TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#US : በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራውያን በሚኖሩባት የቨርጂኒያ ምርጫ የሪፐብሊካን ዕጩ ግሌን ዮንከን አሸነፉ።

ግሌን ዮንከን ምርጫውን ማሸነፋቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

ቀድም ብሎ በዚህ ግዛት ላይ ዲሞክራቶች ከተሸነፉ የጆ ባይደን ቅቡልነት ማጣት አንድ ማሳያ እንደሆነ ተንታኞች ሲናገሩ ነበር።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ጆ ባይደን ቨርጂኒያን በ10 ነጥብ የበላይነት አሸንፈው ነበር።

ከቨርጂኒያ ሌላ በኒው ጀርሲም በዲሞክቶችና በሪፐብሊካን መካከል ጥብቅ ፉክክር እየተደረገ ነው።

ጆ ባይደን ወደ ዋይት ሐውስ ከገቡ ወዲህ ፦
- የዋጋ ግሽበት መባባስ፣
- የተቀዛቀዘው የምጣኔ ሀብት ቶሎ አለማንሰራራት - ዝርክርክ የተባለው የአሜሪካ ከአፍጋኒስታን የወጣችበት መንገድ በሕዝብ ዘንድ ለዲሞክራቶች የነበረው ተስፋና እምነትን ሸርሽሯል እየተባለ መሆኑን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

መረጃው ከኤኤፍፒ እና ቢቢሲ የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
#US #Eritrea

አሜሪካ በኤርትራ ያሉ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ አሳሰበች።

አሜሪካ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና መንግስታቸው የህሊና እስረኞችን እንዲፈቱ አሳስባለች።

አስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፥ " ፕሬዜዳንት ኢሳያስ እና መንግስታቸው በግእዝ የገና በዓል መንፈስ እና በክርስትናውም ሆነ በእስልምናው እምነት ውስጥ ይቅርታ ያለውን ትልቅ ሚና በመገንዘብ የኤርትራ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ አሜሪካ ታሳስባለች ። " ብሏል።

በአስመራ የሚገኘው አሜሪካ ኤምባሲ ስላሰራጨው መልዕክት በኤርትራ መንግስት ሆነ ባለስጣናት በኩል የተሰጠ ምላሽ/አስተያየት የለም።

@tikvahethiopia
#US_Embassy_AA

የሙሉ ጊዜ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የሆናችሁ እና አሜሪካ ውስጥ የልውውጥ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ይህ እድል ለእናተ ነው።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የ2022-23 የፉልብራይት የማስተማር ልቀት እና ስኬት (TEA) ፕሮግራም ማመልከቻ መቀበል እንደተጀመረ ዛሬ ገልጿል።

ስኬታማ የሆኑ አመልካቾች #ለ6_ሳምንታት የአካዳሚክ ሴሚናሮች እና የክፍል ውስጥ ምልከታ ለማድረግ ወደ አሜሪካ ይጓዛሉ።

በአሜሪካ ቆይታቸው ከአስተናጋጅ ዩኒቨርሲቲ እና ከአካባቢው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከሚገኙ መምህራን እና ተማሪዎች ጋር ወደ የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ።

ፉልብራይት (TEA) በስቴት ዲፓርትመንት የትምህርት እና የባህል ጉዳዮች ቢሮ (ECA) የሚደገፍ ፕሮግራም ሲሆን በአሜሪካ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በ #IREX የሚተዳደር ነው።

ለበለጠ መረጃ ፦ https://ow.ly/t4FO50HQPPe
ለማመልከት ፦ https://ow.ly/aIaK50HQPPc

የመጨረሻው ማመልከቻ ቀን እ.ኤ.አ የካቲት 27/ 2022 ወይም የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ/ም ነው።

@tikvahethiopia