TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WFP

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከመደበኛ እርዳታ ውጪ ለ62,900 አባዋራዎች የምግብ እርዳታ አቀርባለሁ ብሏል።

ከቀናት በፊት የሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

ውይይቱ በሶማሊ ክልል ውስጥ በአንድ አንድ ቦታዎች የተከሰተዉን ድርቅ ለመቋቋም ያለመ ነው።

በዉይይቱ ላይ አቶ ሙስጠፋ ፥ በተለይ ዳዋ ዞን ከፍተኛ የድርቅ አደጋ የተከሰተባቸዉ ቦታዎች አንዱ መሆኑን በመግለፅ በአሁኑ ወቅት የዓለም ምግብ ፕሮግራሙ ከሚሰጠው መደበኛ እርዳታ ዉጪ አስቸኳይ እርዳታ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸዉ የሚመሰገን ስራ ነዉ ብለዋል።

በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር ስቲቨን ዌር ኦማሞ ከክልሉ መንግሥት ጋር በድርቁ ሁኔታ ዙሪያ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀው የሶማሊ ክልል መንግስት ድርቁን ለመቋቋም ላደረገው ቁርጠኝነትና 200 ሚሊዮን ብር በመመደብ የሰራዉን ስራ ምስጋና በማቅረብ ድርሻቸዉን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ኃላፊው በዳዋ ዞን ውስጥ ለሚገኙ የድርቁ ተጎጂዎች ለሆኑ 62,900 አባዋራዎች በአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያደርሱ ተናግረዋል።

#SomaliRegionCommunication

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WFP የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከመደበኛ እርዳታ ውጪ ለ62,900 አባዋራዎች የምግብ እርዳታ አቀርባለሁ ብሏል። ከቀናት በፊት የሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር። ውይይቱ በሶማሊ ክልል ውስጥ በአንድ አንድ ቦታዎች የተከሰተዉን ድርቅ ለመቋቋም ያለመ ነው። በዉይይቱ ላይ አቶ ሙስጠፋ ፥ በተለይ ዳዋ ዞን ከፍተኛ የድርቅ አደጋ…
#ALERT🚨

የዓለም ምግብ ፕሮግራም አሁኑኑ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ የማያገኝ ከሆነ በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል በተከሰተው ከባድ ድርቅ ምክንያት በሚቀጥሉት 3 ወራት ውስጥ እስከ 3.3 ሚሊዮን ሰዎች ለከፍተኛ ረሃብ ይጋለጣሉ ብሏል።

ከቀናት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኃላፊዎች ከሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ጋር ውይይት ካደረጉ በኃላ ያወጡት የጋራ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#NDAA

በኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም በኢትዮጵያ ወዳጆች የተጀመረው ዘመቻ በሁሉም የዓለም አካባቢዎች ተጠናክሮ መቀጠሉን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

መግለጫውን የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ሲሆኑ በዚህ ሳምንት በዲፕሎማሲው መስክ ከፍተኛ ውጤቶች የተገኘበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ፥ " ... በተለያዩ አካላት አንድ የተቀነባበረ ሰነድ ለአሜሪካ ኮንግረስ እንዲቀርብ ተደርጎ ነበር ፤ ክሱ በትግራይ ክልል ውስጥ በኢትዮጵያ መንግስት ዘርን የመጨረስ /የማጥፋት/ ተግባር ተፈፅሟል የሚል ነበር። ክሱ ከመነሻው መሰረተ ቢስ ነበር። ምክንያቱም የተመድ ከፍተኛ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ፅ/ቤት እና የአትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባደረጉት ምርመራና ባገኙት ውጤት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ቢኖሩም አንዳችም ዘርን የመጨረስ /Genocide/ ድርጊት እንዳልተፈፀመ አረጋግጠዋል " ብለዋል።

" ይህንን ወደጎን በመተው የተለያዩ ግለሰቦችና አካላት ተባብረው የኢትዮጵያ መንግስት የዘር ጭፍጨፋ አድርጓል ፣ የዘር መጨረስ ተግባር ፈፅሟል በማለት ያቀረቡትን ክስ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በመተባበር የኮንግረስ ሰዎች በመቅረብ ፣ ሌሎችንም አካላት በማግኘትና ጫና በማሳደር እውነታውን በማስረዳት ውድቅ እንዲሆን አድርገዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

" የታሰበው National Defense Authorization Act ሆኖ እንዲፀድቅ በሰነዱ ምክንያትም የወታደራዊ ጣልቃ ገብነት የህግ መሰረት እንዲያገኝ ታስቦ የተደረገ ነበር፤ ነገር ግን ውድቅ ተደርጓል ፤ ለኢትዮጵያውያን፣ ለትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት ዜጎች ላደረጉት አስተዋፆ ምስጋና እናቀርባለን " ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከነገ ጀምሮ ወደ ግንባር እንደሚዘምቱ አሳወቁ። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ዛሬ ምሽት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰራጩት ፅሁፍ ኢትዮጵያ አሁን እያደረገችው ያለው ትግል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትግል ነው ብለዋል። "ትግሉ ልጆቻችን ሀገር እንዲኖራቸው የሚደረግ ትግል ነው። ልጆቻችን ክብርና ነጻነትን ለብሰው፣ በዓለም አደባባይ በኩራት ቀና ብለው እንዲሄዱ የሚደረግ…
#Update

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለተወሰኑ ጊዜያት ወደ ቢሮ መመለሳቸውን አሳወቁ።

ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት ፤ የመጀመሪያውን ምእራፍ አጠናቀው ለተወሰኑ ጊዜያት ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ገልፀዋል።

" ዛሬም ሆነ ወደፊት ጠላቶቻችን ጉልበታቸው ዝሎ የጥላቻና የጠበኝነትን መንገድ ጥለው የፍቅር እና የሰላምን መንገድ እስኪመርጡ ትግላችን ይቀጥላል " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ " ያቀረብኩትን ጥሪ ተቀብላችሁ ህይወታችሁን ፣ ጉልበታችሁን ፣ ሀብታችሁን ፣ እውቀታችሁን ፣ጊዜያችሁንና ሞያችሁን ለሰጣችሁ ሁሉ በኢትዮጵያ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ " ሲሉ ገልፀዋል።

* ሙሉ መልዕክቱ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የደንበኞች ትምህርት ቡድን አባል አቶ ምትኩ አበባዉ ለኢትዮጵያ ቼክ ከተናገሩት ፦ - ደብዳቤዎቹ ከኛ ነዉ የወጡት፤ ትክክለኛ ናቸዉ። - የክልከላው ምክንያት ለንግድ ማይዉሉ የግል መገልገያ ዕቃዎችን ዝርዝር ለመወሰን የወጣዉን መመሪያ 51/2010ን በመጠቀም በተመላላሽ መንገደኞች ከቀረጥ ነጻ የሚገቡ ነገር ግን ለንግድ አላማ እየዋሉ የሚገኙ ዕቃዎች…
የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ውሳኔ እና ቅሬታ ያሳደረባቸው የውጭ ሀገር የተመላላሽ ዜጎች ጉዳይ. ፦

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከውጭ ሀገር ምንም አይነት እቃ (ልብስ እና ጫማን ጨምሮ) ይዞ መምጣት እንደማይቻል መግለፁ ይታወሳል።

ያለ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና ያለ ህጋዊ የዓለም አቀፍ የንግድ አሰራራ በየጊዜው እየተመላለሱ በሻንጣ የንግድ ዕቃ የሚያመላልሱ ግለሰቦችን ከድርጊታቸውን እንዲቆጠቡም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ማንኛውም መንገደኛ የሚያደርገው ጉዞው ለንግድ ዓለማ ከሆነ በማናቸውም እቃ ላይ ተገቢውን የመንግስት ቀረጥ እንደሚከፍል፤ ተመላላሽ ከሆኑ ግን በአስተዳደራዊ ቅጣት እስከ በወንጀል የሚያስጠይቅ ይሆናል ተብሏል።

ውሳኔው ግን በርካታ የውጭ ተመላላሾችን ጭንቀት ላይ የጣለ ሆኗል።

ቅሬታ ካሰሙት መካከል ህጋዊ አይደላችሁም ለሚባለው ጉዳይ ከዚህ በፊት ኮሚቴ ተወክሎ በአካልም ቢሮ ድረስ ቀርበን በምን መልኩ ነው ልታሰሩን የምትችሉት ብለን ጠይቀናል ግን ሁኔታውን መፍትሄ ለመስጠ ከመሄድ ይልቅ የዚህ አይነት ውሳኔ መወሰኑ ያልተጠበቀ እና የብዙ ሰዎችን ህይወት የሚያበላሽ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/ETHIOPIA-12-08
የUNICEF እገዛ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ፦

• UNICEF በኦሮሚያ ክልል ፣ ቦረና ዞን ዲሎ ወረዳ በድርቅ የተጎዱ 78 ሺህ ዜጎችን ለመርዳት የውሃ አቅርቦት / ውሃ ማመላለሻ አገልግሎት / እየሰጠ ይገኛል።

🚨በቦረና ዞን ብቻ ከ500 ሺ በላይ ሴቶች፣ ወንዶችና ህጻናት በድርቅ ተጎድተዋል።

• UNICEF ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች 13 ነጥብ 5 ሚሊዩን ብር የተገመተ የዓይነት ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ ጄነሬተሮች ፣ የንጽህና መጠበቂያ እና ሌሎች ግብዓቶች ያካተተ ነው። ይህ ድጋፍ ካለፈው የቀጠለ ሲሆን ድጋፉ እናቶችንና ህፃናትን ባሉበት ሆነው ለመደገፍ ታሳቢ ያደረገ ነው።

@tikvahethiopia
" አፍሪካችንን የሚመለከቱ ጉዳዮች እና ውሳኔዎች አፍሪካ ሳትሳተፍባቸው እየተወሰኑ ሊቀጥሉ አይችሉም " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ፤ " ወደ 1.3 ቢልዮን የሚጠጋ ሕዝብ ያላት አህጉር በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ ድምጽ እና መቀመጫ እንደሚያስፈልጋት ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ድምጻቸውን አሰምተዋል " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ " ጥሪያቸውን እኔም እጋራዋለሁ " ያሉ ሲሆን " አፍሪካችንን የሚመለከቱ ጉዳዮች እና ውሳኔዎች አፍሪካ ሳትሳተፍባቸው እየተወሰኑ ሊቀጥሉ አይችሉም " ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የፌደራል መንጃ ፈቃድ እድሳት ይመለከታል ፦

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የፌደራል መንጃ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

በአዲሱ የተቋማት አደረጃጀት መሰረት ቀደም ሲል በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ሲሰራ የነበረው የፌደራል መንጃ ፈቃድ እድሳት ከጥቅምት 5/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ በውክልና ተሰጥቶ ነበር።

በዚህም መሰረት ቢሮው ከህዳር 23/2014 ዓ.ም ጀምሮ የፌደራል መንጃ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ተገልጋዮች አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

አዲስ የፌደራል መንጃ ፈቃድ አገልግሎት ደግሞ በቅርቡ ይጀምራል ተብሏል።

ምንጭ፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

@tikvahethiopia
#Germany

ኦላፍ ሾልስ የጀርመን መራኄ መንግሥት ሆነው ተመረጡ።

የ63 ዓመቱ ሾልስ በፖለቲካ አቋማቸው ሶሻል ዴሞክራት ናቸው።

በምርጫው ከፍተኛ ድምፅ ካገኙት ከአረንጓዴ ፓርቲ እና ከነጻ ዴሞክራቶች ፓርቲዎች ጋር በመቀናጀት ሀገራቸውን ለመምራት ተስማምተዋል።

ሾልስ ዛሬ በጀርመን ምክር ቤት በተካሄደው ምሥጢራዊ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ከ707 አባላት የ395ቱን በማግኘት ኦላፍ ሾልስ አዲሱ የጀርመን መሪ ሆነው ተመርጠዋል።

እንዲያም ሆኖ የተጣማሪ ፓርቲዎቹን አባላት ሙሉ ድምፅ አላገኙም። በምርጫው ሂደት 303 አባላት ተቃውመዋል፤ ስድስት የምክር ቤት አባላት ደግሞ ድምፅ አልሰጡም።

ከድምፅ አሰጣጡ ሥርዓት በኋላ ወደ ፕሬዝደንቱ መኖሪያ በመሄድ የሹመት ደብዳቤያቸውን ተቀብለዋል።

ዛሬ ከፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የመራኄ መንግሥትነት ሥልጣናቸውን የተቀበሉት ሾልስ ወደ ምክር ቤት በመሄድ ቃለመሃላ ፈጽመዋል።

የካቢኔ አባሎቻቸውን በማቅረብም አዲስ ሚኒስትሮቻቸውን በይፋ ሰይመዋል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ

@tikvahethiopia
ሆቴሎች ለእንግዶች የ30% ቅናሽ አደረጉ።

አንድ ሚሊየን ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት መምጣት አስመልክቶ ሆቴሎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የ30% ቅናሽ (Discount) እንዳደረጉ የኢትዮጵያ ሆቴል እና መሠል አገልግሎት አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት አሳውቀውናል።

@tikvahethiopia