TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Russia

ሩስያ በሀገሯ ፣ በኩባንያዎችና በህዝቧ ላይ " ወዳጃዊ ያልሆኑ " ድርጊቶችን የፈፀሙና እርምጃ የወሰዱ / ወዳጅ ያልሆኑ ሀገራትን እና ግዛቶችን ዝርዝር በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጋለች።

እነዚህም ፦

🇺🇦 ዩክሬን
🇺🇸 አሜሪካ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇪🇺 የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት
🇦🇺 አውስትራሊያ
🇨🇦 ካናዳ
🇮🇸 አይስላንድ
🇯🇵 ጃፓን
🇲🇨 ሞናኮ
🇲🇪 ሞንቴኔግሮ
🇳🇿 ኒውዚላንድ
🇳🇴 ኖርዌይ
🇹🇼 ታይዋን (ቻይና እንደ ተገንጣይ ግዛቷ የምትቆጥራት ሲሆን እሷ ግን ነፃ እና ሉዓላዊ ሀገር ነኝ በሚል እራሷን ችላ ነው የምትተዳደረው)
🇸🇲 ሳን ማሪኖ
🇸🇬 ሲንጋፖር
🇰🇷 ደቡብ ኮሪያ
🇨🇭 ስዊዘርላንድ
🇦🇱 አልባንያ
🇦🇩 አንዶራ
🇱🇮 ሌይቼንስቴይን
🇫🇲 ማክሮኔዢያ
🇲🇰 ሰሜን ሜቄዶንያ ናቸው።

ከላይ የተጠቀሱት ሀገራት እንዲሁም ግዛቶች በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ጥለዋል ወይም በሚጣለው ማዕቀብ ላይ ተቀላቅለዋል የተባሉ ናቸው።

@tikvahethiopia
#Russia #Poland #Germany

አዲስ አበባ ያለው የሩስያ ኤምባሲ ያሰራጨው መልዕክት መነጋገሪያ ሆኗል፤ በኤምባሲዎች መካከልም ውዝግብ ፈጥሯል።

የሩስያ ኤምባሲ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ለሩስያ ድጋፋቸውን የሚገልፁ በየዕለቱ ብዙ ደብዳቤዎች ፣ በመቶዎች የሚቆጠር አስተያየት እንደሚደርሰው ገልጿል።

ይህ መልዕክት እየደረሰው ያለው ከገፁ ተከታዮች መሆኑን አመልክቷል።

ኤምባሲው " ሀገሮቻችን በችግር ጊዜ በመደጋገፍ እና በመረዳዳት እንደዚህ አይነት ጠንካራ ፣ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ፣ ወዳጃዊ ግንኙነት ስላላቸው ኩራት ይሰማናል " ብሏል።

አክሎም " ልክ አያቶቻችን ከ80 ዓመታት በፊት እንዳደረጉት ናዚዝምን እየተዋጋን ባለንበት በአሁን ጊዜ ያሳያችሁን ድጋፍ እና ከሩስያ ጎን ለመቆም ስለመረጣችሁ በእጅጉ እናደንቃለን " ብሏል።

የሩስያ ኤምባሲ ይህንን መልዕክት ካሰራጨ በኃላ የሌሎች ሀገራት ኤምባሲዎች ምላሽ ሰጥተዋል ፤ ምላሽ ከሰጡት መካከል የፖለንድ ኤምባሲ አንዱ ነው።

ፖላንድ ኤምባሲ ፤ ሩስያ የሀሰተኛ መረጃ እያሰራጨች ነው ሲል ወቅሷል።

ኤምባሲው " የናዚ መስፋፋት የጀመረው በ1939 በፖላንድ ላይ በተደረገ ሕገ-ወጥ ወረራ ነው ፤ በወቅቱም ሞስኮ እንደ አጋር ነበረች ብሏል።

" ሩስያ በዩክሬን ላይ ከፈፀመችው ህገ-ወጥ የሆነ ጥቃት ጋር በተያያዘ ፤ ማን ከናዚዎች ጋር መነፃፀር እንዳለበት ሁለት ጊዜ ማሰብ ይገባል " ሲል ኤምባሲው ገልጿል።

ሌላው ለሩስያ ኤምባሲ ምላሽ የሰጠው የጀርመን ኤምባሲ ሲሆን ኤምባሲው በጉዳዩ ዙሪያ ዝም ሊል እንደማችል ገልጿል።

" ናዚዝም " ን እንዋጋለን በሚል ሉዓላዊ ሀገርን መውረር ፣ ሰላማዊ ዜጎችን እና ሆስፒታሎችን ማፈንዳት (ልክ ትላንት በማሪፖል በሚገኘው የእናቶች እና ህፃናት ሆስፒታል እንደተደረገው) የሚያሳዝን እና የሀሰተኛ መረጃ ማሳያ ነው ብሏል።

ይህ ጦርነት " ናዚዝም " ን ለመዋጋት እንዳልሆነ ይታወቃል ያለው የጀርመን ኤምባሲ ጦርነቱ ለአምባገነን ስርአቶች ትልቁ ፈተና እና ስጋት የሆነውን ዲሞክራሲን፣ የፕሬስ ነፃነትን እና የህዝብ ድምጽን መዋጋት ነው ብሏል።

ኤምባሲው ፤ " የሩሲያ ታንኮች ሰላም ፣ ውሃ ወይም ምግብ አያመጡም ፤ መከራ እና ጥፋት ብቻ ነው የሚያመጡት " ብሏል።

@tikvahethiopia
#Russia

የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚመጡ እና ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎች ለሩሲያ መዋጋት ይችላሉ አሉ።

ፑቲን ፤ " ገንዘብ ሳይከፈላቸው ለሩሲያ መዋጋት የሚፈልጉ ሰዎች አሉ " ካሉ በኋላ፤ " እነዚህን ሰዎች ወደ ጦር ግንባር በመላክ ማድረግ የሚፈልጉትን መተባበር አለብን " ብለዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተነስተው በዶንባስ ግዛት ከሩሲያ ጦር ጎን መሰለፍ የሚፈልጉ 16 ሺህ ሰዎች አሉ ሲሉ ለፑቲን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለፀጥታ ምክር ቤታቸው ምዕራባውያን " በግልጽ ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመተላለፍ ተዋጊዎችን ለዩክሬን እየቀጠሩ ነው " ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ከዚህ ቀደም ዩክሬን በ "አፍሪካ" በተለያዩ ሀገራት በሚገኙት ኤምባሲዎቿ በኩል በ #ቅጥር ለዩክሬን የሚዋጉ ሰዎችን እንደምትፈልግ ማስታወቋ በኃላ ይህ ጥሪው ቁጣን ፈጥሮ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#Russia

ሩስያ ከዛሬ ማክሰኞ ጀምሮ ስንዴ፣ በቆሎ፣ አጃ፣ እና ስኳር ወደ ውጭ እንዳይላክ አገደች።

ሩስያ እህል ለቀድሞ የሶቪየት ሀገራት እንዳይላክ እና በአብዛኛው የስኳር ምርት ወደሌሎች ሀገራት እንዳይላክ ለጊዜው ማገዷ ተሰምቷል።

እገዳው እኤአ እስከ ሰኔ 30 ይቆያል ተብሏል።

ነገር ግን በልዩ የኤክስፖርት ፈቃድ አሁን ባለው የኮታ ሥርዓት ለነጋዴዎች መከፋፈሉ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ሩስያ እህል እና ስኳር እንዳይላክ ለጊዜው ማገዷ መሰማቱን ተከትሎ ከወዲሁ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ መሆኑ ተነግሯል።

ሩስያ በዓለማች ላይ ከፍተኛ እህል ላኪ ሀገር ስትሆን ቱርክ እና ግብፅ ደግሞ ከሩስያ በመግዛት ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ።

@tikvahethiopia
#RUSSIA #USA

ሩስያ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት #ጆ_ባይደንን ጨምሮ ሌሎች የአሁን እና የቀድሞ ባለስልጣናት ወደ ሀገሬ ድርሽ እንዳትሉ ስትል ማዕቀብ ጣለች።

የሩሲያ መንግስት ወደ ሩስያ እንዳይገቡ እገዳ ከጣለባቸው መካከል ፦

👉 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

👉 የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን

👉 የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን

👉 የCIA ዳይሬክተር ዊሊያም በርንስ

👉 የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጀን ሳኪ፣

👉 የመከላከያ ሚኒስትር ሊዮይድ አውስቲን

👉 የቀድሞዋ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ይገኙበታል።

በተጨማሪ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ተሩዶ ወደ ሩሲያ እንዳይገቡ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።

ቀደም ሲል አሜሪካ በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ ላይ ማዕቀብ ጥላ ነበር።

መረጃው የአርቲ ኒውስ እና የአልዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia