TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፡ " የደም ማድረቅ እርቅ ስነ ስርዓት " በሸበል በረንታ ተካሂዷል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን በሸበል በረንታ ወረዳ ገዳያሱ ቀጠና የእርስ በእርስ ግድያን ለማስቆም እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የእርቅ ስነ ስርዓት ተካሄዷል፡፡

🗣 የቀጠናዉ አስተባባሪ ም/ሳጅን ብሩክ አለማየሁ ፦

" ከሃይማኖት አባቶች እና ከሃገር ሽማግሌዎች ጋር በጋራ በመሆን ለ3ኛ ጊዜ እርስ በእርስ የተጋደሉ ቤተሰቦችን አስታርቀናል፡፡ ከዚህም ጐን ለጐን የመግደል ሙከራዎችን አብረን እናስታርቃለን፡፡

ወደፊት እርስ በእርስ የተጋደሉ ቤተሰቦችን የመለየት እና ለማስታረቅ ኘሮግራም ይዘናል፡፡ ጀምረን የምንተወው ነገር የለም ደጋግመን በመልፋት ነው የምናስታርቀዉ፡፡

የደም እርቅ ሲባል በአንድ ቀንና በሁለት ቀን ብቻ የሚበቃ አይደለም ዛሬ የተካሄደው እርቅ 5 ቀን ሙሉ የወሰደብን ነው ተስፋ ቆርጠን የምንተወዉ ነገር የለም፡፡

የሁለት ተጐጂ ቤተሰቦችን ሊያሳምን የሚችል ወገን ጋር አብሮ በመሆን እየሰራን ነው፡፡ ከጠነከርን የሚከብደን ነገር የለም ትልቁ ነገር ተስፋ አለመቁረጥ ነው "

🕊

🗣 አስታራቂ ሽማግሌ ሰምዓኔ ንጉሴ ፦

" ባህላዊ የሽምግልና ስርአቱን በጠበቀ መልኩ ህዝባችን ሲጎዳ አናይም በማለት ደከመን፣ሰለቸን ሳንል ሌሊት ብርዱን ቀን ፀሃዩን ተቋቁመን እየሰራን ነው፡፡

በመጀመሪያ ከተጐጂ ቤተሰብ ፊት እግዚኦታ እንቆማለን ከዚያም የወር ባዕላትን ጠብቀን በመቀጣጠር ሁለት የተጐጂ ቤተሰቦችን እንዲታረቁ የማሳመን፣ የማቀራረብ እና የማስታረቅ ስራ እንስራለን፡፡

ከእርስ በእርስ ግድያ የሚገኘው አንድም ነገር የለም፡፡

ሌላ ግድያ እንዳይፈፀም፣ ዕርቀ ሠላም እንዲወርድ፣ ሽማግሌ ያለውን በመስማት ለሰላም ዘብ በመቆማቸዉ ለታራቂ ቤተሰቦች ፍቅሩን ያጽናልን "

#ሽበል_በረንታ_ወረዳ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ችሎት #ብርጋዴር_ጄነረል_ተፈራ_ማሞ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ተመልክቷል። በዚህም ፤ የጊዜ ቀጠሮውን ጉዳይ መርማሪ ፖሊስ ምርመራየን ጨርሸ የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቢ ህግ ለመላክ በዝግጅት ላይ ነኝ ያለ ሲሆን የክልል ዐቃቤ ህግ በችሎት ቀርቦ አዎ ምርመራው አልቋል የክስ መመስረቻ ጊዜ 15 ቀናት ይሰጠኝ…
#NewsAlert

ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጡ ታዘዘ።

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኔ 3/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ የዋስትና ጥያቄ ላይ ብይን ለመስጠት ተሰይሟል።

በመሆኑም ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ ዋስትና የሚከለክል ሆኖ ስላላገኘው በ30,000 /ሰላሳ ሽህ ብር/ ዋስትና እንዲወጡ አዟል።

መረጃው የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UNHRC የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት በኢትዮጵያ ተፈፅመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለመመርመር ላቋቋመው ቡድን ፋቱዋ ቤንሱዳ ሊቀመንበር አድርጎ ሾመ። ፋቱዋ ቤንሱዳ ጋምቢያዊ ዜግነት ያላቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) በአቃቤ ህግነት አገልግለዋል። በተጨማሪም በመርማሪ ቡድኑ ውስጥ ሌሎችም ሁለት አባላት የተሾሙ ሲሆን የህግ ባለሙያዎቹ…
ፋቱዋ ቤንሱዳ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ።

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት፤ በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል የሚባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲመረምር ያቋቋመውን ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ኮሚሽን በሊቀመንበር ሲመሩ የነበሩት ፋቱዋ ቤንሱዳ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ።

በምትካቸው ኬንያዊቷ የህግ ባለሙያ ካሪ ቤቲ ሙሩንጊ ተሹመዋል።

ጋምቢያዊቷ ፋቱዋ ቤንሱዳ ለምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በፃፉት ደብዳቤ ከሊቀ መንበርነታቸው ሆነ ከአባልነታቸው መልቀቃቸውን አሳውቀዋል።

ከኃላፊነታቸው የለቀቁት፤ በብሪታኒያ እና በጋራ ብልጽግና (ኮመን ዌልዝ) አገራት የጋምቢያ ከፍተኛ ኮሚሽነር ሆነው በሀገራቸው መንግስት በመሾማቸው፤ የጥቅም ግጭትን ለማስወገድ እንደሆነ ገልፀዋል።

በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም በአቃቤ ህግነት ያገለገሉት ቤንሱዳ ይዘውት የነበረው የባለሙያዎች ኮሚሽን የሊቀመንበርነት ቦታ፤ ኬንያዊቷ ጠበቃ ካሪ ቤቲ ሙሩንጊ ተረክበውታል።

ኬንያዊቷን ለቦታው የሾሙት የተድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ ቤት ፕሬዝዳንት ፌዴሪኮ ቪሌጋስ ናቸው።

Credit : www.ethiopiainsidet.com

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

የክረምት ወቅት እየገባ መሆኑን ተከትሎ ከባድ ዝናብ እየጣለ ነው። በተለይ በዚህ ወቅት መኪና የምታሽከረክሩ ልዩ ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል።

🌧 ረጋ ብለው ያሽከርክሩ ፤

🌧 ርቀትዎን ይጠብቁ፤

🌧 መብራት ያብሩ ፤

🌧 በጭለማ ከማሽከርከር ይቆጠቡ፤

🌧 ከባድ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት አያሽከርክሩ ፤

🌧 በድንገት አይቁሙ፤

🌧 በሚሄድ ውሃ ላይ ከማሽከርከር ይቆጠቡ ፤

🌧 እግረኞችን በጥንቃቄ ያስተውሉ ፤

ውድ ቤተሰቦቻችን መልዕክቱን ከአዲስ አበባ ትራፊክ ማነጅመንት ኤጀንሲ የወሰድነው ሲሆን እናተም ለሌሎችም በማጋራት ቤተሰቦቻችሁ፣ ጓደኞቻችሁ፣ ወዳጆቻችሁ ጥንቃቄ ያድረጉ ዘንድ አስታውሷቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA በሃገራችን የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል ! በመጪው እሁድ ሰኔ 5/2014 በአዲስ አበባ ስቲዲዮም ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር በርካታ እንግዶች እየገቡ ይገኛሉ። ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስጠራው ይህ ውድድር ከ56 በላይ ሀገራት የሚወዳደሩበት ሲሆን ለውድድሩ ከፍተኛ ዝግጅት ሲካሄድ ቆይቷል ። ውድድሩን…
#Update

ዛሬ በአዲስ አበባ ሀርመኒ ሆቴል ለዓለም ዓቀፉ የቁርዓን ውድድር ማጣሪያ ሲካሄድ ውሏል።

የፊታችን እሁድ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የቁርኣን ሂፍዝ ውድድር እንደሚካሄድ ይታወቃል።

በዚህ ልዩ ውድድር ላይ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የመጡ ተወዳዳሪዎች መካከል ዛሬ የማጣሪያ ውድድሩ እየተካሄደ ሲሆን ውድድሩ በዓለም ዓቀፍ ዳኞች የተመራ ነበር።

በእሁዱ ውድድር የሶማሌ ክልሉ ተወላጅ ኢብራሒም አብዱራህማን ኢብራሒም ኢትዮጵያን ወክሎ ለውድድሩ መቅረቡን ለማወቅ ተችሏል።

ማስታወሻ ፦

- አዘጋጁ ዘይድ እብን ሳቢት የቁርአን ማህበር

- ውድድሩ የሚካሄደው በአዲስ አበባ ስታዲየም

- እሁድ ሰኔ 5/2014 ከጥዋት 12:00 ጀምሮ

- ከ56 በላይ ሀገራት ይወዳደሩበታል ተብሎ ይጠበቃል

- የመግቢያ ዋጋ መደበኛ 500 ብር VIP 1000 ብር

- ለበለጠ መረጃ የሞባይል ስልክ ቁጥር ፦ 0911755245 / 0911723051

ፎቶ ፦ ቢላል ቲቪ

@tikvahethiopia
ቴሌግራም ፕሪሚየም / Telegram Premium

ቴሌግራም አሁን #በነፃ እየሰጠ ያለው አገልግሎት #እንደተጠበቀ ሆኖ ተጨማሪ አገልግሎት የሚሰጥበትን እና ድርጅቱም ገቢ የሚያገኝበትን በክፍያ የሚሰጥ " ቴሌግራም ፕሪሚየም " የተሰኘ አገልግሎት በዚህ ወር ያስጀምራል።

ክፍያውን በተመለከተ ለጊዜው የተባለ ነገር የለም።

(የቴሌግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ እና መስራች ፓቬል ዱሮቭ የተላለፈ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert አሜሪካ አዲስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሾመች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ፤ በአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ምትክ አምባሳደር ማይክ ሀመር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው እንደሚሾሙ አስታውቀዋል። ሚኒስትሩ አምባሳደር ሳተርፊልድ በስልጣን ቆይታቸው ላበረከቱት አስተዋፆ ምስጋናቸውን አቅርበው አዲሱ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሀመር አሜሪካ በቀጠናው የጀመረችውን…
አምባሳደር ማይክ ሀመር ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሜሪካ በቅርቡ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ የሾመቻቸውን ማይክ ሀመርን ዛሬ በጽ/ቤታቸው አነጋግረዋል።

በውይይታቸውም ፤ በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን እንዲሁም በግጭቱ ወቅት ለተፈጸሙ በደሎች ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎች እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
#ደሴ

በቆሻሻ ማቃጠያ ውስጥ የነበረ የከባድ መሳሪያ ተተኳሽ ፈንድቶ በተማሪዎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

በደሴ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ስልክ አምባ ትምህርት ቤት በተለምዶ ሚካኤል ጀርባ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በነበረ የቆሻሻ ማቃጠያ ቦታ ከቆሻሻ ማቃጠያው የወዳደቁ የቁራሊዬ እቃዎችን እየሰበሰቡ የነበሩ ሶስት የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች የከባድ መሳሪያ ተተኳሽ ፈንድቶ በሶስቱም ላይ ጉዳት አድርሷል።

ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችም በአሁኑ ሰአት የህክምና አገልግሎት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የከተማው ማህበረሰብ አካባቢውን በሚገባ በመፈትሽ የተለየ ነገር ካገኘ ባቅራቢያ ለሚገኝ የጸጥታ ሀይል ጥቆማ በመስጠት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው የደሴ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ ፦ ለቲክቫህ ቤተስብ አባላት ፦

" የተለያዩ ገንዘብ የማግኛ / ሀብት ማፍሪያ መንገዶች " እየተባለ በዲጅታል ሚዲያው በኩል ከቀርብ ጊዜ ወዲህ በርካቶች እጅግ በስፋት እየተከሰቱ ነው።

እነዚህ አካላት ፍቃድ ይኑራቸው አይኑራቸው ፤ የመስሪያ አድራሻቸው ይታወቅ አይታወቅ ፣ የሚመራቸው / የሚያስተባብራቸው ግለሰብ ይኑር አይኑር የሚለውን በግልፅ ለማወቅ አዳጋች ነው።

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከዚህ በፊትም እንዳልናችሁ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችል እንቅስቃሴ ውስጥ ስትገቡ / ኢንቨስት ስታደርጉ እነዚህ ጥያቄዎች እንድትጠይቁ አደራ እንላለን ፦

1. ድርጅቱ / ተቋሙ እውቅና ያለው ፣ ፍቃድ ያለው ነው ? የሚሰራበትን ፍቃድ በይፋ አሳውቋል ?

2. በትክክል የሚታወቅ አድራሻቸው የት ነው ? ቢሯቸው ?

3. ለሚደርስብኝ ማኛውም አይነት ነገር ማንን ተጠያቂ ማድረግ እችላለው ?

4. የሚሰራው ስራ ምን ያህል ቀጣይነት አለው ? ነገ እንደማይቆም ምን ማስተማመኛ አለ ? ይህንን ማንስተማመኛ ማን ይሰጠኛል ? የሚሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ ያስፈልጋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የማጭበርበር እና የማታለል ድርጊቶች እየሰፉ በመሆናቸው ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

ብዙሃንን ሊጠቅም ያሚችል ማንኛውም ህጋዊ ስራ በሚስጥር፣ በድብቅ ፈፅሞ ሊሰራ አይችልም እና ውድ ቤተሰቦቻችን ማኛውም እንቅስቃሴ ስትጀምሩ ከላይ የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች በቅድሚያ መልስ እንዳያገኙ አድርጉ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ነጻሥልጠና

ስቴም ፖወር፣ ቪዛ እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጋራ በመሆን የመሰረታዊ የገንዘብ አያያዝ ትምህርት እና የስራ ፈጠራ ክህሎት ስልጠና በተለያዩ ምዕራፎች በመስጠት ከ600 በላይ ወጣቶች ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።

አሁን ላይ ይህ ስልጠና ተደራሽነቱን ለማስፋት የኦላይን አማራጭ በመጠቀም ስልጠናውን ለመስጠት ዝግጅት ያጠናቀቅን ሲሆን መስፈርቱን የምታሟሉ ለሥልጠናው እንድትመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

ከሥልጠናው በተጨማሪ የንግድ ማማከር እና ድጋፍ (Business development and consultation, including coaching, mentorship, and pitching) መከታተል እንዲችሉ፤ እንዲሁም ቢዝነሱ ፕሮቶታይፕ (prototype) የሚያስፈልገው ከሆነ ፕሮቶታይፕ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ጨምሮ ነጻ የማምረቻ ላብራቶሪ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅታችንን በመጨረስ ላይ እንገኛለን።

ዝርዝር መስፈርቶች https://telegra.ph/ጥቆማ-06-09

ለመመዝገብ : https://bit.ly/3tNHRKL

@tikvahethiopia