TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ERA

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አዲስ አበባን ከክልል ከተሞች ጋር የሚያገናኙ አራት ፈጣን መንገዶችን ለመገንባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገለፀ። ፈጣን መንገዶቹ አዲስ አበባን መዳረሻ በማድረግ ደብረ ማርቆስ፣ ጅማ፣ ነቀምት እና ኮምቦልቻ የሚገነቡ ሲሆን አዲስ አበባ አዳማ ፈጣን መንገድን ጨምሮ በከተማዋ እና በፈጣን መንገዶች መገናኛ ቦታዎች ላይ የማሻሻያ ሥራዎችን የሚጨምር ነው።

Via Addis Maleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ERA

ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የሚያገናኟትን መንገዶች ግንባታ እና ጥገና ማጠናቀቋን አስታወቀች!

(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንዳስታወቀዉ፤ ኢትዮጵያን እና ኤርትራን የሚያገናኙት መንገዶች ጥገናቸዉ ተጠናቋል ብሏል፡፡ የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ቡሬ አሰብ ፤ ራማ መረብ እና አዲግራት ዛላምበሳ መንገዶች ፤ ጥገናቸዉ በመጠናቀቁ የትራንስፖርቱ አገልግሎቱ ካለ መንገዶቹ ዝግጁ ናቸዉ ፤ ባለስልጣኑም የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ተወጥቷል ነዉ ያሉት፡፡

በነዚህ ድንበሮች አማካኝነት የሁለቱ አገራት ዜጎች እንዲገናኙ ከተደረገ በኋላ ድንበሮቹ መዘጋታቸዉ የሚታወስ ሲሆን የአየር በረራዉ ግን አሁንም እንቀጠለ ይገኛል፡፡ አገሪቱ ከኤርትራ ጋር ዕርቀ ሰላም ማዉረዷን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ20 አመታተ በኋላ ወደ አስመራ በረራ መጀመሯ የሚታወስ ነዉ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ድንበሮቹ ለምን ተዘጉ መቼስ ይከፈታሉ? ሲል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን የጠየቀ ሲሆን የሁለቱን አገራት የንግድ እንቅስቃሴ ህጋዊ ማእቀፍ እንዲኖረዉ እየተሰራ ነዉ እሱ እንዳለቀ ድንበሮቹ እንደሚከፈቱ አስታዉቋል፡፡ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ጋር በኢኮኖሚ እና በሌሎችም ዘርፎች የተሻለ ግንኙነት እንዲኖራት በትኩረት እንደምትሰራ በተደጋጋሚ አታስታዉቃለች፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ERA

የአይሳኢታ-አፋምቦ- ጅቡቲ ድንበር 48 ኪሎ ሜትር አስፋልት መንገድ ስራ መጀመሩን ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ። መንግስት በመደበው 1ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ የተጀመረው የአስፋልት መንገድ ስራ በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopiaRoadAuthority ኢትዮጵያን ከኤርትራ አሰብ ወደብ ጋር የሚያስተሳስረው የሜሎዶኒ መገንጠያ - ማንዳ - ቡሬ የመንግድ ግንባታ ፕሮጀክት ሊገነባ መሆኑ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሰልጣን አስታወቀ። በነገው ዕለትም ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ፕሮጀክቱን በይፋ የማስጀመር መርሃ ግብር ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። የሜሎዶኒ መገንጠያ - ማንዳ - ቡሬ መንገድ ሲጠናቀቅ…
#ERA

ዛሬ የሜሎዶኒ መገንጠያ - ማንዳ- ቡሬ የመንገድ ግንባታ መጀመሩ ተገልጿል።

ይህ ኤርትራ አሰብን መዳረሻ የሚያደርገው መንገድ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበት መሆኑን ትላንት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን መግለፁ ይታወሳል።

በሌላ በኩል 78 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የዲቾቶ-ጋላፊ መገንጠያ- በለሆ የኮንክሪት መንገድ ግንባታው ተጠናቆ በዛሬው እለት ለትራፊክ ክፍት ተደርጓል።

PHOTO : Afar Region Communication
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT