TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

የደሴ - ወልዲያ የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና እየተገባደደ ነው።

ፍተሻው በስኬት ከተጠናቀቀ እስከ ወልዲያ ድረስ ያሉት ከተሞች በሰዓታት ውስጥ ኤሌክትሪክ ሊያገኙ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።

ተቋሙ እስከዛሬ ድረስ በተከናወነው ጥገና ጉዳት የደረሰበት መስመርና ምሰሶ ከ97 በመቶ በላይ ተጠናቋል ብሏል።

ቀሪ ሥራዎችን በርብርብ በማጠናቀቅ እስከ ወልዲያ ድረስ ያሉት ከተሞች ማምሻውን አልያም እስከ ነገ እኩለ ቀን ድረስ መብራት እንዲያገኙ ይደረጋል ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Balderas

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአፋር እና አማራ ክልል የሚያደርጉትን ጉዞ ዛሬ ጥር 6 ቀን 2014 ዓ/ም ጀመሩ።

በፓርቲው ፕሬዜዳንት አቶ እስክንድር ነጋ የሚመራው የአመራሮች ቡድን ዛሬ ወደ አፋር ክልል ገብተዋል።

ቡድኑ በአፋር የዛሬ ውሎው ከሰመራ 10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ዱቢቲ ሪፈራል ሆስፒታል በማቅናት በግንባር የተጎዱ የጦር አባላትን ጠይቋል።

ባልደራስ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ የጦር አባላቱ በግንባር ለከፈሉት የህይዎት እና የአካል መስዕዋትነት የተሰማቸውን ታላቅ ክብር በራሳቸውና በድርጅቱ ስም ገልፀው ዕውቅናም እንደሚሰጡት ተናግረዋል።

በአፋር ዱቢቲ ሪፈራል ሆስፒታል በጦርነቱ ሳቢያ የተጎዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣የአፋር ልዩ ኃይል፣ የአፋር ህዝባዊ ሰራዊት እና ሚሊሻ እንዲሁም ቁስለኛ የህወሓት ሰራዊት አባላት እንደሚገኙ ተገልጿል።

አመራሮቹ ከሆስፓታል መልስ በክልሉ መስተዳድር ጥያቄ መሠረት በአፋር ዱፍቲ በአዋሽ ወንዝ እየለማ ያለውን የስንዴ ምርት መጎብኘታቸውን ፓርቲው አሳውቋል።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች በአፋር ጉብኝታቸውን ሲያጠናቅቁ ወደ አማራ ክልል እንደሚያመሩ ይጠበቃል።

ፎቶ ፦ ባልደራስ ፓርቲ

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ጄነራል ባጫ ደበሌ በትግራይ ክልል ተፈፅመዋል ስለተባሉት የአየር ጥቃቶች ለጀርመን ሬድዮ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" የትግራይ ህዝብ ከማንም በላይ ለእኔ ወንድሜ ነው፤ ህዝባችን ነው። ከማንም በላይ የምንሳሳለት እኛ ነን። አየር ኃይል ይሁን፣ እግረኛ ይሁን ፣ መድፈኛ ይሁን ፣ የድሮን ቡድን ይሁን፣ ሁሉም Rules of engagement (ROE) አላቸው ንፁሃን ዜጎችን በአየር የሚደበድብ ማንም እብድ የለም አልተደረገም። " ብለዋል::

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ምን አለ ?

" በትግራይ ክልል በሚፈጸሙ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች ሳቢያ ከ100 በላይ ሰላማዊ ዜጎች መገደልና የንብረት ውድመትን በተመለከተ የደረሱን ሪፓርቶች አሳስቦናል:: ባለፉት ሁለት ሳምንታት ቢያንስ 108 ሰላማዊ ዜጎች ተገድለዋል 75 ሰዎች ቆስለዋል:: " ብሏል::

ያንብቡ : https://telegra.ph/ETHIOPIA-01-14
#AmharaRegion

የአማራ ክልል መንግስት ከፋኖ አደረጃጀት ትጥቅ እንደማያስፈታ አስታወቀ::

" መንግስት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው " የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ ነው ሲል የአማራ ክልል መንግሥት ዛሬ ገልጿል::

የክልሉ መንግሥት ይህን የገለፀው ከፋኖ አደረጃጀት አባላት ጋር በተወያየበት መድረክ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል::

በዚሁ መድረክ : " ፋኖ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሀገርና ሕዝብን እየታደገ ያለ መከታ ኃይል ነው። ስለሆነም የፌደራልም ሆነ የክልል መንግሥት ፋኖን ትጥቅ የማስፈታት ሐሳብ የለውም፤ ሊኖረውም አይችልም " ተብሏል::

በቀጣይ የክልሉ መንግሥት የመሳሪያ አስተዳደር ሥርዓቱን ሊያሻሽል እንደሚችል ተገልጿል።

በውይይት መድረኩ ላይ " ፋኖ በስምም ሆነ በግብሩ የአማራ ሕዝብ ክብር መገለጫ በመሆኑ በፋኖ ስም የሚነግዱ አካላትን ፋኖና መንግሥት በጋራ ይታገላሉ:: ፋኖን ማደራጀትና ማጠናከር የክልሉ መንግሥት አቅጣጫና ተግባር ሆኖ ሳለ ትጥቅ ማስፈታት የሚለው አሉባልታ አማራን የመከፋፈል እርስ በርስ የማጋጨት የማዳከም ሴራ አካል ነው " ተብሏል::

@tikvahethiopia
#Abala

በአፋር ክልል ፣ አብአላ ከተማ በሚሰነዘር የከባድ መሳሪያ ድብደባ የከተማው ነዋሪ ከቄዬው እየተሰደደ መሆኑን የከተማው ከንቲባ ተናገሩ።

ከንቲባው ይህን የተገሩት ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

ከመቐለ ከተማ 40 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው የአፋር የንግድ ከተማ አብአላ ከንቲባ አቶ ጣሂር ሀሰን ህወሓት ተቆጣጥሯቸው ከነበሩት የአፋር እና አማራ ክልሎች እንዲወጣ ከተደረገ በኃላ አብአላ ላይ ተደጋጋሚ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።

የከተማው ከንቲባ ፥ " አሁንም ድረስ አላቋረጠም ንፁሃን መደብደብ ፤ በከባድ መሳሪያ መደብደብ እንስካሁን አላቆመም። በእግረኛም ወረራ እየሞከረ ነው። መጀመሪያውንም እንደሚታወቀው በየአካባቢው የሚያደርገውን ወረራ እና የንፁሃን ጭፍጨፋ ሙከራ ነው ያደረገው ያኔም አልተሳካለትም እስካሁን አላቋረጠም። በከባድ መሳሪያ ንፁሃንን እየደበደበ ነው፤ በእግረኛም እየሞከረ ነው ዘረፋ ለማድረግም እየሞከረ ነው ቢሆንም ግን አልተሳካለትም። ወደላይ ተመልሷል እስካሁን ግን የቆመ ነገር የለም ፤ ከከተማው ራቅ ብሎ ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ነው " ብለዋል።

እየተፈፀመ በሚገኘው ጥቃት ከንፁሃን በተጨማሪ የአምልኮ ቦታዎች ፣ የመንግስት እና የግል ባለሀብቶች ንብረት ላይ ጉዳት መደረሱ ተገልጿል።

የደረሰውን ጉዳት በቁጥር ደረጃ ለመግለፅ ጥናት እየተደረገ መሆኑን የአብአላ ከንቲባ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#USA

አምባሳደር ሳተርፊልድ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።

አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ #ኢትዮጵያን ጨምሮ ሱዳን እና ሳዑዲ አረቢያን እንደሚጎበኙ ተገልጿል።

አምባሳደር ሳተርፊልድ እኤአ ከጥር 17-20 ባሉት ቀናት ነው ሃገራቱን የሚጎበኙት፡፡

በቅድሚያ ወደ ሪያድ እንደሚጓዙ የሚጠበቁት ልዩ መልዕክተኛው ቀጥሎ ካርቱምንና አዲስ አበባን ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ረዳት ጸሃፊ ሞሊ ፊ አብረዋቸው ወደ ሃገራቱ እንደሚጓዙ ተገልጿል።

አምባሳደር ሳተርፊልድ በሪያድ ቆይታቸው በሱዳን ያለውን ወታደራዊ አገዛዝ እንዲያበቃ የሚጠይቁትን የለውጥ ኃይሎችን እንደሚያገኙና በመንግስታቱ ድርጅት አመቻችነት ለማካሄድ ስለታሰበው ሃገራዊ ውይይት እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል፡፡

ወደ ካርቱም ተጉዘው ከተለያዩ የለውጥና የዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር እንዲሁም ከወጣት አደረጃጀቶች ጋር ይወያያሉ፡፡

በኢትዮጵያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

መንግስት የተገኘውን የሰላም ጭላንጭል እንዲያጠናክር፣ የአየር ጥቃቶችን እንዲያቆም እና ሌሎችም መቃቃሮች እንዲያበቁ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገሩም ነው የተገለጸው፡፡

ተኩስ እንዲቆም፣ እስረኞች አሁንም እንዲለቀቁና ሰብዓዊ እርዳታዎች ሳይስተጓጎሉ እንዲቀርቡ ይጠይቃሉ ተብሏል፡፡

መረጃውን #አል_ዓይን_ኒውስ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ነው በድረገፁ ላይ ያስነበበው።

@tikvahethiopia
" ግጭቱ በባህላዊ እርቅ ተቋጭቷል "

በምስራቅ መስቃን ቤተ ጉራጌና ማረቆ የሰላም ጉባኤ በጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ ኢንሴኖ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።

በምስራቅ መስቃን ቤተ ጉራጌና ማረቆ መካከል ተፈጥሮ የነበረው ግጭት በባህላዊ እርቅ ተቋጭቷል።

የእርቅ ስነ-ስርዓቱ ግጭቱ በተከሰተበት ቦታ ኢንሴኖ የተካሄደ ሲሆን የክልልና የዞን አመራሮች የአገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል፡፡

ግጭቱ የተነሳው ከአከላለል ጋር በተያያዘ ሲሆን ከግጭቱ ለማትረፍ ፍላጎት ያላቸው አካላት እንዲባባስ ያደረጉ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በዚህም የሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ዜጎችም ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል።

ግጭቱም የግብርና እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና ፈጥሮ መቆየቱ ነው የተገለጸው፡፡

ሁለቱ ወገኖች ልዮነታቸውን በባህላዊ የዕርቅ መንገድ መፍታታቸውን ተከትሎ የእርቅ ጉባኤ በጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን መረዳ ኢንሴኖ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

#ENA

@tikvahethiopia
#ሹመት

ከጥር 3/2014 ጀምሮ ለኢትዮጵያ ኢንተርፕራዝ ልማት አዲስ አመራሮች ተሹመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፤ አቶ ብሩ ወልዴን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አድርገው የሾሙ ሲሆን አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ደግሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋቸዋል።

@tikvahethiopia
AFCON 🏆 ግጥሚያው ተጧጥፏል!

የዛሬ ጨዋታዎች

⚽️ ጋቦን VS ጋና ከምሽቱ 4:45 ሰዓት

ሁሉንም ጨዋታዎች በላቀ ጥራት በቀጥታ SS AFCON ቻናል 222 ይመልከቱ!

ሁሉንም ጨዋታዎች ከጎጆ (አክሰስ) ፓኬጅ ጀምሮ በሁሉም የዲኤስቲቪ ፖኬጆች ላይ ያገኙታል!

ፈጥነው ዲኮደሩን ይግዙ! ግምትዎን ያጋሩን!

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ 699 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ፡፡

የዲኤስቲቪ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ👇
https://bit.ly/2WDuBLk