TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቻይና ከትላንናው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ እስካሁን አንድም የተረፈ ሰው አልተገኘም ብላለች። ትናንት 132 ሰዎች አስፍርኖ የነበረ " ቦይንግ 737-800 " አውሮፕላን በቻይና ምስራቃዊ ክፍል በደቡባዊ ጓንጊዢ ተራራማ ቦታ ላይ መከስከሱ ይታወሳል። ምባልባት ከአደጋው የተረፈ ሰው ይኖር እንደሆነ በነፍስ አድን ሰራተኞች ፍለጋ ቢደረግም እስካሁን በህይወት የተረፈ ሰው ማግኘት አለመቻሉን…
" የተረፈ ሰው የለም "
ባለፈው ሰኞ 132 ተጓዦችን እና የበረራ ሠራተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው የቻይናው አውሮፕላን መከስከሱን ተከትሎ ሁሉም በውስጡ የነበሩት ሰዎች መሞታቸውን ቻይና አረጋግጣለች።
132 ሰዎች አስፍርኖ የነበረው " ቦይንግ 737-800 " አውሮፕላን በቻይና ምስራቃዊ ክፍል በደቡባዊ ጓንጊዢ ተራራማ ቦታ ላይ መከስከሱ ይታወሳል።
ምባልባት ከአደጋው የተረፈ ሰው ይኖር እንደሆነ በነፍስ አድን ሰራተኞች ፍለጋ ቢደረግም ምንም የተረፈ ሰው እንደሌለ ትላንት ተረጋግጧል።
@tikvahethiopia

#NewsAlert የኦፌኮ ጠቅላላ ጉባኤ ፕ/ር መረራ ጉዲና ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ መረጠ። አቶ በቀለ ገርባ ደግሞ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ ተመርጠዋል። ፕ/ር መረራን ለሊቀመንበርነት የጠቆሟቸው አቶ ጃዋር መሀመድ ሲሆኑ የጉባኤው አባላቶች ለሊቀመንበርነት እና ለተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበርነት አቶ ጃዋር መሀመድን ቢጠቁሙም ጥቆማውን Decline ማድረጉ ተገልጿል። በሌላ በኩል ፤…
#OFC
ትላንት በኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተመረጡት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባላት በጉባኤው ፊት ቃለመሃላ ፈፅመዋል።
በሌላ በኩል ፤ የፓርቲው የኦዲት እና ኢንስፔክሽን አባል የሆነው የተመረጡ አባላትም ቃለመሃላ ፈፅመዋል።
ትላንትና በነበረው የመጀመሪያው ቀን የኦፌኮ ጠቅላላ ጉባኤ ፕ/ር መረራ ጉዲና - ሊቀመበር ፣ አቶ በቀለ ገርባ - ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ፣ አቶ ጃዋር መሃመድ - ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው እና የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ አባላት መመረጣቸው ይታወሳል።
አቶ ጃዋር ምንም እንኳን ለሊቀመንበርነት እና ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበርትነ በጉባኤተኛው ተጠቁመው ውድቅ ቢያደርጉም ጉባኤው የፓርቲው ም/ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧቸዋል።
የኦፌኮ ም/ ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ ለረጅም ዓመታት በውጭ ሀገር ሆነው የ " ኢህአዴግ " መራሹን መንግስት ተገዶ ወደ ለውጥ እንዲገባ በማስገደድ በሚዲያው እና በአክቲቪዝሙ መስክ ጉልህ ድርሻ የተጫወቱ ሲሆኑ በኃላም ወደ ሀገራቸው በመግባት ምርጫቸውን ኦፌኮ በማድረግ ሙሉ በሙሉ የፖለቲካውን ዓለም ሊቀላቀሉ ችለዋል።
አቶ ጃዋር መሀመድ ለአንድ አመት ከመንፈቅም ታስረው ከወራት በፊት ታህሳስ 29/2014 ዓ/ም መፈታታቸው አይዘነጋም።
Photo Credit : Ubuntu TV

#Djibouti #Ethiopia
የጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ገብተዋል።
በሁለት ቀን የስራ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ያደርጋሉ።
የፕሬዚዳንቱን መምጣት ተከትሎ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ወንድሜ ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ወደ ሁለተኛ ቤትዎ እንኳን በደህና መጡ " ያሉ ሲሆን " በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በጋራ ጉዳዮቻችን ላይ ፍሬያማ ውይይት እንደምናደርግ እምነቴ ነው " ብለዋል።

🌧 ቦረና 🌧 ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ አስከፊ ድርቅ ውስጥ የነበሩ አካባቢዎች ዝናብ ጥሏል። ይህም ነዋሪዎች ላይ ደስታን ፈጥሯል። ከሰሞኑን በእነዚህ አከባቢዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ፈጣሪያቸውን በማመስገን ከብቶቻቸው የዝናብ ዉሃ ሲጠጡ የሚያሳይ ፎቶ እና ቪዲዮ በማሕበራዊ ሚዲያ እያጋሩ ይገኛሉ። ቃላቸውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ክፍል የሰጡት የቦረና ዞን ኤልዋዬ ወረዳ ነዋሪው አባ ሾባ ሞሉ ዝናብ…
#BORANA
ከሰሞኑን በከፍተኛ ድርቅ ውስጥ የነበሩ የቦረና አካባቢዎች ዝናብ አግኝተዋል።
ነዋሪዎች ክብር ለፈጣሪ ይሁንና ፈጣሪያቸውን በማመስገን ከብቶቻቸው የዝናብ ዉሃ ሲጠጡ ሚያሳዩ ፎቶ እና ቪዲዮ በማሕበራዊ ሚዲያዎች እያጋሩ ይገኛሉ።
ከሰሞኑ ዝናብ ጋር በተያያዘ አቶ ሙስጠፋ ከዲር በኦሮሚያ የቡሳ ጎኖፋ ጽ/ቤት ሀላፊ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የተናገሩት ፦
" በሁሉም ወረዳዎች ላይ ዝናብ ዘንቧል። በቂ ባይሆንም በቦረና ወረዳ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ምዕራብ ባሌ ዘንቧል።
ጅማሬው ጥሩ ይመስላል። የአየር ትንበያ ዝናብ እንደሚዘንብ ያሳያል። አሁን ያለው ዝናብ የነበረውን ችግር ይፈታል ባንልም፣ ዉሃ ያገኛሉ።
ነገር ግን የሰው እርዳታ ብያንስ ለሚቀጥሉት ሶሰት፣ አራት ወራት ሊቀጥል ይገባል።
ዝናብ ስለጣለ ብቻ እህል አይበቅልም ፣ ሰብል አይዘራም። ስለዚህ የማሕበረሰቡ እርዳታ መቋረጥ የለበትም።
በወንዝ አከባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎችም ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ፤ ከብቶቹን ለጊዜው በማቆያ ውስጥ እንዲያገግሙ ማድረግ አለባቸው። "

🌧 ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ - ዝናብ ጥሏል 🌧
በታሪኳ እጅግ አስከፊ በሆነ ድርቅ ላይ የምትገኘው እና 4.5 ሚሊዮን ህዝቧ ለረሃብ የተጋለጠው ጎረቤታችን ሶማሊያ ዝናብ አግኝታለች።
በሀገሪቱ ብዙ ክፍሎች ላይ ዝናብ መጣሉን የሚገልፁ ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው።
አሁንም ከፍተኛ ደመና በተለያዩ ቦታዎች የሚታይ ሲሆን ብዙ ቦታዎች ተጨማሪ ዝናብ ያገኛሉ ተብሎ ይገመታል።
ዝናቡ ሲጠፋ የድርቅ አደጋ ፤ ዝናቡ ሲገኝ ደግሞ የጎርፍ አደጋው ያሳስባልና ነዋሪዎች በጎርፍ ከሚመጣው አደጋ እንዲጠነቀቁም መልዕክት እየተላለፈ ነው።
የሀገሬው ሰው በማህበራዊ ሚዲያው #አልሃምዱሊላህ እያለ ለፈጣሪው ምስጋናን እያቀረበ ነው።
ቪድዮ - ሃሩን ማሩፍ

🌧 ኢትዮጵያ - ሶማሌ ክልል 🌧
" በሶማሌ ክልል አከባቢዎች የበልግ ዝናብ መዝነብ ጀምሯል " - የሶማሌ ክልል መንግሥት
የሶማሌ ክልል መንግስት ዛሬ አመሻሽ ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ያወጣ ሲሆን የድርቁ ጉዳይ አንዱ ነው።
ክልሉ በመግለጫው ላይ ፤ የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ህዝብና እንስሳትን ለመታደግ በሰራው ስራ ድርቁን መቋቋም መቻሉን ገልጿል።
ከክልሉ መንግሥትና ህዝብ ጎን በመሆን ድጋፍ እና ትብብር ያደረጉ አካላት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን በማንሳትም ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርቧል።
አሁን የድርቅ አደጋ ጊዜ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ያሳወቀው የሶማሌ ክልል መንግስት በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች የበልግ ዝናብ መጣል በመጀመሩ፣ ድርቁን ለመቋቋም እንደተሰራው አሁንም በድህረ ድርቁ እና በዚህ መሸጋገሪያ ወቅት ጠንካራ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን አሳውቋል።
በክልሉ አከባቢዎች የበልግ ዝናብ መዝነብ በመጀመሩ በአጠቃላይ ከሚጥለው ዝናብ በድርቁ የተጎዱ ዜጎች ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም በዝናቡ ምክንያት በወንዞችና ተፋሰስ አከባቢዎች ሊከሰቱ የሚችሉ የጎርፍ አደጋዎች፣ ወረርሽኝና ተዛማጅ ጉዳዮች ለመከላከል ጠንካራ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የተሰሩ መሆኑን ገልጿል።

በኮንሶ ዞን የሰገን ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት ኃላፊ ተገደሉ።
በኮንሶ ዞን የሰገን ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ገረሙ ገለቦ ትላንት መጋቢት 17/2014 ዓ/ም ሰገን ከተማ ላይ ከምሽቱ 3:20 አካባቢ ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር እራት ለመብላት በተቀመጡበት ሆቴል ውስጥ በጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉን የቲክቫህ ቤተሰቦች ገልጸውልናል።
በዛሬው ዕለት የወረዳው ሠላም እና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ባወጣው የሀዘን መግለጫ " አቶ ገረሙ ጽ/ቤቱን መምራት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ስራ በመስራት የወረዳው የገቢ መጠን እንድሻሻል አድርገዋል። በወረዳችን ውስጥ የሚገኙ የነጋዴው ማህበረሰብ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኝ ብሎም የሚጠበቅበትን ግብር እንዲከፍል ጠንካራ ተግባራትን በማከናወን ላይ ነበሩ " ብሏል።
ጸ/ቤቱ ጥቃቱን የፈጸሙት " ቅጥረኛ ሽፍቶች " ናቸው ሲል ገልጿል።
የጥቃቱ አድራሾች እና በጥቃቱ ላይ እጃቸው ያለበት እያንዳንዱ ግለሰብ አድኖ የመያዝ እና ለህግ የማቅረብ ስራ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጥምረት እየሰራ እንደሚገኝም አሳውቋል።
'' የወንጀሉ አፈፃፀም ከመሠረቱ ጀምሮ በደንብ ተጣርቶ የወንጀሉ ፈፃሚና ተባባሪዎች ለህዝብ እናሳውቃለን " ያለው ፅ/ቤቱ መላው የወረዳው ህዝብ በተፈጠረው ችግር ሳይደናገጥ የዕለት ተእለት እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል አሳስቧል።
በሌላ በኩል ፤ በኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር ከኧሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ቦታዎች ግጭት ማገርሸቱን የቲክቫህ ቤተሰቦች የጠቆሙ ሲሆን የሰው ህይወት መጥፋቱን እና እስከ ትላንትና ድረስ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ገልፀዋል።
(ተጨማሪ መረጃዎችን ነገ የምንልክላችሁ ይሆናል)

#Afar
የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመሆን ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ላይ ለተጠለሉ 9,000 ሰዎች የምግብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉ የስንዴ ዱቄት ፣ አተር ክክ ፣ የማዕድ ጨው እና የምግብ ዘይትን ያካተተ ነው፡፡
በሌላ በኩል ፤ ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በአፋር ክልል ከ500,000 በላይ እንስሳትን ከአደገኛ በሽታዎች ለመከላከል የሚረዳ የክትባት ዘመቻ እያከናወነ ይገኛል፡፡
ይህም በግጭት የተጎዱ በክልሉ የሚገኙ አርብቶ አደር ማህበረሰቦች መተዳደሪያ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ይረዳል ተብሏል።
#ICRC

#AmharaRegion
በጦርነት ምክንያት በአማራ ክልል ፤ ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ባለው እጅግ የከፋ ችግር በርካታ ህፃት እና እናቶች ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፤ ይሄ በተደጋጋሚ ተገልጿል።
በችግር ላይ ላሉት ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ ቢሆንም ካለው የከፋ ሁኔታ አንፃር ምንም ነው።
የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለሴቶች እና ሕጻናት 3 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአይነት እና ለ300 እናቶች ደግሞ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አሚኮ ዘግቧል።
እንዲሁም በክልሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እስካሁን 200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ቢያደርጉም ከተከሰተው ችግር ስፋት ጋር የሚጣጣም ሆኖ አልተገኘም።
ችግሩንም መፍታት አልተቻለም።
መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፣ ባለሃብቶች በችግር ላይ ለወደቁ ወገኖች አሁንም ድጋፋቸው አጠናክሮ እንዲቀጥሉ እና ሕጻናትን እና እናቶችን መታደግ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።
ፎቶ ፦ አሚኮ

#AmharaRegion በጦርነት ምክንያት በአማራ ክልል ፤ ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ባለው እጅግ የከፋ ችግር በርካታ ህፃት እና እናቶች ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፤ ይሄ በተደጋጋሚ ተገልጿል። በችግር ላይ ላሉት ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ ቢሆንም ካለው የከፋ ሁኔታ አንፃር ምንም ነው። የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለሴቶች እና ሕጻናት 3 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአይነት እና…
#AmharaRegion
በአማራ ክልል ውስጥ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት " የዕለት ምግብ ያስፈልጋቸዋል " ተብለው ከተለዩት ዜጎች መካከል ፦
👉 50 በመቶ ሴቶች ናቸው።
👉 400 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ሕጻናት ናቸው።
በአማራ ክልል፤ ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ብቻ ፦
👉 በ3 መጠለያ ጣብያዎች የተፈናቃዩ ቁጥር ከ65 ሺ 700 በላይ ደርሷል። ከዚህ ውስጥ:-
• 18 ሺህ የሚያጠቡ ናቸው።
• ከ1 ሺህ 100 በላይ አረጋውያን ናቸው።
• 590 የሚሆኑት አካል ጉዳተኞች ናቸው።
ምንጭ ፦ የአማራ ክልል ሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ / የዋግኽምራ ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ / አሚኮ