TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray , #Mekelle 📍
አሚና መሐመድ ትግራይ ክልልን ጎብኝተዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሐመድ የተመራ ልዑክ ዛሬ በትግራይ ክልል መቐለ ጉብኝት አድርጓል።
የልዑካን ቡድኑ በመቐለ ከተማ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታልን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል ፤ የጤና ባለሞያዎችን አነጋግሯል።
ከዚህ በተጨማሪም በመቐለ የሚገኙ በጦርነት የተፈናቀሉ ወገኖች የሚገኙባቸውን ካምፖች ተመልክቷል ፤ የጦርነት ተጎጂዎችንም አነጋግሯል።
በአሚና መሐመድ የተመራው ልዑክ ዛሬ ጥዋት አማራ ክልል የኮምቦልቻ ከተማ ተገኝቶ ጉብኝት ማድረጉን መግለፃችን ይታወሳል።
ስለ ዛሬው የአማራ እና ትግራይ ክልሎች ጉብኝት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሐመድ / በተመድ የሚሰጥ ማብራሪያ ካለ ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
#AFCON
የአፍሪካ ዋንጫ በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል።
የውድድሩ ፍፃሜ ጨዋታ ተፋላሚዎች #ሴኔጋል እና #ግብፅ ሲሆኑ ጨዋታው ተጀምሯል።
ይህ ጨዋታ በመላው አፍሪካ እንዲሁም በዓለም አቅፍ ደረጃ እጅግ በጉጉት የሚጠበቅ ነው።
የዋንጫው 🏆 ባለቤት ማን ይሆናል ?
@tikvahethiopia
የአፍሪካ ዋንጫ በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል።
የውድድሩ ፍፃሜ ጨዋታ ተፋላሚዎች #ሴኔጋል እና #ግብፅ ሲሆኑ ጨዋታው ተጀምሯል።
ይህ ጨዋታ በመላው አፍሪካ እንዲሁም በዓለም አቅፍ ደረጃ እጅግ በጉጉት የሚጠበቅ ነው።
የዋንጫው 🏆 ባለቤት ማን ይሆናል ?
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Senegal🏆 ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ሆነች። @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AFCON
ከፍተኛው ተጋድሎ በሴኔጋል አሸናፊነት ተደምድሟል።
በጨዋታው መጀመሪያ ላይ ሰኢዶ ማኔ የፍፁም ቅጣት ምት መሳቱ የሴኔጋሉን ፕሬዜዳንት ማኪ ሳል በድንጋጤ አስጩሆ ከመቀመጫቸው ያስነሳ ፤ የጨዋታው ፍልሚያ ከቴሌቪዥን ስክሪን ላይ ለአፍታ አይንን የማያስነቅል፤ እጅግ አጓጊ ተጋድሎ የተደረገበት ነበር።
የግብፁ ግብ ጠባቂ ጋባስኪ በፍልሚያው ያሳየው ተጋድሎ በርካቶችን ያስጨበጨበ ነበር።
ሁለት አሸናፊ አይኖርምና ፍልሚያው በመለያ ምት ሲለይ ግብፅ 4 - 2 ሽንፈትን ስትቀምስ ሴኔጋል በታሪኳ የመጀመሪያ ዋንጫውን አግኝታለች።
በዘንድሮው ውድድር እስከመጨረሻው የደረሱት ግብፃውያን ተጫዋቾች ፣ አሰልጣኞች፣ ደጋፊዎች አነቡ ፤ ዋንጫውን በመነጠቃቸው አዘኑ ፤ በውድድሩ ግን 2ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

#AFCON ከፍተኛው ተጋድሎ በሴኔጋል አሸናፊነት ተደምድሟል። በጨዋታው መጀመሪያ ላይ ሰኢዶ ማኔ የፍፁም ቅጣት ምት መሳቱ የሴኔጋሉን ፕሬዜዳንት ማኪ ሳል በድንጋጤ አስጩሆ ከመቀመጫቸው ያስነሳ ፤ የጨዋታው ፍልሚያ ከቴሌቪዥን ስክሪን ላይ ለአፍታ አይንን የማያስነቅል፤ እጅግ አጓጊ ተጋድሎ የተደረገበት ነበር። የግብፁ ግብ ጠባቂ ጋባስኪ በፍልሚያው ያሳየው ተጋድሎ በርካቶችን ያስጨበጨበ ነበር። ሁለት አሸናፊ…
ፎቶ : ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫን ተረክባለች።
ሴኔጋል የአፍሪካን ዋንጫ ካነሱ ሀገራት መካከል ስሟን አስመዝግባለች። ዋንጫውን ይዛ ወደ ሀገሯ ስትገባ ደግሞ እጅግ ደማቅ የሆነ አቀባበል እንደሚደረግላት ይጠበቃል።
🇸🇳 C H A M P I O N S O F A F R I C A 🏆
#AFCON2021 በዚህ ተደምድሟል።

#EOTC
ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የብፁዕ ወቅዱስ ፖትርያርክ ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋ እና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የስተርሊንግ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የዩታ ግዛት አስተዳደር የንግድ ቢሮ ኃላፊ የሆኑትን ሚስተር ኤድዋርድን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ብፁዕነታቸው መቀመጫውን በአሜሪካ ዩታ ግዛት ያደረገው የስተርሊንግ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የዩታ ግዛት አስተዳደር የንግድ ቢሮ (Edward, CEO of the US-based Sterling Foundation and CEO of the Utah State Business Bureau) ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ሚስተር ኢድዋርድ የሚመራ ልዑክ ባነጋገሩበት ወቅት ሊ/ት ቀሲስ ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ዋና ጸሐፊ ተገኝተው ነበር።
የልዑካን ቡድኑ ወደ #ኢትዮጵያ የመጣበትን ጉዳይ በማንሣት ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በተለይም የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤን በሠላም ግንባታ እንዲሁም በአብሮነት እሴት ሥራ ላይ ተቋሙ በሀገሪቱ የሚሰራውን ሥራ ለማገዝ ያላቸውን ፍላጎት መግለጻቸውን ከኢ/ኦ/ተ/ቤ ውጭ ግንኙነት መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#Update የጉባኤው ተሳታፊዎች እየተሸኙ ነው። የ35ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ መጠናቀቁን ተከትሎ የተሳታፊ ሀገራት መሪዎች እና ልዑካን ቡድኖች ወደ የሀገራቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ። @tikvahethiopia
#AU2022Summit
ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለትም እንግዶቿን እየሸኘች ነው።
የሴኔጋል ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ማኪ ሳልን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
@tikvahethiopi

#Egypt #Djibouti
ኢማኤል ኦመር ጌሌ ግብፅ ገብተዋል።
የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ከፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በተደረገላቸው ግብዣ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ትላንት ለሊት ግብፅ ገብተዋል።
ፕሬዜዳንቱ ካይሮ ኤርፖርት ሲደርሱ አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ናቸው የተቀበሏቸው።
በዛው ዕለት ሁለቱ መሪዎች ስብሰባ የሚኖራቸው ሲሆን በሁለትዮሽ ጉዳዮቻቸውና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።
ፎቶ፦ የጅቡቲ ፕሬዜዳንት (ኢሳማኤል ኦመር ጌሌ)

#AU2022Summit " ... ህብረቱ የኢትዮጵያ ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል " - አምባሳደር ባንኮሌ አዴኦዬ የአፍሪካ ህብረት ለኢትዮጵያ ግጭት ሰላማዊ መፍትሔ ለማፈላለግ ከአህጉሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተጨማሪ ባለሙያዎችን ወደ ስራ እንደሚያስገባ አስታውቋል። የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴኦዬ ፤ በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ህብረት…
#Update
ኦባሳንጆ ኮምቦልቻ ገብተዋል።
የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕከተኛ ኦሊሴንጎን አባሳንጆ ዛሬ ኮምቦልቻ ገብተዋል።
በትላንትናው ዕለት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴኦዬ ፤ የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉን በመግለፅ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በአማራ እና በአፋር ክልሎች በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት እንደሚያደርጉ ማሳወቃቸው አይዘነጋም።
ዛሬ ኮምቦልቻ የገቡት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ በከተማው ያለ የጅምላ መቃብር ስፍራ እና የወደሙ ተቋማትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

#Amhara
የአማራ ክልል መንግስት ፋኖን ሆነ ሌሎች አደረጃጀቶች በሚመለከት አቋሙን እንዳልየቀረ አስታውቋል።
መንግስት ፋኖንም ሆነ ሌሎች የፀጥታ አደረጃጀቶችን በሚመለከተ ኢመደበኛ አደራጀጀቶችን ለማፍረስ ይፈልጋል ተብሎ ከሰሞኑ የተናፈሰው ወሬ የመንግስት አቋም አይደለም ሲል የክልሉ መንግስት አስታውቋል።
መነሻቸው ምን እንደሆነ ለማይታወቅ በየጊዜው ለሚቀርቡ አሉባልታዎችና ያልተጨበጡ ወሬዎች ምላሽ መስጠት አስፈላጊ አለመሆኑን የገለጸው የክልሉ መንግሥት፣ ፋኖን በሚመለከት አቋሙ ከዚህ በፊት እንደነበረው መሆኑን ገልጿል።
የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ጦርነቱ ገና አለማለቁንና ትግሉ መቀጠሉን ገልፀው" ለክልሉንና የአገር ህልውና ለመታደግ የተሳተፉ ኃይሎች በሙሉ ዕውቅና እንሰጣለን" ብለዋል፡፡
የመንግስት አቋም በመርህ ላይ የተመሠረተ መሆኑን በመግለጭ "በህልውና ትግሉ ወቅት የተፈጸሙ ችግሮች ካሉ እርማት ይደረጋል፡፡ ከዚያ ውጪ ግን ትናንት ያሞገስነውን ኃይል ዛሬ ኃጢያተኛ የምናደርግ ሰዎች አይደለንም" ሲሉ ገልፀዋል።
መንግስት የፋኖ አደረጃጀትን ለማፍረስ አቋም ይዟል በሚል ለሚነሳው ጉዳይ አቶ ግዛቸው በክልሉ መንግስትም ሆነ በፌዴራል ደረጃ ይህን መሰል አቋም አለመንፀባረቁን ተናግረዋል፡፡
"ነገርየው ዩቲዩበሮች፣ አክቲቪስቶችና ተንታኝ ነኝ ባዮች የፈጠሩት ተራ አሉባልታ ነው" ሲሉ ገልፀዋል።
የፋኖ አደራጅና መሪ ከሆኑት አንዱ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ፥ ጉዳዩን ለማጥራት ከመንግሥት ጋር ውይይት መጀመሩን ተናግረዋል።
መቶ አለቃ፥ "ከመንግሥት ጋር ንግግር ጀምረናል፣ ስንጨርስ የደረስንበትን ለሕዝብ እናሳውቃለን፤ ጉዳዩ ከየት እንደመጣና መነሻው ምን እንደሆነ በውይይት ይጠራል" ብለዋል፡፡
ያንብቡ : telegra.ph/RP-02-07
#ሪፖርተር

#SomaliPP
በሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ምን ተፈጠረ ? ፓርቲው ለሁለት ተከፍሏል ?
የሶማሌ ክልል የኮሚኒኬሽን ምክትል ኃላፊ አቶ መሀመድ ሮብሌ ፦
" ... ከዚህ በፊት በተለያዩ ቦታ ተሰጥቷቸው በክልሉ በቢሮ ኃላፊ እና በምክትል ኃላፊነት ደረጃ የነበሩና ከዛ በኃላ በነበሩ ግድፈቶች እና ድክመቶች ስራቸውን በትክክል አለመስራት ፣ በሙስና፣ በተለያዩ ምክንያቶች ከስልጣን የተባረሩ ሰዎች ናቸው።
ተሰባስበው Issue ለመፍጠር ሲሉ ነው እንጂ በፓርቲው መሃል ምንም የተፈጠረ ችግር የለም።
እነዚህ Alredy ከሲስተም የወጡ ሰዎች ናቸው። ምናልባት አንዳንድ በትክክለኛ መንገድ ተገምግመው ያልተባረሩ ሰዎች እዛ ውስጥ ሊኖሩ ይችላሉ ፤ ሌላው ግን በትክክል ከሲስተም የወጡና ህብረተሰቡን ማገልገል ሳይችሉ ፣ የተሰጣቸውን ስራ መስራት ሳይችሉ ቀይርተው የተባረሩ ናቸው። "
የሶማሌ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የፅ/ቤት ኃላፊ እንጂነር መሀመድ ሻሌ ፦
" ... እኛም በሶሻል ሚዲያ ያየነው ነገር አለ። የነበረ ነገር ግን ከለውጡ ወዲህ የተለያዩ እርምጃዎች ሲወሰዱ ነበር ከስነምግባር እና ከሙስና ጋር በተያያዘ በዚህም ከስልጣን የተነሱ ሰዎች አሉ።
ትላንትና መግለጫ አውጥተዋል ተብለው በሶሻል ሚዲያ ያየኃቸው ሰዎች ነበሩ። አብዛኛው የካቢኔ አባል የክልሉ ማዕከላዊ ኮሚቴ ያኔ የለውጡ ጅምር አካባቢ የነበሩ ሰዎች ናቸው ነገር ግን በስራ ከኃላፊነት እንዲነሱ እና እንዲታገዱ ተደርጎ ነበር። ከአንድ አመት ተኩል ይሆናል።
አንዳንዶቹ የ #ኢዜማ እጩ ነበሩ የምርጫ አካባቢ፤ አሁን ትላንት ብቻ ነው በድንገት ያየናቸው እኛ ፓርቲ አባል ነን ብለው ፤ ከእኛ ጋር ከታገዱ እና ከስራ ከተነሱ ግማሹ ሁለት ዓመት ሆኖታል ግማሹ አንድ አመት ተኩል ፣ አንዳንዶቹ የሌላ ፓርቲ ዕጩ የነበሩ ናቸው።
ጉባኤ ላይ ውሳኔ የሚጠብቁ አሉ፤ እገዳ የተጣለባቸውም አሉ፤ አንዳንዶቹ ግን ጭራሽ አይመለከቱንም የኢዜማ እጩ የነበሩትን ዛሬ ላይ አባል ነው አይደለም ማለት ተገቢም አይመስለኝም "
አቶ ሲራጅ አደን (የሶማሌ ክልል የብልፅግና ፓርቲ አባል ነኝ ያሉ ሲሆን ፓርቲው ለሁለት መከፈሉን ይናገራሉ ) ፦
" የተፈጠረው የፓርቲው ለሁለት ተከፍሏል። የዚህ ምክንያት ያለ ግምገማ እና በብዛት በዝምድና እና በጋብቻ የተሳሰረ ስለሆነ ብዙ ጊዜ ህግ እና ደንብ አይከተልም በዛ ምክንያት ፓርቲው በሁለት በኩል ተከፍሏል።
አንድ ሰው ላይ በፓርቲ እርምጃ መውሰድ የሚቻለው በህግ እና ደንብ አሰራሩ ነው። ያለ ጉባኤ አንድ የአስፈፃሚ ኮሚቴ ወይም አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አንድ ሰው ውስኖ ከህግ ውጭ አንድን ሰው ከፓርቲ ውጭ ነው ማለት አይችልም በጉባኤ ነው የሚችለው።
የተፈጠረው የ12 አባላት የፓርቲው ማሀከለኛ እና ሁለት የአስፈፃሚ ኮሚቴ ለፌዴራል የፓርቲው ፅ/ቤት አዲስ አበባ ደብዳቤ በመፃፍ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቋል።
... ረብሻ አይደለም ህግ እና ደንቡን መከተል ነው። "
NB : የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
ሁሉም አካላት ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ከሰጡት ቃል የተወሰደ።

" እኔ የምመርጠው እኔ ያገኘሁትን ህዝቦቼ በጥቂቱም ቢሆን እንዲያገኙ ነው " - ሳዲዮ ማኔ
የሊቨርፑል ሴኔጋላዊው 🇸🇳 የፊት መስመር ተጫዋች ሳዲዮ ማኔ ከውድ ቀሳቁሶችን ከመግዛት ለሀገሪቱ ሰዎች እርዳታን ማድረግ ምርጫው እንደሆነ ይገልጻል።
ሳዲዮ ማኔ ፦
" ... ለምን አስር ፌራሪዎችን ፣ ሀያ ውድ ሰዓቶቾን አልያም የግል አውሮፕላኖችን እመኛለው።
ትምህርት ቤቶችን፣ ስታዲየሞችን እገነባለው፤ እኛ አልባሳትን እና ምግቦችን በድህነት ላይ ለሚገኙ ሰዎች መስጠት አለብን።
እኔ የምመርጠው እኔ ያገኘሁትን ህዝቦቼ በጥቂቱም ቢሆን እንዲያገኝ ነው "
የሴኔጋላዊውን ኮከብ ሳድዮ ማኔን ህይወት ውጣ ውረድ ጉዞ ለማንበብ https://t.iss.one/tikvahethsport/25770
More : @tikvahethsport