TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GERD

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ምክትል ጠ/ሚና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የታላቁ ህዳሴ ግድብን የግንባታ ሂደት ጎበኙ፡፡

በጉብኝት መርሀ ግብሩ የተለያዩ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል፡፡

የሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የ100 ቀናት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በህዳሴ ግድብ መገኛ በሆነችው ጉባ እየተካሄደ ነው፡፡

Credit : FBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara በአማራ ክልል የሰዓት እላፊ ገደብ ላይ ማሻሻያ ተደረገ። የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃለፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የክልሉ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ በተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ መወሰኑን ተናግረዋል። ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ጠዋት 12 ሰዓት የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ በክልሉ…
#Update

የአማራ ክልል መንግሥት አስተዳደር ም/ቤት ከአሁን ቀደም የሰዓት እላፊ ገደብ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡30 መንቀሳቀስ እንደማይቻል ውሳኔ በማሳለፍ በክልሉ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ እንደገለጹት ከአሁን ቀደም ተጥሎ የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ ሙሉ ኃላፊነት ለከተማ አስተዳደሮች በመስጠት የፀጥታ ሁኔታውን እየገመገሙ በራሳቸው ሰዓት እላፊ ገደቡን የማንሳትም ሆነ የማስቀጠል ሙሉ ኃላፊነት ከተጠያቂነት ጋር የተሰጣቸው መሆኑን የክልሉ መንግሥት አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

አስተዳደር ምክር ቤቱ አሁን ያለውን ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው የሰዓት እላፊ ገደቡን በተመለከተ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ሲሉ አቶ ግዛቸው መናገራቸውን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 👉 10,758
• ቫይረሱ የተገኘባቸው 👉 3,779
• ህይወታቸው ያለፈ 👉 7
• ከበሽታው ያገገሙ 👉 1,080

በአሁን ሰዓት 413 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EXCLUSIVE አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በዚህ ወር ከኃላፊነታቸው ይለቃሉ ተብሏል። ነገ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ የሚጠበቁት በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከሃላፊነታቸው ሊለቁ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ሮይተርስ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከ9 ወራት የስልጣን ቆይታ በኋላ በዚህ ወር ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ መስማቱን ገልጿል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር…
የአምባሳደር ፌልትማን ጉዞ ተሰርዟል ?

ሮይተርስ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በተያዘው ወር መጨረሻ ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ ዘግቧል (የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያለው ነገር ባይኖርም) ።

ይህ የተሰማው ትላንት ለሊት ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ እና ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሰላም ድርድር ጉዳይ እንደሚነጋገሩ ከተሰማ ከሰዓታት በኃላ ነው።

ምንም እንኳን አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በዚህ ወር ከኃላፊነት እንደሚለቁ ቢገለፅም የሀሙስ የኢትዮጵያ ጉዟቸው እንደተጠበቀ መሆኑን ለመስማት ተችሏል።

አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በዚህ ወር ከኃላፊነታቸው ሲለቁ ይተኳቸዋል የተባሉት በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደርነት ጊዜያቸውን የጨረሱት አምባሳደር ዴቪድ ሰተርፊልድ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የአምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት በተመለከተ ምን አሉ ?

ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፦

" የፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት አዲስ ጉዳይ አዲስ ነገር ይዞ ይኖራል ወይ የሚለው የሚመጡት እሳቸው ስለሆኑ የሚመጡበትን አጀንዳ ይዘው ሲመጡ ወቅቱም የገና በዓል ነው ከበዓሉም ጋር አስተሳስረን እንቀበላቸዋለን።

በፍቅር መቀበል ኢትዮጵያዊ ባህል ነው።

ስለዚህ አዲስ ነገር ይዘው መጡ አዲስ ነገር ይዘውም አልመጡ ያው ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የረጅም ጊዜ የታሪክ ግንኙነት ባለቤቶች ናቸው የትኛውንም ሀሳብ ይዘው ከመጡ ኢትዮጵያን የሚጠቅም እስከሆነ ድረስ ፤ ህዝቦቿን የሚጠቅም እስከሆነ ድረስ ኢትዮጵያ ትቀበላለች።

የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ፣ የኢትዮጵያን ህብረ ብሄራዊ አንድነት ፣ የኢትዮጵያን ልማት ኢትዮጵያን አለማቀፋዊ ተሳትፎ ፣ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፋዊ ተሰሚነት የሚገዳደር ከየትኛውም ወገን ይምጣ ከየት ኢትዮጵያ አትቀበልም።

ስለዚህ የፌልትማን መምጣት በዚህ አቅጣጫ መሰረት የሚፈፀም እና የሚመራ ይሆናል። "

@tikvahethiopia
#GeezWatches

🎁 እነሆ የገና ስጦታ አንድ ግዕዝ ሰዓት ሲገዙ ፤ ተጨማሪ አንድ ማሰሪያ በነፃ።🎁

የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀላሉ 👇
https://t.iss.one/geezwatches

@GeezWatchesjewelryBot

አድራሻችን መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድሞል 2ተኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር 239። ለበለጠ መርጃ 0929157545 /0946663939 ይደውሉልን በየአሉበት ቦታ እናደርሳለን ።
#MedStore

Medsstore.et የህክምና እቃ አስመጪ እና አቅራቢ ነዎት?

እንግዲያዉስ አብረዉን ይስሩ በዲጂታል መድረካችን አማካኝነት ተደራሽነትዎን ያስፉ፡፡

አሰራርዎን ያዘምኑ ከጊዘው ጋር ይራመዱ፡፡

ድህረ ገጻችን https://medstore.et/

Join and Follow
Telegram Linkedin Facebook Twitter
#UPDATE😷

የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ ፦

🇫🇷 ፈረንሣይ ሀገር በኮቪድ-19 የተያዙ ነገር ግን ጥቂት ወይም ምንም ምልክት የሌላቸው የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውን ከማግለል ይልቅ ህመምተኞችን ማከም እንዲቀጥሉ ፈቅዳለች። ውሳኔን የሰራተኞችን እጥረት ለመቅረብ የተወሰደ ነው። በፈረንሳይ የኮቪድ ወረርሽኝ ክፉኛ እየተስፋፋ ነው።

🇳🇱 ኦሚክሮን ዝርዘ በዋነኝነት እየተስፋፋ ነው በተባለበት ኔዘርላንድስ በአንድ ቀን ብቻ ሪከርድ ነው የተባለ 24,500 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።

🇸🇪 የስዊድን ጤና ባለስልጣናት ከሚቀጥለው ሳምንት አንስቶ ምግብ ቤቶች ፣ የባህል ቦታዎች እና የመዝናኛ ማዕከላት ደንበኞቻቸው የኮሮና ቫይረስ ክትባት መከተባቸውን የሚያረጋግጥ ዲጂታል ማረጋገጫ እንዲያሳዩ እንዲያደርጉ መክረዋል።

🇯🇵 የቶኪዮ ባለስልጣናት በከተማው እየተስፋፋ ከመጣው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ የጃፓን መንግስት የአደጋ ጊዜ እርምጃዎችን እንዲመልስ ሊጠይቁ ይችላሉ ተብሏል። ከእርምጃዎቹ መካከል በባር እና ሬስቶራንቶች የስራ ሰዓት ላይ የሚጣል ገደብ የሚጨምር ነው። ከተማይቱ 6ኛ ዙር ማርበል ሳያጋጥማት አልቀረም ተብሏል።

🇮🇱 እስራኤል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ አስመዝግባ የማታውቀውን ከፍተኛ ኬዝ አስመዝግባለች። በሀገሪቱ በአንድ ቀን 11,978 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

🇨🇳 በቻይና ዢያን ከተማ በእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት የምግብ እጥረት ስጋት በመፈጠሩ ነዋሪዎች ንብረታቸውን በምግብ እየቀየሩ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል። በማኅበራዊ ሚዲያ በተለቀቁ መረጃዎች የአካባቢው ነዋሪዎች ሲጋራዎችን እና የቴክኖሎጂ መገልገያዎችን በምግብ ሲቀይሩ ታይተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ የተመራውን ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ዛሬ ተቀብለው አነጋግረዋል። ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ቻይና ባለፉት 100 ዓመታት በCPC መሪነት ያስመዘገበችውን ትልቅ እድገት አድንቀዋል። ዓለም አቀፍ ህግን በማክበር ላይ የተመሰረተ ሚዛናዊ የሆነ አለም አቀፋዊ ስርዓት እንዲመጣ ቻይና ላበረከተችው ጉልህ ሚናም አመስግነዋል። ፕሬዜዳንት…
ዋንግ ዪ ኬንያ ይገኛሉ።

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ትላንት የኤርትራ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ኬንያ ሄደዋል።

በኬንያ የሁለት ቀን ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን ትላንት ሞምባሳ ኤርፖርት ሲደርሱ የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪይቼል ኦማሞ ተቀብለዋቸዋል።

የዋንግ ዪ ጉብኝት በኬንያ እና በቻይና መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ስትራቴጂያዊ ትብብር ስምምነቶችን በመፈረም የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እድል ይሰጣል ተብሏል።

@tikvahethiopia
አሜሪካ ?

እዚሁ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከዚህ ቀደም ከፀጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ ከ15 ጊዜ በላይ ዜጎቹ ሀገር ለቀው እንዲወጡ ሲወተውት ነበር።

ኤምባሲው አሁንም በዚሁ ጥሪው የቀጠለ ሲሆን ዛሬም " በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ እና የደህንነት ሁኔታ አሳሳቢ ነው ያለምንም ማስጠንቀቂያ ሊበላሽ ይችላል " በማለት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሀገር ለቀው እንዲወጡ አሳስቧል።

ይህ የኤምባሲው መልዕክት እንደሁል ጊዜው እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ያስቆጣ ሲሆን የኤምባሲው ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ አስተያየት መስጫ የአሜሪካን ድርጊት በሚያወግዙ መልዕክቶች ተሞልቷል።

አሜሪካ ዜጎቼ ውጡ እያለች ባለችበት በዚህ ጊዜ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን / የአሜሪካ ዜግነትም ያላቸው የሌሎችም ሀገራት ዜጎች ለበዓል ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ይገኛሉ።

የ " ደህንነት ሁኔታ አሳሳቢ ነው " በሚል ዜጎቼ ውጡ እያለች የምትወተውተው አሜሪካ በአንድ በኩል ደግሞ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋን ከፍተኛ የስራ ኃላፊ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማንን ዛሬ ወደኢትዮጵያ እንደምትልካቸው ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የአሜሪካ ኤምባሲ ሆነ ሌሎች በኢትዮጵያ ጉዳይ ሀሰተኛ መረጃ ከማሰራጨት እንዲታቀቡ ፤ ደህንነት አልተሰማንም ካሉም / ለሰራተኞቻቸው ምቹ ሁኔታ የለም ካሉ በየትኛውም ጊዜ መውጣት መብታቸው እንደሆነ ፤ ኢትዮጵያ ግን ሰላሟን፣ ደህንነቷን ይዛ እንደምትቀጥል የኤምባሲዎች መኖር የኢትዮጵያን ደህንነት እንደማያረጋግጥ ማሳወቋ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#SUDAN

ሌ/ጄኔራል አብዱል ፋታህ አል-ቡርሃን ሚመሩት የሱዳን ጦር ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ሳያሳትፍ ለሱዳን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሾም እንደማይደግፉ አሜሪካ ፣ ብሪታኒያ፣ ኖርዌይ እና የአውሮፓ ህብረት አስጠንቅቀዋል።

በሱዳን ወታደራዊ ኃይሉ ላይ አሁንም ተቃውሞ እና የሚደርስበት ጫና ቀጥሏል።

የሱዳን ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ከቀናት በፊት በገዛ ፍቃዳቸው ከስልጣን መልቀቃቸው ይታወሳል። ይህን ተከትክሎ የሱዳን መንግስት ሙሉ ለሙሉ በጦር ሰራዊቱ ቁጥጥር ስር እንዲገባ ያደርገዋል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA❤️

ሀገራችን ኢትዮጵያ🇪🇹የፊታችን እሁድ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ታደርጋለች።

ኢትዮጵያችን በመጀመሪያው ጨዋታ ከኬፕ ቨርዴ ጋር የምትፋለም ይሆናል።

ይህ ጨዋታ በ " ኦሌምቤ ስታዲየም " የሚካሄድ ሲሆን የመክፈቻ ስነ-ስርዓቱን በደማቅ ሁኔታ ለማካሄድ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የሀገራችን ልጆች ለዚሁ ትልቅ ውድድር ቀደም ብለው ካሜሮን ገብተው ጠንካራ ልምምድ እና ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።

ለአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን የሚገኙት የቲክቫህ ስፖርት አባላት በፎቶ እና በቪድዮ የተደገፉ መልዕክቶችን በ @tikvahethsport በኩል ይልኩላችኃል።

https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia