክር ቤት ይቀርባሉ።

በዚህም በ2015 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ እና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል።

በተጨማሪ ፓርላማው በተለያዩ ጉድዮች ላይ ውይይት ያደርጋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ሰሚ አጥተናል፤ ነገስ ዋስታናችን ምንድነው ? " - የቲክቫህ አባላት ቄለም ወለጋ

ከሰሞኑን ጭፍጨፋ በተፈፀመበት የቄለም ወለጋ ፤ አካባቢ የሚኖሩ እና ቤተሰቦቻቸው በቦታው ያሉ ወገኖች አሁን ላይ ፀጥታ ኃይል በአካባቢው ቢኖርም የነገ ዋስትናቸው እንደሚያሳችባቸው ገልፀዋል።

ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ ጥቃት ተፈፅሞ ሌላ ሀዘን እንዳይከተል ፀጥታው መጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል።

" እኛ ሰሚ አጠተናል፣ እጅግ በጣም ተሰቃየን ፣ መፍትሄ እንፈልጋለን ፣ ፍትህን እንፈልጋለን ፣ ተጠናቂነት እንዲሰፍን እንፈልጋለን " ሲሉ በሀዘን ስሜት ውስጥ ሆነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ከጭፍጨፈው የተረፉት ወገኖች " የሀዘን መግለጫ ጋጋታ አንፈልግም ፣ በየጊዜው ንፁሃን ሰው ይጨፈጨፋል መግለጫ እንደጉድ ይወጣል በኃላም ይረሳል ተጎጂዎችን ዞር ብሎ እንኳን የሚያየ የለም " ብለዋል።

" እኛ የሀዘን መግለጫ እና ወሬ ሳይሆን የሚታይ ተግባር ፣ የመኖር ዋስትና መረጋገጥን ብቻ ነው የምንፈልገው ፤ ምንም ስለፖለቲካ የማያውቁ ህፃናት፣ ሴቶች እናቶች ያለሃጢያታቸው ለምን ይጨፈጨፋሉ ? መቼ ነው ይሄ የሚያበቃው " ሲሉ ጠይቀዋል። የንፁሃንን ሞት ለፖለቲካ ንግድ እና በየሚዲያው ለገንዘብ የሚጠቀሙ በሀዘናችን ላይ ሀዘን እየደረቡ ነው ብለዋል።

ለደረሰብን አስከፊ ነገር ሁሉ " አላህ ብቻ ነው ፍርዱን ከሰማይ የሚሰጠው " ሲሉም ገልፀዋል።

ከትላንት ወዲያ ሰኞ ዕለት በተፈፀመው ጭፍጨፋ ህይወታቸው ያለፉትን ሰዎች የመቅበር ስነስርዓት የተከናወነ ሲሆን እዛ አካባቢ ቤተሰቦቹ የሚኖሩ የቲክቫህ አባል አንድ የሚያውቀው ሰው ወንድሞቹ ከነቤተሰቦቹ መገደላቸውን ፤ ከዚህ ባለፈ የታገቱ ሰዎች መኖራቸውን አመልክቷል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Family-07-06

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም !

" ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ከንቲባዋ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም ብለዋል።

ከንቲባዋ በመግለጫቸው የከተማ አስተዳደሩ በየ3 ወሩ የሚታደስ መመሪያ እንደነበረው አስታውሰዋል።

በከተማዋ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በመኖሩ በዜጎች ላይ ጫና እያስከተለ በመሆኑ የቤት ኪራይ መጨመር መከልከሉን አስረድተዋል።

በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ አይቶ ደንቡ እስካልተሻሻለ ድረስ ምንም አይነተ የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ብለዋል።

#አከራዮችም ሆኑ #ተከራዮች ይህንኑ ማወቅ እንዳለባቸው ጠቁመው ክልከላውን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ አሳስበዋል።

በዚህ ዙሪያ ዜጎች መብት እና ግዴታቸውን በቅጡ ተገንዝበው እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ በ3ኛው ዙር የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ 24 ሺህ 491 ቤቶች ነገ ዕጣ ይወጣባቸዋል ተብሏል። በዕጣ አወጣጥ ሥነ ስርአት ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው ላይ " በዕጣ አወጣጥ ሥነ ስርአቱ 79 ሺህ 794 ተመዝጋቢዎች በዕጣ አወጣጥ ውድድሩ ውስጥ ይካተታሉ " ብለዋል። #ከ1997…
#AddisAbaba

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የማውጣት ስነስርዓት ወደ ዓርብ ተሻገረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ14ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ስነስርዓት ነገ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚካሄድ ገልጾ ነበር።

ነገር ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠራው ስብሰባ ምክንያት የእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ወደ ዓርብ ሃምሌ 1 ቀን 2014 የተዛወረ መሆኑን አስተዳደሩ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፥ ለተፈጠረው የፕሮግራም ለውጥ ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን ታዛቢዎች፣ ባለዕድለኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የሚዲያ አካላት በተለዋጩ ፕሮግራም እንዲገኙ (ማለትም ዓርብ) መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከምን ደረሰ ? ሳፋሪኮ ኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመጀመር እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴ እንዲሁም አሁናዊ የተቋሙን እንቅስቃሴ በተመለከተ በቀጣይ ሳምንት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል። ተቋሙ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት ፤ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት ሊጀምር ነው " የሚሉ፣ ቀኖች እና ሌሎች ተቋማዊ መረጃዎችን ያካተቱ ዜናዎችና መረጃዎች በማሕበራዊ ድረገጾች መውጣታቸውን…
#SafaricomEthiopia

ሳፋሪኮም በሃምሌ ወር በድሬዳዋ አገልግሎት ይጀምራል።

በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኤክስተርናል አፌርስ እና ሬጉላተሪ ዋና ኃላፊ ማቲው ሀሪሰን ሀርቪ ፦

" ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኔትወርኩን በማስጀመር አገልግሎቶችን ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው።

ይህንንም በድሬዳዋ በሐምሌ ወር 2014 ዓ/ም በመጀመር በቀጣይ ወራት በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ 24 ከተሞች የሚስፋፋ ይሆናል።

በአሁኑ ወቅት ያለንበት የሙከራ ጊዜ አገልግሎታችንን ሙሉ በሙሉ ስንጀምር ጥራት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ የሚረዳን ነው።

የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና አካታትችነት እቅድ በመደገፍ የገባነውን ቃል ጠንካራ መሠረት በመገንባት እየተገበር ሲሆን ለኢትዮጵያውያን ሕይወት ፋይዳ ያለው አበርክቶ ለማድረግም በትጋት እየሠራን እንገኛለን "

(ሙሉ የሳፋሪኮም መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR ነገ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ህ/ተ/ምክር ቤት ይቀርባሉ። በዚህም በ2015 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ እና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል። በተጨማሪ ፓርላማው በተለያዩ ጉድዮች ላይ ውይይት ያደርጋል። @tikvahethiopia
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ !

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በህ/ተ/ም/ቤት ቀርበው ለተነሳላቸው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል።

የምክር ቤት አባላት በርካታ ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የንፁሃን ዜጎች ግድያን ፣ የህግ ማስከበርን፣ ሰላማዊ ሰልፍ፣ የሰላም ጉዳይን በተመለከተ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

ያንብቡ 👉https://telegra.ph/Dr-Abiy-Ahmed-07-07

(የጠ/ሚ ፅ/ቤት)

@tikvahethiopia
የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ !

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከሰኔ 29 ጀምሮ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

ሚኒሰቴሩ የተደረገውን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ እንዲሁም የትራንስፖርት መለዋወጫ ጭማሪ ምክንያት በማድረግ የአገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

(አዲስ ይፋ የተደረገው የትራንስፖርት ታሪፍ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SafaricomEthiopia ሳፋሪኮም በሃምሌ ወር በድሬዳዋ አገልግሎት ይጀምራል። በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኤክስተርናል አፌርስ እና ሬጉላተሪ ዋና ኃላፊ ማቲው ሀሪሰን ሀርቪ ፦ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኔትወርኩን በማስጀመር አገልግሎቶችን ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው። ይህንንም በድሬዳዋ በሐምሌ ወር 2014 ዓ/ም በመጀመር በቀጣይ ወራት በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ 24 ከተሞች የሚስፋፋ ይሆናል።…
#SafaricomEthiopia

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እስካሁን ምን ምን ስራ ሰራ ?

በሰኔ 2013 ዓ.ም የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪነት ፍቃድ ከተሰጠው ጀምሮ ፦

👉 የኔትወርክ እና የመሰረተ ልማቶች ግንባታዎች ላይ በማተኮር የሞባይል ሬድዮ ታወሮችን፤ ብሔራዊ የማሰራጫ ኔትወርኮን እና ለዓለም አቀፍ ግንኙነት የሚሆኑ ስምምነቶችን ጨምሮ መሠረተ ልማቶችን ገንብቷል።

👉 የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪነት ፍቃድን ጨምሮ ለልዩ ልዩ ሥራዎች 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስት አድርጓል።

👉 ከ300 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ዋጋ የሚያወጡ መገልገያዎችን ወደ አገር ውስጥ አስገብቷል።

👉 ኮር ኔትወርዎርኩ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (1) እንዲሁም ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ማበልፀግ ጀምሯል።

👉 የደንበኞች ጥሪ ማስተናገጃን አደራጅቷል።

👉 ሁለት የመረጃ ቋት ማዕከላት (Data Centers) ገንብቷል።

👉 በቅርቡ የመሠረተ ልማት መጋራት እና #ከአንዱ_ወደ_ሌላው_ለመደወል የሚያስችሉ ስምምነቶችን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ተፈራርሞ ትግበራው በጥሩ መልኩ እየተካሔደ ነው።

#SafaricomEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SafaricomEthiopia ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እስካሁን ምን ምን ስራ ሰራ ? በሰኔ 2013 ዓ.ም የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪነት ፍቃድ ከተሰጠው ጀምሮ ፦ 👉 የኔትወርክ እና የመሰረተ ልማቶች ግንባታዎች ላይ በማተኮር የሞባይል ሬድዮ ታወሮችን፤ ብሔራዊ የማሰራጫ ኔትወርኮን እና ለዓለም አቀፍ ግንኙነት የሚሆኑ ስምምነቶችን ጨምሮ መሠረተ ልማቶችን ገንብቷል። 👉 የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪነት ፍቃድን ጨምሮ…
የቀጠለ ...

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከመሠረተ ልማት ግንባታ በተጨማሪ ሌሎች የሰራቸው ስራዎች ፦

👉 የተሳካ አገልግሎት ለማቀረብ አንዲሁም የሙያ እና የክህሎት ሽግግርን ለማጠናከር ብቃት ያለው የአመራሮች ሰብስቦ አዋቅሯል።

👉 የሰው ኃብቱን ወደ 500 ያሳደገ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 320ዎቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። በቀጣይም ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተውጣጡ ሠራተኞች እንዲኖሩት ለማድረግ እየሰራ ነው።

👉 50 አዲስ ተመራቂ ተማሪዎችን መልምሎ ጊዜውን የዋጁ ኃሳቦችን እና መፍትሔዎችን ሊጠቁም የሚችሉ ዲጂታል የፈጠራ ክህሎት ያላቸው ኢትዮጵያዊያንን ለመፍጠር ጥረት እያደረገ ሲሆን ተጨማሪ 100 አዲስ ተመራቂዎችን ለመመልመል በልዩ ልዩ ክልሎች ውስጥ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር እየሠራ ነው።

👉 በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ሊያዳርሱ የሚችሉ 29 አከፋፋዮችን በአቅራቢነት በመያዝ ድርጅቶቹ አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ እየተሰራ ነው።

👉 አገልግሎት መስጠት ለመጀመር ያዘጋጀነው ዕቅድ የችርቻሮ መደብሮችን እንዲያካትት በማድረግ በአቅርቦት ሰንሰለቱ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጋር አጋርነት ለመፍጠር የሚያስችሉ ጨረታዎች አውጥቷል።

👉 ማህበራዊ ኮንትራቱን ማዘጋጀት የቀጠለ ሲሆን 'ዲጂታልን በመጠቀም ሕይወትን የማሻሻል' ርዕዩን በሚያሳካ መንገድ ለዚህ መሠረት ለመጣል የሚያስችሉ እቅዶችን አውጥቷል።

#SafaricomEthiopia

@tikvahethiopia