TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ። ማዕከሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ነው የተመረቀው። ለኩላሊት ህመምተኞች እፎይታን ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀው ዛራ ለምርቃት የበቃው በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የተሰራው የኩላሊት እጥበት ማዕከል…
#የኩላሊት_እጥበት_ማዕከል
በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል በተመረቀበት ወቅት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተናገሩት ፦
" ሰው በሚያውቀው በተማረበት በርካታ ድንቅ ስራ ሊሰራ እንደሚችል ዛሬ አይቻለሁ፤ ባየሁትም ነገር ተደስቻለሁ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ፕሮፌሽናሊዝም ጠፍቶ በመቆየቱ ምክንያት ማየት የሚገባንን ነገር ለብዙ ጊዜ ማየት ሳንችል ቆይተናል።
በምንችለው በተማርነው ሁላችንም አስተዋፅኦ ማድረግ አለብን።
ለከተማ አስተዳደሩም እንደ አዲስ ሲዋቀር ከተሰጡት ተልእኮ ውስጥ አንዱ የጤና ስራ ማስፋፋት ነው አሁን ተስፋ ሰጪ ነገሮችን ማየት ችለናል።
ሆስፒታሎች ንፁህና ለሁሉም ሰው የሚስማማ መሆን አለባቸው፤ መኖርያዎች ከተማዋ ባጠቃላይ ንፁህና ያማሩ እንዲሁም አረንጓዴ መሆን አለባቸው።
ለውበት ለአረንጓዴነት ለንፅህና ቢያንስ የገባን ሰዎች እንተባበር። ሌሎች ጊዜ ወስዶ ይገባቸዋል፤ ዋናው ፍርድ ቤትና ዳኛ ትውልድ ነው ፤ትውልድ ይፈርዳል። "
@tikvahethiopia