#SouthSudan
ደቡብ ሱዳን ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን /ኢጋድ/ አባልነት ታግዳለች።
ኢጋድ ከአባልነት ያገዳት በየዓመቱ ለተቋሙ መክፈል የሚጠበቅባትን መዋጮ ባለመክፈሏ ነው።
የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ፣ የመገናኛ እና የፖስታ አገልግሎት ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዌ ሀገራቸው በተባለው ምክንያት ከኢጋድ መታገዷ አረጋግጠዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ማይክ አዪ ድንግ በካቢኔ ስብሰባው ላይ ለኢጋድ መዋጮ ሚሆን ገንዘብ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል።
ካቢኔው ከመከረ በኋላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአዲሱ የገንዘብ ሚኒስትር ጋር እንዲወያዩበት መወሰኑን ገልፀዋል።
ይህም ሁሉንም ውዝፍ ለመክፈል የሚያስችል መንገድ የሚያመቻች ነው ብለዋል።
ምንጭ፦ አልዓይን / ሲጂቲኤን
@tikvahethiopia

#Waghimra
የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በዚህ ሳምንት በአማራ ክልል ዋግህምራ ዞን ሳሃላ ሰየምት ወረዳ በግጭት ለተጎዱ ከ6,000 በላይ ሰዎች ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉ ሩዝ፣ ሽንብራ፣ የምግብ ዘይት እና የማዕድ ጨውን ያካተተ የምግብ ድጋፍ ነው።
የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ባሳለፍነው ወር በዚሁ አካባቢ ለሚገኘው ማህበረሰብ የመጠለያ እና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
#ICRC
@tikvahethiopoa

📞30 ሺህ ነፃ የስልክ ጥሪ !
በትግራይ ክልል ሽሬ የሚገኘው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ቡድን በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ለተነጣጠሉ ሰዎች ከ30,000 በላይ ነጻ የስልክ ጥሪ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡
ፍሬወይኒ እና አራት ልጆቿ ከብዙ ወራት ቆይታ በኋላ በቀይ መስቀል የስልክ አገልግሎት በኩል ከባለቤቷ ጋር መገናኘት በመቻላቸው በጣም ተደስተዋል፡፡

ወደሀገር ቤት ለምትመጡ ፦
ከሰሞኑን የጉምሩክ ኮሚሽን የግል መገልገያ እቃዎችን በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ማስገባት እንደማይቻልና ይህን በሚያደርጉት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ማሳወቁ ይታወቃል።
ውሳኔው የአንድ ሚሊዮን ዳያስፖራ ወደሀገር እንዲገባ የቀረበው ጥሪ ተቀብለው ወደሀገር የሚገቡትን አይመልከትም።
ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለህክምና ተቋማት፣ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረጉ ድጋፎችን እና የግል መገልገያ እቃዎችን ይዘው የሚመጡ ዲያስፖራዎችን እርምጃው እንደማይማልከታቸው ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ኮሚሽኑ ቀልጣፋ አግልግሎት እና ልዩ መስተንግዶ ለመስጠት የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱንም ለማወቅ ችለናል።

#Update
ማምሻውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ይፋ ባደረገው መግለጫ ፥ የኢትዮጵያ ጥምር የፀጥታ ኃይሎች ፦
- በምሥራቅ ግንባር ስትራቴጂያዊ የሆኑትን የዞብል ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የአርጆ፣ ፎኪሳ እና ቦረን ከተሞችን ተቆጣጥሯል፡፡ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን በመቆጣጠር የወልድያ መቐለ ዋናውን አውራ ጎዳና ቆርጦታል። በዚሁ ግንባር የድሬ ሮቃና የሶዶማ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ከተሞችና ተራሮች በመቆጣጠር ወደ ሐራ ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል፡፡
- በውጫሌ ግንባር በኩል ደግሞ የአምባሰል ከፍተኛ ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ የሮቢትና የጎልቦን፣ በወረባቦ ወረዳ የሚሌ ኮትቻን፣ በሐብሩ ወረዳ የኮልቦን፣ የመርካታና የፋጂን አካባቢዎችን በመቆጣጣር ወደ መርሳ ከተማ እየገሠገሠ ነው፡፡
* የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ደሴ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኘች። ደሴ ዛሬ ማታ 4:30 ላይ ኤሌክትሪክ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል። @tikvahethiopia
#Update
ባቲ ፣ አቀስታ ፣ መሀል ሳይንት እና ሳይንት አጅባር ከተሞች ኤሌክትሪክ አገኝተዋል።
ዛሬ ጠዋት ላይ ማጀቴ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘቷን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያሳል።
በደሴ ዲስትሪክት ስር አገልግሎት የሚያገኙት ኮምቦልቻ ፣ ደሴ፣ ከሚሴ እንዲሁም ጨፋ ሮቢት ከተሞች ኤሌክትሪክ ማግኘታቸው መገለፁ ይታወሳል።

የአሜሪካ ማዕቀብ እና የቻይና ምላሽ...
አሜሪካ ከቻይና፣ ማያንማር፣ ሰሜን ኮሪያና ባንግላድሽ ጋር ግንኙነት ያላቸው በርካታ ባለስልጣናትና ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ ጣለች።
በቻይና ዢንጂያንግ ግዛት በሰብአዊ መብት ረገጣ 2 ታዋቂ ፖለቲከኞች እና አንድ ኩባንያ ላይ ማዕቀብ መጣሉን የአሜሪካ ግምጃ ቤት አስታውቋል።
ማዕቀብ የተጣለበት የቻይና ኩባንያ ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ የአንድን ሰው ፊት አይቶ ብሄር መለየት የሚችል ፈጠራ ሰርቷል በሚል ማዕቀብ ተጥሎበታል።
ኩባንያው ግን ወቀሳውን አጣጥሏል። ዋሽንግተን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ " አሜሪካ በቻይና የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ገብታለች እንዲሁም የአለም አቀፍ ግንኙነት መሰረታዊ ደንቦችን ጥሳለች " ሲል ወቅሷል።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ኃላፊ ሚኒስትር ዋሊ አዴዬሞ ካናዳ እና ብሪታንያ ማያንማር ውስጥ የሚፈፀምን የሰብአዊ መብት ረገጣ እንደሚቃወሙ እና የአሜሪካን ማዕቀብ እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።
በጆ ባይደን አስተዳደር ዋሽንግተን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰሜን ኮርያ ላይ ማዕቀብ የጣለች ሲሆን በማያንማር ወታደራዊ ተቋማት ላይ ክትትል እንደምታደርግ ማስታወቋን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

" በሚቀጥሉት 3 ወራት ዕጣ የወጣባቸውን 68 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች ለማስረከብ እየሰራን ነው " - የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን በሚቀጥሉት 3 ወራት ዕጣ የወጣባቸውን 68 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች ለማስረከብ እየሰራ መሆኑን ለኢዜአ ገልጿል። ኮርፖሬሽኑ ዕጣ ወጥቶባቸው ወደ ባለዕድለኞች ያልተላለፉ 68 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በቀጣይ 3 ወራት…
" የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን በሚቀጥለው ወር ለማስረከብ እየሰራሁ ነው " - የአ/አ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሶስት ዓመት በፊት በተካሄደው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የወጣላቸውና በተለያዩ ምክንያቶች የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባለቤት የሆኑ ነዋሪዎችን ቤት በሚቀጥለው ወር ሙሉ ለሙሉ ለማስረከብ እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡
በሚቀጥለው ወር ወደ ቤታቸው ይገባሉ የተባሉት ከ63 ሺ በላይ የቤት ባለቤቶች ሲሆኑ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በ16 ሳይቶች የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አውራሪስ ከበደ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል፥ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ላይ ቅድመ ርክክብ ቢደረግም፣ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ባለመጠናቀቃቸው የቤት ባለቤቶች ሙሉ ለሙሉ ተረክበውና አፅድተው አለመግባታቸውን አስታውቀዋል፡፡
እነዚህ የቤት ባለቤቶች በ13ተኛው ዙር የ20/80 ዕጣ፣ በሁለተኛው ዙር የ40/80 ዕጣ፣ እንዲሁም እንደ የልማት ተነሺነት ባሉ ልዩ ልዩ ምክንያቶች የቤት ባለቤት የሆኑ ናቸው፡፡
አቶ አውራሪስ፥ የቤት ባለቤት ከሆኑት ውስጥ እያፀዱ ያሉና መኖር የጀመሩ እንዳሉ ተናግረው ፤ ብዙዎቹ ግን ቤታቸውን ሙሉ ለሙሉ አለመረከባቸውን አስታውቀዋል፡፡
ነዋሪዎቹ ቤቶቹን ላለመረከባቸው ምክንያት የሆነው ቤቶቹ ሙሉ ለሙሉ ተገንብተው አለማለቃቸው ብቻ ሳይሆን እንደ ውኃ፣ መብራትና መንገድ ያሉ የመሠረተ ልማት አቅርቦቶች አለመዘርጋታቸው እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
እነዚህን ቀሪ ሥራዎች አጠናቆ ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲገቡ ማድረግ በኮርፖሬሽኑ የ100 ቀናት ዕቅድ ውስጥ ያለ መሆኑ ያስረዱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ 100 ቀናት የሚጠናቀቀው ጥር 10 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሆነ መግለፃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

#HappeningNow
" አዲስ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ትውልድ "
ሴንተር ፎር አድቫንስመንት ኦፍ ራይትስ ኤንድ ዴሞክራሲ (ካርድ) “የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አዲስ ትውልድ’’ በሚል ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል።
ዛሬ የሚመረቁት 364 የሚሆኑ የመንግሥትና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ፅንሰ ሐሳቦችን፣ የሥርዓተ ፆታ እኩልነት፣ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲሁም የመሰብሰብና የመደራጀት መብቶች ላይ ሥልጠናዎችን ወስደነዋል።
በዛሬው ዕለት በኢንትር ላግዠሪ ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የሰብዓዊ መብት ፌስቲቫል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱኳን ሚዴቅሳ ተገኝተዋል።
መርኃግብሩን የካርድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር በፍቃዱ ኃይሉ በንግግር ከፍተዋል።
🔴 Live : https://fb.watch/9Rmjulyc8J/

ቱርክ ለሶማሊያ የድሮን ድጋፍ አደረገች።
ቱርክ ለሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የወታደራዊ መሳሪያ መለገሷን ጋሮዌ ዘግቧል።
ቱርክ ያደረገችው የሰው አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮን ድጋፍ ሲሆን ድሮኖቹ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ለሀገሪቱ መሰጠታቸው ተሰምቷል።
ዶሮኖቹ የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ለአፍሪካ ቀንድ ትልቅ ስጋት የሆኑትን የአልሸባብ ታጣቂዎችን ለመዋጋት ይጠቅማሉ ተብሏል።
ቱርክ ላለፉት በርካታ አመታት የሶማሊያን ጦር ስታሰለጥን እና ስታስታጥቅ ቆይታለች ፤ አሁንም ለሀገሪቱ ጦር ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች።

#WFP
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ያቋረጠውን ድጋፍ ከቀናት በኃላ እንደሚጀመር አሳውቋል።
ድርጅቱ በአማራ ክልል የነፍስ አድን ምግብ እርዳታ ማድረግ መቀጠሉን ገልጿል።
በሰ/ጎንደር 470,000 ሰዎች በደሴ/ኮምቦልቻ 172,000 ሰዎች በJEOP በኩል መድረሱን አሳውቋል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፤ በዘረፋ እና በደህንነት ማጣት ምክንያት ባለፈው ሳምንት አቋርጦት የነበረውን ድጋፍ በሚቀጥሉት ቀናት ለመቀጠል ተስፋ እንደሚያድረግ ገልጿል።

" ከደቡብ ሱዳን በኩል የሚመጣ ኢትዮጵያን ለመጉዳት ያለመ እንቅስቃሴ አሁንም ሆነ ወደፊት አይኖርም " - ዶ/ር ሪያክ ማቻር
በደቡብ ሱዳን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደር ነቢል መህዲ ከደቡብ የሱዳንን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሪያክ ማቻር ጋር በሁለቱ ሀገራት በጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ዶ/ር ሪያክ ማቻር በኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን እና መካከል ያለውን ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ ግንኙነት አውስተው የደ/ሱዳን ህዝብ በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ የኢትዮጵያ መንግስታት ለሰጡት ያልተቋረጠ ድጋፍ ምስጋናው ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለው ለኢትዮጵያ ሰላም መስፈን ሀገራቸው ቁርጠኛ አቋም እንዳላት ጠቁመው፣ ከደቡብ ሱዳን በኩል የሚመጣ ኢትዮጵያን ለመጉዳት ያለመ እንቅስቃሴ አሁንም ሆነ ወደፊት እንደማኖር ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።
አምባሳደር ነቢል መህዲ በበኩላቸው ፥ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ በተለይ የህወሃት ወራሪ ሀይል በደረሰበት ምት ከያዛቸው ቦታዎች እየወጣ እንደሆነ ፤ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ለማድረስ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲሁም የህወሃት ወራሪ ሀይል ይዟቸው በነበሩ ቦታዎች የፈጸማቸውን አሰቃቂ ጭፍጨፋን በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
አንዳንድ የምዕራባውያን የመገናኛ ብዙሃን ሀሰተኛ ዘገባዎች በማሰራጨት የአገሪቱ እና የአመራሩን ገጽታ ለማጠልሸት የጀመሩትን ስራ እየገፉበት እንደሆነ አምባሳደር ነቢል ማብራራታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በኮቪድ-19 ሳቢያ የሰው ሞት አልተመዘገበም።
ከተደረገው 3,452 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 115 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።