#MoE
የትምህርት ሚኒስቴር በጦርነት ምክንያት የወደሙ እና የፈረሱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ከ1ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ መመደቡን አሳውቋል።
በአማራ እና አፋር ክልሎች ሙሉ በሙሉ የወደሙ 1 ሺህ 93 ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ እነዚህ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው እንደሚገነቡ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
@tikvahethiopia

#Woldia
የወልድያ ከተማ አስተዳደር ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እና ለአማራ ክልል መንግሥት ጥያቄዎችን ማቅረቡን ገልጿል።
ከተማ አስተዳደሩ ቀደም ሲል የተጀመረውና ኅብረተሰቡ ለጤና እክልና ለተለያዩ ችግሮች እያደረገ ያለው የከተማዋ የአስፋልት መንገድ ግንባታ በፍጥነት ወደ ሥራ የሚገባበትን መንገድ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለ ስልጣን አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠው ጥያቄውን አቅርቧል።
በተመሳሳይ ሁኔታ የኅብረተሰቡን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በተገቢው መንገድ ምላሽ ለመስጠት ወቅቱን የሚዋጅ አደረጃጀት መፍጠር የሚያስችለውን የከተማዋን የሪጅዮ ፖሊታንት መዋቅር ጥያቄ ለክልሉ መንግሥት በድጋሜ በጽሑፍ አቅርቧል።
ከተማ አስተዳደሩ ለከተማዋ መልማት ከፍተኛ ሚና ያላቸውን ተገቢ ጥያቄዎች የከተማዋን እድገት የሚመኝ ሁሉ ጉዳዮቹን አጀንዳ በማድረግ ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቡን ከወልዲያ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#Hossana
የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሀዉልት ነገ እሁድ በሆሳዕና ከተማ ይመረቃል።
ለዚህ የምረቃ ስነስርዓት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ወደ ሆሳዕና ከተማ ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
የሀዲያ ዞን አስተዳደር ወደ ከተማው የተጋበዙትን እንግዶች በሠላማዊ መንገድ ለመቀበልና ለማስጎብኘት እንዲያስችል መላዉ የዞኑና የከተማዉ ነዋሪዎች የአካባቢዉን ሠላምና ፀጥታ በመጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።
በሌላ በኩል የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን ጀግንነት የሚዘክር የፎቶ ኤግዚቢሽን ዛሬ በሆሳዕና ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
መረጃው ከሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የተገኘ ነው።

አጭር ማስታወሻ ፦
1ኛ. በአዲስ አበባ በጊዜያዊነት ታግዶ የነበረው መሬት ነክ አገልግሎት አሁን ላይ እግዱ ተነስቶ አገልግሎቱ በየክፍለ ከተማው እየተሰጠ ነው። ታግደው ከነበሩ አገልግሎቶች መካከል ጊዜያዊ እግድ የተነሳላቸው አገልግሎቶች ዝርዝር በዚህ ይመልከቱ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/66990?single
2ኛ. ተቋርጦ የቆየው የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭ ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውል ከሰኞ ጥር 23/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ይጀምራል። አገልግሎቱን ለማግኘትና የጉዳይ መከታተያ ቁጥር በኦንላን ለማግኘት www.dars.gov.et ይጠቀሙ።
3ኛ. ዩኤኢ (UAE) ኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ላይ ጥላው የነበረው የጉዞ እገዳ ከዛሬ ቅዳሜ ጀምሮ ተነስቷል። በተያያዘ ማስታወሻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ የዱባይ በረራውን ይቀጥላል።
4ኛ. በወሰን ማስከበር ምክንያት ሳይጠናቀቅ የቆየው የገርጂ ሮባ ዳቦ -መብራት ኃይል (አዲስ አበባ) አስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።
5ኛ. በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ማስክ ያላደረጉ አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ከተገኙ ብር 1 ሺህ ይቀጣሉ ፤ ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪ በሚጭኑበት ወቅት ደግሞ በአንድ ሰው 500 ብር ይቀጣሉ።
6ኛ. የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ የመታሰቢያ ሀዉልት ነገ እሁድ በሆሳዕና ከተማ ይመረቃል።

#UAE
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዩኤኢ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ አቡ ዳቢ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር የጋራ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

መነጋገሪያ የሆነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ?
የኢትዮጵያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በተረጋገጠ የፌስቡክ ገፁ ላይ ዛሬ ያጋራው የአንድ ግለሰብ የፌስቡክ መልዕክት መነጋገሪያ ሆኗል።
የተረጋገጠው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌስቡክ ገፅ ከአንድ ሰዓት በፊት ያጋራው እና እስካሁን ያልተነሳው " Musa Gobena " በሚል ስም የሚጠራ የግል አካውንት የተሰራጨ መልዕክት ነው።
መልዕክቱ " የፊንፊኔ ከተማ ቦታዎች የጥንት መጠሪያ እና አሁን ተቀይረው የሚጠሩበት ስም " የሚል ዝርዝር ነው።
ምክር ቤቱ በተረጋገጠው አካውንቱ ባጋራው መልዕክት ላይ ከላይ ምንም አይነት ተጨማሪ ማብራሪያ ያልሰጠበት ሲሆን እስካሁን ድረስ ከ290 በላይ የተለያዩ ይዘት ያላቸው አስተያየቶች ተሰጥተዋል።
ከ170 በላይ ሰዎች የፌዴሬሽን ምክር ቤቱን መልዕክት ለሌሎች አጋርተዋል። ከ567 በላይ ሰዎች ስሜታቸውን በተለያዩ ምልክቶች 👍❤️😡😁😱 ገልፀዋል።
ይበልጥ ይህንን ጉዳይ መነጋገሪያ ያደረገው መልዕክቱን ያጋራው ግለሰብ አካውንት ይዘት እራሱ መንግስትን ሚቃወሙ መልዕክቶች የሚጋሩበት መሆኑ ነው።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በተረጋገጠ የፌስቡክ አካውንቱ ስለወጣው መልዕክት በራሱ ገፅ ሆነ በሌላ የሚዲያ አማራጭ የሰጠው ማብራሪያ የለም።

TIKVAH-ETHIOPIA
መነጋገሪያ የሆነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ? የኢትዮጵያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በተረጋገጠ የፌስቡክ ገፁ ላይ ዛሬ ያጋራው የአንድ ግለሰብ የፌስቡክ መልዕክት መነጋገሪያ ሆኗል። የተረጋገጠው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌስቡክ ገፅ ከአንድ ሰዓት በፊት ያጋራው እና እስካሁን ያልተነሳው " Musa Gobena " በሚል ስም የሚጠራ የግል አካውንት የተሰራጨ መልዕክት ነው። መልዕክቱ " የፊንፊኔ ከተማ ቦታዎች የጥንት…
#Update
በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተረጋገጠ የፌስቡክ ገፅ ላይ ተጋርቶ የነበረው መልዕክት አሁን ላይ ጠፍቷል።
መልዕክቱ ለ1 ሰዓት ሳይጠፋ የቆየ ሲሆን የተሰጠ ማብራሪያ የለም።
@tikvahethiopia
በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተረጋገጠ የፌስቡክ ገፅ ላይ ተጋርቶ የነበረው መልዕክት አሁን ላይ ጠፍቷል።
መልዕክቱ ለ1 ሰዓት ሳይጠፋ የቆየ ሲሆን የተሰጠ ማብራሪያ የለም።
@tikvahethiopia
#DStv የደስ ደስ!
ሊያመልጥዎ የማይገባ እድል ከዲኤስቲቪ ፤ ከጥር 2 እስከ መጋቢት 21 ድረስ ብቻ የሚቆይ!
በየወሩ የሜዳ ፓኬጅ 550 ብር ሲከፍሉ ባለ 1,300 ብር የሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ስጦታ ያገኛሉ። በተመሳሳይ የሜዳ ፕላስ ፓኬጅ በ1,300 ብር ሲከፍሉ ባለ 2,600 ብር የፕሪምየር ፓኬጅ ስጦታ ያገኛሉ።
በእድሉ ፈጥነው ይጠቀሙ። ከከፈሉት የዲኤስቲቪ ፓኬጅ በላይ ያግኙ።
ክፍያ ለመፈፀም፣ፓኬጅዎን ለመቀየር እንዲሁም ሌሎች የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ : https://bit.ly/2WDuBLk
የዲኤስቲቪን ቤተሰብ ይቀላቀሉ! https://bit.ly/3D2O1t4

#ATTENTION
የኦሮሚያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር እና ልማት ተነሺዎች ኮሚሽን በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ በ7 ዞኖች ድርቅ መከሰቱን አሳውቋል።
በድርቁ ከ800 ሺህ በላይ ሰዎች ተጎጂ መሆናቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።
የኦሮሚያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር እና ልማት ተነሺዎች ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙስጠፋ ከድር ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፥ " በቦረና ፣ ምስራቅ ጉጂ እና ባሌ ውስጥ ድርቁ በከፍተኛ ሁኔታ ተስተውሏል። በምዕራብ ጉጂ ፣ ምዕራብ ባሌ እና በምዕራብ እና ምስራቅ ሀረርጌ በአጠቃላይ በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ድርቁ ተከስቷል ፤ ይህ የሆነው ባለፈው አመት የመኸር እና የክረምት ዝናብ ሳይዘብ በመቅረቱ ነው " ብለዋል።
ዝናብ ሳይዘንብ በመቅረቱ ሳር አለመብቀሉን፣ ምንጮችም መድረቃቸውን አቶ ሙስጠፋ ተናግረዋል።
በአጠቃላይ 800,244 ሰዎች እርዳታ ለመጠበቅ መገደዳቸውንም አክለው ገልፀዋል።
በድርቅ ሳቢያ በእስሳት ላይ ስለደረሰው ጉዳት በተመለከተ ፥ " በ7ቱ ዞኖች በድርቁ የተጎዱ እንስሳት ቁጥር ከ188 ሺህ በላይ ሆኗል። አብዛኛዎቹ በሰው ድጋፍ ነው ከመሬት የሚነሱት። ቦረና ውስጥ ከ6 ሚሊዮን በላይ የቁም እንስሳት እንዳለ ነው የሚታወቀው በእነዚህ ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው " ብለዋል።
ኮሚሽነሩ መንግስት በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ እና ለእንስሳት መኖ በማቅረብ ጉዳት ለመቀነስ እየሰራ ነው ብለው ፤ ነገር ግን በቂ አንዳልሆነ አስገንዝበዋል፤ መንግስታዊ የሆኑ እና መንግስታዊ ያልሆኑ እንዲሁም የግል ድርጅቶች፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ሰዎች እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ሙስጠፋ ከድር እስካሁን በድርቁ የሰው ህይወት አለማለፉን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

Photo
" ... እንስሳት የሚበሉትን አጥተው አብዛኛዎቹ አልቀዋል፤ ከእንስሳትም አልፎ ለሰው ህይወትም እየሰጋን ነው " - አቶ ጎዳና ሎራ
#NakorMelkaVoA
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የድሬ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጎዳና ሎራ ባለፈው ዓመት መዝነብ የነበረበት የመኸር እና ክረምት ዝናብ ባለመዝነቡ በሰዎች እና በእንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን ገልፀው ፤ ተጨማሪ ጉዳት ለመከላከል ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ጎዳና ሎራ ፦
" ከዝናብ እጥረት የተነሳ ድርቅ አጋጥሞናል።
ክረትም የዘራነው ዘር ሳይበቅል ነው የቀረው። እንስሳትም የሚበሉትን አጥተው አብዛኛዎቹ አልቀዋል፤ ከእንስሳትም አልፎ ለሰው ህይወትም እየሰጋን ነው። ለምሳሌ እኔ 30 ከብቶችን አጥቻለው 80 የሚሆኑ ከብቶች ያለቁበትም አለ።
ባለንበት ቀበሌ በድርቅ ምክንያት ከ10 በላይ ሰዎች ታመው ሰውነታቸው አብጧል።
የቦረና የኑሮ መሰረት የከብት እርባታ ነው። ድርቁ እያሳደረሰው ካለው ጉዳት አንፃር በእዚህ የሚቀጥል ከሆነ የባሰ አደጋ ያጋጥመናል።
መንግስታዊ የሆኑና ያልሆኑም ድርጅቶች እንዲሁም ህዝቡ ድርቁ ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ሊረባረቡ ይገባል "

#Update በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተረጋገጠ የፌስቡክ ገፅ ላይ ተጋርቶ የነበረው መልዕክት አሁን ላይ ጠፍቷል። መልዕክቱ ለ1 ሰዓት ሳይጠፋ የቆየ ሲሆን የተሰጠ ማብራሪያ የለም። @tikvahethiopia
" ... ተለጥፎ የነበረው መልዕክት ከእውቅናዬ ውጭ ነው ፤ የምክር ቤቱንም አቋም አይወክልም " - ፌዴሬሽን ምክር ቤት
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሰዓታት በፊት በተረጋገጠ የፌስቡክ ገፁ ላይ ስለተለጠፈው መልዕክት አጭር መልዕክት አስተላልፏል።
ምክር ቤቱ በገፁ ላይ ተለጥፎ የነበረው መልእክት ከምክር ቤቱ እውቅና ውጪ የተለጠፈ መሆኑን ገልጿል።
እንዲሁም መልዕክቱ የምክር ቤቱን አቋም እንደማይወክል አሳውቋል።
ም/ቤቱ በተረጋገጠ ገፁ ላይ መልዕክቱን ማን እንዳጋራውና እንዴት ሊጋራ እንደቻለ፣ ለዚህ ሚጠየቅ አካል ይኖር እንደሆነ የሰጠው ማብራሪያ የለም።

#DireDawaUniversity
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት የሕክምና ሳይንስ ተማሪ የነበረው ታሪኩ ሶሪ ሐሙስ ጥር 19/2014 ዓ.ም እኩለ ቀን አካባቢ ራሱን ማጥፉቱን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የተማሪውን ህልፈት ምክንያት ለማጣራት ከጸጥታ አካላት ጋር እየሰራ እንደሚገኝ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
የተማሪው አስክሬን ወደ አዲስ አበባ ጳውሎስ ሆስፒታል ተልኮ ምርመራ እንደተደረገበት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ዐቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ደቻሳ ጋንፉሬ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው የምርመራው ውጤቱ እንደደረሰው ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ እንደሚያደርግ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
" ተማሪ ታሪኩ ታንቆ ራሱን እንዳጠፋ ነው የምናቀው " ያሉት ዳይሬክተሩ፤ "ከህልፈቱ ጋር እየተነሱ ያሉ ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው" ብለዋል።
የተማሪው አስክሬን ትላንት ቤተሰቦቹ ወደሚገኙበት ወለጋ ዞን ሆሩ ጉዱሩ መላኩን ዳይሬክተሩ ለቲክቫህ ገልጸዋል።
More : @tikvahuniversity

#ትምህርት_ሚኒስቴር
" በሁሉም ክልሎች በችሎታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው 50 ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች በችሎታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው 50 ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡ አሳወቀ።
ትምህርት ቤቶቹ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱና በችሎታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው ናቸው ተብሏል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሁሉም ክልሎች በዓይነታቸው ልዩ የሆኑና የልህቀት ማዕከል የሚሆኑ 50 ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ ብለዋል።
ት/ ቤቶቹ ቀጣይ የአገር መሪ የሚሆኑ ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎች የሚፈልቁበት በችሎታቸው ብቻ የሚመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።
በትምህርት ቤቶቹ የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መሠረት ባደረገና የትምህርት ሚኒስቴር በሚያወጣውን መመዘኛ የሚያሟሉ ተማሪዎች የሚማሩባቸው መሆናቸው ተገልጿል።
በሁሉም ክልሎች በሚገነቡት እነዚህ የልህቀት ማዕከላት ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የሚመለመሉ ተማሪዎችን ተቀብለው የሚያስተምሩ ይሆናሉ።
ይህንን መረጃ ያጋራው የትምህርት ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገፅ ሚኒስትሩ የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ መቼ ተጀምሮ መቼ ለማጠናቀቅ እቅድ እንደተያዘ የተናገሩት ነገር ስለመኖሩ ያለው ነገር የለም።