TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Telegram

ከ10:20 ጀምሮ ቴሌግራም ተቋርጦ እንደነበረ ተጠቃሚዎች ገልፀዋል።

ችግሩ ሀገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አውሮፓ ሀገራት እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ውስጥ ነው የተከሰተው።

ድርጅቱ ከተጠቀሰው ሰዓት አንስቶ ተጠቃሚዎች አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ #አረጋግጧል ፤ የችግሩን ምክንያት ግን አላሳወቀም።

በአሁን ሰዓት የቴሌግራም አገልግሎት ተቋርጦ በነበረባቸው ሁሉም ቦታዎች ላይ መስራት ጀምሯል ፤ ድርጅቱም ይህንን አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2ተኛው ቀን የ12ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ ተሰጥቷል። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ትላንት የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ/ም መጀመሩ ይታወቃል። በዛሬው ዕለት የ2ኛው ቀን ፈተና በመላ ሀገሪቱ ሲሰጥ ውሏል። ከፈተናው ሂደት ጋር በተያያዘ የተለያዩ አስተያየቶች ከተማሪዎች እና ከተማሪ ወላጆች እያደረሱን ይገኛሉ። አንዳንድ ተማሪዎች ስልክ ይዞ የመገኘትም ነገር እንደነበረ ተፈታኞች ለቲክቫህ እያሳወቁ ነው።…
#Telegram

ቴሌግራም ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰዓታት ተቋርጦ ነበር።

ዛሬ ጥዋት #ቴሌግራም ተቋርጦ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። አገልግሎቱ የ12ኛ ክፍል ፈተና ማብቃት ከታወቀ በኃላ ተመልሷል።

ምንም እንኳን ዛሬ ሙሉ በሙሉ ቢቋረጥም ከትላንት ጀምሮ ፍጥነቱ ቀንሶ ፣ ፎቶዎች እና ቪድዮችን ለመለዋወጥ አስቸጋሪ ሆኖ ነበር።

ከ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር በተያያዘ ከቀናት በፊት የተማሪ ወላጆች እና ተፈታኝ ተማሪዎች ያነሷቸውን ቅሬታ አጋርተን ነበር።

በአንዳንድ ቦታዎች የሞባይል ስልክ ይዘው ወደ መፈተኛ ክፍሎች የሚገቡ ተማሪዎች ፈተናውን ፎቶ በማንሳት በቴሌግራም የመስራት ሁኔታ እንደነበረ በቂ ማስረጃ እንዳላቸው የቲክቫህ አባላት የሆኑ ተማሪዎች እና ወላጆች መግለፃቸው አይዘነጋም።

ምንም እንኳን ቴሌግራም ከትላንት ጀምሮ ፍጥነቱ ቢቀንስም ፥ ዛሬ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ቢዘጋም VPN በመጠቀም የዛሬውን ፈተና ከመፈተኛ ክፍል ውስጥ ፎቶ በማንሳት በሺዎች የሚቆጠሩ አባላት ባላቸው የቴሌግራም ግሩፖች ላይ የማሰራጨት ነገር እንደነበር ተስተውሏል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ የትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ዘንድሮ የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት 8 ፈተናዎች በ32 ስብጥር በማድረግ ኩረጃ እንዳይኖር ለመከላከል መሰራቱን አሳውቃል።

በተጨማሪ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና በፍፁም እንዳልተሰረቀ አረጋግጣለሁ ብሏል ፤ በአንዳንድ የፈተና ጣቢያዎች ስልክ ይዘው የገቡ በጣም ጥቂት ተማሪዎች መኖራቸውን ግን ገልጿል ፤ ይህ ሁኔታ ከፈተና ኩረጃ ጋር የሚያያዝ እንጂ የፈተና ስርቆት ነው ማለት አያስችልም ብሏል የትህምርት ሚኒስቴር።

@tikvahethiopia
#Telegram

ቴሌግራም በተጠናቀቀው 2021 / እ.አ.አ. / ድንቅ የሚባል አመትን እንዳሳለፈ የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ ዛሬ ምሽት አሳውቀዋል።

ጥር ወር ላይ በመላው ዓለም ላይ በብዛት ዳውንሎድ የተደረገ መተግበሪያ ፣ በጥቅምት ወር በአንድ ቀን ብቻ ከ70 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ተጠቃሚዎችን መቀበል የቻለ እንዲሁም በታህሳስ ወር በፍጥነት እያደገ ያለ መተግበሪያ ተብሎ መታወጁ ተገልጿል።

የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፥ " የእድገቱ ሁሉ ባለቤቶች ተጠቃሚዎቹ እንደሆኑ እናውቃለን " ያሉ ሲሆን በተጠቃሚዎች የሚሰጡትን አስተያየቶች በጥሞና በማድመጥ አመቱን ሙሉ ቴሌግራም ለተጠቃሚዎቹ የተሻለ እንዲሆን አድርገናል ብለዋል።

ቴሌግራም በተጠቃሚዎች ጥያቄ መሰረት በቻናሎች፣ ግሩፖች እንዲሁም የአንድ ለአንድ መልዕክ ልውውጥ ወቅት ሪአክሽን መስጫ (👍👎❤️😢...) እንዲሁም የመልዕክት መተርጎሚያ የተካተተበት በዓመቱ 12ኛ ዋና ማሻሻያ ተደርጎበት ተለቋል።

አዲሱ የሪአክሽን ማሻሻያ የሚሰራው የቻናሉ ወይም የግሩፑ ባለቤቶች ክፍት ሲያደርጉ ነው። እንዴት ? (ወደ ቻናሉ /ግሩፕ በመግባት Edit የሚለውን መጫን ፣ በመቀጠል Enable Reactions የሚለውን ON ማድረግ እና የሚሰጡትን Reaction መምረጥ)

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ዋናውን የቴሌግራም መተግበሪያችሁን (ባለ ሰማያዊ ምልክቱን) Update በማድረግ ማሻሻያዎቹን እንድትመለከቷቸው መልዕክት እናስተላልፋለን።

የቴሌግራም መተግበሪያችሁን Update ለማድረግ👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=org.telegram.messenger

@tikvahethiopia