#ሀገራዊ_ምክክር 🇪🇹
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕ/ር መስፍን አርአያ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦
" በሀገራዊ ምክክሩ #ሁሉም ኢትዮጵያዊ አጀንዳ የሚያስይዝበት አሰራር ይዘረጋል።
የውይይት ሃሳቦች ከታች ወደ ላይ ነው የሚሰበሰቡት።
በውይይቱ ይህ ይነሳ ያ አይነሳ የሚባል ነገር የለም ። ኮሚሽኑ በአጀንዳዎች ላይ ጣልቃ አይገባም።
ምክክሩ ልሂቁ ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ባለመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሐሳቡ በጥቂቶች እንዳይጨናገፍ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ እናቀርባለን።
በቀጣይ በየክልሉ እንደ አመቺነቱ ጽሕፈት ቤቶች ይቋቋማሉ ፤ የኮሚሽኑ ምክር ቤት መርሃ ግብር ያዘጋጀ ሲሆን ስትራቴጂክ ዕቅዱን ለባለድርሻ አካላት በማቅረብ ግብዓት ይሰበሰባል።
አጀንዳ የመሰብሰብ ሥራ በገጽ ለገጽ ማህበረሰቡ በሚረዳው ቋንቋ ስለ ኮሚሽኑ በማስረዳት ሃሳቡን እንዲገልጽ ይደረጋል። በሌሎች አማራጮችም በስልክ፣ ኢሜይል እና ፖስታ በመሳሰሉት ማቅረብም ይቻላል።
ማሕበረሰቡ ሃሳቡን ከማቅረብ በተጨማሪ በማዕከል ደረጃ ለሚደረገው ምክክር ወኪሎቹን እንዲመርጥ ይደረጋል።
የአጀንዳ ሃሳቦች መሰብሰብ የሚጀመርበት ጊዜ #በቅርቡ_ይፋ ይደረጋል። "
@tikvahethiopia

#Moot_Court
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አዘጋጅነት ላለፉት 4 ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ሀገር አቀፍ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የምስለ-ችሎት (Moot Court) ውድድር ግንቦት 20/ 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ በተካሄደው የፍጻሜ ዝግጅት ፍፃሜውን አግኝቷል።
በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ዙርያ ያተኮረው የዘንድሮው ውድድር ፦
➡️ በአዲስ አበባ
➡️ በአዳማ
➡️ በሀዋሳ
➡️ በሆሳዕና
➡️ በሚዛን
➡️ በጋምቤላ
➡️ በአሶሳ
➡️ በሰመራ
➡️ በሐረር
➡️ በድሬዳዋ
➡️ በጅግጅጋ እና ጎንደር ከተሞች የተካሄዱ ሲሆን በ10 ክልሎች እና 2 ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ 63 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና 130 ተወዳዳሪ ተማሪዎች ተሳትፈውበታል፡፡
በክልላዊ የቃል ክርክር ውድድሮች 1ኛ እና 2ኛ የወጡ 24 ተወዳዳሪ ቡድኖች የጽሑፍ ክርክራቸውን ለኢሰመኮ በመላክ የተወዳደሩ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ 8 ቡድኖች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከግንቦት 15-20 ቀን 2014 ዓ.ም. በሩብ ፍፃሜ እና ግማሽ ፍፃሜ ዙሮች ተወዳድረዋል።
ከነዚህም ውስጥ ከወላይታ ሶዳ ከተማ፣ ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት የመጡት ተማሪ ሳያት ደሳለኝ እና ተማሪ አስቻለው ማቴዎስ እንዲሁም፣ ከጎንደር ከተማ፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኮሙኒቲ ት/ቤት የመጡት ተማሪ ብሌን ሙሉጌታ እና ተማሪ አማኑኤል ዋሴ ግማሽ ፍፃሜ አሸናፊዎች በመሆን ለፍፃሜ ውድድር መቅረብ ችለዋል።
ዛሬ በተደረጉው ውድድር ተማሪ ብሌን ሙሉጌታ እና ተማሪ አማኑኤል ዋሴ #ከጎንደር_ዩኒቨርሲቲ_ኮሙኒቲ_ትምህት_ቤት የ2ኛው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምስለ-ችሎት ውድድር አሸናፊ ሆነዋል፡፡
(ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ እና ፎቶዎች ከላይ ተያይዟል)
#EHRC

#ስፖርት ፦ ዛሬ ምሽት በመላው ዓለም የእግር ኳስ ወዳጆች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ይካሄዳል።
የዚህ የዋንጫ ፍልሚያ የሚካሄደው በሊቨርፑል እና ሪያልማድሪድ መካከል ሲሆን በመላው ዓለም ሚሊዮኖች ይህንን ጨዋታ ይከታተሉታል።
የስፖርት ወዳጅ የሆናችሁ የቤተሰባችን አባላት ጨዋታውን የተመለከቱ መልዕክቶች እንዲሁም ጎሎች በቲክቫህ ስፖርት በኩል ይደርሳችኃል https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x
@tikvahethsport

TIKVAH-ETHIOPIA
#ስፖርት ፦ ዛሬ ምሽት በመላው ዓለም የእግር ኳስ ወዳጆች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ይካሄዳል። የዚህ የዋንጫ ፍልሚያ የሚካሄደው በሊቨርፑል እና ሪያልማድሪድ መካከል ሲሆን በመላው ዓለም ሚሊዮኖች ይህንን ጨዋታ ይከታተሉታል። የስፖርት ወዳጅ የሆናችሁ የቤተሰባችን አባላት ጨዋታውን የተመለከቱ መልዕክቶች እንዲሁም ጎሎች በቲክቫህ ስፖርት በኩል ይደርሳችኃል https…
#ስፖርት
ፎቶ ፦ ሊቨርፑል 0 - 1 ሪያል ማድሪድ
🏆 የ2021/2022 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ/የዋንጫ ባለቤት ሪያል ማድሪድ 🏆
የስፖርት ወዳጅ የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን ስፖርታዊ መልዕክቶችን በቲክቫህ ስፖርት በኩል መቀበል ትችላላችሁ ⬇️
https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x
Photo Credit : UEFA Champions League

#Tigray
ለ #ሰብዓዊነት ሲባል የግጭት ማቆም ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ #ከፍተኛ ነው የተባለው የሰብዓዊ እርድታ ወደ ትግራይ ተጓጉዟል።
አርብ ዕለት ከአፋር ሰመራ ከተማ 215 የምግብ እርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ አቅንተዋል።
የግብረ ሰናይ ተቋማት በትግራይ ክልል 5.2 ሚሊዮን ሰዎችን ለመመገብ በየሳምንቱ በ500 ከባድ ተሽከርካሪዎች የተጫነ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ክልሉ ሊደርስ እንደሚገባ እየገለፁ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል ፤ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ወደ ትግራይ ክልል ገብተው በነዳጅ እጦት ምክንያት ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎቹ ከትግራይ እየወጡ እንደሆነ በዚህ ሳምንት አመልክቷል።
ተሽከርካሪዎቹ ባለፈው ዓመት 2021 ወደ ክልሉ ገብተው የነበሩ ከድረጅቱ የተገኘው መረጃ ያመልክታል።
የተሽከርካሪዎቹ ከትግራይ ክልል መመለስ በሃገር አቀፍ ደረጃ ያለውን ሰብዓዊ አቅርቦት ለማሻሻል እንደሚያግዝም ድርስክቱ ገልጿል።
#ኤፒ #WFP

#ነዳጅ
ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከፍተኛ የሚባል የውጭ ምንዛሪ ከምታወጣባቸው ምርቶች መካከል ነዳጅ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው፡፡
ለነዳጅ ግዥ የሚወጣው ወጪ ከፍና ዝቅ እያለ ቢቆይም አሁን ላይ በየዓመቱ እየጨመረ መጥቷል፡፡
በተለይ በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩኢትዮጵያ ለነዳጅ ግዥ የምታውለው ወጪ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ሆኗል፡፡
ከፍና ዝቅ እያለ የመጣው የነዳጅ መግዣ በ2011 በጀት ዓመት 2.6 ቢሊዮን ዶላር፣ በ2013 በጀት ዓመት ደግሞ 1.94 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡
በ2014 በጀት ዓመት ብቻ የነዳጅ ግዥ ወጪ 2.8 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ ይህ ወጪ እስካሁን ለነዳጅ ግዥ የወጣ ከፍተኛ የሚባል ወጪ ሲሆን ከዚህ በኋላ ያለው ወጪ እጅግ የበዛ ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያ በ2015 በጀት ዓመት ወደ 3.8 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ያስፈልጋታል፡፡
ከዚህ የነዳጅ ፍላጎት ለዓመቱ ከሚያስፈልገው ነጭ ናፍጣ ግማሽ ያህሉን 1,600 ሜትሪክ ቶንና 860 ሺ ሜትሪክ ቶን ቤንዚን በቪቶል ባህሪን ኩባንያ በኩል ሚቀርብ ነው፡፡
ለዚህ አቅርቦት ኢትዮጵያ 2.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ታደርጋለች፡፡ ይህ ወጪ በ2014 ለዓመት ለሚያስፈልጋት ነዳጅ ያወጣችውን ያህል በ2015 ለግማሽ ፍጆታዋ የምትውለው ነው።
በባህሪኑ ኩባንያ ከሚገባው ነዳጅ ሌላ ቀሪውን የ2015 የነዳጅ ፍላጎት ቀጥታ ሚሞላው በጨረታ በሚደረግ ግዥ ነው፡፡ ቀሪውን ነዳጅ ወደ አገር ለማስገባት ተጨማሪ 2.8 ቢሊዮን ዶላር ይጠይቃል።
ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ በዚሁ ከቀጠለ ኢትዮጵያ በ2015 በጀት ዓመት ለሚያስፈልጋት ጠቅላላ ነዳጅ ግዥ ልታወጣ የምትችለው 5.6 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት መረጃ ያሳያል።
ያንብቡ፦ telegra.ph/RE-05-29-3
#ሪፖርተር

" በጥቁር ገበያ እና በባንክ መካከል ያለው የዶላር ዋጋ ሰፊ ልዩነት ስርዓት ካልተበጀለት መዘዙ አደገኛ ነው "
የምጣኔ ሀብት ባለሞያ የሆኑት ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርሄተስፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በጥቁር ገበያው እና በባንክ መካከል ስላለው የዶላር ዋጋ ሰፊ ልዩነት የሰጡት ማብራሪያ ፦
" አሁን በሀገሪቱ ባንኮችና በጥቁር ገበያ የተስተዋለው ከፍተኛ ዋጋ ልዩነት ተገቢው ሥርዓት ካልተበጀለት የሀገሪቱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል።
ለዶላር ጥቁር ገበያ መፋፋም የተለያዩ ምክንያቶች መጥቀስ ቢቻልም በዋናነት ግን ዶላር በባንክ በኩል በበቂ ሁኔታ ካለማግኘትና እንደ አገር የዶላር አቅርቦት እጥረት የተነሳ ነው።
በአሁኑ ጊዜ አንዱ የአሜሪካን ዶላር የባንክ ምንዛሪ ዋጋ 51 ነጥብ 55 ብር ሲሆን በጥቁር ገበያ ግን 78 ብርና ከዚያ በላይ ይመነዘራል ይህ ልዩነት መፈጠሩ በሀገራዊ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ከባድ ነው።
ልዩነቱ በዚህ ከቀጠለ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የባሰ አደጋ መደቀኑ አይቀሬ በመሆኑ ጠበቅ ያለ የሕግ ሥርዓት ሊበጅለት ይገባል።
የዶላር ከፍተኛ ዋጋ ጭማሪ አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት መንግስት ፍራንኮ ቫሉታ በመፍቀዱ ጋር ምንም ዝምድና የለውም።
ከፍራንኮ ቫሉታ መፈቀድ በፊት የአንድ ዶላር 60 ብር መሆኑ እንዳለ ሆኖ በፍራንኮ ቫሉታ የሚሳተፉ ነጋዴዎች የገንዘብ ምንጫቸው ላይ ቁጥጥር እየተደረገ ነው።
ለችግሩ መፍትሔ የሌሎች ሀገራትን አሠራር ማየት ይገባል።
ለአብነት ሱዳኖች የዛሬ 20 ዓመት ገደማ በአገራቸው የተስተዋለውን የዶላር እጥረት ችግር በመቅረፍ አቅርቦትና ፍላጎትን ለማቀራረብ የተለያዩ የምንዛሪ ሥርዓት አማራጮችን አስቀምጠዋል።
የሱዳን ብሔራዊ ባንክ ዶላርን በገበያው ዋጋ ከደንበኞች ለመቀበል በወሰነው ውሳኔ መሠረት ከውጭ ከሚኖሩ የአገሪቱ ዜጎች በአንድ ጊዜ ቢሊዮን ዶላሮች መሰብሰብ ችሏል።
አንዳንድ የላቲን አሜሪካ አገሮች እንዳደረጉ ሁሉ ከመደበኛው የዶላር ምንዛሪ ተመን በተጨማሪ ተጓዳኝ የምንዛሪ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ፤ እነዚህና ሌሎች አማራጭ ሥርዓቶች ካልተዘረጉ ችግሩ እየተባባሰ ይሄዳል።
በጥቁር ገበያ የዶላር ዋጋ ከሚጠበቀው በላይ መናሩ እና የሀገራቱ ገንዘብ የመግዛት አቅሙ እያሽቆለቆለ በመሄዱ ምክንያት ዚምባብዌና ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ለበርካታ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ተዳርገዋል።
በኢትዮጵያም ችግሩ መላ ሳይበጅለት በዚሁ ከቀጠለ ልክ እንደ ዚምባብዌ ለአንድ የአሜሪካን ዶላር #ክምር_ብር ማቅረብ የምንገደድበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል።
በኢትዮጵያ ፈጣን የማስተካከያ እርምጃ ካልተወሰደ ከጸጥታ አለመረጋጋቱ ጋር ተዳምሮ #መዘዙ_ከፍተኛ ነው።
የዶላር አቅርቦት አማራጮች ላይ ከመሥራት በተጨማሪ ጥቁር ገበያውን ለማክሰም ተዋናዮቹን በማሰር ብቻ ችግሩን መፍታት አይቻልም ፤ ይልቁንም ጠበቅ ያለ የኢኮኖሚና የሕግ ሥርዓት ሊበጅለት ይገባል "