TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የደንበኞች ትምህርት ቡድን አባል አቶ ምትኩ አበባዉ ለኢትዮጵያ ቼክ ከተናገሩት ፦ - ደብዳቤዎቹ ከኛ ነዉ የወጡት፤ ትክክለኛ ናቸዉ። - የክልከላው ምክንያት ለንግድ ማይዉሉ የግል መገልገያ ዕቃዎችን ዝርዝር ለመወሰን የወጣዉን መመሪያ 51/2010ን በመጠቀም በተመላላሽ መንገደኞች ከቀረጥ ነጻ የሚገቡ ነገር ግን ለንግድ አላማ እየዋሉ የሚገኙ ዕቃዎች…
" የሰሞኑ የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ መመሪያ ለዳያስፖራው ከቀረበው ጥሪ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።
ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፥ " ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ያወጣውን መመሪያ በተመለከተ ከዳያስፖራው የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሉ ፤ብዥታው የተፈጠረው መመሪያው የወጣበት ጊዜና ለዳያስፖራው የቀረበው ጥሪ በመገጣጠሙ ነው " ብለዋል።
ሚኒስትሩ መመሪያው ለዳያስፖራው ከቀረበው ጥሪ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም ሲሉ አሳውቀዋል።
መመሪያው የሚመለከተው ተመላላሽ ነጋዴዎችን ብቻ መሆኑን ሁሉም የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ሊገነዘብ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በቀረበው ጥሪ መሠረት ለሀገሩ አጋርነቱን ለመግለጽ ዳያስፖራው ሲመጣ አሠራሩን ቀላል አድርጎ ለመጠበቅ ከተዘጋጁት ተቋማት አንዱ የጉምሩክ መሥሪያ ቤት መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ለገሰ ፥ " የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክም በቅርቡ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ይሰጥበታል " ብለዋል።
በዛሬው መግለጫ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦችን በዚህ ያንብቡ : https://telegra.ph/FDRE-Government-Communication-12-09
@tikvahethiopia

#Update
እስከ ከሜሴ ያለው መስመር ጥገና ተጠናቋል።
ከካራቆሬ - ከሜሴ ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮቹንና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ከሥርጭት ኔትወርክ መስመሮች ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ በርብርብ ሲሰራ ቆይቶ ዛሬ እስከ ከሚሴ ድረስ ያሉት ከተሞች ኃይል ማግኘት ችለዋል፡፡
ከደብረብርሃን ኮምቦልቻ ድረስ ያሉት ከተሞች በ132 እና በ230 ኪሎ ቮልት መስመሮች ኃይል ያገኙ የነበረ ቢሆንም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ይሁንና የኃይል ተጠቃሚው ህብረተሰብ በፍጥነት ኃይል እንዲያገኝ ለማድረግ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር ለጊዜው በማቆየትና ባለ 132 ኪሎ ቮልት መስመሩን በአስቸኳይ በመጠገን ዛሬ እስከ ከሚሴ ድረስ ያሉት ከተሞች ኃይል አግኝተዋል።
የጥገና ሥራው ወደ ደሴ ከተማ ቀጥሎ እስከ ሀርቡ ባለው አካባቢ መስመሮችን የመጠገን ሥራም እየተካሄደ ነው።
አሁን አስቸኳይ ጥገና እየተደረገለት ያለው 132 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የከሚሴ፣ ኮምቦልቻ እና ደሴ እንዲሁም ዓለም ከተማና በምዕራብ አፋር የሚገኙ ከተሞችን ኃይል እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው፡፡
በተያያዘ ዜና በሚሌ ባቲ ያለው መስመር ላይ 2 ኃይል ተሸካሚ ምሶሶዎች በከባድ መሳሪያ በመመታቸውና ጉዳቱ ከባድ በመሆኑ ምሶሶዎቹን እንደገና የመትከል ስራ ተጀምሯል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

#BREAKING ብሔራዊ ባንክ የብድር ክልከላውን ሙሉ በሙሉ አነሳ። ለባለፉት አራት ወራት ተግባራዊ የነበረው የብድር ክልከላ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ አስታወቀ። ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ብድር አገልግሎት ለሁሉም ደንበኞቻቸው እንዲሰጡ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ክልከላው የተጣለው "የኢኮኖሚ አሻጥርን" ለመከላከል እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ተግባራዊ ተድርጎ…
" ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር እሰጣለሁ " - ንግድ ባንክ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተያዘው በጀት ዓመት ለግሉ ዘርፍ፣ ለግብርና ግብዓትና ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን አሳውቋል።
ከዚሁ ገንዘብ ውስጥ 25 ቢሊዮን ብር ለግሉ ዘርፍ፣ 30 ቢሊዮን ብር ለግብርና ግብዓት ሲሆን ቀሪው ለመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚውል ነው።
ገንዘቡ ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ሁኔታ ያነቃቃል፤ ለስራ ፈጠራ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል።
መንግስት አስቀምጦት የነበረው የብድር ክልከላ መነሳት የአገሪቷን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው ተነግሯል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በደብረ ብርሃን ከተማ ተቋርጦ የነበረው የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ እና ታክሲ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ከነገ ታህሳስ 01/2014 ዓ.ም እንዲጀምር ኮማንድ ፖስቱ ወስኗል።
ምንጭ፦ የሰሜን ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን

ከታህሳስ 2 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አፋር ክልል መዲና ሰመራ እለታዊ የበረራ አገልግሎት እንደሚኖረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

ወደሀገር ቤት ለምትመጡ፦
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንግዶቹን ለመቀበል የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል አሳውቀዋል።
በዚሁ መሰረት፦
• የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ የታደሰ ሆነ የአገልግሎት ግዜው ያለፈበት፣በልዩ ሁኔታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ያለ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ መግባት ትችላላችሁ፤ የታደሰም ሆነ ግዜው ያለፈበትን መታወቂያ ኤርፖርት በኢሚግሬሽን ካውንተር ላይ ስለምትጠየቁ በእጅዎ መያዞትን አይዘንጉ።
• የሌላ አገር ፓስፖርት የያዛችሁና የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ አገልግሎት ለማግኘት የምትፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና በውጭ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን የፓስፖርት እድሳት አገልግሎት ከፈለጋችሁ አስፈላጊ ሰነዶችን በማዘጋጀት www.digitalinvea.com/ ድህረ ገጽ ላይ ማመልከት የምትችሉ ሲሆን ተቋሙ በተለየ መልኩ ከ15 ቀን ባልበለጠ ግዜ ውስጥ እናንተ በሞላችሁት አድራሻ ድረስ በመላክ አገልግሎት ይሰጣል።
• ከዚህ በፊት የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ያሌላችሁ ደንበኞች የቪዛ አገልግሎት ለማግኘት በ www.evisa.gov.et ድህረ ገጽ ላይ ማመልከት የምትችሉ ሲሆን፣በሂደቱ ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግሮች [email protected] በሚል የኢሜል አድራሻችን ላይ ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ።
• ጥሪ በተደረገበት የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ሀገር ቤት ለምትገቡ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የመዳረሻ ቪዛ/on arrival visa/ አገልግሎት የምንሰጥ ሲሆን፣ ኤርፖርት ላይ የሚቆዩትን ግዜና ድካም ለመቀነስ በኦንላይን ላይ ቀድሞ ቢያመለክቱ ይበረታታል።

#ሪፖርት : Human Rights Watch !
ሂዩማን ራይትስ ዋች የህወሓት ኃይሎች በአማራ ክልል #ጭና እና #ቆቦ በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን በጅምላ መግደላቸውን ይፋ አደረገ።
በሁለቱ ስፍራዎች ግድያው የተፈጸፀመው ከነሐሴ 25 - ጳጉሜ 04/2013 ዓ.ም. በነበሩት 10 ቀናት ውስጥ ነው።
መጀመሪያ የህወሓት ኃይሎች ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም ጭና ወደተባለችው መንደር በመግባት ከፌደራል ሠራዊትና ከአማራ ኃይሎች ጋር ውጊያ ካካሄዱ በኋላ ቦታውን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት በነበሩ 5 ቀናት በ15 የተለያዩ ስፈራዎች 26 ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል።
በተመሳሳይ በቆቦ ከተማ ጳጉሜ 04/2013 ዓ.ም በ4 የተለያዩ ስፍራዎች ላይ 23 ሰዎችን እንደገደሉ የዓይን ምስክሮች ለሂዩማን ራይትስ ዋች ገልፀዋል።
ድርጅቱ 36 ሰዎች ቃለመጠይቅ ያደረገ ሲሆን 19ኙ ጭና እና ቆቦ ውስጥ የህወሓት ኃይሎች በአጠቃላይ 49 ሰለማዊ ሰዎችን ሲገድሉ ማየታቸውንና ከሟቾቹ የ44ቱን ሰዎች ስም ገልፀዋል፤ በተጨማሪም የሟቾቹን ቁጥር ከፍ የሚያደርግ የስም ዝርዝር ማግኘቱን አመልክቷል።
የሂማን ራይትስ ዋች የቀውስና የግጭት ጉዳዮች ዳይሬክተር ላማ ፋኪህ ስለግድያዎቹ ሲናገሩ " የትግራይ ኃይሎች በጥበቃቸው ስር ያሉ ሰዎችን በመግደል ለሰው ህይወትና ለጦርነት ሕግጋት ጭካኔ የተሞላበት ግድየለሽነት አሳይተዋል" ብለዋል።
አክለው " እነዚህ በኢትዮጵያ የትግራይ እና የአማራ ክልሎች ውስጥ በተካሄዱ ግጭቶች በሁሉም ወገኖች የተፈጸሙ ግድያዎችና ጭፍጨፋዎች ገለልተኛ ዓለም አቀፍ ምርመራ እንደሚያስፍልግ ያመለክታሉ " ሲሉ ተናግረዋል።
ሙሉ ሪፖርት : www.hrw.org/news/2021/12/09/ethiopia-tigray-forces-summarily-execute-civilians

#HappeningNow
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ላይ የሚውል ያለውን አዲስ አገልግሎት (መተግበሪያ) ስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እያከናወነ ይገኛል።
አገልግሎቱ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኢግል ላይን ሲስተምስ ቴክኖሎጂ ትብብር እንደተዘጋጀ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፥ " አዲሱ የሆቴሎች መተግበሪያ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ላይ የሚውለው ሲሆን የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉን አሰራር እንደሚያዘምን ይጠበቃል " ብሏል።

" የታሪፍ ማሻሻያው ተጠናቆ ይፋ እስኪሆን ቀደም ሲል በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ ይቀጥላል " - ትራንስፖርት ቢሮ
የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የታሪፍ መጠን እንደሚሻሻል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
የዓለም አቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናቱን በማጠናቀቅ ላይ ሲሆን፥ በቀጣይ ቀናት ይፋ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በመሆኑም የታሪፍ ማሻሻያው ተጠናቆ ይፋ እስኪሆን ቀደም ሲል በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
በከተማዋ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎችም የታሪፍ መጠኑ ይፋ ሳይሆን ምንም ዓይነት ዋጋ ባለመጨመር አገልግሎቱን በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቢሮው አሳስቧል።
ምንጭ፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

#Update እስከ ከሜሴ ያለው መስመር ጥገና ተጠናቋል። ከካራቆሬ - ከሜሴ ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮቹንና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ከሥርጭት ኔትወርክ መስመሮች ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ በርብርብ ሲሰራ ቆይቶ ዛሬ እስከ ከሚሴ ድረስ ያሉት ከተሞች ኃይል ማግኘት ችለዋል፡፡ ከደብረብርሃን ኮምቦልቻ ድረስ ያሉት ከተሞች…
" ኮምቦልቻና ደሴ ኤሌክትሪክ ዛሬ ማግኘት እንዲችሉ በርብርብ እንሰራለን "- የኢ.ኤ.ኃ. የጥገና ባለሙያዎች
በሸዋ ሮቢት - ኮምቦልቻ መስመር የተጎዳውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የሚጠግነው የጥገና ቡድን አባላት የኮምቦልቻና ደሴ ከተሞች ዛሬ ኤሌክትሪክ ማግኘት እንዲችሉ በርብርብ እንሰራለን ብለዋል።
የጥገና ቡድኑ ትናንት ምሽት የጥገና ሂደቱን፣ በየከተሞቹ የደረሰውን ጉዳትና የህብረተሰቡን ስሜት የተመለከተ አጠቃላይ ግምገማ ካደረገ በኋላ ዛሬ የኮምቦልቻና ደሴ ከተሞች ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ የቻለውን ያህል ጥረት እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል፡፡
የጥገና ቡድኑ ትናንት ከካራቆሬ - ከሜሴ ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና አጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ አድርጓል።
የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ውቤ የቴክኒክ ቡድኑ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከሸዋሮቢት እስከ ከሚሴ ያለውን መስመር ጠግኖ ለአገልግሎት ለማብቃት ያደረገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
አቶ ሀብታሙ ፥ " ከባድ መስዋዕትነት በመክፈል የህዝቡን ችግር ለመፍታት ያደረጋችሁትን ርብርብ ተቋማችንና ህብረተሰቡ ሁሌም ሲያስታውሰው ይኖራል " ብለዋል፡፡

#NewsAlert
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
መንግስት በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ይሁኝታ አግኝቶ ሲመረጥ ቃል ከገባባቸው አገራዊ ጉዳዮች መካከል ሁሉን አካታች የሆነ አገራዊ ምክክርና ውይይት በማካሄድ አገራዊ መግባባት እና በአገር ጉዳይ የጋራ አቋም እንዲኖር የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
በዚሁ መሰረት መሠረታዊ በሚባሉ አገራዊ ጉዳዮች በተለያየ ጎራ የተሰለፉ የፖለቲካ ልሂቃንም ሆኑ ምልዓተ ህዝቡ ተቀራራቢና በአገራዊ አንድነት ገንቢ አቋም እንዲይዙ ለማድረግ አካታች አገራዊ ምክክሩን ተግባራዊ ለማድረግ በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ቅቡልነት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ ቀርቧል።
ምክር ቤቱም በቀረበው የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።
#PMOEthiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" የጦር አውሮፕላኖቹ የሩሲያን ድንበር ከመጣስ ተገትተዋል " - የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር
በጥቁር ባህር በኩል #የሩሲያን ድንበር አቋርጠው ሊገቡ የነበሩ #የፈረንሳይ እና #የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በSU-27 የሩሲያ ጄቶች ተጠልፈው መመለሳቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
እኤአ ታህሳስ 9 የሩሲያ የኤሮስፔስ መቆጣጠሪያ ሲስተም በራሪ አካላት ጥቁር ባህርን አልፈው ወደ ሩሲያ ድንበር እየበረሩ እንደሆነ ማመላከታቸውን ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ተጠቅሷል።
የሩሲያ ኤርክራፍት በረራ ቡድን ወደሩሲያ ድንበር አቅጣጫ ሲበሩ የነበሩት Mirage-2000 ጀትና ከፈረንሳይ አየርና ስፔስ ሃይል የመጣች የፈረንሳይ Rafale ጄት እንዲሁም የአሜሪካ ጦር CL-600 ያሳተፈ የጥናት እንቅስቃሴ ነበር ተብሏል፡፡
የፈረንሳይ KC-135 አውሮፕላን ነዳጅ የምትሞላ እና እጀባ የምታደርግ በጥቁር ባህር ላይ ሲበሩ እንደነበር መግለጫ አመልክቷል፡፡
የጦር ጄቶች አማካኝነት የጦር አውሮፕኖቹ የሩሲያን ድንበር ከመጣስ ተገትተዋል ያለው መግልጫ የሩሲያ ውጊያ ጄቶች የጦር አውፕላኖቹን ከድንበር ወደ ኋላ ከመለሱ በኋላ በሰላም መመለሳቸው ተገልጿል።
መረጃው የአል ዓይን ኒውስ ነው።
ቪድዮ : የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር