TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ማስታወሻ

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የተሟለ መረጃ እንዲያጠናክሩ የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃል።

ከተሰጠው ቀነ ገደብ በኋላ መረጃዎችን ያልሰጡ ደንበኞች አካውንታቸውን #ማንቀሳቀስ አይችሉም።

ባንኮች ባለፉት 6 ወራት መመርያው በሚጠይቀው መሥፈርት መሠረት የደንበኞቻቸውን መረጃ እየሰበሰቡ ነው፡፡ 

ይህንኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ተከትለው ደንበኞቻቸው በግንባር ወደ ባንክ ቀርበው በመመርያው መሠረት አስፈላጊ መረጃ እንዲሰጡ እያደረጉ ቢሆንም ጥቂት የማይባሉ ደንበኞች በመመርያው መሠረት ወደ ባንክ በመሄድ መረጃ እየሰጡ አይደለም ተብሏል።

በዚሁ የቀነገደቡ ማብቂያ ሳምብት ባንኮች በስልክ ጭምር እያስተናገዱ ነው።

ባንኮች መረጃ ሰብስበው እንዲያጠናቅቁ የተሰጣቸው ጊዜ የሚጠናቀቀው የካቲት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ሲሆን ከየካቲት 21 ቀን 2014 በኋላ መረጃዎቻቸውን ለባንክ ያልሰጡ የባንክ ደንበኞች አካውንታቸውን ማንቀሳቀስ አይችሉም።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ [NBE] የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር አቶ ፍሬዘር አያሌው መረጃቸውን ባለመስጠት አካውንታቸው እንዳይንቀሳቀስ የሚደረጉት ደንበኞች አካውንታቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉት በአዲሱ አሠራር መሠረት በመመርያው የተቀመጠውን መረጃ ሲሰጡ ብቻ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የባንክ ኃላፊዎች በተለይ #ቼክ የሚያንቀሳቅሱ የባንክ ደንበኞች፣ በብሔራዊ ባንክ ድንጋጌ መሰረት መረጃውን ቀርበው ካልሞሉና በዚሁ ምክንያት አካውንታቸው የማይንቀሳቀስ ከሆነ ይከፈል ያሉት ቼክ የማይከፈል መሆን ጋፀው ለማይቀረው ነገር በቶሎ የሚፈለግባቸውን ይሙሉ ማለታቸውን ሪፖርተር አስነብቧል።

ያንብቡ : telegra.ph/Reporter-02-25

@tikvahethiopia