TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DESSIE የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በደሴ ከተማ ለሚገኙ የኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸው አረጋዊያን የምሳ ግብዣ ተደረገ። የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር መለስ መኮንን በእዚህ ወቅት እንደገለጹት ግብዥው የተደረገው አረጋዊያን በዕድሜ ዘመን ቆይታቸው ለሃገራቸው ያበረከቱትን ውለታ በማሰብ የተደረገ ነው። አረጋዊያን መደገፍና ማገዝ የወጣቱን የመርዳት ባህል ከማሳደጉም ባለፈ በዕድሜ ቆይታ ጉልበታቸው የደከመ አረጋዊያን በህዝባቸው ኩራትና ደስታ እንዲሰማቸው የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል። ከንቲባው እንዳሉት ለአረጋዊያኑ የምዛ ግብዥ ከማድረግ በተጨማሪ የአልባሳት ድጋፍ ተደርጓል። ድጋፉን ከተማ አስተዳደሩ ከወሎ ዩኒቨርሲቲና ከፍሬው የአረጋውያን በጎ አድራጎት ማህበር ጋር በጋራ ያዘጋጁት መሆኑንም ተናግረዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WolaitaSodo #Dessie

በወላይታ ሶዶና በደሴ ከተማ የታየው የመጠጥ ውሃ ጥራት በሌሎችም ከተሞች ሊታይ እንደሚገባ የውሃ ልማት ኮሚሽን አስታወቀ። የወላይታ ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ለህብረተሰቡ የሚያሰራጨውን ውሃ በኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት ተመርምሮ የኢትዮጵያ የመጠጥ ውሃ የተቀመጠለት መስፈርት በማሟላቱ የ ሲኢኤስ - 58 አይሶ ፡ 2019 (CES-58 ISO :2019) ጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አገኘ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር በሻህ ሞገሴ የሰርተፍኬት ማግኘቱን ምክንያት በማድረግ ትናንትና በብሉ ስካይ ሆቴል የዕውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ እንደገለፁት በሀገራችን በሁለቱ ከተሞች የታየው የውሃ ጥራት በኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት ተመርምሮ አልፏል፤ ይህ ተሞክሮ ሌሎች የሀገራችን ከተሞች ሊተገብሩት ይገባል ብለዋል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DESSIE

በሞጣ ከተማ የደረሰውን የመስጂዶችና ንብረት ቃጠሎ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች አወገዙ!

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ አስተዳደር ታኅሣሥ 10 ቀን 2012ዓ.ም በመስጅዶችና ንብረት ላይ የደረሰውን ቃጠሎ የደሴ ከተማ አስተዳደር ሙስሊሞች በሠላማዊ ሰልፍ አወገዙ፡፡ ነዋሪዎቹ ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ በደሴ ከተማ ሠላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡

(AMMA)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#DESSIE

በደሴ ከተማ አስተዳደር በከተሞች ምግብ ዋስትና እና ሥራ እድል ፈጠራ ፕሮግራም አንድ ሺህ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ከጎዳና የማንሳት ስራ መጀመሩን የከተማው ምክትል ከንቲባ አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Dessie

ሀጂ ሠይድ ያሲን ከሠሜን ወሎ ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምግብ እና አልባሳት ድጋፍ አደረጉ።

በደሴ ከተማ በ4 ጊዜያዊ መጠለያዎች ተፈናቃዮች የሚገኙ ሲሆን ሀጂ ሠይድ ያሲን በእነዚህ መጠለያዎች ላሉ ወገኖች ነው ድጋፍ ያደረጉት።

የሀጂ ሠይድ ያሲን ድጋፍ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሲሆን ነጭ ዱቄት ፣ ብርድ ልብሶችና የሠሌን ምንጣፎችን ያካተተ ነው ፤ ድጋፉ በደሴ ከተማ ህዝባዊ መጅሊስ አማካይነት መደረጉን ከደሴ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#Dessie : የደሴ ከተማ ፀጥታ ምክር ቤት ከዚህ ቀደም ካሳለፋቸው ውሳኔዎች በተጨማሪ ሌሎች ውሳኔዎችን በዛሬው ዕለት አሳልፋል።

ከዚህ ቀደም የተላለፈው የሰዓት እላፊ ገደብ ባለበት የሚቀጥል ሲሆን ማንኛውም የንግድ ድርጅትም ሆነ የሰዎች እንቅስቃሴ ከምሽቱ 2፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በተጣለው የሰአት እላፊ ገደብ መሠረት ቁጥጥሩ ተጠናክሮ ስለሚቀጥል ማህበረሰቡ ለፀጥታ ሃይሎች ተባባሪ እንዲሆን ተጠይቋል።

የፀጥታ ም/ቤት በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተፈናቃይ በመኖሩ እና የከተማውን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል ያልተፈቀዱ ስብሰባዎች እና ህገ-ወጥ ሰልፎች ማድረግ በጥብቅ መከልከሉ አሳውቋል።

ማንኛውም ሰው ከተፈቀደለት የፀጥታ ሃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስም ሆነ በመዝናኛ ቦታ ይዞ መገኘት የተከለከለ መሆኑን ም/ቤቱ አሳስቧል።

በተከለከለ ቦታ ባጃጅ ማሽከርከር፣ ያለ ሰሌዳ ተሽከርካሪ ማሽከርከርና ከተፈቀደላቸው ተሽከርካሪ ውጭ ሰአት እላፊ ማሽከርከር በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ የደሴ ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ም/ቤት አሳውቋል።

* ሙሉ የደሴ ከተማ ፀጥታ ም/ቤት መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#Dessie : ዛሬ ሮይተርስ በድረገፁ ከደሴ ከተማ የተሰራ ሰፋ ያለ ዘገባ አስነብቧል።

በዚሁ ዘገባ አንዲት ሀብታም አከለ የምትባል እናት በምግብ እጥረት ምክንያት ልጇን እንዳጣች ተናግራለች።

ሀብታም የ3 ዓመት ህፃን ልጇን በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ባለፈው ወር ነው ያጣችው (ከቆቦ) ወደ ደቡብ የአማራ ክልል ክፍል ከመሸሻቸው በፊት።

ሀብታም ፥ ዶክተሮች ልጇ በምግብ እጥረት በጣም እንደተጎዳች በዚህም ምክንያት ልጇን ሊረዷት እንዳልቻሉ እንደነገሯት ተናግራለች። ዶክተሮቹ መድሃኒት ቢሰጧትም ትንሿ የሀብታም ልጅ ከሳምንት በኃላ ህይወቷ አልፏል።

ሀብታም የሰሜኑን ጦርነት ሽሽት ወደ ደሴ ከተሰደዱ በሺዎች ከሚቆጠሩ የአማራ ቤተሰቦች አንዷ እንደሆነች ሮይተርስ ፅፏል።

በደሴ ተፈናቃዮች በትምህርት መማሪያ ክፍል ውስጥ በተጨናነቀ ሁኔታ በረድፍ ነው የሚተኙት ዳግም በከፍተኛ ሁኔታ ያገረሸው ግጭት ደግሞ ይህን ያባብሰዋል ተብሎ ይሰጋል።

ሀብታም በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች አነስተኛ ምግብ እንዳለ እንዲሁም የትግራይ ኃይሎች በአካባቢው ከሚገኙ ፋርማሲዎች ያለውን አነስተኛ መድኃኒቶችን እንደዘረፉ ተናግራለች።

የህወሓቱ ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ይህንን ክስ እንደማይቀበሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል፤ ይልቁንም ሃብታም ትኖር በነበረበት አካባቢ በጄኔሬተር ያለውን ውሃ እጥረት ለመቅረፍ መስራታቸውን ገልፀዋል።

ሌላ በካምፕ ውስጥ የምትገኝ እና ሮይተርስ ያነጋገራት አንዲት ሴት በታጠቀ የትግራይ ኃይል መደፈሯን ገልፃለች። ይህ የተፈፀመባት በትግራይ ኃይሎች ስር ባለ የአማራ ክልል አካባቢ ነው።

ስሟ ሰዓዳ ይባላል እድሜዋ 26 ሲሆን ከደሴ 80 KM በምትገኘው በመርሳ ከተማ ቤቷ ውስጥ እያለች ነው ይህ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባት።

ሰዓዳ ትክክለኛውን ቀን ባታስታውሰው። ድርጊቱ ነሐሴ መጨረሻ አካባቢ መፈፀሙን ተናግራለች።

ሰዓዳ እንደደፈራት የገለፀችው የትግራይ ኃይል ፥ " እኛ ቤታችንን ጥለን የወጣነው ለመግደልም ለመሞትም ነው። እኔ ከጫካ ነው የመጣሁት የፈለኩትን የማድረግ ሙሉ መብት አለኝ፤ ልግድልሽም ሁሉ እችላለሁ" ብሎ ጠመንጃውን ከፍ አድርጎ ካስፈራራት በኃላ እንደደፈራት ለሮይተርስ ተናግራለች።

ሰዓዳ ሮይተርስ ሙሉ ስሟን እንዳይጠቀም የጠየቀች ሲሆን ከተደፈረች በኃላ ለህክምና ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መሄዷንም የሚያሳይ ካርድ አሳይታለች።

የደሴ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ልዑል መስፍን ስለሲቪል ጉዳት፣ ስለ አስገድዶ መድፈር ወይም ስለ ግለሰብ ጉዳይ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል ፤ ለዚህ ምክንያታቸው የውጭ ጋዜጠኞችን ስለማያምኑ መሆኑ እንደገለፁ ሮይተርስ ፅፏል።

https://telegra.ph/Dessie-10-18-2

@tikvahethiopia
#Dessie : በዛሬው ዕለት የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል ወቅታዊ ሁኔታን ተንተርሶ ለከተማው ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባው ባስተላለፉት መልዕክት " የጸጉረ ልውጦችን እንቅስቃሴ ለመግታት ያመች ዘንድ #ከዛሬ ጀምሮ የሞተር እና የባጃጅ እንቅስቃሴ በከተማዋ ላይ እንዲቆም በጸጥታ ምክር ቤት ውስኗል ሲሉ አሳውቀዋል።

በከተማው የተዘጉ የተለያዩ የንግድ ቤቶች በተለይ መድሀኒት ቤቶች በአስቸኳይ ተከፍተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ያሳሰቡ ሲሆን ይህን በማያደርጉት ላይ አስፈላጊውን የህግ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።

አቶ አበበ ፥ የከተማው ነዋሪ አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ጸጉረ ልውጦችን ለጸጥታ ሀይሉ የማስረከብ ስራ ከምንግዜውም በላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ከንቲባው ፥ "ለሰራዊታችን የሚደረገው የምግብና የውሀ አቅርቦት በአደረጃጀት ተጠናክሮ እንዲቀጥል" ያሉ ሲሆን " ወጣቱ ፣ አመራሩ፣ የመንግስት ሰራተኛው፣ እና አጠቃላይ ህዝባችን የጀመረውን የግንባር ደጀንነት አጠናክሮ እንዲቀጥል" ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኬላ እና የውስጥ ከተማውን ጥበቃ በማጠናከር የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅ ሁሉም ማህበረሰብ እርብርብ እንዲያደርግ ፤ የከተማዋ ማህበረሰብም በመደራጀት ከጸጥታ አካሉ ጋር በመሆን የከተማውን ቁልፋ እና መለስተኛ በሮች በመዝጋት የጥላት ሰርጎ ገበች እንዳይገቡ መከላከል እንደሚገባም በመልዕክታቸው ገልፀዋል።

አቶ አበበ ፥ " ነዋሪው ከተለመደው የጥላት የሀሰት ወሬ እና ፕሮፖጋንዳ እራሳችንን በማራቅ ከተማችን ላይ ተረጋግተን መቀመጥ አለብን" ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Dessise : ከደሴ ከተማ ውጭ ካለ ስፍራ ወደ ደሴ ከተማ በተተኮሱ የመድፍ አረሮች ምክንያት 1 ሰው ሲገደል 3 ሰዎች መቁሰላቸውን የደሴ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል አስታውቁ። አቶ አበበ ገብረ ይህን ያሳወቁት ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ነው። ከንቲባው ጥቃቱ ትናንት ሐሙስ ጥቅምት 18/2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በግምት 9:30 የተፈፀመ መሆኑን ገልፀው ፥ "የህወሓት ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎች በሚገኙባቸው…
#Dessie

ደሴ ትላንት ከሰዓት መጠነኛ አለመረጋጋት ተከስቶ ነበር፤ አስተዳደሩ ክስተቱ የተፈጠረው " የህወሓት ተላላኪዎች በፈጠሩት ሀሰተኛ ውዥንብር ነው " ብሏል ፤ አለመረጋጋቱ ተስተካክሎ ማህበረሰቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው እየተመለሰ መሆኑም ለኢዜአ ገልጿል።

ለከተማው አለመረጋጋት ምክንያት የነበሩትንም ከማህበረሰቡ ውስጥ ተለይተው በማውጣት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል ተብሏል።

በሌላ በኩል ትላንት ወደ ደሴ በተወረወረ ከባድ መሳሪያ አንድ ሰው መገደሉን ከከተማው አስተዳደር ተሰምቷል፤እስካሁን ወደከተማው በተወረወረ ከባድ መሳሪያ የተገደሉ ሰዎች 3 ደርሰዋል።

የደሴ ም/ከንቲባ ሰይድ የሱፍ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል፥ በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) በሚወረወረው ከባድ መሳሪያ እስካሁን 3 ሰዎች መሞታቸውና 10 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ላይ ናቸው ብለዋል።

ህወሓት ከደሴ ከተማ ውጭ ሆኖ የሚተኩሳቸው የከባድ መሳሪያ አረሮች የሚያርፉት በጦርነት ምክንያት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ዜጎች የተጠለሉባቸው ቦታዎች መሆኑን፤ ትላንት ይኸው የከባድ መሳሪያ አረር የወደቀው ተፈናቃዮች መጠለያ አካባቢ ነው ብለዋል አቶ ሰይድ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል።

@tikvahethiopia
#Dessie #Kombolcha

ወሎ ህብረት የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ኃይሎች በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተሞች በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን መጨፍጨፋቸውን የተለያዩ ምንጮች ማረጋገጣቸውን ገልጿል።

ማህበሩ ፤ እነዚህ ኃይሎች ወጣቶቹን የጨፈጨፏቸው በከተማቸው ለመቆየት ስለወሰኑ ነው ብሏል።

በተጨማሪ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ የሟቾችን አስክሬን መንገድ ላይ እንዲቀር መደረጉንና ይህም ህዝቡን በማሸበር በግዳጅ እንዲፈናቀል በማድረግ ወራሪዎቹ ኃይሎች የህዝብ እና የግል ንብረቶችን በነፃነት ለመዝረፍ እንዲያመቻቸው ነው ሲል አሳውቋል።

ወሎ ህብረት በኮምቦልቻ እና ደሴ ከተሞች ህዝብን ለማሸበር በTPLF ኃይሎች ሆን ተብሎ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው ግድያ በአለም አቀፍ ደረጃ የጦር ወንጀል የሆነ የሽብር ተግባር ነው ብሎታል።

ህብረቱ ይህን አረመኔያዊ የሽብር ድርጊት እናወግዛል ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ወንጀለኞችን በህግ እንዲጠየቅ እና ተጨማሪ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ እንዲከላከል አሳስቧል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በማያሻማ መልኩ በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) የተፈፀመውን አሳፋሪ የሽብር ድርጊት እንዲያወግዝ ሲል አሳስቧል።

ወሎ ህብረት የልማት እና በጎ አድራጎት ማህበር በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ የተመዘገበ ህጋዊ ሰውነት ያለው ሀገር በቀል ድርጅት ነው።

@tikvahethiopia
#Dessie

" የህክምና ቁሳቁሶቹን ባለሞያዎች መጥተው ነው የፈቷቸው " - የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

በአማራ ክልል እጅግ ከፍተኛ ውድመት ከደረሰባቸው ሆስፒታሎች መካከል የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዋነኝነት ይጠቀሳል።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሃይማኖት አየለ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ ሆስፒታሉ 80 ዓመቱ ሲሆን የደረሰበት ጉዳት 80 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ከ0 እንዲጀምር እንደሚያደርገው ነው የምንቆጥረው ብለዋል።

ሆስፒታሉ በህወሓት ኃይሎች የመድሃኒት ቤቱ አንድም ሳይተርፍ ተዘርፏል/ወድሟል፣ የላብራቶሪ እቃዎች ተዘርፈዋል፣ በምስራቅ አማራ ብቸኛው የኦክሲጅን ማምረቻው ተዘርፎ ተወስዷል የተረፈው አገልግሎት እንዳይሰጥ ተደርጎ ወድሟል፤ በምስራቅ አማራ ብቸኛው የካንሰር ህክምና መስጫ ቁሳቁሶች ተዘርፎ ተወስዷል።

ዶ/ር ሃይማኖት አየለ ዝርፊያው በተጠና መልኩ እንደተካሄደና ባለሞያዎች መጥተው እንደፈቷቸው አሳውቀዋል።

ሆስፒታሉ አሁን ላይ በተወሰነ መልኩ ወደአገልግሎት የተመለሰ ሲሆን የወሊድ፣ ድንገተኛ አገልግሎት እና የተመላላሽ ታካሚዎችን እያስተናገደ ሲሆን ሆስፒታሉ ታካሚዎችን እያስተናገደ ያለው ቁሳቁስ ስላለው ሳይሆን ባለሞያዎች ባላቸው ሞያ ብቻ አገልግሎት መስጠት ስላለባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ዶ/ር ሃይማኖት ገለፃ በሆስፒታሉ በወር በአማካይ 800 እናቶች በሆስፒታሉ ሲወልዱ እንደነበር አስታውሰው አገልግሎት በመቋረጡ በርካቶች ለጉዳት መዳረጋቸውን ገልፀዋል።

ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአማራ ክልል ምስራቅ አማራ፣ አፋር ክልል እንዲሁም የትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በአጠቃላይ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይገለገሉበት እንደነበር የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ለሬድዮ ጣብያው በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Dessie #Hayq

ትምህርት ሚኒስቴር በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ እና ሀይቅ ከተሞች በህወሓት የሽብር ቡድን ወረራ ምክንያት ከ2 ወር በላይ ተቋርጦ የቆየው ትምህርት በድጋሚ እንደጀመረ አሳውቋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን (ጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kombolcha📍 የኮምቦልቻ ከተማ ከሶስት ቀን ቡኃላ የምግብ ዘይት ስርጭት ይከናወናል ብሏል። የከተማው ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት ከ3 ቀን በኃላ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ቀበሌዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የዘይት ስርጭት እንደሚያደርግ አስታውቋል። ፅ/ቤቱ ከሚያደርገው የቁጥጥር ሥራ በተጨማሪ አቅርቦቱ ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ስለሆነ ነዋሪዎች በተፈጠረው ያልተገባ የዋጋ ንረት አላስፈላጊ…
#Dessie📍

ደሴ ከተማን ሙሉ በሙሉ ማዳረስ የሚያስችል ከ605 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ከፌቤላ የዘይት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጋር በመተባበር በተያዘው ሳምንት ለነዋሪዎች እንደሚከፋፍል የከተማዋ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የዘይት አቅርቦቱ በ 'ሸማች ማህበር' በኩል ይቀርባል የተባለ ሲሆን በገበያው ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመከላከል የቁጥጥር ስራም እየተሰራ ነው ተብሏል። 

በከተማዋ በሸማች ማህበራት በኩል የሚቀርበው የዘይት ዋጋ ፡-

1. ባለ 3 ሊትር 👉 290 ብር ከ06 ሳንቲም

2. ባለ 5 ሊትር 👉 474 ብር ከ40 ሳንቲም

3. ባለ10 ሊትር 👉 936 ብር ከ69 ሳንቲም

4. ባለ 20 ሊትር 👉 1 ሺህ 834 ብር ከ66 ሳንቲም

5. ባለ 25 ሊትር 👉 2 ሺህ 277 ብር ከ90 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

 @tikvahethiopia