TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በአሁኑ ወቅት ጅግጅጋ ከተማን ጨምሮ መላው የሶማሌ ክልል እንደ ወትሮው ሁሉ ሰላም እና መረጋጋት የሰፈነበት ነው " - የሶማሌ ክልል መንግስት

የሶማሌ ክልል የክልሉን ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ ከተማን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

አመሻሹን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጅግጅጋ ከተማ ውስጥ ረብሻ፣ አለመረረጋጋትና መፈንቅለ መንግሥት እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ሀሰት እና ከእውነት የራቀ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የሶማሌ ክልል መንግስት በአሁኑ ወቅት ጅግጅጋ ከተማን ጨምሮ መላው የሶማሌ ክልል እንደ ወትሮው ሁሉ ሰላም እና መረጋጋት የሰፈነበት መሆኑን ገልጿል።

ክልሉ " በአንዳንድ ቦታዎች ፀረ ለውጥ የሆኑና በሙስና እንዲሁም በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ለውጥ አደናቃፊ አካላት በድብቅ ግንኙነት ሲያደርጉ ተደርሶባቸው ከመንግስት መዋቅር የወጡ ሀይሎች ሰላም ለማደፍረስ ያደረጉት ሙከራ ከሰላም ወዳዱ ህዝባችን ጋር በመተባበር መክሸፉን እንገልፃለን " ብሏል።

የሶማሌ ክልል መንግሥት ከሰላም ወዳዱ ህዝብ ጋር በመሆን የህዝቡን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደማይታገስና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የፊታችን ማክሰኞ በመንበረ ፓትርያርኩ የቋሚ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይገኛሉ። ያሉትን ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትም ቀጠሮ ተይዟል። ቅዱስ ሲኖዶስ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ እና በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ለመነጋገር ለከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል። በስብሰባው ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ…
#Update

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ካቢኔያቸው ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ እና ካቢኔያቸው ዛሬ የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተገኝተዋል።

ቋሚ ሲኖዶስ የካቲት 4 ቀን 2014 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ፣ በወይብላ ማርያም ጉዳይ፣ በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት እና በሌሎች የቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች ዙሪያ ተወያይቶ አሉ የሚባሉ ችግሮችን በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ለመፍታት ይዞት የነበረው ቀጠሮ በወቅቱ የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ስብሰባ ስለነበረውና ከንቲባዋም በዚያ መገኘታቸው የግድ ስለሆነ ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር የነበረው ቀጠሮ ለዛሬ እንዲተላለፍ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና ከአስተዳደሩ የተወከሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአካል ተገኝተው ለቋሚ ሲኖዶስ በገለጹት መሰረት የውይይቱ ጊዜ ለዛሬ እንዲተላለፍ መደረጉ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ከንቲባዋና የካቢኔ አባላቶቻቸው ዛሬ በሰዓቱ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ሲሆን ከቋሚ ሲኖዶስ አባላት በተጨማሪ ሌሎች ብፁአን አባቶች ፣ የህግ ባለሙያዎች ፣ ከመምሪያ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ።

በውይይቱ አሉ የሚባሉና ቤተክርስቲያን የምታቀርባቸው ጥያቄዎች ሁሉ ፍጹም ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ መፍትሔ የሚያገኝበትን ሁኔታ ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚገመት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ገልፃለች።

ከዚህ ቀደም በቋሚ ሲኖዶስ አባላት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መካከል ሊደረግ የታሰበው ውይይት በተለያዩ ምክንያቶች እንቅፋት እየገጠመው መቆየቱ ይታወሳል።

መረጃው ፦ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#State_of_Emergency ከሳምንታት በፊት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ቀሪ እንዲሆን ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት ምርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ም/ ቤቱ ውሳኔውን መርምሮ የሚያፀድቀው ነገ በሚያካሂደው አስቸኳይ ስብሰባ ነው። በውሳኔ ሃሳቡ ላይ ድምጽ ከመስጠቱ በፊት የም/ቤቱ የሕግ፣ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ…
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነሳ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በሃገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስቷል።

ምክር ቤቱ በ63 ተቃውሞ በ21 ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የወሰነው።

ይህን ውሳኔ ተከትሎ÷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ስራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኗል፡፡

በተመሳሳይ የፍትህ አካላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የጀመሯቸውን ጉዳዮች በመደበኛው የፍትህ አሰጣጥ ስርአት እንዲያጠናቅቁም መወሰኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Oromia , #QelemWollega📍

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር (ERCS) የቄለም ወለጋ ቅርንጫፍ ንብረት የሆኑና ማኅበሩ ለሰብዓዊ አገልግሎት የሚጠቀምባቸው ሁለት የታርጋ ቁጥር ET05-02121 እና ታርጋ ቁጥር ET05-02108 አምቡላንሶቹ ሰሞኑን በቄለም ወለጋ ለሰብዓዊ አገልግሎት ሲንቀሳቀሱ ማህበሩ በውል በማያውቀው ሁኔታ እና በግዳጅ ተወስደዋል።

ድርጊቱ ኢትዮጵያ የፈረመችውን አለምአቀፍ የጄኔቫ ኮንቬንሽን የሚፃረርና፣ ከማህበሩ ዓላማ ውጪ መሆኑን ማኅበሩ ገልጿል።

ከላይ የታርጋ ቁጥራቸው የተገለፁት 2 አምቡላንሶች በማኅበሩ ቁጥጥር ስር የሌሉ መሆኑን ተረድተው ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አምቡላንሶቹን ወደ ማህበሩ ተመልሠው ለህብረተሠቡ የተለመደውን ሰብዓዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንዲሰጡት ማህበሩ በተገልጋይ ወገኖች ስም ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ካቢኔያቸው ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ከንቲባ እና ካቢኔያቸው ዛሬ የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተገኝተዋል። ቋሚ ሲኖዶስ የካቲት 4 ቀን 2014 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ፣ በወይብላ ማርያም ጉዳይ፣ በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት እና በሌሎች የቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች ዙሪያ…
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዛሬው እለት የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በመስቀል አደባባይና በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ቦታዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ የጋራ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

ውይይቱ በፍጹም ቅን ልቡና፣ መደማመጥና መግባባት በተሞላበት ስሜት መካሄዱ ተገልጿል።

በውይይቱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመስቀል አደባባይና የጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀትን በተመለከተ የተነሱትን ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም ቀጣይ ውይይቶችን መሠረት በማድረግ የማያዳግም ምላሽ ለመስጠት የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ወደፊት ቤተ ክርስቲያንና የከተማ አስተዳደሩ በልማት፣ በሰላምና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበው እንደሚሰሩ ይፋ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#DStv

🗓ከጥር 2 እስከ መጋቢት 21 ድረስ ብቻ የሚቆይ የደስ ደስ ከዲኤስቲቪ!

⚽️የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን የዲኤስቲቪ ደንበኞች በሜዳ ፓኬጅ ላይ በነፃ ማየት እንደሚችሉ ያውቃሉ ?

👉 የሜዳ ፓኬጅ 550ብር ሲከፍሉ ባለ 1,300 ብር የሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ስጦታ ያገኛሉ ! በዕድሉ ፈጥነው ይጠቀሙ ።

በእርግጥም ከከፈሉት የዲኤስቲቪ ፓኬጅ በላይ ያግኙ!

ክፍያ ለመፈፀም ፣ ፓኬጅዎን ለመቀየር እንዲሁም ሌሎች የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ : https://bit.ly/2WDuBLk

የዲኤስቲቪን ቤተሰብ ይቀላቀሉ: https://bit.ly/3D2O1t4
#መግለጫ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ዛሬ " ለዜጎች መብት መከበር የሚሟገተው ጋዜጠኛ መብት ይከበር " በሚል መግለጫ አውጥቷል።

ማህበሩት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት መሻሻል እያሳየ እንደነበርና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ሲመሰክሩ እንደነበር አስታውሷል።

ይሁንና ይህ መሻሻል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተሸረሸረ መሄዱን በብዙ ማሳያዎች መግለጽ እንደሚቻል እና ይህንንም የተለያዩ ማሳያዎች በመጥቀስ አብራርቷል።

(ከማህበሩ የተላከውን ሙሉ መግለጫ በዝርዝር ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተፈርዶበታል

በጣልያን ሀገር ገጠራማ ስፍራ በሆነችው ፍራሲሎንጎ ከተማ ፍየሎችን እያረባች በአይብና በፍየል ምርቶቿና በጠንካራ ሰራተኝነቷ የታወቀችውን ኢትጵያዊቷን አጊቱ ጉደታን ቤቷ ውስጥ እያለች በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው የ33 ዓመቱ ጋናዊ ስደተኛ ሱሌይማን አዳምስ 20 ዓመት እስር ተፈርዶበታል።

የትሬንቶ ፍርድ ቤት ሰኞ ዕለት በዋለው ችሎት ጋናዊው ሱሌይማንን በነፍስ ማጥፋት ወንጀል 15 ዓመት ከስምንት ወር እንዲሁም አራት ዓመት ከአራት ወር ወሲባዊ ጥቃት በመፈጸም ፍርድ አስተላልፎበታል።

በተወሰነው ቅጣት ቤተሰቧ ደስተኛ አይደለም።

ኢትዮጵያ ውስጥ የምትገኘው የአጊቱ እህት ሀወኒ ኤዳዎ ጉደታ ለቢቢሲ በሰጠችው ቃል ቤተሰቧ ፍርድ ቤቱ በገዳዩ ላይ ያሳለፈው የእስር ቅጣት በቂ ነው ብሎ እያምንም ብላለች።

ሀወኒ ኤዴዎ " ምንም እንኳን ቅጣቱ እሷን የሚመልሳት ባይሆንም፣ ከተፈጸመው ወንጀል አኳያ ውሳኔው በቂ አይደለም። እኛ የእድሜ ልክ አስራት ይፈረዳል ብለን ጠብቀን ነበር" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች።

@tikvahethiopia