TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar " በእሳት አደጋው 160 የሚጠጉ ሱቆች እና የመኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በድንገት በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ በግምት ከ160 በላይ የሚጠጉ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን የወረዳው አስተዳድር አሳውቋል። የሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ አስተዳድር አቶ ሀሰን ሀንዲ ለአፋር ብዙሀን መገናኛ በሰጡት ቃል…
" ሰዎች ከቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ነው ያሉት ፣ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋል " - አቶ ሀሰን ሀንድዬ
ትናንት ከሰአት 11 ሰአት ገደማ በሰሙሮቢ ወረዳ ኮማሚ ቀበሌ በተነሳው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ በርካታ ንብረት በመውደሙ የተነሳ ህብረተሰቡ ለከፍተኛ ችግር በመዳረጉ አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀሰን ሀንድዬ ጥሪ አቅርበዋል።
" ሰዎች ከቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ነው ያሉት ፣ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋል " ብለዋል።
አልባሳት፣ ምግብ ነክ ነገሮች፣ መጠለያና የመጠጥ ውሃ በአፋጣኝ እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል።
ከ3 ቀን በፊት በተቋረጠው ኤሌክትሪክ ምክንያት ህብረተሰቡ ለውሃ ጥም መዳረጉን ገልፀው አሁን የደረሰው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ሲጨመርበት በዚህ #የፆም ሰአት ህብረተሰቡን የበለጠ ተጎጂ አድርጓል ብለዋል።
አቶ ሀሰን እንዳሉት በትላንቱ አደጋ እያንዳንዳቸው 80 የንግድ ቤቶች ውስጥ የነበሩ 500 ሺ ብር በላይ ሸቀጣ ሸቀጥና ጥሬ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን በ80 መኖሪያ ቤቶችም የነበሩ እቃዎችና እንዲሁም ጥሬ ገንዘብ እያንዳንዳቸው 200 ሺህ ብር ገደማ ወድሟል።
አጠቃላይ ንብረት ላይ የቤቶችን ግምት ሳያካትት በቤት ውስጥ የነበረ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ እቃዎችና ጥሬ ብር የደረሰው አደጋ አሀዝ 56 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ነው።
በአቅራቢያ በሚገኙት ሸዋሮቢት ሆነ ደብረብረሃን ከተሞች አንድም የእሳት አደጋ መከላከያ ባለመኖሩ ምክንያት ውድመቱን መቀነስ እንዳልተቻለ ዋና አስታዳዳሪው ገልፀዋል።
" መነሻው በቀዳሚነት በቤንዚን ነው ተብሎ ታስቦ የነበረው ትክክል አልነበረም " ያሉት አቶ ሃሰን በተደረገ ማጣራት መነሻው የኤሌክትሪክ ንክኪ ተፈጥሮ ወደ ቤንዚን ቤት በማምራቱ ነው ብለዋል።
መረጃው ከአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።
@tikvahethiopia

#Russia
የሩሲያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸውን ሩስያን ለማግለል የሚደረገው ሙከራ አይሳካም ሲሉ ምእራባውያንን አስጠነቀቁ።
ሩስያ በዩክሬን የጀመረችውን " ልዩ ወታራዊ ዘመቻ " ተከትሎ ጠንከር ያሉ ማዕቀቦችን በጣሉባት ምእራባውያን እና አሜሪካ ላይ እምነት እንደማይኖራት ገልጻለች፡፡
ፕሬዜዳንት ፑቲን ፥ " በሶቬት ህብረት ጊዜ ጠቅላላ ማእቀብ ተጥሎ ነበር፤ ሙሉ በሙሉ ተገልላም ነበር፤ ነገርግን ሶቬት አሁንም በስፔስ ቀዳሚ ነች " ሲሉ ተደምጠዋል።
ፕሬዝደንቱ የመገለል ፍላጎት እንደሌላቸው እና በዚህ ዘመናዊ አለም ማግለል እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡
በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ሩሲያ በዩሪ ጋጋሪ አማካኝነት ወደ ስፔስ ያደረገችው በረራ እና በፈረንጆቹ 1957 የስፑትኒክ አንደኛ ወደ ስፔስ መብረር አሜሪካን አስደንግጦ ነበር፡፡ በወቅቱ አሜሪካ ከሩሲያ ጋር ለመወዳደር ስትል ናሳን አቋቁማ ነበር፡፡
ፕሬዜዳንት ፑቲን በዩክሬን " ወታደራዊ ዘመቻ " ለማድረግ የተገደዱት፤ አሜሪካ ዩክሬንን እና ኔቶን በመጠቀም ለማስፈራራት ስለሞከረች እና ይህንም መከላከል ሲለሚገባ ነው ብለዋል፡፡
ፑቲን ሩሲያ በዩክሬን ሁሉንም የምትፈልገውን አላማ ታሳካለች ብለዋል፡፡
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

#Update የደቡብ ክልል ፖሊስ ፤ በጂንካ ከተማና አካባቢው በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ተሳትፈዋል ተብሎ የተጠረጠሩ 133 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ። በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል 4 የፖሊስ አባላት አሉበት ተብሏል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ለዋልታ ቴሌቪዥ በሰጠው ቃል. ፤ " በመንግሥት መዋቅር ስር ያሉ የአመራር አካላት፣ ራሳቸውን የሕዝብ ወኪል አድርገው…
#Udpate
በጂንካና አካባቢው ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች 22 ሲፈቱ ቀሪዎቹ ላይ ምርመራ መቀጠሉ ተሰምቷል።
ዞኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የተከሰተው ችግር በቁጥጥር ስር ውሎ ማኅበረሰቡም ወደ ቀደመው የኑሮ ሁኔታ እየተመለሰ ነው ብሏል።
የዞኑ ም/አስተዳዳሪና የሰላም እና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ደሞ በዛብህ ፤ ከፀጥታው ችግር ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ካሉበት አድኖ በሕግ ጥላ ሥር የማዋል ሥራ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን ለጊዜው እስካሁን 132 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፤ ከእነዚህ መካከል በተደረገ የማጥራት ሥራ 22ቱ ዛሬ ተፈተዋል ሲሉ ተናግረዋል።
[NB. ትላንት የደቡብ ፖሊስ ሰጥቶ በነበረው ቃል የተያዙ ተጠርጣሪዎች 133 ናቸው ብሎ ነበር]
አቶ ደሞ የጸጥታ ኃሎች በሰሩት ስራ አብዛኛው አካባቢ አንፃራዊ መረጋጋት መፈጠሩን ገልፀዋል።
በዚህም የቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ ድጋፍ በሚመች መልኩ ተግባራቸውን ለማከናወን ተንቀሳቅሰዋል።
ኃላፊው፤ የፀጥታው ኮማንድ ፖስት ባካሄደው ወቅታዊ ሁኔታ ግምገማ በቶልታና መጸር 145 ቤቶች በእሳት የተቃጠሉ ሲሆን ከዚህ መካከል 1 መስጂድ ይገኝበታል ብለዋል።
አንድ ቀበሌ ያልተጣራ ያለ በመሆኑ ኮማንድ ፖስቱ በቀጣይ አጣርቶ ለሕዝብ ግልጽ ያደርጋል ሲሉ ገልፀዋል።
በጂንካ ዙሪያ 6 ቤቶች መቃጠላቸውን አሳውቀዋል።
በፀጥታ መዋቅሩ የተገመገመና የተለየ የተፈናቀሉ አባወራ 237፤ እማወራ 136 በአጠቃላይ 333 አባወራና እማወራዎች ተፈናቅለው በት/ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች ተጠልለው ይገኛሉ።
979 ቤተሰቦች ከቤት-ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ይህም ለጊዜው በጸጥታ አካላት ተለዩ ናቸው። የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሪፖርት ሲመጣ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በላይ ሊያሻብቅ እንደሚችል ተገምቷል።

#Udpate በጂንካና አካባቢው ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች 22 ሲፈቱ ቀሪዎቹ ላይ ምርመራ መቀጠሉ ተሰምቷል። ዞኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የተከሰተው ችግር በቁጥጥር ስር ውሎ ማኅበረሰቡም ወደ ቀደመው የኑሮ ሁኔታ እየተመለሰ ነው ብሏል። የዞኑ ም/አስተዳዳሪና የሰላም እና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ደሞ በዛብህ ፤ ከፀጥታው ችግር ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ካሉበት…
ቀይ መስቀል ድጋፍ እያደረገ ነው።
የደቡብ ኦሞ ዞን ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቶልታ፣ መጸርና በርካ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አፍርጓል።
የሰሞኑን ፀጥታ ችግር ተከትሎ በደቡብ አሪ ወረዳ መፀር፣ ቶልታና በርካ አካባቢዎች ከፍተኛ የቤት ቃጠሎና የንብረት ውድመት የተከሰተ ሲሆን ነዋሪዎቹም ከስፍራው ሸሽተዋል፡፡
ራሳቸውን ለማዳን በሐይማኖት ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶችና በፖሊስ ጣቢያዎች የተጠለሉት የማኅረሰቡ አካላትን የደቡብ ኦሞ ዞን ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከራሱና ማኅበረሰቡን በማስተባባር የዕለትና ሌሎችንም ድጋፍ ለመስጠጥ ችሏል፡፡
የተደረገው ድጋፍ ፦ ለሶስቱም አካባቢዎች ለበርካ፣ ቶልታና መፀር 130 ደርዘን እሽግ ውሃ፣ 3 ሺህ ዳቦ፣ 50 አገልግል እንጀራ፣ 10 ኩንታል ሞኮሮኒ፣ 2 ኩንታል ሩዝ፣ 6 ኩንታል ነጭ ዱቀት፣ 2 ኩንታል ጤፍ፣ 18 ደርዘን ጁስ፣ 6 ደርዘን ብስኩት እና ሌሎችም ይገኙበታል።
አሁንም ድጋፉን ለማጠናከር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ቀይ መስቀል ጥሪ አቅርቧል፦ ችግር ላይ የወደቁ ወገኖችን ለማገዝ በገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የሚፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ERCS 1000040792981 መላክ እንደሚችሉ ተገልጿል።

#ትኩረት📣
የሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎና ከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ፤ " የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወደ ቅዱስ ላልይበላ ዓለም አቀፍ ቅርስ ሊመለከት ይገባል " ሲሉ ጥሪ አቀረቡ።
ብፁዕነታቸው ቅዱስ ላልይበላን በማስመልከት ዛሬ በተሰጠ መግለጫ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በነበረው ጦርነት የቅዱስ ላልይበላ ቅርስ የቱሪዝም እና የከተማው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጫና ውስጥ መውደቁን ገልጸዋል፤ በዚህም አገልጋዮች ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን አሳውቀዋል።
ቅዱስ ላልይበላ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሐብት እንደመሆኑ አቅም በፈቀደ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ለድጋፍ እጁን እንዲዘረጋ ጥሪ አቅርበዋል።
ብፁዕነታቸው " ሁላችንም የድርሻችንን በመወጣት ቅርሳችን እንጠብቅ " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዜጎች ድጋፋቸውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አቢሲኒያ እና ዳሽን ባንኮች በ 👉 0712 የባንክ የሒሳብ ቁጥር ማድረግ ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911061164 እና 0913912457 መደወል ይቻላል።
ምንጭ፦ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት

የሲዳማ ክልል ወጣቶች ጥያቄ 💬
(የድምፅ ባለቤት ዶቼ ቨለ ሬድዮ ሲሆን - ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በሚሆን መልኩ በፅሁፍ የተዘጋጀ)
በሀዋሳ ከተማ ፤ የብልፅግና ፓርቲ ከሲዳማ ወጣቶች ጋር ለመምከር የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር።
በዚህ መድረክ የተሳተፉ አብዛኞቹ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች ሲሆኑ ለበርካታ አመታት ያለ ስራ መቀመጣቸውን በመግለፅ ጠንካራ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ፦
" አሁን ወጣቱን አደራጅተን እንደዚህ እያደረግን ነው ብላችሁ እያወራችሁ ነው። የትኛውን ነው ?
ለምሳሌ ፦ ኮንቴነር በየክፍለ ከተማው ፈትሹ ያለውን ነገር ታያላችሁ ፤ አመራሩ እጅ ነው ያለው ኮንቴነር። አደራጅ እና አስተባባሪ ተብሎ የተቀመጡ ሰዎች እነሱ እጅ ነው ያለው ኮንቴነር ለወጣቱ ይሰጥ ተብሎ የተሰራው ፤ የምን ብልፅግና ነው እናተ ምትመሩት ?
ይህንን ወጣት ፤ በቀን 3 ጊዜ መብላት ያልቻለን ህዝብ እየመራችሁ እንዴት ነው ? እናተ በV8 እና በተለያየ ላንድክሩዘር መኪኖች እየዘነጣችሁ የምትሄዱት ? በምን አግባብ ነው ? "
ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ፦
" ... ብልፅግና ፓርቲ መነፅር ብቻ ነው የቀየራችሁት ። ሙሉ ኢህአዴግ የነበሩ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ደግሞ ለውጡን ለመቀበል ዝግጁ አይደሉም። በሌብነት ፣ በዘረኝነት የተጠመዱ ሰዎች ናቸው።
ብልፅግና ፓርቲ ቢያንስ ወጣቱን የሚሰማ ከሆነ እኛ በትዕግሥት መንግስቱ አልተረጋጋም ፣ ጫና አለበት የውስጥም የውጭም ብለን በትዕግስት ጠብቀናል ሶስት ዓመት ሙሉ አሁን 4ኛ ዓመት ልንይዝ ነው ሁሌ በዚህ ይቀጥላል ? የኛም ዝምታ በዚህ ይቀጥላል ? እሱን ጊዜ የሚፈታው ነገር ነው። "
ከዚህ በተጨማሪ የውይይት ተሳታፊዎች ጥያቄያቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ ቢጥሩም እንዳልቻሉ ፤ በክልላቸው ዴሞክራሲና ነፃነት የለም ሲሉ ምሬታቸውን ገልፀዋል።
እንዲሁም በክልሉ ፦
👉 ሰብአዊ መብቶች ይጥሳሉ፣
👉 የመልካም አስተዳደር ጉድለት አለ፤
👉 ሙስና ተንሰራፍቷል ፤
👉 ባለስልጣናት ለወጣቶች መገልገያ የተገነቡ ተቋማትን ለዘመዶቻቸዉና ለቤተሰቦቻቸዉ ሰጥተዋል፣
👉 ባለስልጣናት ዉሳኔዎችን የሚያሳልፉት ለእነሱና ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ በሚጠቅም መልኩ ነዉ ብለዋል።
በወጣቶች ለተነሱት ጥያቄዎች በመድረኩ ከተገኙት አንዱ የሲዳማ ብልፅና ፓርቲ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘማች እርጥባ ተከታዩን ብለዋል ፦
" ቁጥር ብዙ ለሆነ ወጣት ስራ እድል ያልተፈጠረለት ሁኔታ አለ። እየተፈጠረም ያለው እራሱ የባለሃብት ቤተሰብ ፣ የአመራር ቤተሰብ የሚለው ትክክል ነው።
ምን እያደረጋችሁ ነው ያላችሁት ? ቢሚል ለነሳችሁት መጀመሪያ የሚሆነው ይህን ሲፈፅም የነበረው ሊመራ ኃላፊነት የተሰጠው አመራር በአግባቡ ያልመራውን እርምጃ ወስደናል አሁን።
በዚህ ዓመት አሁን እስካለንበት ከ80 በላይ በሆኑት ላይ እርምጃ ተወስዷል። ይሄ ብቻም አላቆመም ቀጥሎም በኃላፊዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ በከተማ ፓርቲ ደረጃ ፤ በመንግስት ደረጃ የሚኬድበት ሁኔታ ይቀጥላል "
የብልፅግና ወጣቶች ሊግ አመራር አንዱ ታረቀኝ ለገሰ ፦
" የምታነሷቸው ጥያቄዎች በሰፊው አሉ። ስራ አጥነት አለ። የ3 ዓመት ብቻ አይደለም ፤ የ7 ዓመት ስራ ያልተቀጠረ ወጣት ፤ ስራ ያላገኘ ወጣት ያለው እኛ ጋር በዝርዝር አለ። እያንዳንዱን ጥያቄ በዝርዝር ይዘናል ፤ እንደተባለው ቀጥታ ይሄ ለፌዴራል ብልፅግና ፓርቲ ግብአት ሆኖ የሚሄድ ነው። "
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

አሜሪካ ከወራት በፊት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ የሾመቻቸው አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በቅርቡ (ከሰኔ በፊት) ከስልጣናቸው ሊለቁ ነው።
ከስድስት ወር ላነሰ ጊዜ በልዩ መልዕክተኛነት ያገለገሉት ሳተርፊልድ ከስልጣናቸው ሲለቁ ምክትል ልዩ መልዕክተኛ ፔይቶን ኖፕፍ ቦታውን እንደሚረከቡ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸድ ምንጮች መስማቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
በቅድሚያ የአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በቅርቡ ከኃላፊነታቸው ሊለቁ እንደሚችሉ መረጃውን ያወጣው ፎሬይን ፖሊሲ ሲሆን የእሳቸው ከኃላፊነት መልቀቅ፤ ከፍተኛ የፖለቲካ አለመራጋጋት፣ የጅምላ ጭፍጨፋዎች እና የረሃብ ስጋት ባለበት የአፍሪካ ቀንድ ትልቅ የዲፕሎማሲ ክፍተት የሚፈጥር እንደሆነ አስፍሯል።
በሌላ በኩል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ እና ምክትላቸው ኖፕፍ ዛሬ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ አስታውቋል።
2ቱ የአሜሪካ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጠናት ፣ ከዲፕሎማቲ አጋሮች እና ከረድዔት ድርጅቶች ጋር ተገናኝተው ይመክራሉ ተብሏል።
የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከኃላፊነት መነሳት ላይ በይፋ የሰጠው አስተያየት አንደሌለ ሮይተርስ ፅፏል።

#ዋግኽምራ📍
ጦርነት ክፉኛ ከጎዳቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች አንዱ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ነው።
በእዚህ አካባቢ ያሉ ወገኖች ለከፋ ችግር ተጋልጠው ሜዳ ላይ መውደቃቸው እና አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ጥሪ ሲቀርብ እንደነበር ይታወሳል።
ምንም እንኳን በቂ ባይሆንም የተለያዩ ድጋፎች ሲደረጉ ተስተውሏል።
ዛሬ ከዋግ ኽምራ ኮሚኒኬሽን በተገኘ መረጃ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ሳቢያ ከቤታቸው ተፈናቅለው በሰቆጣ መጠለያ ለሚገኙ የዋግ ተፈናቃዮች 1.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የስንዴ (300 ኩንታል) ድጋፍ አድርጓል።
ዩኒቨርሲቲው በችግር ላይ ለወደቁት ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አሳውቋል።
በተጨማሪ በዞኑ የተለያዩ ምርምሮችን ተግባራዊ በማድረግ የህብረትሰቡን ችግር ለመፍታት የበኩሉን እንደሚወጣ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ በከተማዋ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም የካዳስተር ምዝገባ እና እወጃ ሥራ እንደሚካሄድ አሳውቋል።
ከዚህ ቀደም የመሬት ይዞታቸውን በካዳስተር ያላስመዘገቡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መረጃዎቻቸውን ለሚቀጥሉት ተከታታይ 15 ቀናት ማዘጋጀት እንደሚችሉ ተነግሯል።
ከተማ አስተዳደሩ ከ10 ዓመት በፊት ጀምሮ ሕጋዊ የመሬት ይዞታ የማረጋገጥ (ካዳስተር) ሥራ እየሠራ ሲሆን በዚህ ዓመት በመዲናዋ የለሚኩራ ክ/ከተማን ሳይጨምር በ10 ክፍለ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ 25 ቀጠናዎች ላይ የመሬት ይዞታን የማረጋገጥ እና የእወጃ ሥራ እንደሚሠራ ተገልጿል።
በዚሁ መሰረት ይዞታ የማረጋገጥ እና የእወጃ ሥራው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ለ5 ወራት እንደሚሠራ ተመላክቷል፡፡
በዚህ ወቅት በሕግ ተይዘው ካሉ የመሬት ጉዳዮች እና የሕግ ክርክሮች ውጪ ምንም ዓይነት #የስም_ዝውውር_እንደማይካሄድ ነው የተገለጸው፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ከ2008 ዓ. ም እስከ 2011 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ከ118 ሺህ በላይ የመሬት ይዞታዎችን እና ከ161 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በካዳስተር መመዝገቡ ተጠቁሟል።
ኤጀንሲው የምዝገባ ሒደቱ ተዓማኒ እንዲሆን ከማህበረሰቡ የተውጣጡ ታዛቢዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ማለቱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።