TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#PressBrifing ዛሬ ሰኔ 2/2013 "ከሠዓት 9:30" የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል። ይኸው መግለጫ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ዩትዩብ ቻናል ላይ የቀጥታ ሽፋን እንደሚያገኝ ተጠቁሟል። @tikvahethiopia
#Update

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በዛሬው መግለጫ ምን አለ ?

በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ በተመለከተ :

የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ከተናገሩት ፦

- ከ5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወይም 135 ሚሊዮን ዶላር በላይ ግምት ያለው ምግብ ሸቀጥ ተሰራጭቷል።

- በመጀመሪያ ዙር 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎች ተጠቃሚ ተደርገዋል። በሁለተኛና በሶስተኛ ዙር 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

- 170 ሺህ 798 ሜትሪክ ቶን ምግብ ቀርቧል። ለዚህም ከ5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል።

- በ1ኛና በ2ኛ ዙር የተሰራጨው የሰብዓዊ ድጋፍ ወጪ 70 በመቶ በመንግስት እንዲሁም ቀሪው 30 በመቶ በአጋሮች የተሸፈነ ነው። በ3ኛ ዙር ድጋፍ መንግስትን ጨምሮ 6 አካላት ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ።

- የዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ ወርልድ ቪዥን፣ ኬር ኢንተርናሽናል፣ የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት እና ፉድ ፎር ሀንግሪ በክልሉ የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎች ላይ እየሰሩ ነው።

- መንግስት እየተደረገ ያለውን ድጋፍ እየተቆጣጠረ እንደሚገኝ ገልጸው፤ የእርዳታ አሰጣጥ ሂደቱ እንዲሳካ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ነው።

ያንብቡ : https://telegra.ph/ENA-06-09 #ኢዜአ

@tikvahethiopia
#BREAKING

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፌዴራል መንግስት ሰብዓዊነትን መሰረት ባደረገና ተጨማሪ ጉዳት በማያስከትል መልኩ #የተኩስ_አቁም_ስምምነት እንዲያደርግ ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ እንዳስታወቁት፥ ክረምት እየገባ በመሆኑ የትግራይ ክልል አርሶ አደር ተረጋግቶ የእርሻ ስራውን እንዲያከናውን፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ለተረጂዎች ያለምንም ችግር እንዲደርስ ወቅቱን የሚመጥን ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርግ ተጠይቋል ብለዋል።

ዶ/ር አብርሃም በላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጥያቄውን ባለፈው ሳምንት በይፋ ማቅረቡን ገልፀዋል።

ይህ ጥያቄ የቀረበው የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ከክልሉ ህዝብ ተወካዮች ፣ ከቢሮ እና ዞኖች አመራር አባላት፣ በተለያየ ቦታ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች፣ ከትግራይ ምሁራን፣ ከባለሀብቶችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር ተከታታይ ምክክር ካደረገ በኋላ ነው ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/ENA-06-28-2

#ኢዜአ

@TIKVAHETHIOPIA
"... የ2ኛው ዓመት የውሃ ሙሌት #ነሃሴ መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል" -ኢንጅነር ጌዲዮን አስፋው

የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪና የባለሙያዎች ቡድን ሰብሳቢ ኢ/ር ጌዲዮን አስፋው ለኢዜአ በሰጡት ቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተከናወነ ያለው ሶስቱ አገሮች በፈረሙት የመርህ ስምምነት መሰረት መሆኑን አሳውቀዋል።

ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን እ.ኤ.አ. በ2015 በመሪዎቻቸው አማካኝነት በሱዳን ካርቱም የህዳሴ ግድቡን ድርድር አስመልክቶ የመርሆች ስምምነት ተፈራርመዋል።

የመርህ ስምምነቱ አስር አንቀጾችን ያካተተ ሲሆን የሶስቱንም አገሮች ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም ኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳን በተስማሙት የመርህ ስምምነት መሰረት ሁለተኛው ዙር የግድቡ የውሃ ሙሌት እየተከናወነ ኢንጅነር ጌዲዮን አስፋው ገልፀዋል።

በታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ላይ የሶስቱ አገሮች ባለሙያዎች የተስማሙባቸው ነጥቦች የተቀመጡ መሆኑን አስታውሰው አገሮቹ በዚሁ መሰረት መስማማታቸውን አስረድተዋል።

ግብጽና ሱዳን በመርሆች ስምምነት ውስጥ ሁለት ጥናቶች እንዲካሄዱ የሚያስቀምጥ ቢሆንም ግብጽ እና ሱዳን ጥናቱ እንዳይካሄድ ሲያስተጓጉሉ ነበር ብለዋል።

አገሮቹ ስምምነቱን ከተፈራረሙ በ15 ወር ውስጥ ሁለት (2) ጥናቶችን ማከናወን እንዳለባቸው ቢያስቀምጥም ጥናቶቹ እንዳይካሄዱ ግብጽና ሱዳን በያዙት ግትር አቋም ሳይሳካ ቀርቷል ነው ያሉት።

አለም አቀፉ ማህበረሰብ ግብጽ እንዲሁም ሱዳን የግድቡን ውሃ ሙሌት በተመለከተ የሚሰጡትን የተዛባ መረጃ ሊመረምር እንደሚገባም ገልጸዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/ENA-07-07

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
"...ሰዎቹን በህይወት የማግኘት እድሉ ጠባብ ነው" - ፖሊስ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ 13 የሚደርሱ ሰዎችን አሳፍራ በጣና ሃይቅ ጉዞ የጀመረች አነስተኛ ጀልባ ተሰወረች።

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ቸርነት አስማረ ጀልባዋ የተሰወረችው በወረዳው አዲሰጌ ድንጌ ተብሎ ከሚጠራ ቀበሌ አባን ላይ ጎጥ መነሻቸውን በማድረግ ወደ ጎርጎራ ወደብ ጉዞ ከጀመረች በኋላ ነው ብለዋል።

ተጓዥቹ ሐምሌ 9 ቀን 2013 ዓም ለሊት ድንች ጭነው ጉዞ መጀመራቸውን ከቤተሰቦቻቸው መረጃው ለፖሊስ መድረሱን ገልፀዋል።

ተሳፋሪዎቹ ከ10 እስከ 13 እንደሚደርሱና አብዛኞቹም በስም ዝርዝር መለየታቸውን የገለፁት ምክትል ኮማንደሩ ተሳፋሪዎቹ ከመዳረሻው ጎርጎራ ወደብ እንዳልደረሱ መረጋገጡን ተናግረዋል።

ከትናንት እኩለ ቀን ጀምሮ በሁለት ቡድን የተዋቀረ የፖሊስና የባለሙያዎች ቡድን ፍለጋ እያካሄደ መሆኑን አመልክተው እስካሁን ምንም አይነት ፍንጭ ማግኘት እንዳልተቻለ አስታውቀዋል።

በዛሬው እለት ፍለጋው መቀጠሉን ጠቁመው ተጓዦቹ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወይ በማዕበል ተወስደዋል፤ አለበለዚያም ከአቅም በላይ በሆነ ጭነት ጀልባዋ ሰምጣለች የሚል ድምዳሜ ላይ መደረሱን አብራርተዋል።

ተጓዦቹ የተነሱበት ሰዓት ለሊት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ፍለጋውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ጠቅሰው ከዚህ በኋላ ሰዎችን በህይወት የማግኘት እድሉ ጠባብ እንደሆነም አመልክተዋል።

ከመነሻው እስከ መዳረሻው ድረስ ያለው የውሀ ላይ ጉዞ የ15 ኪሎ ሜትር ርቀት እንዳለው አመልክትው በፍለጋው የሚገኘውን ዝርዝር ውጤት በቀጣይ ህዝቡ እንዲያውቀው እንደሚደረግ አስታውቀዋል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። ዶ/ር ለገሰ ፥ መንግስት ለያዘው ሀገራዊ ምክክርና ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል ብለዋል። ይህን ሀገራዊ አንድነት ለማምጣትም ብዙ ተከታይ ያላቸውን እስረኞች ክስ ማቋረጥ ማስፈለጉን ነው የተናገሩት። በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ፣ የተመቻቸ…
#DrLegesseTulu

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ምን አሉ ?

ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፦

" ... በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ከስር መሰረቱ ለመፍታት የእስረኞችን ክስ ማቋረጥ አስፈልጓል።

የክሱ መቋረጥ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት እና ዋስትና ያለው የዴሞክራሲ ስርዓት በመገንባት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስቀጠል ከማሰብ የመነጨ መሰረታዊ ጉዳይ ነው።

በእነ አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ እስክንድር ነጋ ስር የነበሩ ተከሳሾች ክስ መቋረጥ በስራቸው በርካታ ተከታይ ያላቸው መሆናቸውን ከግንዛቤ በማስገባት ለብሔራዊ አካታች ምክክሩ ጉልህ ሚና እንዳላቸው በመገንዘብ ነው።

በሽብር ቡዱኑ መሪ ደብረፂዮን ገብረ ሚካኤል ስር ያሉ የክስ ሂደት መቋረጥ ከጤና እና እድሜ መግፋት ጋር የተያያዘ ነው።

ኢትዮጵያዊያን ክሳቸው የተቋረጡ ዜጎችን በሚመለከት ህዝብና መንግስትን በማጋጨት እራሳቸውን ደብቀው የሚያራግቡ አካላትን በቃቹህ በማለት ለዘላቂ ብሔራዊ ጥቅም ዘብ መሆን ይገባል "

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
#Safaricom

" ሳፋሪኮም በፈረንጆቹ 2022 በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ 300 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ወጪ ያደርጋል " - አንዋር ሱሳ

የኬንያው የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም በፈረንጆቹ 2022 በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ 300 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ወጪ መዋዕለ ነዋይ እንደሚያፈስ ገልጿል።

የሳፋሪኮም የኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አንዋር ሱሳ ኩባንያው በተያዘው የፈረንጆቹ 2022 ወደ 300 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በኢትዮጵያ ፈሰስ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ስራውን ለመጀመር የኔትወርክ ዝርጋታ እያካሄደ መሆኑንና የመጀመሪያ የመረጃ ማዕከሉን በ100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ መዘርጋቱን ተናግረዋል።

ሳፋሪኮም በመጪዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ አገልግሎቱን በይፋ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GeneralDagallo ጄነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር እንዲሁም ከሌሎች አመራሮች ጋር መገናኘታቸውን ገልፀዋል። ጄነራሉ ባጋሩት ፎቶ : ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፣ ከኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ከሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ጋር መገናኘታቸውን ያሳያል። …
" ከሱዳን ጋር ተቀራርበን መስራት እንደሚገባን መግባባት ላይ ደርሰናል " - ዶ/ር አብርሃም በላይ

ከሱዳን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበን መስራት እንደሚገባን መግባባት ላይ ደርሰናል ሲሉ የአገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ገልፀዋል።

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ወደ አገራቸው ሲመለሱ ዶክተር አብርሃም አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።

የጄኔራል ዳጋሎን የኢትዮጵያ ቆይታን በተመለከተ ዶክተር አብርሃም ለኢዜአ እንደገለጹት ፤ በኢትዮጵያ እና በሱዳን የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

“አብረንና ተቀራርበን መስራት እንደሚገባን ተግባብተናል” ሲሉም ገልጸዋል።

ትናንት አዲስ አበባ የገቡት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

ጄኔራሉ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ከአገር መከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ እና ከኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia