TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Hosaena

ቤተ-ክርስቲያኒቱ ለ40 ዓመታት ስታቀርብ የነበረው ጥያቄ ተመለሰላት።

የሆሳዕና ከተማ የጥምቀት እና የመስቀል ደመራ ማክበሪያ ቦታ ምላሽ ማግኘቱን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ፅ/ቤት በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

ቤተ-ክርስቲያኒቱ ከጥንት ጀምሮ ስትጠቀምበት የነበረውን የባህረ ጥምቀት እና የመስቀል ደመራ በዓል ማክበሪያ ቦታ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲያገኝ ከ1974 ዓ/ም ጀምሮ በየደረጃው ለሚገኙ የመንግስት አካላት ጥያቄ ስታቀርብ መቆየቷን ፅ/ቤቱ አስታውሷል።

ነገር ግን ጥያቄው ምላሽ ባለማግኘቱ እና ቦታውም ለሌላ ማህበራዊ አግልግሎት እንዲውል በመደረጉ በቦታው ላይ የአደባባይ በዓላቶች ማክበር የማያስችሉ በርካታ ችግሮች በመፈጠራቸው ቤተ-ክርስቲያኒቱ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ የአደባባይ በዓላቶቿን ማክበር ሳትችል መቅረቷ ተገልጿል።

በመጨረሻም ለ40 ዓመታት ሲቀርብ የነበረው ጥያቄ የደቡብ ክልል መንግስት ፣ የሀዲያ ዞን እና የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ለችግሩ ትኩረት በመስጠት ባደረጉት ጥረት ለጥያቄው ተገቢው ምላሽ መሰጠቱን የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ፅ/ቤት ዛሬ አሳውቋል።

ቤተክርስቲያኒቱ ፥ የ2014 ዓ/ም የጥምቀት በዓልን ምዕመናን በጋራ እንዲያከብሩ ጥሪዋን አቅርባለች።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 👉 6,094
• ቫይረሱ የተገኘባቸው 👉 881
• ህይወታቸው ያለፈ 👉 15
• ከበሽታው ያገገሙ 👉 1,731
• ፅኑ ታማሚዎች 👉 420

ዛሬ ፣ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ አጠቃላይ 3,647 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 45 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሱዳን 2 ሰዎች ተገደሉ። ጎረቤት ሀገር #ሱዳን በተቃውሞ መናጧን የቀጠለች ሲሆን ትላንት እሁድ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉን ለማወቅ ተችሏል። በኦምዱርማን እንዲሁም በካርቱም በሀገሪቱ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም ሰልፍ አካሂደዋል። የሱዳን የዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ በትላትናው ሰልፍ የሁለት ሰዎች ማለፉን ሪፖርት ያደረገ ሲሆን አንደኛው ሟች ትላንት አንዱ ደግሞ ዛሬ…
#SUDAN

ዛሬ በጎረቤት ሀገር ሱዳን 7 ሲቪሎች ተገደሉ።

የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ በዛሬው እለት በተካሄደ የፀረ መፈንቅለ መንግስት ሰላማዊ ተቃውሞ ሰልፍ 7 ንፁሀን ዜጎች በፀጥታ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን አሳውቋል።

ኮሚቴው ፥ " የጁንታው ኃይሎች ጭፍጨፋቸውን ቀጥለውበታል፣ ሰላማዊ የሱዳን ተቃዋሚዎች ገዳይ ከሆነ ሃይል ጋር እየተጋፈጡ ነው " ብሏል።

በዛሬው ሰልፍ በቀጥታ በተተኮሱ ጥይቶች ምክንያት በርካታ ጉዳቶች ሪፖርት መደረጋቸውን እና ጉዳት የደረሰባቸው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ገልጿል።

ኮሚቴው ፤ መላው ዓለም በሰላማዊ መንገድ ለ ነጻ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊት አገር ወደፊት እየተጓዘ ያለውን የሱዳን ህዝብ ላይ ሆን ተብሎ የሚፈፀመውን አሰቃቂ ወንጀሎች በቅርበት መከታተል እና ለማስቆምም ከበድ ያለ እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል ሲል አስገንዝቧል።

የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ ፥ ከወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ወዲህ የተገደሉ ሰላማዊ ሰዎች ቁጥር 71 እንደደረሰ ሪፖርት አድርጓል።

@tikvahethiopia
#UAE

ዛሬ UAE ውስጥ በድሮን መሆኑ በተገመተ ጥቃት ቢያንስ 3 ሰዎች ሲገደሉ ፤ 6 ሰዎች ቆስለዋል።

የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ (UAE) ባለሥልጣናት የደሃቢ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካል በሆነው ስፍራ የሚገኙ 3 የነዳጅ ማጠራቀሚያ ታንከሮች በድሮን መሆኑ የተገመተ ጥቃት የደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የአገሪቱ መንግሥት ዜና አገልግሎት ባለሥልጣናቱን ጠቅሶ እንዳስታወቀው በደረሰው ጥቃት ቢያንስ ሶስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ሌሎች ስድስት ደግሞ መቁሰላቸው ተመልክቷል፡፡

ከሟቾቹ መካከል 2 ህንድ እና 1 የፓኪስታን ዜጋ እንደሚገኙበት ተነገሯል፡፡

ፖሊስ ሁኔታው እየተጣራ መሆኑን ቢገልጽም የየመን ሁቲዎች ዛሬ ሰኞ በሰጡት መግለጫ ወደ ዩናይትድ አረብ ኤምሬት (UAE) ጠልቆ የሚገባ ጥቃት የሰነዘሩ መሆናቸውን ቢያስታውቁም ስለ ሁኔታው ግን ዝርዝር መግለጫ አልሰጡም፡፡

ሁቲዎች ዩናይትድ አረብ ኤምሬት ላይ ተጨማሪ ጥቃት ሊፈፅሙ እንደሚችሉም አስጠንቅቀዋል።

የዩናይትድ አረብ ኤምሬት (UAE) እ.ኤ.አ. ከ2015 ጀምሮ የየመን ሁቲዎችን የሚወጋውና በሳኡዲ አረብያ የሚመራው የጦር ህብረት አባል መሆንዋ ይታወቃል፡፡

ዘገባውን ቪኦኤ አሶሼይትድ ፕሬስ እና አጃንስ ፍራንስ ፕሬስን ዋቢ አድርጎ ያዘጋጀው ሲሆን በተጨማሪ የአልጀዚራ መረጃ ተካቶበታል።

@tikvahethiopia
እንኳን አደረሰን ፤ አደረሳችሁ !

እንኳን ለከተራ በዓል አደረሰን ፤ አደረሳችሁ።

ውድ ቤተሰቦቻችን የከተራ በዓል ድባብ በአካባቢያችሁ ምን ይመስላል ?

@tikvahethiopiaBot ላይ አጋሩን።

ስትንቀሳቀሱ የምትመለከቷቸውን ሁነቶች በእጅ ስልካችሁ ካሜራ በማስቀረት አጋሩ፤ መልዕክቶቹን ስትልኩ ፎቶውን ያነሳውን ሰው ስምና የተነሳበትን ከተማ መፃፍ እንዳትዘነጉ።

#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopia
#AFRICA

#AFCON_2021 ውድድር ከወዲሁ ምድባቸው ማለፍ የቻሉ አራት ሀገራት ፦

🇨🇲 ካሜሩን
🇲🇦 ሞሮኮ
🇳🇬 ናይጄሪያ
🇧🇫 ቡርኪናፋሶ

ከምድቧ ማለፍ ሳትችል ቀርታ ከውድድሩ ቀድማ መሰናበቷ የተረጋገጠው ደግሞ ኢትዮጵያ 🇪🇹 ናት።

More : @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
#UAE ዛሬ UAE ውስጥ በድሮን መሆኑ በተገመተ ጥቃት ቢያንስ 3 ሰዎች ሲገደሉ ፤ 6 ሰዎች ቆስለዋል። የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ (UAE) ባለሥልጣናት የደሃቢ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካል በሆነው ስፍራ የሚገኙ 3 የነዳጅ ማጠራቀሚያ ታንከሮች በድሮን መሆኑ የተገመተ ጥቃት የደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል። የአገሪቱ መንግሥት ዜና አገልግሎት ባለሥልጣናቱን ጠቅሶ እንዳስታወቀው በደረሰው ጥቃት…
#Update

ትላንት በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (ዩኤኢ) ላይ ከሁቲዎች የተፈፀመውን የድሮን ጥቃት ሀገራት እና ተቋማት እያወገዙት ይገኛሉ።

ሳዑዲ አረቢያ ትላንት ሰኞ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ውስጥ በሲቪል አካባቢዎች እና መገልገያዎች ላይ ያነጣጠረው የሁውቲ ጥቃት " የሽብር ጥቃት " መሆኑን በመግለፅ በፅኑ አውግዛዋለች።

ባህሬን፣ ኩዌት ፣ ኳታር ፣ ሞሮኮ፣ ግብፅ ፣ ኦማን እንዲሁም የአረብ ፓርላማ ጥቃቱን አውግዘዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ የሃውቲውን ጥቃት አውግዘዋል ሁሉም አካላት ከፍተኛ ቁጥጥር እንዲያደርጉ አሳስበዋል። የአንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች “በሲቪሎች እና በሲቪል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች በአለም አቀፍ ህግ የተከለከሉ ናቸው” ብለዋል። በየመን ላለው ግጭትም ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለው ተናግረዋል።

አሜሪካ ጥቃቱን አውግዛ ጥቃቱን ስለመፈፀሙ ኃላፊነት የወደሰው ሀውቲን ተጠያቂ ለማድረግ ይሰራል ስትል ዝታለች።

የየመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥቃቱ ባለፈው ሳምንት ሙሉ በሙሉ በሻብዋ እና በነዳጅ ዘይት የበለፀገችው ማሪብ ግዛት ላይ ሚሊሻዎች ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ የተሰማቸውን ብስጭት ያሳያል ብሏል።

ሚኒስቴሩ ሳዑዲ እና ዩኤኢ የሽብር ድርጊቶችን ለመከላከል ፣ የዜጎቻቸውን እና ነዋሪዎቻቸውን ደህንነት ለመጠበቅ የሚወስዱትን እርምጃ እንደሚደግፍም ገልጿል።

ጥቃት የተፈፀመባት የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ለተፈፀመባት ጥቃት ምላሽ የመስጠት መብቷ የተጠበቀ መሆኑን የገለፀች ሲሆን ሁቲዎች ተጨማሪ ጥቃት ሊፈፅሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ትላንት በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (ዩኤኢ) ላይ ከሁቲዎች የተፈፀመውን የድሮን ጥቃት ሀገራት እና ተቋማት እያወገዙት ይገኛሉ። ሳዑዲ አረቢያ ትላንት ሰኞ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ውስጥ በሲቪል አካባቢዎች እና መገልገያዎች ላይ ያነጣጠረው የሁውቲ ጥቃት " የሽብር ጥቃት " መሆኑን በመግለፅ በፅኑ አውግዛዋለች። ባህሬን፣ ኩዌት ፣ ኳታር ፣ ሞሮኮ፣ ግብፅ ፣ ኦማን እንዲሁም የአረብ ፓርላማ…
የመን ሰነዓ ውስጥ 12 ሰዎች ተገደሉ።

በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው ጥምር ጦር በየመን ዋና ከተማ ሰነዓ ላይ የአየር ድብደባ ፈፅሟል።

የአየር ድብደባ የተፈፀመው ሁቲዎች በተባበሩት አረብ ኤሜሪት ላይ ጥቃት ሰንዝረው 3 ሰዎች መግደላቸው እና 6 ሰዎች መቁሰላቸው ከተሰማ በሰዓታት ውስጥ ነው።

በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው ጥምረት በሰነዓ በፈፀመው የአየር ድብደባ ከ12 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እንደገለፁ አልጀዚራ ዘግቧል።

ሀውቲዎች ግን የሞቱ ሰዎች 20 እንደሚደርሱና በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን አመልክተዋል።

ዩኤኢ ላይ ተጨማሪ ጥቃት ሊፈፅሙ እንደሚችሉ የዛቱት ሁውቲዎች ሲቪሎች እና የውጭ ሀገር ሰዎች ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ ወሳኝ ከሆኑና አስፈላጊ ተቋማት እንዲርቁ አስጠንቅቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA አምባሳደር ሳተርፊልድ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ። አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ #ኢትዮጵያን ጨምሮ ሱዳን እና ሳዑዲ አረቢያን እንደሚጎበኙ ተገልጿል። አምባሳደር ሳተርፊልድ እኤአ ከጥር 17-20 ባሉት ቀናት ነው ሃገራቱን የሚጎበኙት፡፡ በቅድሚያ ወደ ሪያድ እንደሚጓዙ የሚጠበቁት ልዩ መልዕክተኛው ቀጥሎ ካርቱምንና አዲስ አበባን ይጎበኛሉ…
#Update

ዴቪድ ሳተርፊልድ እና ሞሊ ፊ ሳዑዲ አረቢያ ይገኛሉ።

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ትላንት ሳዑዲ አረቢያ ገብተዋል።

የሳውዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን ሁለቱን የአሜሪካ ባለስልጣናት ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸው ወቅት በሳዑዲ አረቢያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት እና ሁሉን አቀፋዊ ትብብርና የጋራ ቅንጅት የሚያስፈልጋቸውን ዘርፎች ማሳደግ የሚቻልባቸው መንገዶችን አስንተዋል ተወያይተዋል።

ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጉዳዮቻቸው ላይም ተወያይተዋል።

በአፍሪካ አህጉር ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋትን ለማጠናከር፣ ለአፍሪካ ህዝቦች እና ሀገራት እድገትና ብልፅግና ሁለቱ ሀገራት የሚያበረክቱት ሁሉን አቀፍ ጥረት ላይም ተወያይተዋል ተብሏል።

በውይይቱ ላይ የሳዑዲ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር አምባሳደር ኢድ አልታቃፊ እና በሳዑዲ አረቢያ የአሜሪካ ኤምባሲ ኃላፊ ማርቲና ስትሮንግ ተገኝተው እንደነበር ተገልጿል።

ሞሊ ፊ እና ዴቪድ ሳተርፊልድ በቀጣይ ወደ ሱዳን እና ኢትዮጵያ በመምጣት ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

በተለይም በኢትዮጵያ ጉዳይ ዲፕሎማቶቹ የአየር ድብደባ እና ሌሎች ግጭቶች እንዲቆሙ፣ በድርድር ላይ የተመሰረተ ተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲመቻችና ለሁሉ አቀፍ ብሔራዊ ውይይት የሚያስፈልጉ ነገሮች እንዲመቻቹ በአሁኑ ወቅት የተከፈተውን የሰላም ዕድል እንዲጠቀሙበት የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናትን ያበረታታሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ሊቀ ጳጳስ ዘኢሉባቡር አረፉ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የኢሉባቡር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም ረፋድ ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የብፁዕነታቸው የቀብር ሥነሥርዓት እና ቀብራቸው የሚፈጸምበት ቦታን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ ይገለፃል…
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ የብፁዕ አቡነ ሚካኤል የኢሉባቡር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር ጥር 16/2014 ዓ.ም በታላቁ የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እንዲፈጸም ወሰነ።

ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል።

ብፁዕ አቡነ ሚካኤል በሀገረ ስብከታቸው ርዕሰ መንበረ ጵጵስና መቱ በአገልግሎት እያሉ ሕመም አጋጥሟቸው ወደ ሆስፒታል አቅንተው ሕመማቸው ከባድ በመሆኑ በአምፑላንስ ወደ ጋምቤላ ሄደው ለተሻለ ሕክምና ከጋምቤላ በልዩ አውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ መጥተው በሀሌሉያ ሆስፒታል የሕክምና ድጋፍ ሲደረግላቸው ቢቆይም ከዚህ ዓለም ድካም ጥር 9 አርፈዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰጡት መመሪያ መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ ዕለት ተሰብስቦ የብፁዕነታቸው ሥርዓተ ቀርብር ጥር 16 ቀን 2014 ዓ.ም በታላቁ የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እንዲፈጸም ወስኗል፡፡

በዚሁ መሠረት ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው በዕለቱ ተገኝተው ብፁዕነታቸውን መሸኘት እንደሚችሉና በሥርዓተ ቀብራቸውም ላይ መገኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ኢኦተቤ ቴቪ

@tikvahethiopia
#Somaliland

በሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የሚመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ዛሬ ማለዳ ወደ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ማቅናቱ ተነግሯል።

ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተደረገላቸው ይፋዊ ግብዣ መሰረት ነው ወደኢትዮጵያ እንደሚመጡ የተገለፀው።

በሌላ በኩል ፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢሳ ካይድ የሚመራ የልዑካን ቡድን ከፕሬዜዳንቱ ሙሴ ቢሂ አብዲ ቀደም ብሎ ትላንት አዲስ አበባ ገብቷል። የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ቡድኑን ተቀብለው አነጋግረዋል።

#MFA_Somaliland

@tikvahethiopia
#DStv...ከተማው

የአንድ ክ/ከተማ አስተዳደር ቢሮ ሰራተኞች ከአለቆቻቸውና ወደ ቢሮው ከሚመጡት የተለያዩ የከተማው ነዋሪዎች ጋር የሚያሳልፉት ውጥረት የተሞላበትን ውሎና ገጠመኝ የሚያሳይ አዝናኝ ድራማ (ሲትኮም)

ማክሰኞ ከምሽቱ በ1፡30 በድጋሚ ቅዳሜ ከሰዓት 09:00 ሰዓት እንዲሁም እሁድ ከሰዓት 09:30 በአቦል ቻናል ቁጥር 146

#DStvየራሳችን