ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ውጭ አማራጭ ገበያ እየፈለገች ነው።
አሜሪካ የኢንዱስትሪ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገሯ ገበያ እንዲገባ ይፈቀድ የነበረው ስምምነት (AGOA) እንዲቋረጠ በፕሬዜዳንቷ ጆ ባይደን አማካኝነት ውሳኔ ማሳለፏ ይታወሳል።
ይህ የአሜሪካ ውሳኔ በርካቶችን ከስራ ውጭ የሚያደርግ ውሳኔ መሆኑ በተደጋጋሚ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ በAGOA ምክንያት ይገኝ የነበረው የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት አማራጭ ገበያ እየፈለገች መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ፥ " የገበያ መዳረሻዎቻችን በሪፎርም ስራዎች ውስጥ አንዱ ዋና ስራ ተደርጎ ከተወሰዱት የገበያ መዳረሻዎች ማስፋት ነው። ከዚህ አኳያ AGOA በተሰጠን እድል መሰረት አሜሪካ ያለንን የገበያ እድል ሌላ ጋር መፈለግ ማለት ነው። ሌሎች ሀገራት በዚህ አይነት ሁኔታ የተጠቀሙ ብዙ አሉ። ጫናና ማዕቀብ ሲጣልባቸው ከሌሎች ሀገራት ጋር ተደራድረው ያንን ምርቶቻቸውን ሌሎች ሀገራት የተቀበሏቸው አሉ። ኢትዮጵያም ያንን እያሰበችበት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ አክለው ፤ በኮቪድ-19 ጊዜ የአለም ገበያ ሲዘጋ ለኤክስፖርት ተብለው የተመረቱ እቃዎች በሀገር ውስጥ መሸጥ እንዲችሉ እድሉን መንግስት አመቻችቶ ነበር ይሄም አንዱ መታየት ያለበት መሆኑን አንስተዋል።
ዶክተር ፍፁም አሰፋ ፥ ጦርነቱ ኢትዮጵያ ልማት ላይ ልታውል ያቀደችውን ገንዘብ ለጦርነት እንዲውል ስለሚደረግ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ዜጎች ኢኮኖሚውን ለመደገፍ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝት ለማሳደግ በህጋዊ መንገድ ገንዘብ እንዲልኩ ጠይቀዋል።
@tikvahethiopia

" አብዲአዚዝ ለሀገሩ፣ ለወገኑና ለሃይማኖቱ በድፍረት እና ያለ እረፍት የሰራ ታታሪ ጋዜጠኛ እና የሀገር ጀግና ነበር " - ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ
አልሸባብን በመተቸት የሚታወቀው ሶማሊያዊ ጋዜጠኛ ትላንት ሞቃዲሾ ውስጥ በተፈጸመ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ተገደለ።
አብዲአዚዝ መሀሙድ ጉሌድ ወይም አብዲአዚዝ አፍሪካ በመባል የሚታወቀው ይህ ጋዜጠኛ ትላንት ከቀትር በኋላ በከተማው ከሚገኝ ሬስቶራንት ሲወጣ ኢላማ ተደርጎ ነው የተገደለው።
ከጋዜጠኛው በተጨማሪ በአካባቢው የነበሩ ሁለት ሰዎች በፍንዳታው ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
በሬድዮ ሞቃዲሾ ይሰራ የነበረው ይህንን ጋዜጠኛ ኢላማ እንዳደረገውና ጥቃቱንም እንዳቀነባበረ #አልሸባብ አስታውቋል።
የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃቱ የደረሰው ጉሌድ ከሶማሌ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ዳይሬክተር እና አንድ ሹፌር ጋር ሬስቶራንቱ አቅራቢያ በሚገኝ አንድ መኪና ፊት ለፊት መሆኑን የሬድዮ ሞቃዲሾ ድረገፅ የፖሊስ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
የጋዜጠኛውን ግድያ ተከትሎ የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ ሃዘናቸውን ለጉሌድ ቤተሰቦች መግለፃቸውን ተዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ "አብዲአዚዝ ለሀገሩ፣ ለወገኑ እና ለሃይማኖቱ በድፍረት እና ያለ እረፍት የሰራ ታታሪ ጋዜጠኛ እና የሀገር ጀግና ነበር" ብለዋል።
ጉሌድ በአልሸባብ ታስረው ከተፈቱ ተጠርጣሪዎች ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ የሚታወቅ ሲሆን የሚያቀርበው ስርጭቱም በርካታ ታዳሚዎችን ይስባል።
መረጃውን ሬድዮ ሞቃዲሾን ዋቢ አድርጎ ያስነብበው ቢቢሲ ነው።

#SUDAN
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ወደ ቀደመው ኃላፊነታቸው ለመመለስ የሱዳን የፖለቲካ እና ወታደራዊ ኃይሎች ከስምምነት መድረሳቸው ተሰምቷል።
የሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ሀገሪቱን ከቀውስ ለማውጣት እያካሄዱት ባለው ድርድር ላይ በወታደራዊ ኃይሎች ከስልጣናቸው ተነስተው የነበሩትን አብደላ ሀምዶክ ወደ ቀድሞ ኃላፊነታቸው ለመመለስ ተስማምተዋል።
የሱዳን ሉዓላዊ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃ እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክም በጉዳዩ ላይ ከመግባባት ደርሰዋል ተብሏል።
በስምምነቱ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ ካቢኔያቸውን እንዲያዋቅሩ ከስምምነት ተደርሷል።
በተጨማሪ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞችን ከእስር እንዲለቀቁ ከስምምነት መደረሱን ታውቋል።
Credit : አል ዓይን

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ቀይ መስቀል (አ/አ ቅርንጫፍ) ተለዋጭ ቦታ ተሰጠው።
በአዲስ አበባ ከተማ ከ1973 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተለዋጭ ቦታ ማግኘቱንና ከኅዳር 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ አዲሱ ሕንፃ ተዘዋውሮ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰብዓዊ፣ የዲፕሎማሲና የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሰለሞን ዓሊ (ዶ/ር) ፥ የአዲስ አበባ ከተማ የቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ይገለገልበት የነበረውን ቦታ ለልማት በመፈለጉ ምክንያት የቦታ ይዞታውን እንዲለቅ ተደርጓል ብለዋል።
በዚህ መሠረት የከተማ አስተዳደሩ በምትኩ ሰእሊተ ምሕረት አካባቢ ከሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ፊት ለፊት የሚገኘውን የቀድሞ የማምረቻዎች ልማት ኤጀንሲ ጽሕፈት ቤት የነበረውን ጂ+4 ሕንፃ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አገልግሎት እንዲውል በስጦታ መልክ ማበርከቱን ኃላፊው ገልፀዋል።
አዲሱ ጽሕፈት ቤት ከ15 በላይ አምቡላንሶችን የመያዝ አቅም እንዳለው የሚናገሩት ዶ/ር ሰለሞን፣ " ከዚህ ቀደም አገልግሎት ይሰጡበት ከነበረው ሕንፃ የተሻለ፣ እንዲሁም እጅግ ዘመናዊ የሆነ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ቀይ መስቀል አ/አ ቅርንጫፍ ከዚህ ቀደም የነበረበት ሕንፃ መፍረሱን ተከት ቅሬታ ማስነሳቱ፤ በተለይም ደግሞ ለተቋሙ የሚሆን ተለዋጭ ቦታ አለመሰጠቱ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም።
#ሪፖርተር

#SUDAN የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ወደ ቀደመው ኃላፊነታቸው ለመመለስ የሱዳን የፖለቲካ እና ወታደራዊ ኃይሎች ከስምምነት መድረሳቸው ተሰምቷል። የሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ሀገሪቱን ከቀውስ ለማውጣት እያካሄዱት ባለው ድርድር ላይ በወታደራዊ ኃይሎች ከስልጣናቸው ተነስተው የነበሩትን አብደላ ሀምዶክ ወደ ቀድሞ ኃላፊነታቸው ለመመለስ ተስማምተዋል። የሱዳን…
#SUDAN
አብደላ ሀምዶክ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ተመለሱ።
ሃምዶክ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው የተመለሱት በሀገሪቱ የተፈረመውን አዲስ ፖለቲካዊ ስምምነት ተከትሎ ነው።
የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በሀገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግስት ከተፈፀመ 3 ሳምንታት በኋላ ስልጣን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመመለስ የሚያስችል ስምምነት ዛሬ ፈርመዋል።
ዛሬ በካርቱም በሚገኘው ቤተ መንግስት ውስጥ የተካሄደውን የፖለቲካ ስምምነትም ሌተናል ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ መፈረማቸው ተነገሯል።
ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሀን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላህ ሃምዶክ በ14 ጉዳዮችን ዙሪያ መፈራረማቸውም ነው የተገረው።
ከተስማሙባቸው ጉዳዮች መካከልም ፦
- ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እና አንድ ወጥ የሆነ የሱዳን ጦር መመስረት፣
- የሱዳንን ግዛታዊ አንድነት ማስጠበቅ፣
- የሽግግር ጊዜውን የሚመራውን ሕገ መንግሥታዊ፣ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ አስራሮች መወሰን የሚሉት ይገኙበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ ከስምምነቱ በኋላ ባደረጉት ንግግር፤ " አንድነት ለሱዳን አስፈላጊ ነው " ያሉ ሲሆን " የሱዳን ጥቅም ማስጠበቅ ቀዳሚ ጉዳይ ነው " ሲሉ አሳስበዋል።
“ዛሬ የተፈረመው ስምምነት ለሳምንታት የተሰራ የጠንካራ ስራ ውጤት ነው” ያሉት ሀምዶክ፤ “ሱዳን ምንም መመለስ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ብትደርስም መመለስ እንደምትችል ያረጋገጠ ነው” ብለዋል።
ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሀን በበኩላቸው “ዛሬ የተፈረመው ስምምነት የሱዳናውያን የስራ ውጤት ነው፤ ይህ የእውነተኛ ሽግግር ጅማሮ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

" በቦረና ዞን የሞቱ እንስሳት ቁጥር 70 ሺህ ተሻግሯል "
በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሞቱ እንስሳት ቁጥር ከ70 ሺ ማለፉን የዞኑ አርብቶ አደር ልማት ኃላፊ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ አስታወቁ።
ድርቁ ከእንስሳት ሞት ባሻገር በሰዎች ህይወት ላይ ማህበራዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም አመልክተዋል።
ዶ/ር ቃሲም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ " 70,185 ከብቶች ሞተዋል ፤ 117,462 እራሳቸው መነሳት የማይችሉ በሰው ድጋፍ የሚነሱ ናቸው" ብለዋል።
ጉዳት ከፍተኛ ነው ያሉት ዶ/ር ቃሲም ጉዮ ፥ " 50,552 አባወራዎች ናቸው ከብቶቻቸውን በጉልበታቸው እያነሱ የሚገኙት ፤ ከብቶች የሞቱባቸው 28,238 አባወራዎች ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።
ድርቁ እንስሳት ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ በማህበራዊ ህይወት ላይ ተፅእኖ እያሳረፈ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።
ለድርቅ ተጎጂዎች የእንስሳት መኖ ድጋፍ ይዞ ወደ ቦረና ዞን ሄዶ የነበረው የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ልዑካን ቡድን በስፍራው ያለድ ጉዳት በመገናኛ ብዙሃን ከሚነገረው በላይ ነው ብሏል።
የሶማሊ ክልል ደግሞ ባለፈው ሳምንት ከ50 ሺህ በላይ እንስሳት እንደሞቱበት ያሳወቀ ሲሆን ድርቁን ለመከላከል መንግስት ከሚያደርገው ጥረት በተጨማሪ በውጭ ያሉ የሶማሊ ክልል ተወላጆች ድርጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/BORANA-11-21-2
Credit : Addis Checkol - VOA
Photo : Haramya University

Telegraph
BORANA
" በቦረና ዞን የሞቱ እንስሳት ቁጥር 70 ሺህ ተሻግሯል " በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሞቱ እንስሳት ቁጥር ከ70 ሺ ማለፉን የዞኑ አርብቶ አደር ልማት ኃላፊ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ አስታወቁ። ድርቁ ከእንስሳት ሞት ባሻገር በሰዎች ህይወት ላይ ማህበራዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም አመልክተዋል። ዶ/ር ቃሲም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ " 70,185 ከብቶች ሞተዋል ፤ 117,462 እራሳቸው መነሳት የማይችሉ…
TIKVAH-ETHIOPIA
" በቦረና ዞን የሞቱ እንስሳት ቁጥር 70 ሺህ ተሻግሯል " በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሞቱ እንስሳት ቁጥር ከ70 ሺ ማለፉን የዞኑ አርብቶ አደር ልማት ኃላፊ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ አስታወቁ። ድርቁ ከእንስሳት ሞት ባሻገር በሰዎች ህይወት ላይ ማህበራዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም አመልክተዋል። ዶ/ር ቃሲም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ " 70,185 ከብቶች ሞተዋል ፤ 117,462 እራሳቸው መነሳት…
#BORANA
• " ነፍሴን ካወቅኩ ጀምሮ ግን እንደዚህ አይነት ድርቅ አይቼ አላዉቅም " - የ88 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋው አቶ አብጃሀታኒ ሞሉ
• " ምን እንደሚገጥመንም ፈጣሪ (ዋቃ) ብቻ ነዉ የሚያወቀው " - ወ/ሮ ደቦ ዋቅቶላ
ወይዘሮ ደቦ ዋቅቶላ አካባቢቸውን ለቀው ወደ ሌላ ስፍራ ለስደት ከሄዱ አርብቶ አደሮችን መካከል ሲሆኑ ቀበሌያቸው በድርቅ በመጎዳቱ ለእንስሳቱ ዉሃና ሳር ለሰዉም የሚሆን ምግብ በመጥፋቱ እንስሳቶቹን እየነዱ ወደ ድሬ ወረዳ መሰደዳቸውን ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ኤፍ ኤም 91.5 ተናግረዋል።
ወ/ሮ ደቦ፥ " ምን እንደሚገጥመንም ፈጣሪ (ዋቃ) ብቻ ነዉ የሚያወቀው " ብለዋል፡፡
የ88 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋው አቶ አብጃሀታኒ ሞሉ በበኩላቸው፥ ከዚህ በፊትም አልፎ አለፎ ድርቅ ይመጣል፣ ነፍሴን ካወቅኩ ጀምሮ ግን እንደዚህ አይነት ድርቅ አይቼ አላዉቅም ብለዋል።
" ከእኔ ብቻ 132 ከብቶች አልቀውብኛል " የሚሉት እኚህ አባታችን " አሁን ደግሞ እኔና በአካባቢዬ ያሉ ሰዎች እየተራብን ነዉ፣ በቦረና ሰማይ ላይ ደመናም አይታይም ስለዚህ ፈጣሪ፣ ህዝብና መንግስት ተረባርበዉ ካልደረሱልን እንኳን እንስሳት እኛም በረሀብ ልናልቅ ስለሆነ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲረዳን ጥሪዬን አቀርባለሁ " ብለዋል፡፡
በቦረና ዞን በድርቅ በተመቱት 5 ወረዳዎች ከሌሎች እንስሳት በተለየ መልኩ አህያዎች በራሳቸዉ ያሉበትን አካባቢ በመልቀቅ ደመና ወዳለበት እየጠፉ ሲሆን ይህም የተለመደ የአህያ ልዩ ባህሪይ በመሆኑ በርካታ አርብቶ አደሮች አህያዎቻቸውን ፍለጋ ተሰማርተዋል።
በቦረና ዞን በድርቅ በተመቱ አካባቢዎች በየቦታው የሞቱ እንስሳቶች ቅሪት ፣ በህይወት ያሉትም በጣም ተዳክመው አጥንታቸው ከቆዳቸው ጋር ተጣብቆ ይታያል።
ከሀዩ ኤፍ ኤም የተወሰደ።

የተቃውሞ ሰልፎች ፦
በ27 የተለያዩ ዓለም አቀፍ ከተሞች በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ ተደረገ።
በዓለማ አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያን በ27 ከተሞች የአሜሪካ መንግስት እና አንዳንድ የምእራባዊያንን መንግስታት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ያሉትን ጣልቃ ገብነትና ጫና የሚቃወም ሰልፍ አድርገዋል።
በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ " ኋይት ሃውስ ቤተ መንግስት " በርካቶች የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍም ተካሂዷል። በዚሁ ሰልፍ ሽብረተኛ ተብሎ የተፈረጀውን ህወሓት መደገፍ የአፍሪካ ቀንድን እና መላ አህጉሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል አካሄድ መሆኑን የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር እንዲገነዘብ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።
በእስራኤልና እንግሊዝ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ብዛት ያለው ህዝብ በመሳተፍ የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የሀሰት ዘገባ እና መንግስታት በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣ መንግስትን ለመጣል የሚያደርጉትን ጥረት ክፉኛ ኮንነዋል።
ሰልፈኞቹ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ በተለይም የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦችን በመከፋፈል ላይ የተመሰረተ ፖሊሲዋን እንድታርም ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያን እጅ ለመጠመዘዝ የሚደረግ ሙከራ የአፍሪካን ነጻነት መግፈፊያ ዳግም የቅኝ አገዛዝ ፖሊሲ አካል በመሆኑ “#NoMore” በሚለው መሪ መፈክራቸው ተቀባይነት እንደሌለው ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፎቶ ፦ ሶሻል ሚዲያ