TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሲቪል ህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሰላምና ልማት ማዕከል የምዝገባ ፈቃድ ሰረዘ።

በባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ጂማ ዲልበ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚገልፀው የድርጅቱ ፍቃድ የተሰረዘው የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ባሳለፈው ውሳኔ ነው።

ፈቃዱ ስለተሰረዘበት ምክንያት በደብዳቤው ላይ እንደሚከተለው ሰፍሯል፦

"በአገር ህልውናና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንቀፅ 4 ንዑስ አንቀፅ 9 መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የአገርን ህልውናና ሉዓላዊነት እንዲሁም የሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የሞራልም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል ብሎ የሚጠረጥረውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ፈቃድ እንዲሰረዝ ሊያዝ ይችላል ተብሎ ተደንግጓል።

በዚህም መሰረት ከላይ የተጠቀሰው (የሰላም እና ልማት ማዕከል) ድርጅት ፈቃድ እንዲሰረዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ውሳኔ ያሳለፈ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር በቁጥር ፍ/ሚ-01/ባሰ-9/500773 ሕዳር 17/2014 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ አሳውቋል።

በዚሁም መሰረት የሰላምና ልማት ማዕከል የተባለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የምዝገባ የምስክር ወረቀት (ፈቃድ) ከዛሬ ህዳር 17 ጀምሮ የተሰርዟል"

ባለስልጣን መ/ቤቱ የሲ/ማ/ድ/ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አግባብነው ካለው አካል ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ የድርጅቱን ንብረት እንዲረከብ ትዕዛዝ መተላለፉም በደብዳቤው ላይ ተገልጿል።

ድርጅቱ ከሰሞኑን በፕ/ር ኤፍሬም መሪነት ከህወሓት ጋር ግንኝኑት ያላቸው አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ጨምሮ፣ እነዶ/ር እሌኒ ገ/መድህንና ሌሎች የውጭ ዜጎች የተካፈሉበት የኦንላይን ውይይት አዘጋጅቶ ነበር።

@tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የተሰጠ መግለጫ !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቤት ኪራይ ጭማሪ ለ90 ቀናት ታገደ:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በቀን 18/12/13 ባደረገው መደበኛ ስብሰባው የቤት ኪራይ ጭማሪን ለ90 ቀናት ለማገድ በቀረበ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡ በዚህም መሠረት ደንቡ ከፀደቀበት 18/12/13 ዓ.ም ጀምሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ለ90 ቀናት የተከለከለ ሲሆን በቀጣይም ታይቶ ለተጨማሪ…
" ለቀጣይ 3 ወራት የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስለቀቅ ፈጽሞ የተከለከለ ነው " - የአ/አ ከተማ አስተዳደር

የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከተከራየበት ቤት ማስለቀቅ እንደማይቻል ውሳኔ ማተላለፉ ይታወሳል፡፡

አስተዳደሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፥ " ይህ ያለንበት ወቅት አገርን ከተጋረጠባት የህልዉና አደጋ የማዳን በመሆኑ ውሳኔውን ለቀጣይ ሶስት ወራት ባለበት እንዲጸና ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ብሏል።

በመሆኑም ከዛሬ ሕዳር 17 / 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ወራት የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስለቀቅ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video : የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ግንባር ዘምተው ሰራዊቱን እንደሚመሩ በይፋ ካሳወቁ በኃላ ዛሬ በቴሌቪዥን መስኮት ለህዝብ ታይተዋል። እየመሩት ያለው ሰራዊት ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ መሆኑን አሳውቀዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ለሚዲያ በሰጡት አጭር መግለጫ ካሳጊታ መያዙን ዛሬ ደግሞ ጭፍራ እንዲሁም ቡርቃ እንደሚያዙ ገልፀዋል። "ነገምይቀጥላል ትላልቅ ድሎች አሉ " ብለዋል። ዶክተር ዐቢይ…
#Update

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሰራዊት ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን መቆጣጠሩን አስታወቀ።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን በመግለጫው ፥ " በጠ/ሚኒስትሩ ቁርጠኝነት የተነቃቃው ጀግናው ሠራዊታችን በባቲ ካሳጊታ ግንባር ሲደረግ በነበረው ውጊያ ካሳጊታን አስቀድሞ ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ ያወጣ ሲሆን ወደፊት በመገሥገሥ ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን ተቆጣጥሮ ወደ ባቲ ኮምቦልቻ እየገሠገሠ ነው " ብሏል።

በተጨማሪም፥ "በአፋር ክልል ፣ በጭፍራ ግንባር ጪፍቱን ፣ የጭፍራ ከተማንና አካባቢውን ከወራሪው ነጻ አውጥቶ ወደፊት በመገሥገሦ ላይ ነው " ሲል አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መላውን የጸጥታ ኃይል ራሳቸው በመምራት የህልውና ዘመቻውን ከዳር ለማድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቃል በገቡት መሠረት በግንባር ተገኝተው ቃላቸውን ተግባራዊ እያደረጉ ነው ብሏል።

ፎቶ ፦ ፋይል
ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ/ም

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 13 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,235 የላብራቶሪ ምርመራ 172 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 229 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#LeliseDhugaa

የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ የ2021ን የፓን-አፍሪካ ቼንጅ ሜከርስ ሽልማት ተሸለሙ፡፡

ይህን ሽልመትና እውቅና ያገኙት በቱርኳ ኢስታንቡል ከተማ "አብረን እንጠነክራለን" ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለበለጸገች አፍሪካ (“Stronger Together: Strategic Partnership for a Prosperous Africa”) በሚል መሪ ቃል የተካሄደው 6ኛው የፓን አፍሪካ ሰብዓዊነት እና ኢንቨስትመንት ጉባዔ (𝟔𝐭𝐡 𝐏𝐀𝐍 𝐀𝐅𝐑𝐈𝐂𝐀𝐍 𝐇𝐔𝐌𝐀𝐍𝐈𝐓𝐀𝐑𝐈𝐀𝐍 & 𝐈𝐍𝐕ST𝐓𝐌𝐄𝐍𝐓 𝐒𝐔𝐌𝐌𝐈𝐓) ላይ ነው።

ኮሚሽነር ሌሊሴ ለዚህ ሽልማት የታጩት በአመራር ብቃት የላቀ አፈጻጸም ማስመዝገባቸው፣ በስራ እድል ፈጠራና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት የሰሩት ተጨባጭ ሥራ ለሃገር ግንባታ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ስለታመነበት ነው፡፡

የሽልማቱ አዘጋጆች እንደተናገሩት ከሆነ ኮሚሽነር ሌሊሴ በምሳሌያዊነቱ ሊጠቀስ የሚችል ጥረታቸው እያደገ ያለውን የሃገሪቷን የቱሪዝም ሴክተር የላቀ ደረጃ ያደርሰዋል ተብሎ በመታሰቡና ቁርጠኝነታቸው ይህን ያልተነካ የሃገሪቷን ሃብት ለመጠቀም እንዲቻል መሰረት የጣለ መሆኑ ለዚህ ሽልማት እንዲበቁ ምክንያት ሆኗል።

ምንጭ ፦ Visit Oromia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የጎረቤታችን ሱዳን የፖለቲካ ቀውስ ! ጎረቤታችን ሱዳን በከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ናት። ዛሬ ደግሞ ከባለፈው ሌላ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሳይደረግ እንዳልቀረ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየተዘገበ ነው። የታጠቁ ወታደሮች በርካታ የአገሪቱ የሽግግር መንግሥት አባላትን በቤታቸው ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው ይነገራል። ማንነታቸው ያልተወቁ ወታደራዊ ኃይሎች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሐምዶክን…
አብደላ ሃምዶክ የሱዳን ጦርን እርምጃ ቀድመው ያውቁ ነበር ?

የሱዳን ገዥ ሉዓላዊ ም/ ቤት ምክትል ኃላፊ ጄኔራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ)፥ ጠ/ሚ አብደላ ሃምዶክ ባለፈው ወር የሱዳን ወታደራዊ ኃይል የወሰደውን እርምጃ ቀድመው የሚያውቁት እንደሆነና በውሳኔውም " ሙሉ በሙሉ " ተስማምተው እንደነበረ ተናገሩ።

ዳጋሎ (ሄሜቲ) ይህን የተናገሩት ከአልጀዚራ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ነው።

አብደላ ሃምዶክ እኤአ ጥቅምት 25 በወታደሮች ከስልጣን እንደተነሱ በኃላም ወደ ሲቪል አገዛዝ የሚደረገውን ሽግግር ለመመለስ እሁድ እለት ከሱዳን ከፍተኛ ጄኔራል ጋር ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ ወደ ጠ/ሚኒስትነታቸው መመለሳቸው ይታወቃል።

ዳጋሎ (ሄሜቲ) የጥቅምት 25ቱ ክስተት የረዥም ሂደት የመጨረሻ ውጤት መሆኑን አስረድተዋል።

"ብዙ ውይይቶች ተደርገዋል፣ ብዙ ሃሳቦች ቀርበዋል" ያሉት ዳጋሎ፥ "ጠ/ሚኒስትሩ ራሳቸው በስብሰባዎች ላይ ሁለት ሃሳቦችን አቅርበዋል፤ ሦስት ምርጫዎች ቀርተውን ነበር ፣ ከመካከላቸው ጥሩው የወሰድነው እርምጃ ነበር። ይህም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘንድ ሙሉ በሙሉ ስምምነት የነበረው ነው" ብለዋል።

አክለውም፤ "እኛ በራሳችን እንዲህ አይነት እርምጃ አልወሰድንም" ሲሉ ተናግረዋል።

እ.ኤ.አ. ጥቅምት 25 ሌ/ጄኔራል አብደል ፋታህ አል- ቡርሃን መንግስት መበተናቸው፤ የሲቪል አመራሩን ማሰራቸውና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው፤ ይህም ውሳኔ አለም አቀፍ ውግዘት ያደረሰባቸውና ሰፊ የህዝብ ተቃውሞ ያስነሳ መሆኑ ይታወሳል።

ባለፈው እሁድ በሌ/ጀነራል አል-ቡርሃን እና በጠ/ሚ አብደላ ሃምዶክ መካከል የስልጣን ክፍፍል ስምምነት መደረጉ አይዘነጋም።

ምንም እንኳን ስምምነት ቢደረግም አሁንም ሙሉ የሲቪል አስተዳደር እንዲመለስ የሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎች ቀጥለዋል።

@tikvahethiopia
#WFP

በትላንትናው ዕለት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (የዓለም ምግብ ፕሮግራም) ቃል አቀባይ ቶመሰን ፉሪ በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦

• ከጦርነት ጋር በተያያዘ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 9.4 ሚሊዮን ደርሷል።

• የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር ክልሎች ወስጥ የሚገኙ 9.4 ሚሊዮን ሰዎች አስከፊ ሕይወት እየገፉ ነው።

• 7.8 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በጦርነቱ ምክንያት ሰብአዊ እርዳታ ማድረስ አዳጋች የሆኑባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ሰዎች ናቸው።

• የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ለውጥ የታየበት #በአማራ_ክልል ነው። በአሁኑ ጊዜ በአማራ ክልል ብቻ 3.7 ሚሊዮን ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

• ከትግራይ፣ ከአማራ እና ከአፋር ክልሎች የተሰበሰቡ መረጃዎች እንዳመለከቱት በሦስቱ ክልሎች ከሚገኙ ሕጻናት መካከል ከ16 እስከ 18 በመቶ የሚሆኑት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል። ነፍሰጡር ከሆኑ እና ከሚያጠቡት እናቶች መካከል 50 በመቶ ያህሉ በተመሳሳይ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል።

• UN የምግብ አቅርቦት የጫኑ ተሸከርካሪዎች ከኮምቦልቻ ወደ ደቡባዊ ትግራይ እየላከ ነው። በቀጣይ ቀናት 2200 ሜትሪክ ቶን ሕይወት አደን ምግብ መቐለ ይደርሳል።

• WFP በትግራይ 2.5 ሚሊዮን ሕዝብ ጋር መድረስ ሲኖርበት እስካሁን መድረስ የቻለው 180 ሺህ የሚሆኑትን ብቻ ነው።

ምንጭ፦ https://www.wfp.org/news/millions-more-need-food-assistance-direct-result-conflict-northern-ethiopia-says-wfp

@tikvahethiopia
#Kenya #USA

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከኬንያ ጋር ተነጋገሩ።

ትላንትና የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ
መወያየታቸው ገልፀዋል።

ብሊንከን በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ላይ ፥ “በኢትዮጵያ እየተባባሰ በመጣው ወታደራዊ ግጭቶች አሜሪካን እንደሚያሳስባት ለፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አሳውቄያለሁ” ብለዋል።

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ግጭት የምስራቅ አፍሪከ ቀጠናን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በግጭቱ እየተሳፉ ያሉ ሁሉም አካላት የሀገሪቱን ሉአላዊነት እና አንድነት ባስጠበቀ መልኩ ወደ ሰላም ለመምጣት ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስዱም ጥሪ አቅርበዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኒድ ፕራይስ ውይይቱን አመስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ በውይይቱ ወቅት በግጭቱ የሚሳተፉ አካላት በአፋጣኝ ወደ ድርድር እንዲመጡ አሜሪካ ጥሪ ማቅረቧን አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ኬንያታ እና አንቶኒ ብሊንከን በግጭቱ ለተጎዱ ማህበረሰቦች ያልተቋረጠ የሰብአዊ ድጋ አቅርቦት አስፈላጊነት ላይ መምከራቸውን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እንዲደረግ አሜሪካና ኬንያ ድጋፍ ለማድረግ መስማማታቸውንም ቃል አቀባዩ ማስታወቃቸውን አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጥቂት ቀናቶች በፊት ኬንያ መጥተው ስለኢትዮጵያ እና ሌሎችም ጉዳዮች ከኬንያ ጋር ውይይት አድርገው መመለሳቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia