TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስር ስለተፈቱ ግለሰቦች ምን አሉ ? ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፦ " ... ትላንት ክስ የተቋረጠላቸው የተሸነፉ ኃይሎች ክስ እንዲቋረጥ እና ከእስር ቤት እንዲወጡ ሲደረግ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል። ይህ ቁጣ የተቀሰቀሰው በሁለት ቡድኖች ነው። አንደኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ጭር ሲል የማይወድ ፣ ሁል ጊዜ እያጋጨ በሰበር ዜና ብር የሚሰበስብ፣ የት እንዳለ የማይታወቅ ካለበት ሆኖ ስንዋጋ…
#ተጨማሪ

ከእስር ስለተፈቱት ግለሰቦች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን ተናገሩ ?

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" ... ክስ የተቋረጠላችሁ ወገኖች ስላሸነፍን መበቀል እየቻልን ይቅር ማለትን ስለመረጥን ክስ አቋርጠን እናተን ሳይሆን ከእናተ ጀርባ ያለውን ህዝብ አክብረን የወሰን መሆናችንን አውቃችሁ ይህን እድል ሳታበላሹ እንድትጠቀሙበት ላሳስባችሁ እፈልጋለሁ።

ክስ ማቋረጥ ማለት ምህርተ መስጠት ማለት አይደለም። ክስ የተቋረጠለት ሰው በአግባቡ መጠቀም ካልቻለ መልሶ የክስ መዝገቡን መምዘዝ የሚቻል ስለሆነ።

በዚህ ጉዳይ ያዘኑ፣ የተቆጡ፣ የኢትዮጵያ ቁርጥ ቀን ልጆች እንዲገነዘቡ የምፈልገው የወሰድነው መድሃኒት ማስታገሻ አይደለም የወሰድነው መድሃኒት ፈዋሽ በመሆኑ የጎንዮሽ ጉዳት አለው ፤ ይጎረብጣል ያማል ! ለማዳን ብቻ ሳይሆን በጎንም የመጎርበጥ ባህሪ አለው።

ለጊዜው የሚያስታግስ ሳይሆን ለልጆቻችንም የድልና የአሸናፊነት መንፈስ የሚያላብስ ስለሆነ እንደኛ ደጋግማችሁ ስታስቡት ጠቀሜታው ጎልቶ ይታያችኃል እናም ደግማችሁ ለማሰብ ልባችሁና አእምሯችሁ እንዲከፈት ዋናው አላማ የምትወዷትን ሀገር ኢትዮጵያን አንድ አድርገን ለማፅናት ካለን ፍላጎት አንፃር ብቻ የመነጨ መሆኑን እንድትገነዘቡ ቢያንስ ቢያንስ ጉቦ በልተን እንዳለቀቅናቸው እንድታስቡ ላሳስባችሁ እፈልጋለሁ። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ድርድርን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አሉ ? ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦ " እስካሁን የተደረገ ድርድር የለም፤ እስከዚህ ደቂቃ ድረስ ፤ ስለድርድር ብዙ ሲወራ ሰማለሁ ግን እስካሁን ድርድር አላደረግንም፤ አላደረግንም ማለት እስከነአካቴው ድርድር የሚባል ነገር አይኖርም ማለት አይደለም። ድርድር ፣ ውይይት ማለት ችግር ተወግዷል ማለት ሳይሆን ችግር ለማስወገድ አማራጭ Alternative መንገድ አለው…
#ተጨማሪ

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስለ ድርድር የተናገሩት ፦

" ... አንድ የእስራኤል ፕሬዜዳንት በአንድ ወቅት ያሉትን ማስታወስ ፈልጋለሁ፤ እኚህ ፕሬዜዳንይ እስራኤል እየተዋጉ ከሀማሶች ጋር ከሂዝቦላህ ጋር ይደራደራሉ።

በነገራችን ላይ TPLF ከኦነግ ጋር ይደራደር ነበር፣ ደርግ ከሻዕቢያ እና TPLF ጋር ይደራደር ነበር ድርድር ማለት እርቅ ማለት አይደለም። ድርድር ውስጥ ብዙ የሚገኙ ነገሮች አሉ። ከምሳሌ ... ምሳሌው ይቅርብኝ ግን አሉ ጥቅሞች።

እናም እኚህ የእስራኤል ፕሬዜዳንት በጦርነት ጊዜ ምንም የሰላም ጫላንጭል እንደሌለ ሰላም ተስፋ እንደሌለው አስበን ጨክነን እንዋጋለን ፤ በድርድር ጊዜ ተጋጭተን እንደማናውቅ ጦርነት የሚባል እንዳልነበር በሰከነ መንፈስ እንደራደራለን ሁለቱንም የምናደርገው ለእስራኤል ጥቅም ነው ብለዋል።

እኛ በውጊያው ጊዜ የነበረን አቋም እና ሂደት ለምክር ቤት መግለፅ አይጠበቅብኝም አቋማችን ግልፅ ነው። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ምንም የማንደራደር መሆኑ ግልፅ ነው።

አሁንም የምናደርገው የዛ ተገላቢጦሽ ሆኖ መታየት አለበት። ታስታውሳላችሁ በዝግ ስንወያይ ኢትዮጵያን አፍርሰው እነዚህ ሰዎች አዲስ አበባ አይገቡም ብያቹ ነበር በቲቪ አልተላለፈም ያ ውይይት ነበራችሁ ብዙዎቻችሁ ያኔ የተወያየነው ነገር ነው ተፈፅሞ ያየነው።

አሁንም #በድርድር የሚባል ነገር ካለ በዛው sprint ማየት ጥሩ ነው። የሰላም አማራጭ ካለ ፤ TPLF ቀልብ ከገዛ በጦርነት እንደማያዋጣው እንደማያሸንፍ ከተገነዘበ እኛ በደስታ ነው የምናየው። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba📍 በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ፤ የቦሌ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ሃላፊ በህገ ወጥ ንግድ ምክንያት የታሽገን የንግድ ቤት እከፍትልሃለሁ በሚል 100 ሺ ብር #ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ መያዙን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ፤ የንግድ ፅ/ቤት ሃላፊው አቶ አለማየሁ ዋንዴቦ ታሽጎ የነበረን የንግድ ቤት በህገ ወጥ መንገድ ለመክፈት ተስማምቶ…
#ተጨማሪ

የቦሌ ክ/ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊው አቶ አለማየሁ ዋንዴቦ 100 ሺህ ብር ጉቦውን የተቀበሉት ታሽጎ የነበረውን " አቤኔዘር የተሽከርካሪ እጥበት አገልግሎት ድርጅት " ን አስከፍታለሁ ፤ የንግድ ፈቃዱንም እንዲታደስ አደርጋለሁ በማለት ነው።

የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንዳለው ከሆነ፤ የድርጅቱ ባለንብረት በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ታሽጎ የነበረው ድርጅታቸው እንዲከፈትና ንግድ ፈቃድ እንዲታደስላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ መነሻ በማድረግ የስራ ኃላፊው 100,000 ብር ጉቦ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በኃላም 22 ጎላጎል ህንጻ በሚገኘው ካፌ ውስጥ ብሩን ሲቀበሉ #እጅ_ከፍንጅ ተይዘዋል ፤ አሁን ላይም ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ፖሊስ አስረድቷል።

#AMN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Tigray, #Mekelle 📍 ትላንትና በጉዞ ላይ እንደነበሩ የተነገረላቸው አስፈላጊ የሆኑ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶችን የጫኑት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሸከርካሪዎች የትግራይ ክልል መዲና መቐለ ደርሰዋል። ሁሉም (50ውም) ተሸከርካሪዎች በሰላም ነው መቐለ የደረሱት። ምን ይዘዋል ? ➡️ 1,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ እና ጥራጥሬ ፤ ➡️ 700 ሜትሪክ ቶን የጤና ፣ የተመጣጠነ ምግብ…
#WFP #USA #Ethiopia #TigrayRegion

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ወደ ትግራይ ክልል #ተጨማሪ ኮንቮይዎችን ለመላክ ዝግጁ መሆኑና ፍቃድም እንዳለው ገልጿል።

ቀጣዩ የሰብዓዊ እርደታ ኮንቮይ በተቻለ ፍጥነት በሰላም እንዲሄድ በአፋር ክልል ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፥ አሜሪካ ትላንት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ ፤ ከ1,700 ሜትሪክ ቶን በላይ ነፍስ አድን ሰብአዊ እርዳታ ትግራይ መግባቱ መልካም ዜና ነው ብላለች።

የእርዳታው እንዲደስ ትብብር ያደረጉትን የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች እና የአፋር ክልል አስተዳዳሪዎችን እንደምታደንቅም ገልፃለች።

በተጨማሪም ፤ አሜሪካ የትግራይ ኃይሎች ከአፋር ክልል ኤሬብቲ መውጣታቸውን እንደምትደግፍ ገልፃ ከሌሎችም የአፋር አካባቢዎች የትግራይ ኃይሎች ቢወጡ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብላለች።

አሜሪካ በትላንት መግለጫዋ የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ባለስልጣናት አሁን በታየው ለውጥ ቀጥለው ግጭቱን በድርድር፣ በዘላቂነት መፍታት የሚችሉበት መንገድ ማግኘት አለባቸው ብላለች።

ይህ እንዲሆንም በትግራይ ክልል መሠረታዊ አገልግሎቶች መመለስ እንዳለባቸው እና አካታች ፖለቲካዊ አካሄድ መተግበር እንዳለበት ገልጻለች።

የአሜሪካ መግለጫ : https://www.state.gov/delivery-of-humanitarian-assistance-in-tigray/

@tikvahethiopia