TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.9K photos
1.58K videos
216 files
4.29K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DawitNega

በትግርኛ የሙዚቃ ስራዎች በእጅጉ የሚታወቀው አርቲስት ዳዊት ነጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ።

አርቲስት ዳዊት ህመም አጋጥሞት ያለፉትን ቀናት በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበር ተነግሯል።

የአርቲስት ዳዊት ነጋ የሙዚቃ ስራዎች የትግርኛ ቋንቋ ከሚያደምጡ ሰዎች ባለፈ ቋንቋውን በማያዳምጡትም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበሩ ናቸው።

ከሙዚቃ ስራዎቹ መካከል ፦ ባባ ኢለን፣ ዘዊደሮ፣ ወዘመይ፣ ቸቸኮላታ፣ ኣጆኺ ትግራይ፣ ቕዱስ ፀባያ የሚሉት ይጠቀሳሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DawitNega በትግርኛ የሙዚቃ ስራዎች በእጅጉ የሚታወቀው አርቲስት ዳዊት ነጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ። አርቲስት ዳዊት ህመም አጋጥሞት ያለፉትን ቀናት በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበር ተነግሯል። የአርቲስት ዳዊት ነጋ የሙዚቃ ስራዎች የትግርኛ ቋንቋ ከሚያደምጡ ሰዎች ባለፈ ቋንቋውን በማያዳምጡትም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበሩ ናቸው። ከሙዚቃ ስራዎቹ መካከል ፦ ባባ ኢለን፣…
#DawitNega

የአርቲስት ዳዊት ነጋ ቤተሰቦች እና ጓደኞች ለቢቢሲ ትግርኛ የሰጡት ቃል ፦

" ባደረበት ድንገተኛ ህመም ዓርብ ዕለት ነው አዲስ አበባ አዲስ ህይወት ሆስፒታል የገባው።

ባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት በጉንፋን መልክ የጀመረ ህመሙ ከተባባሰ በኋላ ዓርብ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ እስከ ቅዳሜ ድረስ ህክምና ሲደረግለት ቆይቷል።

ትናንት እሁድ ከሰዓት በኋላ ህመሙ ሲጸናበት ወደ ጽኑ ህሙማን ክትትል ክፍል ገብቷል ማታ 1፡ዐዐ ሰዓት አካባቢ ህይወቱ አልፏል።

ወደሆስፒታሉ ከመምጣቱ በፊት ህመሙን ለማስታገስ በቤት ውስጥ ግሉኮስ ይወሰድ ነበር።

ህመሙ ሲበረታበት ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ የስኳር መጠኑ መጨመሩን እና ህመሙ ወደ የሳንባ ምች (ኒሞኒያ) መቀየሩን ተነግሮታል።

የዳዊት አስከሬን ላይ ተጨማሪ ምርመራ ይደረጋል። "

Via BBC Tigrinya

@tikvahethiopia