TIKVAH-ETHIOPIA
#Ukraine በዩክሬን ያሉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ድንጋጤ እና ፍርሀት ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የቻለውን ሁሉ ጥረት አድርጎ እንደ ፖላንድ ወዳሉ ጎረቤት ሀገራት እንዲሄዱ እንዲያመቻችላቸው ተማፅነዋል። ሌሎች ሀገራት ከዩክሬን ዜጎቻቸውን በማስውጣት ላይ ይገኛሉ። ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ዩክሬን ሀገር የሄዱ 49 የሀገራችን ዜጎች የሆኑ ተማሪዎች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ ግን ከ400…
#Update
" ከመንቀሳቀሳችሁ በፊት ከኤምባሲያችን ጋር ተመካከሩ " - በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ
በዩክሬይን በትምህርት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከመንቀሳቀሳቸው በፊት በርሊን፣ ጀርመን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲያሳውቁ መልዕክት ተላልፏል።
በርሊን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት " ዩክሬይን ውስጥ በትምህርት ላይ የምትገኙ የኢትዮጵያ ዜጎች በአሁኑ ወቅት በገጠማችሁ ችግር ምክንያት ከመንቀሣቀሣችሁ በፊት ለዜጎቻችንን ደህንነት በማንኛውም ጊዜ በሞባይል ስልክ ቁጥር +491767269094 እና በemail [email protected] ከኢምባሲያችን ጋር እንድትመካከሩ በአደራ ጭምር እናሣስባለን " ብሏል።
ትላንት በዩክሬን ያሉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ድንጋጤ እና ፍርሀት ውስጥ እንደሚገኙ መግለፃቸውና የኢትዮጵያ መንግስት የቻለውን ሁሉ ጥረት አድርጎ እንደ ፖላንድ ወዳሉ ጎረቤት ሀገራት እንዲሄዱ እንዲያመቻችላቸው መማፀናቸው አይዘነጋም።
ለከፍተኛ ትምህርት ዩክሬን የሚገኙ በርካታ የሀገራችን ዜጎች የሆኑ ተማሪዎች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ ከ400 እስከ 500 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ እንደሚገኙ ይገመታል።
@tikvahethiopia

የኪዬቭ እጣፋንታ ምን ይሆን ? " ኪዬቭ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በሩሲያ ኃይሎች እጅ ልትወድቅ ትችላለች " - የደህንነት ባለስልጣን አንድ ስማቸው ያልተገለፀ የምዕራቡ ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣን የዩክሬን አየር መከላከያ ስለተወገደ ኪየቭ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በሩሲያ ኃይሎች ልትወድቅ እንደምትችል መናገራቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል። ባለስልጣኑ የሩሲያ ወታደሮች በዲኒፐር ወንዝ በሁለቱም በኩል ወደ ዩክሬን…
" ሩስያ ፕሬዝዳንቱን ለመግደል አቅዳለች " - የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ
የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ ሚካሂሎ ፖዶሊያክ ሩስያ ኬያቭን ለመያዝ እና ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን ለመግደል አቅዳለች ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን አሁንም ድረስ በኪዬቭ እንደሚገኙ የገለፁት አማካሪው በዩክሬን ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን በሰጡት መግለጫ " ባለን መረጃ ጠላት እኔን ቁጥር አንድ ኢላማ አድርጎኛል፤ ቤተሰቦቼን ደግሞ ቁጥር ሁለት ኢላማ አድርጓል። የሀገሪቱን መሪ በማጥፋት ዩክሬንን በፖለቲካ ማጥፋት ነው የሚፈልጉት ። የጠላት አጥፊ ቡድኖች ወደ ኪዬቭ መግባታቸውንም መረጃ አለን ነዋሪዎች ተጠንቀቁ የታወጀውንም ሰዓት እላፊ አክብሩ " ብለዋል።
ፕሬዜዳንቱ " እኔ በዋና ከተማዋ ነው የምቆየው፣ ቤተሰቦቼም ዩክሬን ናቸው። ልጆቼም ዩክሬን ናቸው። ቤተሰቦቼ ከዳተኞች አይደሉም የዩክሬን ዜጋ ናቸው " ሲሉም ተደምጠዋል።
ዩክሬን NATO እንዲደርስላትም እየተማፀነች ነው።
እስካሁን ድረስ ምዕራባውያኑ ኃያላን ሀገራት ማዕቀብ ከመጣል ባለፈ ወደ ዩክሬን ገብተው ከሩሲያ ጋር ውጊያ የመግጠም ሀሳብ ያላቸው አይመስልም፤ አሜሪካም ትላንት በፕሬዜዳንቷ ጆ ባይደን አማካኝነት ወታደሮቿን ከሩሲያ ጋር ለማዋጋት ወደ ዩክሬን እንደማታስገባ ማሳወቋ ይታወሳል።
አሁንም ጦርነት ቆሞ ለሰላም እድል እንዲሰጥ ጥሪዎች የቀጠሉ ሲሆን ሩስያ ውስጥም ጦርነቱን በመቃወም ሰልፎች እየተደረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ከዚህ ጋር በተያያዘም የታሰሩ ሰዎች በርካታ ናቸው።

#Update " ከመንቀሳቀሳችሁ በፊት ከኤምባሲያችን ጋር ተመካከሩ " - በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዩክሬይን በትምህርት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከመንቀሳቀሳቸው በፊት በርሊን፣ ጀርመን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲያሳውቁ መልዕክት ተላልፏል። በርሊን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት " ዩክሬይን ውስጥ በትምህርት ላይ የምትገኙ የኢትዮጵያ…
#update
" በተቻለ ፍጥነት ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጣችሁ ግቡ " - በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ
በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት የኢትዮጵያ ዜጎች ችግር እንዳይገጥማቸው በጀርመን በርሊን የሚገኘው ኤምባሲ ክትትል እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።
ዜጎቻችን ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው መግባት እንዲችሉም ከፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር መነጋገር እና መፃፃፍ መቻሉን የገለፀው ኤምባሲው ኢትዮጵያውያን ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው እንዲገቡ ተፈቅዷል ብሏል።
በዩክሬን የሚኖሩ እና ወደ ድንበር ጉዞ በማድረግ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በተቻለ ፍጥነት ወደ ፖላንድ ግዛት በመግባት ወደ ኢትዮጵያ በተቻለ ፍጥነት እንዲጓዙ አሳስቧል።

" ሩስያ ፕሬዝዳንቱን ለመግደል አቅዳለች " - የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ ሚካሂሎ ፖዶሊያክ ሩስያ ኬያቭን ለመያዝ እና ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን ለመግደል አቅዳለች ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን አሁንም ድረስ በኪዬቭ እንደሚገኙ የገለፁት አማካሪው በዩክሬን ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ገልፀዋል። በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን በሰጡት መግለጫ " ባለን መረጃ…
" ሁሉም ፈርቷል "
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ፦
" ዛሬ 27 የአውሮፓ መሪዎችን ዩክሬን በNATO ውስጥ እንድትሆን ጠየኳቸው ፤ በቀጥታ ነው የጠየኳቸው፤ ሁሉም ሰው ፈርቷል ፤ መልስ አይሰጥም። እኛ ግን አንፈራም ፤ እኛ ምንም ነገር አንፈራም።
ሀገራችንን ለመከላከል አንፈራም ፤ ሩሲያን አንፈራም ፤ ከሩሲያ ጋር ለመነጋገር አንፈራም፤ ስለአገራችን የደህንነት ዋስትናዎች ለመናገር ፤ ስለማንኛውም ነገር ለመናገር አንፈራም ፤ ስለ ገለልተኝነት ለመናገር አንፈራም።
በአሁኑ ጊዜ የNATO አባል አይደለንም ግን ምን ዋስትና እናገኛለን ? ከሁሉም በላይ ደግሞ የትኞቹ አገሮች ዋስትና ይሰጡናል ? "

" ሁሉም ፈርቷል " የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ፦ " ዛሬ 27 የአውሮፓ መሪዎችን ዩክሬን በNATO ውስጥ እንድትሆን ጠየኳቸው ፤ በቀጥታ ነው የጠየኳቸው፤ ሁሉም ሰው ፈርቷል ፤ መልስ አይሰጥም። እኛ ግን አንፈራም ፤ እኛ ምንም ነገር አንፈራም። ሀገራችንን ለመከላከል አንፈራም ፤ ሩሲያን አንፈራም ፤ ከሩሲያ ጋር ለመነጋገር አንፈራም፤ ስለአገራችን የደህንነት ዋስትናዎች ለመናገር ፤ ስለማንኛውም…
#Update
" ብቻችንን አጋፍጠውናል " - ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ " ብቻችንን አጋፍጠውናል " ሲሉ ምዕራባውያንን ወቅሰዋል።
ዜሌኒስኪ " ሃገራችንን ለመጠበቅ በብቸኝነት እየተዋጋን ያለነው እኛው ነን " ሲሉ ተናግረዋል፡፡
" ማን አግዞን ከጎናችን ሆኖ ተዋጋ? " ሲሉ የሚጠይቁት ፕሬዝዳንቱ " ማንም "ሲሉ መልሰዋል።
" ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደተወን ነው የተሰማኝ፤ እንደሚደግፉን ነበር ቃል ሲገቡልን የነበሩት፤ ሆኖም ሞትን እንድንጋፈጥ ብቻችንን ትተውናል " ሲሉም ነው ፕሬዝዳንቱ የተናገሩት፡፡
ዜሌንስኪ ሃገራቸው ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን የተናገሩ ሲሆን ይህን ማለቷ ግን ከፍራቻ እንዳልሆነ መጠቆማቸውን አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

#ማስታወሻ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የተሟለ መረጃ እንዲያጠናክሩ የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃል።
ከተሰጠው ቀነ ገደብ በኋላ መረጃዎችን ያልሰጡ ደንበኞች አካውንታቸውን #ማንቀሳቀስ አይችሉም።
ባንኮች ባለፉት 6 ወራት መመርያው በሚጠይቀው መሥፈርት መሠረት የደንበኞቻቸውን መረጃ እየሰበሰቡ ነው፡፡
ይህንኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ተከትለው ደንበኞቻቸው በግንባር ወደ ባንክ ቀርበው በመመርያው መሠረት አስፈላጊ መረጃ እንዲሰጡ እያደረጉ ቢሆንም ጥቂት የማይባሉ ደንበኞች በመመርያው መሠረት ወደ ባንክ በመሄድ መረጃ እየሰጡ አይደለም ተብሏል።
በዚሁ የቀነገደቡ ማብቂያ ሳምብት ባንኮች በስልክ ጭምር እያስተናገዱ ነው።
ባንኮች መረጃ ሰብስበው እንዲያጠናቅቁ የተሰጣቸው ጊዜ የሚጠናቀቀው የካቲት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ሲሆን ከየካቲት 21 ቀን 2014 በኋላ መረጃዎቻቸውን ለባንክ ያልሰጡ የባንክ ደንበኞች አካውንታቸውን ማንቀሳቀስ አይችሉም።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ [NBE] የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር አቶ ፍሬዘር አያሌው መረጃቸውን ባለመስጠት አካውንታቸው እንዳይንቀሳቀስ የሚደረጉት ደንበኞች አካውንታቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉት በአዲሱ አሠራር መሠረት በመመርያው የተቀመጠውን መረጃ ሲሰጡ ብቻ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የባንክ ኃላፊዎች በተለይ #ቼክ የሚያንቀሳቅሱ የባንክ ደንበኞች፣ በብሔራዊ ባንክ ድንጋጌ መሰረት መረጃውን ቀርበው ካልሞሉና በዚሁ ምክንያት አካውንታቸው የማይንቀሳቀስ ከሆነ ይከፈል ያሉት ቼክ የማይከፈል መሆን ጋፀው ለማይቀረው ነገር በቶሎ የሚፈለግባቸውን ይሙሉ ማለታቸውን ሪፖርተር አስነብቧል።
ያንብቡ : telegra.ph/Reporter-02-25

#Update " ብቻችንን አጋፍጠውናል " - ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ " ብቻችንን አጋፍጠውናል " ሲሉ ምዕራባውያንን ወቅሰዋል። ዜሌኒስኪ " ሃገራችንን ለመጠበቅ በብቸኝነት እየተዋጋን ያለነው እኛው ነን " ሲሉ ተናግረዋል፡፡ " ማን አግዞን ከጎናችን ሆኖ ተዋጋ? " ሲሉ የሚጠይቁት ፕሬዝዳንቱ " ማንም "ሲሉ መልሰዋል። " ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደተወን ነው የተሰማኝ፤…
ሩስያ ከዩክሬን ጋር ልትነጋገር ነው።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ከዩክሬን ልዑክ ጋር ለመነጋገር ከፍተኛ የልዑካን ቡድናቸውን ወደ ቤላሩስ ሚኒስክ ሊልኩ መሆኑ ተሰምቷል።
ይህ የተሰማው የዩክሬን ፕሬዜዳንት ዜሌንስኪ ሃገራቸው ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ከተናገሩ ከሰዓታት በኃላ ነው።
ሞስኮ ዩክሬን የኔቶ አባል ለመሆን ያላትን ጥያቄ እንድታቆም እና ገለልተኛ አቋም እንድትይዝ ትፈልጋለች።
ሚኒስክ የቀድሞው የሰላም ስምምነት የተደረገባት ከተማ መሆኗ ይታወቃል።

Photo
#NEAEA
" ይሄ አዲስ ውሳኔ አይደለም። ለዓመታት ሲሰራበት የቆየ ነው። ማንኛውም ተማሪ ለማለፍ ከግማሽ በላይ ውጤት ማምጣት አለበት " - አቶ ተፈራ ፈይሳ
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ከሆነ ሰዓት ጀምሮ ከተማሪ ወላጆች እንዲሁም ከተማሪዎች በርካታ ጥያቄዎች ደርሰውን ተመልክተናል።
ከጥያቄዎቹ መካከል ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ገብቶ ለመማር የተላለፈው 50% ማስመዝገብ ውሳኔ ከነበርንበት ሁኔታ አንፃር፣ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የጦርነቱ ጫና ተዳምሮ ትክልል አይደልም ይህ ሊታይ ይገባል የሚል ነበር።
የተላኩትን ቅሬታዎች በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአገር አቅፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አቅርቦ ምላሽ አግኝቷል።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ " ማንኛውም ተማሪ ብሔራዊ ፈተናውን ለማለፍ ቢያንስ 50 በመቶ ውጤት ሊያመጣ እንደሚገባ " ገልጸውልናል።
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር የተፈተኗቸው የትምህርት አይነቶች አጠቃላይ አማካይ ውጤት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
" ይሄ አዲስ ውሳኔ አይደለም። " ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ " ለዓመታት ሲሰራበት የቆየ ነው። ማንኛውም ተማሪ ለማለፍ ከግማሽ በላይ ውጤት ማምጣት አለበት " ብለዋል።
ከተማሪዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን እየተቀበሉ መሆኑን የገለጹት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ፤ አጠቃላይ አማካይ ውጤታቸው ከ300 በታች ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር ገና አለመታወቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ የመግቢያ ነጥብ ወደፊት በትምህርት ሚኒስቴር የሚገለጽ መሆኑም ታውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahuniversity

ጊታ ፓሲ ተሰናበቱ። ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር ጊታ ፓሲ ዛሬ አሰናበቱ። አምባሳደሯ የሹመት ደብዳቤያቸውን ከአንድ ዓመት በፊት የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ማቅረባቸው እንደሚታወስ ከፕሬዚደንት ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል። አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጡረታ እንደሚወጡ ማሳወቃቸውን ተከትሎ አሜሪካ በአዲስ አበባ ለሚገኘው ኤምባሲዋ ትሬሲ…
#AddisAbaba
ትሬሲ አን ጃኮብስን አዲስ አበባ ገብተዋል።
አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጡረታ እንደሚወጡ ማሳወቃቸውን ተከትሎ አሜሪካ በአዲስ አበባ ለሚገኘው ኤምባሲዋ በጊዜያዊነት በኃላፊነት ቦታ ላይ ያስቀመጠቻቸው አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብስን ስራቸውን ለመጀመር አዲስ አበባ መግባታቸውን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አሳውቋል።
@tikvahethiopia
ትሬሲ አን ጃኮብስን አዲስ አበባ ገብተዋል።
አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጡረታ እንደሚወጡ ማሳወቃቸውን ተከትሎ አሜሪካ በአዲስ አበባ ለሚገኘው ኤምባሲዋ በጊዜያዊነት በኃላፊነት ቦታ ላይ ያስቀመጠቻቸው አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብስን ስራቸውን ለመጀመር አዲስ አበባ መግባታቸውን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አሳውቋል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሩስያ ከዩክሬን ጋር ልትነጋገር ነው። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ከዩክሬን ልዑክ ጋር ለመነጋገር ከፍተኛ የልዑካን ቡድናቸውን ወደ ቤላሩስ ሚኒስክ ሊልኩ መሆኑ ተሰምቷል። ይህ የተሰማው የዩክሬን ፕሬዜዳንት ዜሌንስኪ ሃገራቸው ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ከተናገሩ ከሰዓታት በኃላ ነው። ሞስኮ ዩክሬን የኔቶ አባል ለመሆን ያላትን ጥያቄ እንድታቆም እና ገለልተኛ አቋም እንድትይዝ ትፈልጋለች። ሚኒስክ…
#ታገደች
ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ሩስያ ከአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት መታገዷ ተገልጿል።
በሌላ በኩል የሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬን ጦር በኬዬቭ ያላው ስርዓት እንዲገለብጥ ጥሪ አቅርበዋል።
@tikvahethiopia
ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ሩስያ ከአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት መታገዷ ተገልጿል።
በሌላ በኩል የሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬን ጦር በኬዬቭ ያላው ስርዓት እንዲገለብጥ ጥሪ አቅርበዋል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ሩስያ ፥ ስዊድንን እና ፊንላንድን አስጠነቀቀች።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስዊድን እና ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል ከሞከሩ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ] እንደሚኖሩ አስጠንቅቋል።
አሁን በዩክሬን እና ሩስያ መካከል ያለው ጦርነት ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ሩስያ ፊንላንድ እና ስዊድንን ማስፈራራቷ ሌላ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ፈጥሯል።
የኃያላን ሀገራቱ ግብግብ በተለይ እንደኛ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ላይ ይዞት የሚመጣው መዘዝ እንዲሁ በቀላሉ የሚታይ አይደለም።