TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#COVID19Ethiopia በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,916 የላብራቶሪ ምርመራ 890 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 247 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 76,988 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,208 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 31,677 ደርሷል። @t…
መስከረም 22/2013 ዓ/ም

የኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 208 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሰው በኮቪድ-19 መያዙ ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 120 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 23 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 566 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 104 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#DireDawa

በድሬዳዋ 168 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 67 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል።

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 311 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 103 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 451 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 135 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 3,274 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 333 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Gambella

በጋምቤላ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 92 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 5 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ትላንት 2 ሰዎች አገግመዋል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 822 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 61 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopiaBOT
ጥቅምት 1/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 142 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 104 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 39 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1,154 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 99 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ99ኙ መካከል 64 ከምዕ/ጎጃም ዞን ፣ 16 ከባህር ዳር ከተማ ይገኙበታል።

#DireDawa

በድሬዳዋ 142 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 47 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 468 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 19 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 471 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 169 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 3,913 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 365 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#Harari

በሐረሪ ባለፉት 24 ሰዓት 120 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 53 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 645 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 50 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 184 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 18 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

@tikvahethiopiaBOT
ጥቅምት 2/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሶማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት የላብራቶሪ ምርመራ አልተደረገም። ትላንት 10 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 60 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 659 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 93 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 349 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 16 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1132 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 201 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 2,763 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 399 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopiaBOT
ጥቅምት 4/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሶማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 146 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሰው አልተገኘም።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 85 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 27 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 765 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 76 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የ2 ሰው ህይወት አልፏል (1 ከእንጅባራ ህክምና ማዕከል፣ 1 ከሃይቅ)

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 579 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 102 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 142 የላብራቶሪ ምርመራ 54 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 94 የላብራቶሪ ምርመራ 13 ሰዎች በቫረረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1304 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 55 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#AddisAbaba

በአ/አ ባለፉት 24 ሰዓት 3,246 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 308 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

* ያልተካከቱ የክልል ሪፖርቶችን ቆይት ብላችሁ ይህንኑ ፖስት ተመልከቱ !

@tikvahethiopiaBOT
ጥቅምት 6/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 137 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 35 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 606 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 115 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የ1 ሰው ህይወት አልፏል (ከጎንደር)

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 560 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 101 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ1 ሰው ህይወት አልፏል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 185 የላብራቶሪ ምርመራ 12 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 94 የላብራቶሪ ምርመራ 05 ሰዎች በቫረረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

* ላልተካከቱ የክልል ሪፖርቶችን ቆየት ብላችሁ ይህንኑ ፖስት ተመልከቱ !

@tikvahethiopiaBOT
#Metekel

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን "የጸጥታ ችግር" ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት የተረጋገጠ ከፍተኛና በየደረጃው ያሉ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋል እንደጀመሩ የክልሉ መንግስት ዛሬ ምሽት ገልጿል።

እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ፦

• አቶ ቶማስ ኩዊ ፡- የኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ

• አቶ አድጎ አምሳያ፡- የቀድሞው የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር

• አቶ ሽፈራው ጨሊቦ፡-የቀድሞ የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር

• አቶ ባንዲንግ ማራ፡- የመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

• አረጋ ባልቢድ፡- የመተከል ዞን የቀድሞ አመራር የነበሩ

#BenishangulGumuz #MetekelZone

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#BenishangulGumuz

የኢትዮጵያ መንግሥት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ያለውን ችግር ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ ማድረጉን ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ዛሬ ጥዋት አሳወቁ።

በክልሉ መተከል ዞን ውስጥ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በተፈጸመው ኢሰብአዊ የሆነ ተግባርም በእጅጉ ማዘናቸውን ገልፀዋል።

ጠ/ሚሩ ችግሩን በተለያዩ መንገዶች ለመፍታት የተደረገው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት አላመጣም ብለዋል። መንግስት አሁን ላይ የተቀናጀ ኃይል እንዲሰማራ ማድረጉን በፌስቡክ ገፃቸው አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BenishangulGumuz

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት አቶ አሻድሊ ሀሰን የሚመሩት ክልል ከአየር ሰዓት ኪራይ ወጥቶ የራሱ ሳታላይት የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዲኖረው የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መሆኑን አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳደሩ ይህን ያሉት ዛሬ ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረቡት የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ነው።

አቶ አሻድሊን ሀሰን ፥ "ክልሉ በራሱ ሳታላይት የቴሌቪዝን ጣቢያ በሙሉ አቅሙ ስርጭት እንዲጀምር ለማስቻል ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ እየተሠራ ነው" ብለዋል፡፡

እስካሁን ድረስ በተደረገው ጥረት አብዛኛው ሥራ የተጠናቀቀ ሲሆን ፣ በቅርብ ውስጥ ጊዜ ውስጥ የሙከራ ስርጭት እንደሚጀምር አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia
#BenishangulGumuz : ወደ 9ኛ ክፍል የማለፊያ ዉጤት ይፋ ሆነ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ወደ 9ኛ ክፍል የማለፊያ አማካይ ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል።

በዚህም ለወንዶች 30 ለሴቶች ደግሞ 29 መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በ2013 የትምህርት ዘመን በክልሉ በ211 ትምህርት ቤቶች 13 ሺህ 631 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ሲሆን 13 ሺህ 049 (95 ነጥብ 73 በመቶ) ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ አስመዝግበዋል።

በክልሉ ለፈተናው ከተቀመጡት አጠቃላይ ተማሪዎች ውስጥ 4 ሺህ 106 ተማሪዎች 50 እና በላይ አማካይ ውጤት አምጥተዋል።

ዘንድሮ በክልሉ የተመዘገበው ከፍተኛው አማካይ ውጤት 95 ነጥብ 21 ሆኗል።

በጸጥታ ችግር ምክንያት የ8ኛ ክፍል ፈተናውን መውስድ ያልቻሉ ተማሪዎች በቀጣይ ትምህርት ቢሮ በሚያስቀምጠው የጊዜ ሠሌዳ ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

የ2014 ዓ.ም ትምህርት ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

@tikvahethiopia
#BenishangulGumuz : ኢሰመኮ በመተከልና ካማሺ ዞኖች የዜጎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ሊፋጠኑ እንደሚገባ አሳስቧል።

* የኢሰመኮ መግለጫ ከላይ ተያይዟል፤ ያንብቡ!

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሀሰን ጨምሮ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ የሰራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ወደ ግንባር ለመዝመት ውሳኔ አሳለፉ። " በግንባር ተገኝቼ ጦሩን እመራለሁ " ብለው ወደ ግንባር ያቀኑት የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብይ አህመድ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ የሰራ አስፈጻሚ…
#BenishangulGumuz

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ግንባር ዘምተው ጦሩን እንደሚመሩ በይፋ ካሳወቁ በኃላ " እኛም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ወደ ጦር ግንባር እንዘምታለን " ያሉት ከፍተኛ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለስልጣናት መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና እየወሰዱ እንደሚገኙ ታውቋል።

ከትላንት አርብ አንስቶ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጠናት መሠረታዊ የውትድርና ስልጠና እየወሰዱ ሲሆን ስልጠናው ዛሬ ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው የክልሉ መንግስት ያስታወቀው።

ባለስልጣናቱ ዛሬ አካላዊ የስፓርት እንቅስቃሴ ጨምሮ ፣ መሠረታዊ የቦታ አያያዝ፣ ዒላማና የተኩስ ልምምድ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በስልጠናው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ባለስልጣናት ፥ " ከስልጠናው በኋላ ህወሓትና ተላላኪዎቹ አገራችን ለማፍረስ የከፈቱትን ጦርነት ለመቀልበስ በግንባር ተገኝተን ፊት ለፊት ጦርነቱን ለመምራት ቁርጠኛ ነን " ሲሉ ተናግረዋል።

ለ ክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እየተሰጠ የሚገኘው መሠረታዊ የውትድርና ስልጠና ለቀጣዮቹ 5 ቀናት እንደሚቀጥልም ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ዞኖች በፀጥታ ችግር ምክንያት ከ2 ዓመት በላይ ምንም አይነት የመብራት አገልግሎት አላገኙም።

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መለሰ በየነ ለአሐዱ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፥ ባለፉት ዓመታት በመተከል እና ካማሽ ዞኖች በታጣቂዎች የተስተጓጎለው የመብራት አገልግሎት መፍትሔ ሳያገኝ እስካሁን ድረስ ዘልቋል ብለዋል፡፡

በዚህም ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት ተዳርጓል ፤ በተለይም በከተሞች አካባቢ በመብራት ኃይል ብቻ ስራቸውን የሚሰሩ ዜጎችን ለስራ አጥነት ተጋላጭ አድርጓቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ችግሩ መቼ ይፈተል በሚል ከቴሌቪዥን ጣቢያው ለቀረበላቸው ጥያቄ ፥ " በቀጣይ የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ሲስተካከል እግር በግር በመከተል ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመመለስ ይሰራል " ሲሉ መልሰዋል።

ምንጭ ፦ አሐዱ ቴሌቭዥን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአንደኛው ዙር በፀጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ዛሬ ፈተናቸውን ጀምረዋል። መልካም ፈተና! @tikvahethiopia
#Update

የመጀመሪያው ቀን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሲሰጥ ውሏል።

ፈተናው በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተሰጥቷል።

#Amahra

በአማራ ክልል ከ37 ሺ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ዛሬ ፈተና ሲሰጥ ውሏል። ፈተናው በደቡብና ሰሜን ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞኖችና በደሴ ከተማ ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን 3 ወረዳዎች፣ በሰሜን ጎንደር ዞን በ1 የፈተና ጣቢያ ፈተናው ነው የተሰጠው።

በሌላ በኩል ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ተፈናቅለው ለመጡ 220 ተማሪዎችም በልዩ ሁኔታ በቡሬ በተቋቋመ የመፈተኛ ጣቢያ ተፈትነዋል።

#OromiaRegion

በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን በ12 ወረዳዎች በ42 የፈተና ጣቢያዎች 14,228 ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸው ፤ ፈተናውን እንደሚወስዱ ከተጠበቁት 16,608 ተማሪዎች መካከል 1, 243 በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና ላይ አለመቀመጣቸው ተገልጿል።

በምዕራብ ወለጋ የቤጊ እና ቆንደላ ወረዳዎች 1,137 ተማሪዎች በአራት የፈተና ጣቢያ ፈተናው ላይ የተቀመጡ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች 931 ተማሪዎች ፈተናው ላይ እንዳልተቀመጡ ተገልጿል።

#Afar

በአፋር ክልል ፈተናውን ይወስዳሉ ተብለው ከተጠበቁት 257 ተማሪዎች 154 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ጀምረዋል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን አንፃራዊ ሠላም ተመዝግቦባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሲሰጥ ውሏል።

• የሁለተኛው ቀን ፈተና ይቀጥላል።

መረጃ ፦ ኢብኮ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ የአማራክ ክልል ትምህርት ቢሮ

ፎቶ ፦ የደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ የወልዲያ ከተማ ፣ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮዎች ፣ የቤ/ጉ ክልል ትምህርት ቢሮ

@tikvahethiopia
#BenishangulGumuz , #Kamashi📍

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሺ ዞን አስተዳደር በአገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች በኩል፣ በዞኑ ከሚገኙ ታጣቂዎች ጋር እየተነጋገረ መሆኑ ተገልጿል።

በዞኑ አስተዳደርና በታጣቂዎች መካካል የሚደረገው ንግግር " ጥሩ ደረጃ " ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ ያሏቸውን ጥያቄዎች በሽማግሌዎች በኩል በደብዳቤ አቅርበው ሁለቱም አካላት በተነሱ አጀንዳዎች ላይ መስማማታቸው ታውቋል፡፡

በቅርቡ አዳዲስ አመራሮች የተሾሙለት ካማሺ ዞን፣ አዲሶቹ አመራሮች ያዋቀሯቸው የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ወደ የሚገኙበት ያሶ ወረዳ ሄደው ታጣቂዎቹን ማነጋገራቸው ተገልጿል፡፡

ከዞኑ አስተደዳር የተላኩት እነዚህ ልዑካን ከታጣቂዎች ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ በታጣቂዎቹ በኩል የተወከሉ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶችን ይዘው ወደ ካማሺ ከተማ መመለሳቸው ተሰምቷል፡፡

በሁለቱም በኩል ያሉ ልዑካን ጥር 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ይዘው የመጡትን የውይይት ሪፖርት በተመለከተ፣ ከዞኑ አመራሮች እንዲሁም በዞኑ ከሚገኙና ከክልሉ የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብጅጋ ጻፊዮ ፤ ከውይይቱ በኋላ በሁለቱም ወገን ያሉ ሽማግሌዎች ተመልሰው ወደ ታጣቂዎቹ ዘንድ መሄዳቸውን አስረድተዋል፡፡

በካማሺ በተደረገው ውይይት ላይ ታጣቂዎቹ ለሰላም ፍላጎት እንዳላቸው በሽማግሌዎቹ በኩል መግለጻቸውን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው፣ ታጣቂዎቹም ሆነ የክልሉ መንግሥት ባሏቸው አጀንዳዎች ላይ መግባባት እንዳለ ገልጸዋል፡፡

የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባን ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-02-09

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BenishangulGumuz , #Kamashi📍 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሺ ዞን አስተዳደር በአገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች በኩል፣ በዞኑ ከሚገኙ ታጣቂዎች ጋር እየተነጋገረ መሆኑ ተገልጿል። በዞኑ አስተዳደርና በታጣቂዎች መካካል የሚደረገው ንግግር " ጥሩ ደረጃ " ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ ያሏቸውን ጥያቄዎች በሽማግሌዎች በኩል በደብዳቤ አቅርበው ሁለቱም አካላት በተነሱ አጀንዳዎች…
#BenishangulGumuz , #Kamashi📍

የካማሺ ዞን ታጣቂዎች ያናሷቸው ጥያቄዎች ምንድናቸው ?

የካማሺ ዞን ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ኮሎኔል ዓለሙ በሽር  ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደተናገሩት ታጣቂዎቹ በእስር ላይ ያሉ አባሎቻቸው እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

የዞኑ አስተዳደሮች ይሄ ጥያቄ በዞኑ የሚመለስ እንዳልሆነ አስረድተው፣ በጉዳዩ ላይ ከበላይ አካላት ጋር ንግግር በማድረግ መልስ እንደሚሰጡ አሳውቀዋል።

ሌላው በመተከል ዞን የሚገኙና ከክልሉ ውጪ ያሉ የፀጥታ ኃይሎች እንዲወጡ ታጣቂዎቹ ጠይቀዋል።

ኮሎኔል ዓለሙ በሽር ፥ " የሌሎቹን አላውቅም፤ የፌዴራል ፖሊስ እና መከላከያ ሠራዊትን ግን ማስወጣት አይችሉም፣ ይኼ አይመለስላቸውም እርግጠኛ ነኝ " ብለዋል።

በተጨማሪም ታጣቂዎቹ " በክልሉ ውስጥ ድርሻ ይኑረን " የሚል ጥያቄም አንስተዋል።

የካማሺ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብጅጋ ጻፊዮ ፤ ታጣቂዎቹ ያቀረቧቸውን ጥያቄዎች በተመለከተ በካማሺ ዞን ደረጃ ሚስተናገዱትን እንደሚመለሱ በክልል ወይም በፌዴራል ደረጃ የሚመለሰውን ደግሞ የዞኑ አስተዳደር ለበላይ አካላት እንደሚያስታውቅ ስምምነት ላይ መደረሱን ለጋዜጣው አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia