" ምዕራቡ ዓለም ወደ ድሀ አገራት የሚልከውን እርዳታ ወደ አውሮፓ ማዞሩን ያቁም " -የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት
የዩክሬን ስደተኞችን ለመርዳት የሚጣደፈው ምዕራቡ ዓለም ወደ ድሀ አገራት የሚልከውን እርዳታ ወደ አውሮፓ ማዞሩን እንዲያቆም የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት ጠየቀ።
የኖርዌይ የስደተኞች ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ያን ኢግላንድ " ዩክሬንን እርዱ ነገር ግን በሌላው የዓለም ክፍል ያለውን ቀውስም አትዘንጉ " ሲሉ ጠይቀዋል።
ሃላፊው ምዕራባውያን በጎ ፈቃደኞችና ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የዩክሬን ስደተኞችን ለመርዳት የሚያደርጉት ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው ለዩክሬን የተጠየቀው 1.7 ቢሊዮን ዶላር በቀናት ውስጥ ሲደርስ ለየመንም እንዲሰጥ የጠየቅነው ገንዘብ እንዲህ በፍጥነት ቢደረሰ ምንኛ ደስ ባለን ነበር ብለዋል።
ኢግላንድ እንዳሉት ፤ ለየመን እርዳታ ከተጠየቀው 4.2 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ የተገኘው ለዩክሬን ከተፈቀደው ያነሰ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ነበር ብለዋል።
የዩክሬን ጦርነት ሳህል አካባቢ ለሚኖሩ ሀገራት መጥፎ ዜና መሆኑን የገለጹት ኢገላንድ ዛሬ በነዚህ አካባቢዎች የምግብ እና የነዳጅ ዋጋ እንዲንር ማድረጉንም ተናግረዋል።
አንዳንድ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ለድሀ ሀገራት ይለግሱ የነበረውን እርዳታ ወደአውሮፓ ማዞራቸው ችግሩ ይበልጥ እንዲባባስ አድርጓል ብለዋል።
ኢግላንድ በአውሮጳ በተለይም በዩክሬን የሚፈለገውን እርዳታ ከመስጠት ጎን ለጎን የሌሎች ሀገራትን የእርዳታ ጥያቄዎችንም በእኩል ሁኔታ ማስተናገድ ይገባል ሲሉ ማሳሰባቸውን AFPን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ ዘግቧል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Oxfam " ኦክስፋም " ከአፍሪካ ቀንድ አስከፊ ድርቅ ጋር በተያያዘ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ኦክስፋም ፥ በአፍሪቃ ቀንድ በተከሰተው አስከፊ ድርቅ ለረሐብ ለተጋለጠው ሕዝብ መርጃ የሚዉል ገንዘብ ካልተገኘ ከፍተኛ ሰብአዊ ድቀት ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቋል። 👉ኢትዮጵያን፣ 👉 ሶማሊያን 👉 ኬንያን በመታዉ ድርቅ 13 ሚሊዮን ሕዝብ ለረሐብ መጋለጡን WFP ካስታወቀ 2 ወር ሊሞላ ነው። ድርጅቱ እንዳስታወቀዉ…
ለማስታወስ ...
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ፦
👉 በኢትዮጵያ 🇪🇹
👉 በሶማሊያ 🇸🇴
👉 በኬንያ 🇰🇪 ከተከሰተው ድርቅ ጋር በተያያዘ 13 ሚሊዮን ህዝብ ለከፋ ችግር መጋለጡን ከገለፀ ሁለት ወር ሊሞላው ነው።
ተመድ ለረሃብ ለተጋለጠዉ ሕዝብ መርጃ የሚዉል የምግብ እህል መግዢያ ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ዓለም አቀፉን ማህብረሰብ ተማፅኖ ነበር።
ነገር ግን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በ ' ዩክሬን ' ጦርነት ላይ ሙሉ ትኩረቱን ስላደረገ ላቀረበው ጥያቄ ተገቢ መልስ አላገኘም።
ከቀናት በፊት በወጣው መረጃ ማግኘት የቻለው 3 በመቶ ብቻ ነው።
በተለይም ደግሞ በጎረቤታችን ሶማሊያ ለረሃብ ለተጋለጠው 4.5 ሚሊዮን ህዝብ መርጃ ይሆን ዘንድ የተጠየቀው 1.46 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን እስካሁን የተገኘው 3 በመቶ ብቻ ነው።

#Update ዛሬ የአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የዉጪ ግንኙነት ኮሚቴ ኢትዮጵያን በሚመለከተዉ S.3199 በተባለዉ ረቂቅ ሕግ ላይ ይነጋገራል። በ2021 ላይ የተረቀቀዉ ሕግ የኢትዮጵያን ሠላም እና ዴሞክራሲን ለመደገፍ (ለማበረታት) ያለመ እንደሆነ አርቃቂዎቹ አስታዉቀዋል። ይህ S.3199 ረቂቅ ሕግ ከዚህ ቀደም ለአሜሪካ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት ከቀረበዉና H.R.6600 በሚል መለያ ከሚታወቀዉ…
#Update
በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር ሮበርት ሜንዴዝ የቀረበው S.3199 ረቂቅ ህግ ዛሬ ማለፉ ተሰምቷል።
ኮሚቴው ፤ "በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማበረታታ " በሚል ርዕስ የቀረበው S.3199 ላይ ተወያይቶ ማማሻያ ካደረገ በኃላ ነው ማሳለፉ የታወቀው።
የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ ተመልክቶ ያሳለፈው S.3199 ረቂቅ ህግ በጠቅላላ የምክር ቤቱ አባላት እንዲፀድቅ የሚመራ ሲሆን ህግ ሆኖ ለመውጣት የህግ አውጪው ምክር ቤት ድምፅ እና የፕሬዜዳንቱን ፊርማ ማግኘት አለበት።
S.3199 ረቂቅ ህግ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበው ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ላይ ሲሆን ከዚህ ረቂቅ ጎን ለጎንም HR.6600 የተሰኘ " በኢትዮጵያ መረጋጋት፣ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማስፈን " በሚል ርዕስ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ በህግ አውጪው ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ እንዲያየው መላኩን ቪኦኤ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን ሊፀድቁ በመንገድ ላይ ናቸው የተባሉት S.3199 እና HR.6600 ፤ ኢትዮጵያን ከሌሎች አገራት ጋር የሚኖራትን የጸጥታ፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ግንኙነት በሌሎች ኃይሎች በጎ ፈቃድ እንዲንጠለጠል እና ራሷን የማትከላከል ሽባ አገር የሚያደርጋት በመሆኑ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ረቂቅ ህጎቹ እንዳይፀድቁ ከፍተኛ ዘመቻ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል።

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
#Sport ግብፅ እና ሴኔጋል ዳግም ተገናኝተዋል። ግብፅ እና ሴኔጋል ለኳታሩ የአለም ዋንጫ ለማለፍ የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ በግብፅ መዲና ካይሮ እያደረጉ ይገኛሉ። በደርሶ መልስ (መጋቢት 15 እና 19) ከሚደረገው ጨዋታ በኃላ ግብፅ ወይም ሴኔጋል / ሞሀመድ ሳላህ ወይም ሳድዮ ማኔን በ2022 ዓለም ዋንጫው የምንመለከታቸው ይሆናል። ሁለቱ ሀገራት በአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ ላይ እልህ አስጨራሽ…
ሴኔጋል ለ2022 ዓለም ዋንጫ አለፈች።
የአፍሪካ ዋንጫ ባለድሏ ሴኔጋል በፍፃሜው ያገኘቻትን ግብፅን በድጋሚ በመለያ ምት በማሸነፍ ለኳታሩ 2022 ዓለም ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች።
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ሴኔጋል ካይሮ ላይ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፋ ነበር።
ዛሬ በሀገሯ ላይ በተካሄደው የመልስ ጨዋታ አንድ ጎል አስቆጥራ በመደበኛው እና ተጨማሪው ሰላሳ ደቂቃ በድምር ውጤት 1-1 ከተጠናቀቀ በኋላ ጨዋታው በመለያያ የፍፁም ቅጣት ምት በሴኔጋል 3-1 ውጤት ተጠናቋል።
ሴኔጋላዊው ኮከብ ማኔ በዓለም ዋንጫው ላይ የሚታይ ሲሆን ግብፃዊው ኮከብ ሳላህ በዓለም ዋንጫው ድንቅ ብቃቱን የሚያሳይበት ዕድሉ መክኗል።
@tikvahethsport

#ETHIOPIA ከነገ ጀምሮ ዜጎቻችንን የመመለስ ስራ ይጀመራል ተብሏል። ለረጅም ጊዜያት ሲጠበቅ የነበረው በሳዑዲ አረቢያ በከፋ ስቃይ ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ ነገ እንደሚጀመር ተገልጿል። የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ አረቢያ ሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ወደ አገራቸው የመመለስ ሥራ እንደሚጀመር አስታውቋል። ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን…
#ETHIOPIA
ኢትዮጵያ ከሳዑዲ ተመላሽ ዜጎቿን መቀበል ጀምራለች።
በዛሬው ዕለትም 157 ህፃናት እና 314 ሴቶች በድምሩ 498 ዜጎች በሰላም ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
በቀጣይ ከ7 እስከ 11 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎችን ለመመለስ እቅድ ተይዟል።
Via @tikvahethmagazine

በግንባት እቃዎች ላይ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ ምንድነው ? በግንባታ ግብዓቶች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ ከእጥፍ በላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ነጋዴዎች እየገለጹ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። በተለይ በቤት ክዳን ቆርቆሮ እና በሚስማር ምርቶች ላይ በ2 ሳምንታት ውስጥ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል። ለጋዜጣው ቃል የሰጡ ነጋዴዎች ፥ በቆርቆሮ ምርት ላይ ከ150 ብር በላይ ጭማሪ መታየቱን ገልፀዋል በአንድ…
" ለምን ? ብለን ስንጠይቅ ነፃ ገበያ ነው፤ ካዋጣችሁ መግዛት ካልሆነ መተው ትችላላችሁ ይሉናል " - የብረት ነጋዴ
በግንባት እቃዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እየታየ መሆኑ ከተነገረ ወራት አልፈዋል ይህ ጉዳይ አሁን ድረስ መፍትሄ ሳያገኝ ቀጥሏል።
ዛሬ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይዞት በወጣው መረጃ ላይ እደተመለከትነው ከግንባታ እቃዎች አንዱ በሆነው ፌሮ ብረት ላይ በሳምንት ውስጥ ብቻ የ300 ብር ጭማሪ ታይቷል።
ጋዜጣው ያነጋገራቸው በአዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ በረት ሻጭ የሆኑ አንዲት ነጋዴ ፤ የፌሮ ዋጋ በየዕለቱ፣ በየሰዓቱ ይጨምራል ያሉ ሲሆን ደንበኞች የዋጋ ጭማሪውን ፈርተው መግዛት አቁመዋል ብለዋል።
እኚሁ ብረት ሻጭ እንዳሉት የፌሮ አከፋፋዮች በማንአለብኝነት የውጭ ምንዛሬ ጨምሯል፣ ነፃ ገበያ ነው በማለት አሳማኝ ያልሆኑ ምክንያቶች እያቀረቡ ደስ ባላቸው ዋጋ ይሸጣሉ ሲሉ ተናግረዋል።
ሌላ ለጋዜጣው ቃላቸውን የሰጡት የብረት ሻጭ ፤ ከ3 ዓመት በፊት 75 ብር የነበረውና ከ1 ወር በፊት 200 ብር የነበረው ባለ8 ተብሎ የሚጠራ ፌሮ አሁን 500 ብር ገብቷል ብለዋል።
በዋጋ ንረቱ የደንበኞቻቸው ቁጥር መቀነሱንም ገልፀዋል። አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ስራውን ጥለው ሊወጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
የፌሮ ዋጋ በየጊዜው የሚጨምረው ከፋብሪካው ነው የሚሉት የብረት ሻጯ ፤ " ጠዋት ገዝተን ዕቃውን ለማስጫን ስንሄድ ጨምሯል፤ ብር ጨምሩ እንባላለን " ሲሉ አስረድተዋል።
ምክንያት ሲጠይቁም " ነፃ ገበያ ነው ፤ ካዋጣችሁ መግዛት ካልሆነ መተው ትችላላችሁ የሚል መልስ እንደሚሰጣቸው ገልፀዋል።
ያንብቡ https://telegra.ph/EPA-03-30

#Freedom_and_Equality ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን በትናንት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች በተገኙበት አካሂዷል። ጉባኤው የተሻሻለውን የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። የተጓደሉ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትንም ምርጫ አካሂዷል፡፡ ቀደም ሲል በነበረው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት 35 የነበረው ማዕከላዊ ኮሚቴ ብሄራዊ ምክር ቤት በሚል…
#Freedom_and_Equality
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ መጋቢት 18 ካካሄደው አንደኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ በኃላ ባለ10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
ነእፓ በዚህ የአቋም መግለጫው ላይ ካነሳቸው ጉዳዮች ቀዳሚዎቹ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ የፀጥታ ችግሮች ናቸው።
ፓርቲው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ላይ የተለኮሰው የጦርነት እሳት ሙሉ ለሙሉ ይቆም ዘንድ ሁሉም አካላት ግጭቱን ለማስቆም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል።
መንግስት በቅርቡ ለትግራይ ክልል ተጨማሪ ሰብአዊ ድጋፍ ከወትሮው በተሻለ መጠን እና ስፋት እንዲደርስ ለማድረግ ያሳየውን ተነሳሽነት እንደሚያደንቅ የገለፀው ነእፓ ውሳኔው በተቻለ ፍጥነት ተግባራዊ ይሆን ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።
ነእፓ ፤ ምንም እንኳን በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያለው ግልጽ እና ሰፊ ጦርነት የተለየ ትኩረት ያገኘ ቢሆንም፣ በሀገራችን የተለያዩ ግጭቶች እንዳሉ ይታወቃል ያለ ሲሆን በእነዚህ ግጭቶች ምክንያት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያ፣ መፈናቀል እና የንብረት ውድመት ዛሬም ድረስ ሊቆም አልቻለም ብሏል።
መንግስት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ላይ የተፈጠረውን ችግር እልባት ለመስጠት ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጎን ለጎን በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ለመጠበቅ በቂ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ሲል አሳስቧል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#Freedom_and_Equality ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ መጋቢት 18 ካካሄደው አንደኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ በኃላ ባለ10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። ነእፓ በዚህ የአቋም መግለጫው ላይ ካነሳቸው ጉዳዮች ቀዳሚዎቹ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ የፀጥታ ችግሮች ናቸው። ፓርቲው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ላይ የተለኮሰው የጦርነት እሳት ሙሉ ለሙሉ ይቆም ዘንድ ሁሉም አካላት…
" የኢኮኖሚ ቀውሱን ለማስተካከል መንግስት አፋጣኝ የማሻሻያ እርምጃዎች ይውሰድ " - ነእፓ
መንግስት እየናረ የሚገኘውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ።
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ካካሄደው አንደኛ ጠቅላላ ጉባኤ በኃላ ባወጣው የአቋም መግለጫ መንግስት በየጊዜው እየናረ የሚገኘውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስስ አፋጣኝ እና ተገቢ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሊያደርግ ይገባል ብሏል።
ፓርቲው የዋጋ ግሽበቱን ከሚያባባሱት ኢኮኖሚያዊ እና አስተዳደራዊ ምክንያቶች መካከል ፦
👉 በመረጃ እና እውቀት ላይ ያልተመሰረቱ ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች፣
👉 ወጥነት የጎደለው እና ያልተቀናጀ የመንግስት አሰራር፣
👉ሙስና ይገኙባቸዋል ብሏል።
በሀገራችን በፍጥነት እያደገ ለሚሄደው የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ዋነኛ ተጠያቂ መንግስት ነው ያለው ነእፓ የተፈጠረውን አጠቃላይ የኢኮኖሚ ቀውስ ለማስተካከል መንግስት አፋጣኝ የማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወስድ አሳስቧል።

#AddisAbaba🪧
በአዲስ አበባ ከተማ ህገወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች እየተነሱ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02፣ 08፣ 10 እና 13 በህገ ወጥ መንገድ መሰረተ ልማት አውታሮች እና የዋና መንገድ ኤልክትሪክ ፖሎች ላይ የተሰቀሉ ህገ ወጥ የውጭ ማስታውቂያ ማንሳቱን አስታውቋል።
ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያዎች የተነሱባቸው ቦታዎች ፦
👉 ከሳህሊተ ምህረት እስከ የተባበሩት ግራ እና ቀኝ ፣
👉 ከተባበሩት እስከ ፍየል ቤት ፤
👉 ከፍየል ቤት እስክ ፊጋ
👉 ከተባበሩት እስከ አያት አደባባይ
👉 ከአያት አደባባይ እስከ ጣፎ አደባባይ ድረስ በግራና በቀኝ በኩል ተሰቅለው የነበሩ ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን አሳውቋል።
በቀጣይም በሌሎች ክፍለ ከተሞች የተሰቀሉ ህገወጥ የውጭ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች የማንሳት ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
መረጃው የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ነው።

#EthioTelecom
ኢትዮ ቴሌኮም ለተማሪዎች ልዩ ጥቅል ማቅረቡን ገለፀ።
ኢትዮ ቴሌኮም ለኮሌጅ እና ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልዩ የሆነ የተማሪ ጥቅል ማቅረቡን አሳውቋል።
በዚህም :
ወርሃዊ ፦
• ዋጋ 👉 34 ብር ፤ ጥቅል 👉 180 ደቂቃ (ጥሪ) ፤ ስጦታ 90 ደቂቃ (ጥሪ) + 100 መልዕክት ፤
• ዋጋ 👉 64 ብር ፤ ጥቅል 👉 360 ደቂቃ (ጥሪ) ፤ ስጦታ 200 ደቂቃ (ጥሪ) + 150 መልዕክት ፤
• ዋጋ 👉 42 ብር ፤ ጥቅል 👉 1 GB (ዳታ) ፤ ስጦታ 512 MB (ዳታ) + 100 መልዕክት ፤
• ዋጋ 👉 82 ብር ፤ ጥቅል 👉 2 GB (ዳታ) ፤ ስጦታ 1.1 GB (ዳታ) + 150 መልዕክት ፤
ሳምንታዊ ፦
• ዋጋ 👉29 ብር ፤ 3 GB (ዳታ) መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም ፤ ሳምንታዊው የዳታ ጥቅል እና ለደንበኞች የቀረቡት ስጦታዎች የሚያገለግሉት ከለሊቱ 6 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት መሆኑን አሳውቋል።
ተማሪዎች ተማሪነታቸውን የሚገልፅ " መታወቂያ " በመያዝ በኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከሎች በመቅረብ ጥቅሎቹን መግዛት ይችላሉ ተብሏል።