TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ድሬ❤️

"ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ
ከቶ አይዘነጋም ድሬ ላይ መሆኑ! "

በድሬዳዋ ሁሌም ቢሆን የነዋሪዎቿ #ፍቅር#አንድነት እና #አብሮነት ብሎም አሁናዊ የከተማዋ ሰላም ለሌሎች ምሳሌና ማሳያ ነው መባሉ በምክንያት ነው።

በጥምቀት ከተራ በዓል የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ወንድምና እህቶች በቀፊራ ፣ በለገሀሬ ፣ ኮኔል ፣ በድልድይ መጋላ እና በሌሎችም አካባቢዎች ለህዝበ ምእመኑ ውሀ፣ ኩኪሲችና ጣፍጭ ምግቦችን በማቅረብ እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ ወንድማዊና ቤተሰባዊ ፍቅራቸውን ገልፀዋል።

ፎቶ ፦ ድሬ ፖሊስ ሚዲያ

@tikvahethiopia
" የጥምቀት ከተራ በአል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ተከብሯል " - ድሬዳዋ ፖሊስ

የጥምቀት ከተራ በአል በሀይማኖታዊ ስርአቱ መሰረት በደማቅ ሁኔታ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ በድሬደዋ የተከናወነ ሲሆን ታቦታቱም ከማደሪያቸው ጥምቀተ ባህሩ መድረሳቸውን የድሬደዋ ፖሊስ ገልፆል።

በመሆኑም ለጥምቀት ከተራ በአል ፍፁም ሰላማዊነት ምዕመኑ ፣ መላው የድሬደዋ ነዋሪ እና የፀጥታ ሀይሉ ላበረከተው አስተዋፆና ተኪ የለሽ ሚና የድሬደዋ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርባል።

ምንጭ፦ ድሬዳዋ ፖሊስ

@tikvahethiopia
ፎቶ : የከተራ በዓል በጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ጎንደር ❤️ ከተማ ፤ ጥር 10 ቀን 2014 ዓ/ም ።

የፎቶ ባለቤት 👉 ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው

@tikvahethiopia
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ !

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ - ኢትዮጵያ አባላት የጥምቀት በዓልን ስናከብር ከአጠገባችን በችግር ላይ ያሉ የተጎዱ ወገኖችን በማገዝ ፣ አቅም የሌለንም ስለእነሱ በማሰብ እና ፈጣሪን በመለመን ፣ ለሀገር ሰላም እና ለሰው ልጆች ሁሉ ደህንነት በመፀለይ እንዲሆን አደራ እንላለን።

ዛሬም በሀገራችን የተለያዩ አቅጣጫዎች በችግር እና ስቃይ ያሉ ወገኖች በርካቶች መሆናቸውን በመገንዘብ ፣ እንደኛ ይህን በዓል በሰላም እና በደስታ ማክበር የማይችሉ ወገኖቻችን መኖራቸውን በማወቅ ፈጣሪ ለሁላችን ሰላም እና ፍቅር ፣ መተሳሰብና አንድነት አድሎ በጋራ በሰላም በመሰባሰብ እንድናከብር እንዲረዳን እንለምናለን።

ያዘኑ ወገኖችን ምናፅናናበት፣ የተጣላን የምንታረቅበት፣ የተኳረፍን የምንነጋገርበት ፣ ያስቀየምን ይቅርታ የምንጠይቅበት፣ የበደልን የምንክስበት፣ ያስከፋን የምናስደስትበት ፣ የታመሙ የተጎዱ የሚፈወሱበት ፣ የተጨነቁ ከጭንቀት ነፃ የሚሆኑበት የሰላም ፣ የደስታ፣ የአንድነት፣ የፍቅር በዓል ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

መልካም በዓል !

@tikvahethiopia