TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#USA

በአሜሪካ ሀገር ካሊፎርኒያ ግዛት ሳክራሜንቶ ከተማ በተከፈተ ተኩስ በትንሹ 6 ሰዎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ድንገተኛው የተኩስ እሩምታ መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች በሚበዙበት አካባቢ የተከፈተ ሲሆን ሰዎችም እራሳቸውን ለማዳን በየጎዳናዎቹ ሲሯሯጡ እና የድረሱልን ጥሪያቸውን ሲያሰሙ ነበር ተብሏል።

ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ በቦታው ሲደርስ በርካታ ሰዎች በአካባቢው ተሰብስበው እንደነበር የገለፀ ሲሆን እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር እንዳልዋለ አመልክቷል።

የሟቾች ቁጥር አሁን ከተጠቀሰውም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ተገምቷል።

የከተማዋ አስተዳዳሪ የሆኑት ዴረል ሰቲንበርክ በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፈና ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር ማሰብ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጸዋል።

አክለውም ፤ " በጦር መሳሪያ የሚፈጸሙ ጥቃቶች የከተማችን፣ የግዛታችን እንዲሁም የአገራችን ስጋት ነው። ይህንን ለመቀነስ የሚደረጉ ማንኛውም አይነት እርምጃዎችን እደግፋለው " ማለታቸውን ቢቢሲ በደረገፁ አስነብቧል።

እንደ Gun Violence Archive ድረገፅ መረጃ በአሜሪካ ሀገር ከጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ በየዓመቱ #አርባ_ሺህ (40,000) ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን ይህ ደግሞ በመሳሪያዎች እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ያካታታል።

@tikvahethiopia
#USA

መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች በርካቶች በሚገደሉባት ሀገረ አሜሪካ ከሰሞኑን ተፈፅመው በነበሩ ጥቃቶች ሰዎች ተገድለዋል ፤ ቆስለዋል።

ሰሞኑን በኒው ዮርክ ግዛት በፋሎ ከተማ አንድ ነጭ ታጣቂ ጥቁሮች የሚበረክቱበት መገበያያ ሥፍራ ገብቶ ጥቃት ፈፅሞ 10 ሰዎችን ገድሏል።

ይኸው ተጠርጣሪ 18 ዓመቱ ሱሆን ፔይተን ጌንድሮን ይባላል ጥቃቱን 320 ኪሎ ሜትር ተጉዞ መጥቶ መፈፀሙን ፖሊስ ገልጿል።

አሜሪካዊው ታጣቂ ጥቁሮችን ብቻ ነጥሎ ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል።

ጥቃቱ #በዘረኝነት መንፈስ የተፈፀመ ሊሆን ይችላል በሚልም ምርመራ እየተደረገበት ነው።

የበፋሎ ከተማ ከንቲባ ባይረን ብራውን ተጠርጣሪው "የቻለውን ያክል #የጥቁር_ነፍስ ለማጥፋት ነው የመጣው" ብለዋል።

ግለሰቡ ከጥቃቱ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን ጥቃቱን አልፈፀምኩም ሲል ቃሉን ሰጥቷል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ምንም እንኳ ምርመራው ባይጠናቀቅም " ይህን ዘረኛ ጥቃት እቃወማለሁ " ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ትላንት እሁድ አንድ የታጠቀ ሰው በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ቤተክርስትያን ውስጥ ተኩስ ከፍቶ አንድ ሰው ገድሎ 5 ሰዎችን አቁስሏል። 4ቱ ሰዎች በፅኑ የቆሰሉ ናቸው።

ተጠርጣሪው እድሜው በስልሳዎቹ ሲሆን አሁን ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛል።

እንደ Gun Violence Archive ድረገፅ መረጃ በአሜሪካ ሀገር ከጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ በየዓመቱ #አርባ_ሺህ (40,000) ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን ይህ ደግሞ በመሳሪያዎች እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ያካታታል።

@tikvahethiopia