ፎቶ / ቪድዮ ፦ ዛሬ በአዲስ አበባ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ ፈረንሳይ 41 እየሱስ አካባቢ በፎቶው እና በቪድዮው የምትመለከቱትን ይመስል ነበር። ከዚህ አካባቢ በተጨማሪ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት አካባቢ ከ1 ሰዓት በላይ በረዶን የቀለቀለ ዝናብ ጥሎ ነበር።
ወቅቱ ክረምት በመሆኑ በሚቻለው አቅም ጥንቃቄ እናድርግ ፤ በተለይ ደግሞ አሽከርካራዎች ወቅቱን ባገናዘበ መልኩ ጥንቃቄያችንን ከምን ጊዜውም በላይ እናጠናክር።
(ዧ - Tikvah Family)
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
መቆሚያው የት ነው ? ባለፉት ዓመት ንፁሃን ዜጎች በተለይ ህፃናት እና ሴቶች እጅግ በጣም አረመኔያዊ በሆነ መንገድ ሲጨፈጨፉ ፣ ሲሳደዱ፣ ከገዛ ቤታቸው ሲፈናቀሉ አይተናል። ይህን ተከትሎም በርካቶች ሀዘናቸውን እና ቁጣቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ ያጋራሉ ፤ ከልባቸው ተጠያቂነት እንዲሰፍን ይወተውታሉ። መንግስት ተቀዳሚ ስራው የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ እንደሆነ ደጋግመው ያሳስባሉ። በአንፃሩ…
" የትኛውም ቦታ የሚፈፀም የንፁሃን ግድያ ለሁለት እና ሶስት ቀን አጀንዳ ሆኖ ሊያልፍ አይገም " Tikvah Family
ባለፉት ዓመታት በአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫ በርካታ ከግጭ ነፃ የሆኑ፣ ስለ ፖለቲካ ሆነ በሀገሪቱ ስላለው ነገር በቅጡ መረጃው የሌላቸው ንፁሃን ገበሬዎች፣ ህፃናት፣ ሴቶች፣ አዛውንቶች፣ ታዳጊዎች ፣ ነገ የተሻለ ህይወት ለመኖር የሚያስቡ በርካታ ወጣቶች ሲገደሉ፣ ከቤታቸው ሲፈናቀሉ፣ ሲሳደዱ ተመልክተናል።
በዚህ ጊዜ ውስጥ ለየትኛው ጉዳይ #በሰብዓዊትነት መርህ አንድ ላይ ተቁሞ እንደተወገዘ ፤ ለተጠናቂነት እና ለመፍትሄ ሁሉም እንደጮኸ ለማስተወስ ይከብዳል።
ለአብነት አንድ ቦታ ላይ ችግር ሲፈጠር ከዚህ በፊት ከነበረው ጋር በማወዳደር ፤ ያኔ እናተ መቼ አወገዛችሁ ይባላል ፤ በዚህኛው በኩል ችግር ሲፈጠር እናተስ ባለፈው መቼ አወገዛችሁ ፤ መቼ ስለኛ ተናገራችሁ ይባላል ፤ ሌላም ቦታ እንዲሁም ያለፈውን በማወዳደር አጀንዳ ሲሆን ይከርምና የንፁሃን ደም ከንቱ ሆኖ ይቀራል።
በእጅ አዙር ጥፋተኛው እንዳይጣየቅ ሽፋን ይሰጣል (ለምን ? ምክንያቱም የአንዱ ወገን ስለሆነ፤ ከሰውነት ብሄር ስለገነነ) ፣ ስልጣን ላይ የተቀመጠውም ደጋፊ ስላለው ስለተጠናቂነት ቢናሳ ሊከላከልለት ብቅ የሚለውም ብዙ ነው። ይሄ መቼ ነው የማቆመው ?
" ተቀዳሚ ስራህ የዜጎችን ደህንነት ማስጠቅ ነው ፣ ሰላም ማረጋገጥ " ነው የተባለው መንግስት በየጊዜው ተመሳሳይ ነገር ይናገራል ግድያ እና ሞት ግን ይኸው ዛሬም ድረስ ቀጥሏል።
በተለይም በታጣቂዎች የሚፈፀም ጥቃት በሚገርም ሁኔታ አሁን ድረስ ቀጥሏል፤ በመጀመሪያ ለውጥ በተባለ ሰሞን መንግስት አልተረጋጋም ጊዜ ይፈልጋል ሲባል ከረመ ፤ አመታት አለፉ ሁኔታዎች አልተቀየሩም ዛሬም ሰው በወጣበት ይቀራል ፤ ቤቱ በተቀመጠበት ይገደላል።
በዚህ ሁሉ ሁኔታ ምን ያህል እንባ እንደታበሰ ፣ ምን ያህል ዜጋ ፍትህ እንዳጋኘ በቅጡም አይታወቅም።
ይበልጥ ችግሩን እያባባሰው ያለው መርጦ የማዘኑ ፤ የኔ ወገን ፣ ሃይማኖት ተናካ ሲባል ብቻ ወጥቶ መናገሩ ፣ ግፍን ማወዳደሩ፣ ያለፈውን ስላልተናገራችሁ አሁን ይበላችሁ የሚል አዙሪት ውስጥ መገባቱ ነው።
ስለንፁሃን ሲነገር እርግማን መብዛቱ፣ ስም መለጠፉ፣ ማሸማቀቁ እስካልቆመ ድረስ ፤ ሁሌም ግፎችም እያወዳደሩ ከሰውነት ተራ መውጣቱ እስካልቆመ ፣ ሁሉም ነግ በእኔ ነው ብሎ ስለፍትህ ካልጠየቀ ፤ እንዴት ችግር ይፈታል ?
ግድያ እና ግፍ የንፁሃን ሞት የሁለት እና የሶስት ቀን አጀንዳ ሆኖ መቅረት የለበትም። ዛሬ መፍትሄ ካላገኘ ነገ መቀጠሉ አይቀርም ፤ በእርግጥ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚታየው ሌላ ነው ዛሬ ይጮሃል ነገር ይረሳል።
ቤተሰቦቹን በግፍ ያጣ ፣ የሚወደን ከጎኑ የተነጠቅ ፣ የተገደለበት፤ የነገ ተስፋው የጨለመበት እንዲሁ የሚረሳው ይመስለናል ? እነዚህ ወገኖች ስለሀገራቸው ምን ይሰማቸዋል ? ብለን መጠየቅ አለብን።
ትላንት የሆነውን እኛ ብንረሳው ፤ ዘለለማዊ ጠባሳን በህይወታቸው ላይ ጥሎ የሚያልፍ ሰዎች በየጊዜው ቁጥራቸው እየበዛ ነው።
ከዚህ በፊት በታሪክ ፣ በፅሁፍ ነበር ግፍ እና በደልን ሲሰማ የነበረ አሁን ግን በቪድዮ/በፎቶ እየተቀረፀ ሰው በግፍ እየተረሸነ፣ የሰው ልጅ በቁሙ እየተቃጠለ በቪድዮ እየተቀረፀ፣ እጁ ላይ አንዳች ነገር ያልያዘ ሰው በጥይት ተደብድቦ እየተገደለ በቪድዮ የተቀረፀ ቀጣዩ ትውልድ ይህን እያየ እንዲያድግ ከተፈረደበት ነገ ከዛሬውም እጅግ በጣም የከፋ እንደሚሆን አያጠራጥርም።
ያለንበትን ሁኔታዎች በፍጥነት ማስተካከል ለዚህም መረባረብ እና ሌላ ለትውልድ #ጥላቻን እና #ቂምን ሊያወርስ የሚችል ተጨማሪ ችግር ከመደራረቡ በፊት ያሉትን መፍታት፣ የተበደሉትን እምባ ማበስ፣ ፍትህ ማስፈን ይጋባል።
#TikvahFamily

" ቴሌግራም ፕሪሚየም " ቴሌግራም በነፃ ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ በክፍያ አገልግሎት የሚሰጥበትን " ቴሌግራም ፕሪሚየም " ትላንት ለሊት ይፋ አድርጓል። የቴሌግራም ፕሪሚየም ወራዊ ክፍያ 5.99 የአሜሪካ ዶላር መሆኑም ታውቋል። አሁን ላይ የIOS (አይፎን) ተጠቃሚዎች መተግበሪያቸውን Update ማድረግ የሚችሉ ሲሆን ፤ ዛሬ አልያም በቀጣይ ቀናት ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።…
#Update #Android
ከአንድ ቀን በፊት ቴሌግራም ለIOS (አይፎን ስልክ) ተጠቃሚዎች ' ቴሌግራም ፕሪሚየም ' የተካተተበትን መተግበሪያ #Update ማድረጉ ይተወሳል።
ትላንት ለሊት የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱ እንዲደርሳቸው ሆኗል።
ዋናውን በድርጅቱ በኩል የሚቀርበው የቴሌግራም መተግበሪያ (ባለ ሰማያዊ ምልክቱ) ይጠቀሙ። #Update ለማድረግ ሊንክ ይኸው https://play.google.com/store/search?q=telegram&c=apps
" ቴሌግራም ፕሪሚያም " አሁን በነፃ እየተሰጠ ካለው አገልግሎት በተጨማሪ አዳዲስ አገልግሎቶች የተካተቱበት ሲሆን በወር 5.99 ዶላር ያስከፍላል።
በአዲሱ #Update በነፃ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ከዚህ በፊት ከነበረው ማሻሻያ እና የነበሩትን ችግሮች የመቅረፍ ስራ መሰራቱ ድርጅቱ አሳውቋል።

#Update " ፍትህ እንፈልጋለን፣ ጥፋተኞች በጠቅላላ ይጠየቁ " - የምዕራብ ወለጋ ቲክቫህ አባላት ከቀናት በፊት በምዕራብ ወለጋ ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ ሲገልፁ የነበሩ የቤተሰባችን አባላት ህዝብ እና ሀገር አስተዳደራለሁ የሚል አካል ካለ ጥፋተኞች እንዲጠየቁ እንዲያደርግ አሳስበዋል። ቤተሰቦቻቸውን በግፍ የተነጠቁ የቲክቫህ አባላት በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ሆነው ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። ፍትህ…
ከሰኔ 11ዱ ጥቃት የተረፉ ወገኖች ችግር ላይ ናቸው !
በምዕራብ ወለጋ ዞን በጊምቢ ወረዳ ፣ ቶሌ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ከሰኔ 11ዱ ጥቃት የተረፉ ነዋሪዎች አስፈላጊውን የምግብ እርዳታ ስላላገኙ ችግር ላይ ይገኛሉ።
ነዋሪዎቹ ቤት ንብረታቸው ከመውደሙ ባሻገር ንግዳቸው እንዲሁም የቀንድ ከብቶቻቸው ስለተዘረፉ የምግብ ችግር እንደገጠማቸው እየተናገሩ ነው።
ቤት ንብረታቸው የወደመባቸው ሰዎች ዘመዶቻቸው ጋር ተጠልለው እንደሚውሉና የተወሰኑት ምሽት ላይ በመስጅዶች ውስጥ እንደሚጠለሉ ገልፀዋል።
በቶሌ ቀበሌ በሚገኙት ፦
- ጉቱ፣
- ጨቆርሳ፣
- ስልሳው፣
- በገኔ፣
- ጫካ ሰፈር እና ሀያው በተባሉ መንደሮች (ጎጦች) ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ. ም. በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ከ300 የሚልቁ ንጹሀን ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች ተናግረዋል፤ ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ይገለፃል።
“ እየራበን እየጠማን ተቀምጠናል ”
የሰባት ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ ፎዚያ * ወንድማቸው ቤት ተጠልለው እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የአራት ዓመቱ የመጨረሻ ልጃቸውን ጨምሮ በአንድ ቤት ውስጥ አምስት ቤተሰብ እየኖረ ነው።
በግብርና ይተዳደሩ የነበሩት ወ/ሮ ፎዚያ በጥቃቱ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ ወድሟል። ስልሳው በሚባለው መንደር ይኖሩ የነበረ ሲሆን፣ ሁለት ጥማድ በሬ፣ ሦስት ላሞች እና አንድ ጎተራ እህል ወድሞባቸዋል።
ዛሬ ለልጆቻቸው ንፍሮ ቢያበሉም፣ ነገ እና ከዚያ ወዲያ ያሉት ቀናት እንደሚያሰጓቸው ገልጸዋል።
“ ቤተሰቦቻችን አልቀው ብቻችንን እያለቀስን፣ እየራበን እየጠማን ተቀምጠናል” ብለዋል ወ/ሮ ፎዚያ።
" ያንን ሁሉ ሬሳ አይተን ልቦናችን ወደ ሥራ አይመራንም "
የቶሌ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አሕመድ " ወደ 10 ይሁን 20 ኩንታል የሚጠጋ ስንዴ መጥቷል። ስድስት ካርቶን ኮቾሮ ነበር ልጆች በልተውታል። ስኳርም የተወሰነ ከረጢት መጥቷል። ሰው እናክማለን ብለውም ቦታ እየያዙ ነው " ብለዋል።
በግብርና የሚተዳደሩት አቶ አሕመድ እንደሚሉት፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ እርሻቸው ለመመለስ ቸግሯቸዋል።
“. . . ያንን ሁሉ ሬሳ አይተን ልቦናችን ወደ ሥራ አይመራንም። ሰው ዝም ብሎ ሐዘኑን እየተካፈለ ነው። ቅዳሜ ከሞተው ሰው መካከል የተቀበረ፣ አሞራ የጎተተውም አለ” ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል።
ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት ማሳ ውስጥ ተደብቀው ሕይታቸውን እንዳተረፉ ተናግረዋል።
አሁን መከላከያ ሠራዊት እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል በመኖሩ መረጋጋት ቢመለሰም፣ ሙሉ በሙሉ ከስጋት እንዳልተላቀቁ ገልጸዋል።
" ይሄ ማስጠንቀቂያ ነው፣ ከሦስት ቀን በኋላ ወደ አገራችሁ ግቡ፣ እዚህ እንዳትቀመጡ፣ መጨረሻ ላይ ስንመጣ የሚተርፍ ሰው የለም ብለውናል። መንግሥት ከዚህ ያንሳን " ሲሉ ተማጽነዋል።
“ ሰባት ልጆቼን ምን ላብላቸው ? ”
በቶሌ ቀበሌ፣ ጨቆርሳ መንደር የሚኖሩት የሰባት ልጆች አባት የሆኑት አቶ አብዱ* አሁን በአካባቢው የመከላከያ ሠራዊት እና ልዩ ኃይል በመግባቱ ሰላም ቢመለስም፣ ልጆቻቸውን የሚያበሉት ምግብ እንደሌላቸው ተናግረዋል።
አርሶ አደሩ አቶ አብዱ በጥቃቱ የአጎቶቻቸውን ልጆች አጥተዋል። ቤት ንብረታቸውም ተዘርፏል።
ከመጋዘናቸው 110 ኩንታል በቆሎ እና 15 ኩንታል ሩዝ እንዲሁም አምስት በሬን ጨምሮ በግ እና ፍየል እንደተዘረፉ ተናግረዋል።
“የተፈጸመው አሰቃቂ፣ ዘግናኝ ጥቃት ነው። ትላንትም ሰው ቀብረናል። ሳይቀበር ጫካ የቀረም አለ። አንድ ጉድጓድ ውስጥ 63 ሰው የተቀበረበት ቦታ አለ። ከእነዚህ 40 የሚሆኑት ሕጻናት ናቸው” ይላሉ።
ጨምረውም “. . . አሁን እኮ አንድ ኪሎ ምግብም የለንም። ልብስም ጫማም የለንም። መንግሥትም አልረዳንም። ከዝርፊያ የተረፈውን እህል ቀቅለን ንፍሮ ነው የምንበላው። ተጨፈጨፍን አሁን ደግሞ የረሃብ ጦር እየወጋን ነው ” ብለዋል።
አቶ አብዱ፣ ልጆቻቸውን መመገብ እንዳልቻሉና በአካባቢው የተሰማሩት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለሕጻናት ብስኩት እየሰጧቸው እንደሚገኙ ተናግረዋል።
“መከላከያዎች የተወሰነ ኮቾሮ እየሰጧቸው ነው እንጂ ሰባት ልጅ እንዴት ይደረጋል? ገና ዓመት ያልሞላት ልጅ አለችኝ. . . ረሃቡ አሳሳቢ ነው።”
ጥቃቱ የተፈጸመ ዕለት እሳቸው ከቀበሌው ወጥተው እንደነበርና ባለቤታቸው እና ልጆቻቸው ማሳ ተደብቀው እንደተረፉ ተናግረዋል።
አቶ አብዱ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሰው ቤት ተጠልለው እንዳሉና እናቷ የተገደለችባት የ15 ቀን ልጅን ጨምሮ በአንድ ቤት ውስጥ በርካቶች እንደሚገኙ ገልጸዋል።
“አሁን እኮ አባ ወራ ብቻውን፣ እማወራ ብቻዋን ቀርተዋል። ምን ተረፍን ይባላል? ከዚያም ብሶ ረሃብ ሊጨርሰን ነው” በማለት እርዳታ እንዲደረግላቸው ተማጽነዋል።
“ ለምን እናርሳለን ? ”
ስልሳው የተባለ መንደር ውስጥ ተወልዶ ያደገው ከማል* በጥቃቱ ወንድሙን አጥቷል።
የሸቀጥ ሱቁ እንደተዘረፈ እና ዘመድ ቤት ተጠልሎ እንደሚገኝ ተናግሯል።
“ዘመድ ቤት፣ ጓደኛ ቤት፣ በየበረንዳው፣ በየመስጆዱ ነው ተጠልለን ያለው” ብሏል።
ከማል ያሳርሰው የነበረው መሬት እንደነበረው፣ ከጥቃቱ ወዲህ ግን ወደ እርሻ የተመለሰ ሰው በመንደራቸው እንደሌለ ገልጿል።
“ለምን እናርሳለን? ወቅቱ እኮ ታርሶ፣ ነጭ ማዳበሪያ የሚደረግበት ነበር። ግን ስንት ንብረት ቀለጠ! 4 ሄክታር በቆሎ እና አንድ ሄክታር ሩዝ አዘርቼ ነበር። ያው ቀልጦ ቀረ።
እና ለምን ብዬ ነው ሁለተኛ ወጪ አውጥቼ ማዳበሪያ የማስረጨው ? ለምን አስኮተኩታለሁ። ላስኮትኩት ብልስ መቼ ገንዘብ አለን? ገንዘባችን፣ ንብረታችን ተወስዷል። ሰው እንዲሁ እየተንቀዋለለ ነው።”
ከማል እንደሚለው ከሆነ ፣ ከየትኛውም የመንግሥት አካል የምግብ እርዳታ እስካሁን አልደረሳቸውም። የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለሕጻናት ብስኩት ሲሰጡ መመልከቱን ጠቅሷል።
“የተራረፈ በቆሎ እየቀቀልን ተካፍለን ነው የምበላው። ጨው እንኳን የለንም። መከላከያዎች ከቀለባቸው አዋጥተው ለሕጻናት እና ለእናቶች ጠዋት አንድ፣ ማታ አንድ ብስኩት ሲሰጡ አይቻለሁ። ግን ይሄ እስከ መቼ ያዘልቃል?” ይላል።
የሰኔ ወር ሰብል የሚኮተኮትበት እንደነበረ፣ በጥቃቱ ሳቢያ ሥራ በመስተጓጎሉ ግን አዝመራው በአረም እየተበላ መሆኑን ተናግሯል።
“. . .ሰብል መኮትኮቱ ቀርቶ እኛ ሰው አጥተናል። ስለ በቆሎ አዝመራ ማን ያስባለል? ነፍስ ይቀድማል። የሞተው ሰው ወደ 500 ደርሷል እየተባለ ነው።”
ማኅበረሰቡ አሁን ያለውን ምግብ ተካፍሎ ቢበላም፣ ከጥቂት ቀናት በላይ እንደማያልፍ ይናገራል። እርዳታ በአፋጣኝ እንዲሰጣላቸውም ይጠይቃል።
“መከላከያ ስላለ አሁን ሰላም ነን። መከላከያ ከወጣ ግን ራሱን መከላከል የሚችል ሰው የለም። አሁንም ፈርተን ግማሻችን ስንተኛ፣ ግማሻችን እንጠብቃለን። አንድ ሸንኮራ ‘በሥነ ሥርዓት ተጠቀሙ’ ተብሎ ለሁለት ተካፍለን እንበላለን። በቋፍ ነው ያለነው” ሲል አክሏል።
* ቃላቸውን የሰጡ ግለሰቦች ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው ተቀይሯል።
Credit : ቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት

#DoubleA
የ “Double A QR Ethiopia” የሞባይል መተግበርያን በስልክዎ በመጫን በትክክለኛው የ Double A ወረቀት ካርቶን ላይ የሚገኘውን የ QR ኮድ የሞባይል መተግበሪያውን ተጠቅመው ስካን በማድረግ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ይሸለሙ::
መተግበርያውን ለማውረድ:
Link: https://bit.ly/3KGYCxC Or
https://da-cloud.advanceagro.net/index.php/s/WYovIsmE4u2Kz6y
ለተጨማሪ መረጃ: https://DoubleArewards.com/Ethiopia

" ፏን ኋን ሲሚንቶን እንዳትጠቀሙ " - ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
ፏን ኋን ኃ/ተ/የግ/ማህበር ፏን ኋን ሲሚንቶ CEM II 32.5N እና CEM I 42.5N የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ CES 28: 2013 ያላሟላ በመሆኑ ማስተካከያ እስኪያደርግ ድረስ ከሐምሌ 09/2013 ዓ ም ጀምሮ የብሔራዊ ደረጃ ምልክት እና ምርት ጥራት ሰርተፍኬት የመጠቀም ፈቃዱ ታግዶ ነበር።
ነገር ግን የብሔራዊ ደረጃ ምልክት የመጠቀም ፈቃድ እና ምርት ጥራት ሰርተፍኬት ላይኖራቸው CEM II 32.5 N ሲሚንቶ ምርት በገበያ ላይ በመገኘቱ እና ከምርቱ ጥራት ጋር ተያይዞ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በደረሰው ጥቆማ መሰረት ሰኔ 10/2014 ዓ.ም በፋብሪካው በአካል በመገኘት ምርት ማምርቱና እና አለማምርቱን ማረጋገጥ መቻሉን አሳውቋል።
በመሆኑም የብሔራዊ ደረጃ ምልከት የመጠቀም ፈቃድ እና ምርት ጥራት ሰርተፍኬት ታግዶ እያለ ጥራቱና ድህንነቱ ያልተረጋገጠ ምርት በተጭበረበር መልኩ በማምርት የህብረተሰብ ድህንነት እና ኢኮኖሚ የሚጎዳ ፏን ኋን ሲሚንቶ ወደ ገበያ ያሰራጨ በመሆኑ በድርጅቱ ላይ ውሳኔ መተላለፉን ገልጿል።
የተላለፈው ውሳኔ ፦
1. በራሱ ወጭ ፏን ኋን ሲሚንቶ ምርቱን ከሰራጨበት የሀገሪቱ የገበያ ቦታዎች ላይ እንዲሰበስብ
2. ፏን ኋን ሲሚንቶ ምርት ጥራት ያልተረጋገጠ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ ከማዋል እንዲቆጠብ ተወስኗል ሲል ሚኒስቴሩ ዛሬ አሳውቋል።

#ነዳጅ
የነዳጅ ማደያ በሌለባቸው ከተሞችና አከባቢዎች በሕገወጥ ንግድ ለሚከናወነው የነዳጅ ችርቻሮ ሽያጭ የወጣ አዲስ መመርያ፣ የነዳጅ ማደያ ካለበት በ20 ኪሎ ሜትር በሚርቁ አካባቢዎች የነዳጅ ውጤቶች በቸርቻሪዎች እንዲሸጡ መፈቀዱን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
አዲሱ መመርያ ማደያ በሌለባቸው አካባቢዎች የነዳጅ ውጤቶች የሚሸጡበትን የዋጋ ተመን የሚሰላበትን መንገድ ያስቀመጠ ሲሆን ቸርቻሪዎች የትርፍ ህዳጋቸው 5 በመቶ እንደሚሆን ወስኗል፡፡
ይህ የትርፍ ህዳግ መንግሥት ለመደበኛ የነዳጅ ማደያዎች ካወጣው የ0.23 በመቶ ትርፍ ህዳግ አንፃር ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡
መመሪያውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን በጋራ እንዳወጡት የተገለፀ ሲሆን በችርቻሮ የሚቀርበው ነዳጅ ተገቢ ባልሆነ ዋጋና በሕገወጥ ንግድ መልክ የሚከናወን በመሆኑ ይህንኑ የአሠራር ክፍተት ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
መመርያው የነዳጅ ችርቻሮ ንግድ የሚመራበት የነዳጅ ዋጋ የሚወሰንበት፣ ቁጥጥር የሚደረግበትና የአካባቢ ደኅንነት የሚጠበቅበት የአሠራር ሥርዓት የሚዘረጋ ነው፡፡
ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-06-22-2
(ሪፖርተር ጋዜጣ)

#AddisAbabaUniversity
የፀጥታ ችግር ካለባቸው ምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች የመጡ መደበኛ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች የክረምት እረፍት ጊዚያቸውን በዩኒቨርሲቲው እንዲቆዩ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ በመጠበቅ ላይ ናቸው።
ቲክቫህ በጉዳዩ ዙሪያ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑትን ማቲዎስ እንሰርሙ (ዶ/ር) ጠይቋል።
"የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች ጥያቂያቸውን ለተማሪዎች አገልግሎት በማመልከቻ በማቅረብ ምላሽ እንደሚሰጣቸው" ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
"ከተማሪዎች ዲን ጋር በመሆን እያንዳንዱን ጥያቄ ኬዝ በኬዝ በማየት እና አመልካቾቹን ቃለመጠይቅ በማድረግ ምላሽ ይሰጣል" ብለዋል።
በተጨማሪም አካል ጉዳተኛ የሆኑ እና የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ተማሪዎችንም በመለየት ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በግቢው ስለሚቆዩ እና የክረምት ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ስለሚገቡ የዶርም እጥረት መኖሩን በመግለጽ የተማሪዎቹ ጥያቄ ኬዝ በኬዝ እንደሚታይ ተናግረዋል።
More : @tikvahuniversity

#ፍርድ
በጉራ ፈርዳ የእርስ በርስ ግጭት በማስነሳት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አንዲደርስ ያደረጉ 45 ተከሳሾች እንደ ወንጀል ተሳትፏቸው እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አንዲቀጡ መወሰኑን የፍትህ ሚኒስቴር አሳውቋል።
በደቡብ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን በጉራ ፈርዳ የእርስ በርስ ግጭት በማስነሳት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አንዲደርስ ያደረጉ 45 ተከሳሾች እንደ ወንጀል ተሳትፏቸው እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አንዲቀጡ ተወሰኖባቸዋል ።
የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሚዛን -ቦንጋ-ጋምቤላ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት ነው ።
ተከሳሾች ከ2011 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ባሉ ጊዚያት የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም በወረዳው የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች ምንም መሬት የላቸውም፤ መሬታችንን ለቀው መሄድ አለባቸው በማለት በደቡብ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን በጉራ ፈርዳ ወረዳ የሚኖሩ የሸኮና የመዠንገር ብሔረሰቦች በአማራ ብሔር ላይ የጦር መሳሪያ አንስተው የእርስ በርስ ጦርነት እንዲነሳ ለማድረግ በማሰብ ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም በጉራ ፈረዳ ወረዳ ጌኒቃ ቀበሌ ሌንጣ መንደር አንድ የሸኮ ብሔረሰብ ተወላጅ ተገድሎ በመገኘቱ ይህን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ገዳዩ ማን እንደሆነ ባልታወቀበት ሁኔታ ልጃችንን የገደሉት አማራዎች ናቸው፤ የእኛ ሰው ሞቶ አማራ እዚህ ሀገር ቆሞ አይሄድም በማለት ሌሎች የጦር መሳሪያ እንዲያነሱ በማድረግ ፦
- የ30 (ሰላሳ) ሰዎች ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ አንዲጠፋ፤
- 14 (አስራ አራት) ሰዎች የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ፤
- 3,930,850. (ሶስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ሺህ ስምንት መቶ ሀምሳ ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም
- 5,273 (አምሰት ሺ ሁለት መቶ ሰባ ሶስት ) የሚሆኑ የአከባቢው ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉ ያደረጉ በመሆኑ ተከሳሾች በህብረትና በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የእርስ በርስ ጦርነት ማስነሳት ወንጀል በጠቅላይ አቃቤ ህግ ዘርፍ የተደራጁና ደንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶ ነበር።
ዐቃቤ ህግ ወንጀሉ በተፈፀመበት ቦታ በመገኘት ከፖሊስ ጋር በመሆን ከወንጀል ምርመራው አንስቶ ክስ መስርቶ ሲከራከር እንዲሁም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሚዛን -ቦንጋ-ጋምቤላ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን ሲመለከተው ከቆየ በኋላ በ45 ተከሳሾች ላይ እንደ ወንጀል ተሳትፏቸው የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።
በዚህም መሰረት የፌዳ,ደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሚዛን -ቦንጋ-ጋምቤላ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት በ45 ተከሳሾች ላይ የሚከተለውን የቅጣት ወሳኔ አስተላልፏል።
➡️ ኮ/ብል ኢሳቅ ጃፍሮ የተባለ #ፖሊስን ጨምሮ ስምንት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ23 ዓመት ፅኑ እስራት፤
➡️ ሶስት ተከሳሾች በ18 ዓመት፣
➡️ አራት ተከሳሾች በ16 ዓመት ፣
➡️ አራት ተከሳሾች በ15 ዓመት ፣
➡️ ሰባት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ10 ዓመት
➡️ አስራ ዘጠኝ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው ከ8 ዓመት ከ5 ወር እስከ 3 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል።
#ፍትህ_ሚኒስቴር

#FAO #ETHIOPIA
የዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) በትግራይ ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮች ለክረምቱ መዝራት እንዲችሉ አስፈላጊው ግብዓት በአስቸኳይ እንዲደርሳቸው መደረግ እንዳለበት ገልጿል።
ዘርና ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮቹ በወቅቱ መድረስ ካልቻለ የእርሻ ወቅቱ ሊያልፍ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩ ተገልጿል ፤ ይህም ሁኔታ በጦርነት ለተጎዳችው የትግራይ ክልል የምግብ ዋስትና በበለጠ የከፋ እንደሚያደርገው FAO ትላንት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።
በተያዘው ክረምት የዝናቡ ሁኔታ ጥሩ ሊሆን እንደሚችል እየታየ ሲሆን ይህም በክልሉ የመነመነውን የምግብ አቅርቦት ለማሻሻል ወሳኝ ዕድል እንደሆነም ነው።
እንደ FAO ከሆነ በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የትግራይ አርሶ አደሮች የመሬት ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው የዝናብ መምጣቱን እየተጣበበቁ ቢሆንም የግብርና ግብዓቶች በተለይ የማዳበሪያና ዘር አቅርቦት ውስንነት ስጋትን ደቅኗል።
FAO እና አጋሮቹ የኢትዮጵያ መንግሥት ማዳበሪያን ለመግዛት ባቀረበው ጊዜ በአፋጣኝ ለመሸመትም 96 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገናል ብለዋል።
በባለፉት ወራት FAO እና አጋሮቹ 11 ሚሊዮን ዶላር በማሰባሰብ 10 በመቶውን የማዳበሪያ ፍላጎት ለማሟላት ቢችሉም ቀሪውን ግብዓት ለመሸፈን 85 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
ተቋሞቹ 60 ሺ ቶን ማዳበሪያ እና በአገር ውስጥ የሚመረተውን 4 ሺ ቶን ዘር ከሚያስፈልገው 8 % ቢሆንም ይህንን ለአርሶ አደሮቹ ለማቅረብ መንገዶችን በመፈለግ ላይ ናቸው።
ዘር መዘራት ባለበት ወቅት ለማድረስ ያለው ጊዜ አጭር መሆኑ ጋር ተያይዞም ግብዓቶቹ በአስቸኳይ ሁኔታ መቅረብ እንዳለባቸውም FAO አፅንኦት ሰጥቷል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/FAO-06-23

የነዳጅ ድጎማው መነሳት !
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ (ከቀናት በፊት በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ/ኢቲቪ ላይ ቀርበው የተናገሩት) ፦
" ነዳጅ ላይ መንግስት እያደረገው ያለው ድጎማ ብንፈልገውም ይዘነው መቀጠል የምንችለው አይደለም። ስለ 100 ቢሊዮን፣ 130 ቢሊዮን ነው እያወራን ያለነው።
ይሄ የስንት ድሃ ጎሮሮ ይዘጋ፣ ስንት ት/ቤት ይከፍታል፣ ስንት መንገድ ይሰራል የሚለውን ማሰብ ነው ያለብን። በጣም የተሳሳተ አቅጣጫ ነው።
የአሜሪካ ኤምባሲን ነዳጅ ምንደጉመው ለምንድነው ? የመንግስትም ተቋማት በጀታቸውን ይዘው በስነስርዓት ባለው ቆጥበው መጠቀም እየቻሉ እንደገና በተዘዋዋሪ የምንደጉማቸው ለምንድነው ? ከዚህኛው ኪዝ አውጥቶ ወደ ሌላኛው ኪስ ይሄ ደግሞ ምን ይፈጥራል የተዝረከረከር አሰራር ሁል ጊዜ ለስርቆት መንገድ ይከፍታል።
ወደ ጎረቤት ሀገሮች ነዳጅ በጄሪካን፣ በቦቴ እየተጫነ የሚሄደው ለምንድነው ? ይሄ ከአንዲት ድሃ እናት በመጣ ገንዘብ የሚገዛ ነው። ይሄ ፖሊስ (የድጎማው መነሳት) የሚጠቅመው በዋነኝነት ድሃውን የኢትዮጵያን ህዝብ ነው ብሎ ማሰብ በጣም ጠቃሚ ነው።
እንደጉማቸው የነበሩ ሰዎች መግዛት የሚችሉ ናቸው። ግን ይሄ ፖሊሲ Targeted ነው። አሁንም ሁሉንም በጥቅሉ መደጎም ትተን የሚገባውን እንደጉም ነው ዋናው የፖሊሲው ሀሳብ የማይገባው አቅም ያለው ገዝቶ ይጠቀም አነስተኛ ገቢ ያለውን ግን እንደጉም ነው። በዚህ አንፃር በጣም የታሰበበት ትክክለኛ ፖሊሲ ነው።
... የኑሮው ውድነት ላይ ያለው expectation direct impact የሚያደርጋቸው ነገሮች አሉ። እንዱሁ ግን የእኛ የንግድ ስርዓት ችግር ስለበት አንድ ይሄ ነገር ጨመረ ሲባል ሌላውን 10 ብር ስለሚጨምር ችግር ነው እሱን መቆጣጠር አለብን እንጂ ልክ ድጎማው ስለተነሳ አጠቃላይ የዋጋ ጭማሪ ይመጣል ማለት አይደለም መሆንም የለበትም እሱን መቆጣጠር አለብን።
ፖሊሲው ግን ለነገ የምናቆየው አይደለም በጣም important የፖሊሲ እርምጃ ነው። ታስቦበት የተሰራ ነው።
እርግጠኛ ነኝ ህዝቡም ውጤቱን እያየው ሲመጣ እውነትም ይሄ የዘገየ ፖሊሲ ነው ይላል። እንዴያውም ለምን እስካሁን አቆያችሁ ነው ጥያቄው መሆን ያለበት እሱን ሳይጠይቁን ያለፈው አልፏል ቶሎ ወደ ስራ ማስገባት ያለብን ነው የሚመስለኝ። "

#ZH
ያገለገሉ እና አዲስ ካሜራ እና የካሜራ እቃዎችን እንገዛለን እንሸጣለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ያገኙ https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEUTeB3LSYVFukiuQw
ይደውሉልን 0911284905
አድራሻ= ቦሌ ወሎ ሰፈር HMM ህንፃ 2ኛ ፍቅ 205