TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Gambella

" በጥቃቱ የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 5 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል " - ፖሊስ

በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት ጥቃት ማድረሳቸውን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ።

በጥቃቱ የ8 ሠዎች ህይወት ሲያልፍ በ5 ሠዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ተገልጿል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቡላ ኡቦንግ ፥ በጋምቤላ በዚህ ሰዓት በጋ ስለሆነ እና ክልሉን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያጋራው ድንበር ሰፊና ክፍት ስለሆነ የታጣቂዎች የመግባትና የመውጣት አዝማሚያ አለ ብለዋል።

የሙርሌ ታጣቂዎች ትናትና ድንበር አቋርጠው በመግባት በኑዌር ዞን አኮቦ ወረዳ በካንካን ቀበሌ ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት የ8 ሠዎች ህይወት ወዲያው ሲያልፍ 5 ሠዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል።

ኮሚሽነር አቡላ አክለውም ክልሉ በአሁኑ ሰዓት ልዩ ኃይሉንና ሚሊሻ በመጠቀም ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ስራውን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ ፤ የአካባቢው ማህበረሰብ የታጣቂ ቡድኑን እንቅስቃሴ ነቅቶ በመጠበቅ ለመንግሥት ተገቢውን ጥቆማ ማድረግ እንደሚኖርበት አሳስበው በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ገልጸዋል።

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከዓመታት በፊት፤ በኑዌር ዞን እና አኙዋ ዞኖች ገብተው በርካታ ሕፃናት አፍነው ሲወስዱ፣ ከአንድ መቶ ሰባ በላይ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።

ከ2 ሺህ በላይ ከብቶች መውሰዳቸውንም ኮሚሽነሩ አስታውሰዋል።

በወቅቱ የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት ወደ ደቡብ ሱዳን በመግባትና ታጣቂዎቹ የሚኖሩበት አካባቢ ላይ ጥቃት በመፈፀም ታፍነው ከተወሰዱት ሕፃናት መካከል ከ100 ሕፃናት በላይ ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሱን አስረድተዋል።

ምንጭ፦ የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gambella " በጥቃቱ የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 5 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል " - ፖሊስ በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት ጥቃት ማድረሳቸውን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ። በጥቃቱ የ8 ሠዎች ህይወት ሲያልፍ በ5 ሠዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ተገልጿል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቡላ ኡቦንግ ፥ በጋምቤላ…
#Gambella

ትላንትና በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት በዲማ ስደተኛ ካምፕና በጎግ ወረዳ ጥቃት ማድረሳቸውን የጋምቤላ ክልል አስታውቋል።

በጥቃቱ የአንድ ሠው ህይወትሲያልፍ ሁለት ሠዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና ሶስት ህፃናት ታፍነው ተወስደዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በጎግ ወረዳ ከፑኝዶ ከተማ ወደ ቴዶ ቀበሌ የሚሄድ ሞተር ሳይክል ላይ ባደረሱት ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ተገልጿል።

በቅርቡም መነሻውን ከጋምቤላ ከተማ አድርጎ ወደ ኑዌር ዞን በመጓዝ ላይ ባለ የጭነት መኪና ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ባደረሱት ጥቃት የመኪናው አሽከርካሪ እና ረዳቱ ህይወታቸው እንዳለፈ የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።

ጥቃት ያደረሱትን ግለሰቦች በክልሉ ልዩ ሀይልና ሚሊሻዎች አማካኝነት ተከታትሎ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ጠንካራ ስራ እየተከናወነ እንደሆነ ክልሉ ገልጿል።

ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል።

በአሁኑ ሰዓት ክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በመጠቀም ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ስራውን እየሰራ መሆኑንና የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በየቦታው ሾልከው ሊገቡ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በቅርቡ፤ በኑዌር ዞን እና አኙዋ ዞኖች ገብተው 4 ሕፃናት አፍነው በመውሰድ፣ የከብት ዝርፊያ በማካሄድ አስራ አንድ ሰዎችም ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።

መረጃው የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት ነው።

@tikvahethiopia
#Gambella , #Akobo📍

" የኔትወርክና የመንገድ መሠረተ ልማት ባለመሟላቱ የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት አዳጋች ሆኗል " - አቶ ኮንግ ጋትዮቴ

በጋምቤላ ክልል በአኮቦ ወረዳ ከደቡብ ሱዳን በሚነሱ የሙርሌ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው ህብረተሰቡ ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን የወረዳዉ አስተዳደር አስታውቋል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኮንግ ጋትዮቴ እንዳሉት ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙሩሌ ጎሳ ታጣቂዎች በተለያዩ ጊዜያት ድንበር አቋርጠዉ በመግባት ጥቃት ሲፈፅሙ ቆይተዋል ብለዋል።

ታጣቂ ቡድኑ በሰዉ ህይወት ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባለፈ ህፃናትንና የቁም እንስሳትን ሲዘርፉ እንደነበር ጠቅሰዉ በአሁኑ ወቅት ከክልሉ የጠጥታ አካላት ጋር በመቀኛጀትና የስጋት ቀጠናዎችን በመለየት መሰል ጥቃት እንዳይፈፀም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በወረዳዉ የኔትወርክና የመንገድ መሠረተ ልማት ባለመሟላቱ የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት አዳጋች እንደሆነባቸዉ ገልፀዉ መንግስት እነዚህ መሠረተ ልማቶች ላይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል የክልሉ መንግስት በጥቃቱ ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ከ2,500 በላይ ወገኖች በ2 ሚሊዮን ብር 600 ኩንታል በቆሎ በመግዛት ድጋፍ ማድረግ መቻሉን የክልሉ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ መግለፁን ከጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል

@tikvahethiopia
#Gambella

ትናንት ምሽት ላይ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰው ላይ የመቁሰል አደጋ መደረሱ ተገልጸ።

የክልሉ ፖሊስ ፤ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በክልል ፖሊስ እና በፌደራል ፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በአንድ ሰው ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሷል ሲል አሳውቋል።

በአሁኑ ሰዓት የአካባቢው ሠላም ወደነበረበት ተመልሷል፤ ግጭት ፈጥረዋልም የተባሉ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢው ማጣራት እየተካሄደ ነው ሲል የክልሉ ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ የግጭቱን መንስኤ እያጣራ እንደሆነም አሳውቋል።

ከተማዋ ሰላም መሆኗን እና ህብረተሰቡም ወደ ተለመደው የሰላም ሁኔታ መመለሱንም ገልጿል።

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ነዋሪዎች ረብሻና ሁከት ከሚፈጥሩ አንዳንድ ማህበራዊ የሚዲያ ገፆችና ያልተረጋገጠ መረጃ ከሚሰጡ ዘገባዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia