TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኬንያ ውስጥ እንደአገራቸው በነፃነት እንዲኖሩ እፈልጋለሁ " - ኡሁሩ ኬንያታ

የኬንያ ፕሬዚዳንት የሆኑት ኡሁሩ ኬንያታ በኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለምን በጽ/ቤታቸው ዛሬ ተቀብለው አነጋገሩ።

በዚህም ወቅት ፤ ፕሬዜዳንቱ " ኢትዮጵያ የኬንያ የቁርጥ ቀን ወዳጅ ናት " ያሉ ሲሆን " ኢትዮጵያ ችግር ባጋጠማት ጊዜ ሁሉ እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ከጎኗ እንደምንቆም እናረጋግጣለን " ብለዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል በኢኮኖሚው መስክ በመሠረተ-ልማት ትስስር፣ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት ዘርፎች የተጀመሩ ትብብሮች ተጠናከረው እንደሚቀጥሉ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ኡሁሩ በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ኬንያ ውስጥ እንደአገራቸው በነፃነት እንዲኖሩም እፈልጋለሁ ብለዋል።

https://telegra.ph/Ethiopia-Kenya-05-05

Via Ethiopian Embassy in Kenya

@tikvahethiopia
" ጋዜጠኛን ከሕግ ውጭ ሰውሮ ማቆየት ይቁም " - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከቀናት በፊት ማንነታቸውን ባልገለጹ የመንግስት ሰዎች ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ ተይዞ መወሰዱንና የት እንዳለ አለመታወቁን ከሰማበት ጊዜ ጀምሮ መልስ የሚሰጥ አካል ባለመኖሩ በእጅጉ እንዳሳሰበው ገልጿል።

ማህበሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፤ ጋዜጠኛው በምን ጥፋት ተጠርጥሮ እንደተያዘና ምክንያቱ ምን እንደሆነ በግልጽ ካለመነገሩ በላይ የት እንደሚገኝ አለመታወቁ ከዚህ ቀደምም ማሕበሩ ሲቃወመው የቆየው በሌሎች ጋዜጠኞችም ላይ የደረሰው መሰል ድርጊት አካል ሆኖ እንዳገኘው አሳውቋል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ የማህበሩ መስራች አባል መሆኑን በማሳት ታፍኖ ተወስዶ እንዲሰወር የተደረገው የዓለማችን የፕሬስ ነጻነት ሳምንት በሚከበርበት ወቅት መሆኑ መንግስት በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በመገናኛ ብዙኃን ላይ ጥቃት እንደከፈተ ያስቆጥረዋል ሲል ገልጿል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ያጠፋው ጥፋት ቢኖር እንኳን የፍትህ አካላት እንደማንኛውም ተጠርጣሪ በህግ ቁጥጥር ስር ሊውልና ዳኝነት ሊሰጠው ሲገባ ከተያዘበት ቀን አንስቶ የት እንደሚገኝ ሳይገለፅ መቆየቱ የመብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን መንግስት ይህን ያልተገባ አደገኛ አዝማሚያ በጋዜጠኞች ላይ ማድረስ እንደመብት የቆጠረው አስመስሎታል ሲል ኮንኗል።

ማህበሩ ፤ ጋዜጠኛ ጎበዜ ለምን እንደታሰረ፣ የት እንደሚገኝ እና የተያዘበት ምክንያት በግልጽ እንዲነገር በጽኑ ጠይቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#iጤና

• በስትሮክ፣ በአደጋ፣ እና በሌሎች በሽታዎች ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ለተፈጠረ አለመንቀሳቀስ (Paralysis)
• እድሜ በመግፋት ለሚፈጠሩ ጉድለቶች እንደ አልዛይመርስ፤ ዲሜንሻ
• ከተለያዩ ቀዶ ጥገናዎች ለማገገም
• በሙሉ (Coma) ወይም በከፊል የንቃተ ህሊና መቀነስ ላላቸው ታካሚዎች እንክብካቤ
• ለካንሰር እና ተከታታይ የህክምና ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች

👉 በ0901222233 ይደውሉልን
Telegram | FB | IG | Twitter 🌍
🏥 አድራሻችን ጀሞ ከ ጀሞ ሞል 200m ገባ ብሎ፡፡
#USA #ETHIOPIA

በአሜሪካ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ስለሺ በቀለ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ለአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ቺፍ ፕሮቶኮል ቢሮ ትላንት አቅርበዋል።

አምባሳደር ስለሺ በቀለ በዚሁ እለት እንደገለጹት በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለው ታሪካዊ ወዳጅነት እንዲጎለብት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #USA

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ የሆኑት አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ የሚስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በአሜሪካ ኤምባሲ በኩል ይፋ በሆነ መረጃ ውይይታቸው ትኩረቱን ፥ በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር ፣ ሙሉ በሙሉ ግጭት ስለሚቆምበት መንገድ ፣ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ድጋፍ ስለሚያገኙበት ሁኔታ እንዲሁም ስለ ሰብዓዊ መብቶች ተጠያቂነት ላይ ያደረገ ነበር።

የአሜሪካ ጉዳይ ፈፃሚዋ ተሹመው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ ከተቋማት ኃላፊዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
" ሁሌም ግጭቱ እንዲቆም ፣ ሰብአዊ እርዳታ በሁሉም ቦታ እንዲዳረስ እንዲሁም ሰላምን የሚያመጣ ውጤታማ ድርድር እንዲደረግ ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ " - አንቶኒዮ ጉተሬዝ

የተባበሩተ መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዲያበቃ ከሁለቱም ወገኖች ጋር በርካታ ግንኙነቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ይህን የተናገሩት በዚህ ሳምንት የምዕራብ አፍሪካ አገራት በሆኑት በሴኔጋል፣ በኒጀር እና በናይጄሪያ ጉብኝት ባደረጉበት ጊዜ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ነው።

ዋና ፀሀፊው ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ከህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር ግንኙነቶችን በመፍጠር ጦርነቱ መቋጫ እንዲያገኝ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ አመቺ ሁኔታ እንዲፈጠርና በመጨረሻም በውይይት ሰላም እንዲወርድ አዘውትረው ሲጥሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ጉተሬዝ ፥ " ሁሌም ግጭቱ እንዲቆም፣ ሰብአዊ እርዳታ በሁሉም ቦታ እንዲዳረስ እንዲሁም ሰላምን የሚያመጣ ውጤታማ ድርድር እንዲደረግ ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ " ሲሉ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
የዜጎች መረጃን የማግኘት መብት እስከምን ድረስ ነው?

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት ረ/ፕሮፌሰር ዶ/ር ሙላቱ አለማየሁ ፦

" ለሀገራዊ ደኅንነት ከሚያሰጉና በልዩነት ከሚቀመጡት ውጪ ያለ ማንኛውም መረጃ የህዝብ መረጃ ነው ተብሎ ይታሰባል።

ይህ ሕግ ከላይ ከተጠቀሱት ውስን ገደቦች ውጭ ማንኛውም ሰው መረጃ ጠይቆ የማግኘት መብትን ያጎናጽፋል።

ለምሳሌ ፦ አንድ ግለሰብ የህ/ተ/ምክር ቤት የተወያዩበትን ቃለ ጉባዔ አሳዩኝ ብሎ የመጠየቅ መብት ጭምር አለው። ይህ በግለሰብ ደረጃ መተግበር የሚገባው ሕግ ለሚዲያዎች እንኳን ተፈጻሚ አይሆንም። "

◾️

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ፦

" የመረጃ መዛባት አንደኛው መንስዔ የመረጃ እጦት ነው።

መረጃ አሰጣጡ ተቋማዊ ቅርጽ አለመያዙና በግለሰቦችና በኃላፊዎች ፈቃድ መወሰኑ የመረጃ ነጻነትን የሚጋፋ ጉዳይ ሆኗል። ለዚህም መረጃ በመስጠት የሚሞገስ፤ መረጃ ባለመስጠት የሚወቀስበት ዘመን መምጣት አለበት።

'መረጃ ከልካዮች ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን የሚያደርጉት ይመስላቸዋል። የመንግሥት ተቋማት የህዝብ ሀብትን መሰረት አድርገው የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው ይህንን በግልጽና ተጠያቂነት በሰፈነበት መልኩ ለህብረተሰቡ ማቅረብ በሕግ ይገደዳሉ "

ያንብቡ 👉 https://telegra.ph/Tikvah-Family-05-06

@tikvahethiopia
" ልጆቻችን እንዳይራቡ እና ቤተሰብም ችግር ላይ እንዳይወድቅ ከፍተኛ ችግር እየየን እየሰራን ነው " - የባለ ሶስት እግር (ባጃጅ) አሽከርካሪዎች

በተለያዩ ከተሞች በባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ እና ኑሯቸውን በዛ ያደረጉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በነዳጅ (ቤንዚን) እጥረት እና አለመገኘት ሳቢያ ከፍተኛ ችግር እየገጠማቸው እንደሆነ ገልጸዋል።

ለአብነት በሀዋሳ ከተማ በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ችግሩ ወራትን ማስቆጠሩን ፤ ነገር ግን አሁንም ነዳጅ (ቤንዚን) ማግኘት ፈተና እንደሆነ መቀጠሉን ገልፀዋል።

" ነዳጅ (ቤንዚን) የለም ይባላል ፤ ሱቅ ውስጥ እና በየመንገዱ በህገወጥ መልኩ ከዋናው ዋጋ በእጥፍ ጨምሮ ሲሸጥ ይውላል፤ ነዳጅ (ቤንዚን) ከማደያ እየወጣ በየግለሰብ እጅ ገብቶ እና በየሱቁ ሲሸጥ የሚቆጣጠር እና መፍትሄ የሚሰጥ አካል አልተገኘም። በዚህ ላይ የተለያዩ አካላትም እጃቸውን ሊኖርበት ይችላል " ሲሉ ገልፀዋል።

ከማደያ ውጭ አንድ ሊትር እስከ 70 ብር ድረስ ነው የሚሸጠው ፤ እነዚህ አካላት እንደልብ ነዳጅ እያገኙ እና እየሸጡ ነዳጅ (ቤንዚን) ጠፋ ማለት ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

" ልጆቻችን እንዳይራቡ እና ቤተሰብ ችግር ላይ እንዳይወድቅ ከፍተኛ ችግር እየየን እየሰራን ነው በዚህ ጉዳይ መፍትሄ እንሻለን " ሲሉ ገልፀዋል።

በመንግስት መዋቅር ውስጥና በነዳጅ ማደያዎች ይህ ችግር እንዳይፈታ የሚፈልጉ የህገወጥ ድርጊቱ የጥቅም ተጋሪዎች ስለሚኖሩ አስፈላጊው እርምት ሊደርግ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

ውድ ቤተሰቦቻች እናተስ በአካባቢያዎችሁ ላይ ተመሳሳይ ችግር አለ ? መልዕክታችሁ በዚህ አስቀምጡልን @tikvahethiopiaBOT
#EKA_KOTEBE

ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ትላንትና #የመጨረሻውን የኮቪድ-19 ታካሚ በሰላም ወደ ቤቱ መሸኘቱን እና ሆስፒታሉ በሁለት አመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ኮቪድ19 ታካሚ ውሎ ማደሩን ስራ አስኪያጁ ዶ/ር ያሬድ አግደው ገልፀዋል።

ዶ/ር ያሬድ አግደው፤ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ላለፉት ሁለት አመታት የኮቪድ-19 ህክምና መዕከል ሆኖ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንዳለን አስታውሰዋል።

" በትናንትናው ዕለት የመጨረሻውን ታካሚ ወደ ቤቱ በሰላም ሸኝተናል " ያሉት ስራ አስኪያጁ " በሁለት አመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆስፒታላችን ያለ ኮቪድ19 ታካሚ ውሎ አድሯል " ሲሉም ገልፀዋል።

" ከዚህ በኋላ ሀገርን በሚጎዳ መልኩ የኮቪድ19 ማዕበል በሀገራችን በድጋሚ እንዳይከሰት ሁላችንም የድርሻችን መወጣት ይኖርብናል " ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
#Tigray

የዓለም ምግብ ፕሮግራም እንዳሳወቀው በዚህ ሳምንት እስካሁን 16 የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ፣ መቐለ የደረሱ ሲሆን ሌላ ኮንቮይ 64 ተሽከርካሪዎች በጉዞ ላይ ይገኛሉ ይህ በ2022 6ኛው ኮንቮይ ነው።

ድርጅቱ ፥ በሚያዚያ ወር በሸራሮ ወረዳ ለሚገኙ 45,000 ሰዎች ምግብ ማቅረቡን የገለፀ ሲሆን የተመጣጠነ የምግብ ችግር ያለባቸውን 11,000 ሴቶች እና ህፃናትን መድረስ መቻሉን ገልጿል።

በትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ ሁኔታን ምላሽ ለመስጠት በየዕለቱ ወደ ክልሉ 100 ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መግባት ያለባቸው መሆኑን ከዚህ ቀደም የዓለም ምግብ ፕሮግራም መግለፁ ይታወሳል።

ከወራቶች በፊት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ በፊት ከነበረው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መሻሻሎች ቢታዩም አሁንም ካለው ፍላጎት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛና የተቸገሩ ወገኖችን ሰብዓዊ ፍላጎት ለማሟላት ሰፊ ስራ እንደሚጠብቅ የሚገልፁ በርካቶች ናቸው።

@tikvahethiopia