TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ወደ ታህሳስ ወር ተራዝሟል " - የጤና ሚኒስቴር

በኅዳር 2014 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ የነበረው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ወደ ታህሳስ ወር መራዘሙን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የፈተናው ምዝገባ ለሁለት ጊዜ በመራዘሙ ምክንያት ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ወደ ታህሳስ መሸጋሸጉን በሚኒስቴሩ የብቃት ምዘና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አበባው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

የምዘና ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ ከጥቅምት 05/2014 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል።

የግል አመልካቾች የትምህርት ማስረጃ ሕጋዊነትና ትክክለኛነት ማረጋገጫ እንዲያገኙ ለማስቻል ምዝገባው ሁለት ግዜ መራዘሙን አስታውሰዋል።

ተማሪዎች ለሙያ ብቃት ምዘና ፈተናው ዝግጅት ተጨማሪ ጊዜ መጠየቃቸውንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

በመሆኑም የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተናው በታህሳስ ወር እንደሚሰጥ ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል።

More : @tikvahuniversity
#ማሳሰቢያ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ኢትዮጵያ የህልውና ዘመቻ ላይ መሆኗ በማስታወስ የተቃጣውን የህልውና አደጋ ለመከላከል፣ ኢትዮጵያ የተደቀነባትን የግዛት አንድነት ስጋትና ሉአላዊነት ጥሰት ለመከላከል ሁሉን አቀፍ የጥንቃቄ እርምጃዎች መውስድ አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮሙዩኒኬሽንና የመገኛኛ መሳሪያዎች በእጁ የሚገኝ ማንኛዉም ግለሰብ፣ ተቋም፣ ኤምባሲ ወይም ዲፕሎማት፣ በመንግስታዊም ሆነ በግል ተቋማት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ አካላት፣ በዘርፉ የተሰማሩ አስመጪዎች እና ላኪዎች በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እንዲያሳዉቁ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

1. ወታደራዊ የቅኝት መሳሪያዎች ፦
• የጦር ሜዳ መነጽር (binokular)
• ኮምፓስ (Compass)
• የጂፒኤስ መሳሪያ (GPS)

2. ወታደራዊ እና ሲቪል የመገናኛ መሳሪያዎች ፦
• መገናኛ ሬዲዮ (Walkie Talkies radio)
• ሳተላይት ስልክ (satellite phone)

3. ቪሳት እና ቢጋን (A very small aperture terminal (VSAT) and Broadband Global Area network (BGAN))

4. ድሮኖች (Drones)

እነዚህን የመገናኛ እና ኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎች በግለሰቦች እጅ ወይም በተቋማት ውስጥ ሲጠቀም ያየ ማንኛዉም አካል ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጅንሲ በነጻ ስልክ ቁጥር 933 ወይም 0113851193 ፣ 0904049625 እና 0114701321 ማሳወቅ እንደሚጠበቅበት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#EMA : ሲኤንኤን ፣ ቢቢሲ ፣ ሮይተርስ እና ኤፒ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለአራት የውጭ ሚዲያዎች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ፅፏል።

እነዚህ ሚዲያዎች ሲኤንኤን (CNN)፣ ቢቢሲ (BBC)፣ ሮይተርስ (Reuters) እና አሶሺየትድ ፕሬስ (AP) ናቸው።

በማስጠንቀቂያ ደብዳቤው ላይ ሚዲያዎቹ ፦

- TPLFን ዓላማ ለማገዝ በኢትዮጵያ ላይ የሀሰት ዜናዎች እና የዜና ትንታኔዎችን ማዘጋጀታቸው እና ማሰራጨታቸው ፥

- የህግ ማስከበር ዘመቻውን የዘር ማጥፋት (Genocide) ዘመቻ አድርገው ሪፖርት ማድረጋቸው ፥

- በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመፍታት መንግስት የሚያደርገውን ጥረት የሚያበላሽ ዘገባዎችን መስራታቸው፣

- በትግራይ ክልል መንግስት ረሃብንን እና አስገድዶ መድፈር እንደጦር መሳሪያ እንደተጠቀመበት ሪፖርት ማድረጋቸው ፤

- በሀገሪቱ መሪ ተቋማት ላይ የስም ማጥፋት ሪፖርቶችን ማዘጋጀታቸው፤

- የሀገሪቱን መሪ በዓለም አቀፍ መድረክ ለማጣጣል እና ሀገሪቱን ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና ውሥጥ የሚከቱ ዜናዎችን ማዘጋጀታቸው ተገልጿል።

ተቋማቱ የጋዜጠኝነት መርህን አክብረው እንዲሰሩ መደበኛ እና መደበኛ ባልሆነ መልኩ ተደጋጋሚ ምክርና ማሳሰቢያ ሲሰጥ መቆየቱን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፤ መገናኛ ብዙኃኑ ከድርጊታቸው ከመታቀብ ይልቅ አባብሰው መቀጠላቸውን አስታውቋል።

ለኢትዮጵያዊያን ደህንነት ሲባል የሚዲያ ተቋማቱ በቀጣይ ከዚህ ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ ባለስልጣኑ በተሰጠው ስልጣን እና ሃላፊነት በመጠቀም የሰጣቸውን የሥራ ፈቃድ ለመሰረዝ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል።

በኢመብባ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ ኢድሪስ ተፈርሞ የወጣው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#ካማላ_ሃሪስ

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ክትትል ላይ በመሆናቸው ምክትላቸው ሥልጣን ተረክበዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ክትትል እያደረጉ በመሆኑ ምክትላቸው የሆኑት ካማላ ሃሪስን ፕሬዝዳንትነት ሥራውን መረከባቸውን ዛሬ የዋይትሐውስ ቃላቀባይ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ የጤና ምርመራቸውን ለማድረግ ወደ ሆስፒታል ያቀኑት ዛሬ ሲሆን ከማደንዘዣው እስኪነቁ ድረስ ነው ምክትላቸው የፕሬዝዳንቱን ሥራ እንዲሰሩ የወከሉት።

በአሜሪካ ታሪክ ካማላ ሀሪስ የፕሬዝዳንትነት ስልጣን የያዙ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነዋል።

አሜሪካን እስካሁን ከመሯት ፕሬዝዳንቶች ጆ ባይደን በእድሜ የመሪውን ደረጃ ይይዛሉ ፤ በነገው ዕለት 79 ዓመታቸውን ይደፍናሉ።

NB : በአሜሪካ ፕሬዘዳንትነት ታሪክ እኤአ ከ2002 እስከ 2007 ዓመት ስልጣነ ላይ የነበሩት ፕሬዘዳንት ደብሊው ቡሽ ለህክምና ክትትል ሆስፒታል ሲገቡ ስልጣናቸውን ለምክትላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አሳልፈው ሰጥተው ነበር።

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 7 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,830 የላብራቶሪ ምርመራ 200 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 265 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#Soamlia

ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ያለው የድርቅ ሁኔታ በከፍተኛ ፍጥነት እየተባባሰ መሆኑን UN አስጠንቅቋል።

በዚህም ተነሳ ሶማሊያ ውስጥ 2.3 ሚሊዮን ሰዎች የውኃ እና የምግብ እጥረት ሊገጥማቸው እንደሚችል ተገልጿል።

UNOCHA በድርቁ የተነሳ ወደ 100,000 የሚጠጉ ሰዎች ከቀዬያቸው መፈናቀላቸውን ማስታወቁን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#SouthOmoZone

በድርቅ ምክንያት ከብቶች እየሞቱ ነው።

በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ላይ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ምክንያት 98 ሺህ ሄ/ር ለግጦሽ ሲውል የነበረው መሬት ሙሉ በሙሉ በጎርፍ በመያዙ በተከሰተ ድርቅ የአርብቶ አደሩ የኢኮኖሚ ምንጭ የሆኑ ከብቶቻቸው በግጦሽ ሳር እጦት እየሞቱ ነው።

በዛሬው እለት የዞኑ ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ምህረት አስራቱ የተመራ ቋሚ ኮሚቴ የመስክ ምልከታ በማድረግ ይህንን አረጋግጧል።

በአካባቢው ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ ፎቶ ከላይ ተያይዟል።

Photo Credit : የደቡብ ኦሞ ዞን ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ካማላ_ሃሪስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ክትትል ላይ በመሆናቸው ምክትላቸው ሥልጣን ተረክበዋል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ክትትል እያደረጉ በመሆኑ ምክትላቸው የሆኑት ካማላ ሃሪስን ፕሬዝዳንትነት ሥራውን መረከባቸውን ዛሬ የዋይትሐውስ ቃላቀባይ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ የጤና ምርመራቸውን ለማድረግ ወደ ሆስፒታል ያቀኑት ዛሬ ሲሆን ከማደንዘዣው እስኪነቁ ድረስ ነው ምክትላቸው…
ባይደን ወደ ፕሬዜዳንት ስልጣናቸው ተመለሱ።

ለ85 ደቂቃዎች ያህል በህክምና ክትትል ምክንያት የአሜሪካ ፕሬዜዳንትነት ስልጣናቸውን ለምክትላቸው ካማላ ሃሪስ አስረክበው የነበሩት የ79 ዓመቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ፕሬዝዳንትነት መንበራቸው ተመልሰዋል።

ትላንት ካማላ ሐሪስ በአሜሪካ ታሪክ ለ85 ደቂቃዎች አገሪቱን በመምራት የመጀመሪያዋ ሴት ሆነዋል። በተጨማሪ የመጀመሪያዋ ጥቁር ደቡብ ኤስያዊት ሴት ፕሬዜዳንትም ሆነዋል።

ፕሬዝዳንቱ ሕክምና ላይ በነበሩበት ጊዜ ሐሪስ ከዋይት ሐውስ የምሥራቅ ክንፍ ካለው ቢሯቸው ሥራቸውን ሲያከናውኑ ነበር።

የጆ ባይደን ሐኪም ፕሬዝዳንቱ ደህና እንደሆኑ እና ወደ ሥራቸው መመለስ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

የጆ ባይደን ሐኪም ኬቨን ኦኮነር ፤ ፕሬዜዳንቱ ጤናማና ጠንካራ ናቸው ያሉ ሲሆን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ይችላሉ ብለዋል።

ባይደን ከሆስፒታል ወደ ዋይት ሐውስ ሲመለሱ "ጥሩ ስሜት ይሰማኛል" ብለው መናጋረቸውን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

@tikvahethiopia
ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የከፋ ችግር ላይ ናቸው።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን፥ " አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች የሚገኙ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለከፋ የምግብና የመድሃኒት ችግር በመዳረጋቸው የበርካታ ዜጎች ሕይወት እያለፈ ነው " ሲል አሳወቀ።

የኮሚሽኑ ይህን ያሳወቀው ለኢፕድ በሰጠው ቃል ነው።

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ዕርዳታ ድርጅቶች ሕወሓት በወረራቸው አካባቢዎች በችግር ላይ ለሚገኙ ዜጎች የመድሃኒትና ምግብ ድጋፍ እንዲያቀርቡ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢቀርብላቸውም ድጋፉን አላቀረቡም፡፡

በዚህም ምክንያት በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለከፋ የምግብና የመድሃኒት ችግር በመዳረጋቸው የበርካታ ዜጎች ሕይወት እያለፈ መሆኑን ኮሚሽኑ አሳውቋል።

በዋግኸምራ እና ሌሎች አካባቢዎች በርካታ ማኅበረሰብ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ በመሆኑ በሴፍትኔት ፕሮግራም ይረዳ ነበር ፤ ቡድኑ አካባቢዎችን ከወረረበት ጊዜ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ምንም ዓይነት የምግብና የመድሃኒት አቅርቦት የለም።

በዋግኸምራ፣ በመቄትና በሌሎችም ቦታዎች እየተገኙ ባሉ መረጃዎች በርካታ ወገኖች በረሃብና በመድሃኒት እጦት ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን የሚያመላክቱ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል።

@tikvahethiopia