TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአዲስ አበባ አዲስ የተዘረጋው የፀጥታ አደረጃጀት ምን ይመስላል ?

የአዲስ አበባን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ ታልሞ የህልውና ዘመቻ ወቅትን ያገናዘበ አዲስ የፀጥታ አደረጃጀት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ እየተዘረጋ መሆኑን የአ/አ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለፀ።

ቢሮው ፥ አደረጃጀቱ ከመንደር ጀምሮ እስከ ክፍለ ከተማ ደረጃ የተዋቀረ ነው ብሏል።

የቢሮው የሰላም እሴት ግንባት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አደረጃጀቱ በተመለከተ ለአዲስ ቲቪ በሰጡት ቃል ፥ " አደረጃጀቱ ከመንደር በጓድ ይጀምራል፤ በቀጠና በመቶ አለቃ ይደራጃል፣ በብሎክ በሻምበል ይደራጃል ፣ በወረዳ ደረጃ በሻለቃ ይደራጃል እንዲሁም በክ/ከተማ ደግሞ በብርጌድ ይደራጃል " ብለዋል።

የየአካባቢው ነዋሪዎችንም በአባልነት የሚያቅፍ መሆኑ ምክትል ቢሮ ኃላፊዋ ጠቁመዋል።

ይህ አዲስ አደረጃጀት በሁሉም ክ/ከተማ የሚኖር ማንኛውም የሰላም እና የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ ደጀን የሚሆን ህብረተሰቡ እራሱ ሰላሙን የሚጠብቅበት እንደሆነም ተገልጿል።

በአጠቃላይ በአደረጃጀቱ ከ121 ሺ በላይ ነዋሪዎች በአባልነት የታቀፉ ሲሆን ወቅቱ የሚጠይቀውን የፀጥታ ስጋት ለመቀልበስ ያለመ መሆኑ የአ/አ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" በመማሪያ ቁሳቁስ ዕጥረት ምክንያት መደበኛ ትምህርታቸውን ለመከታተል ተቸግረናል " - የግልገል በለስ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች

በመተከል ዞን የግልገል በለስ ከተማ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በተቋሙ ከፍተኛ የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት በመኖሩ ትምህርታቸውን ለመከታተል መቸገራቸውን አሳውቀዋል።

ተማሪዎቹ በምን ሁኔታ እየተማሩ እንደሆነ ከላይ በፎቶ ተያይዟል።

ተማሪዎቹ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ብቁ ሆነው ለመማር እንቅፋት የሆኑ ፦

• የመማሪያ ክፍል ዕጥረት፣
• የመጽሐፍ ዕጥረት፣
• በቂ የመጸዳጃ ቤት አለመኖርና እና የቤተ ሙከራ ቤቶች ዕጥረት በሰፊው የሚስተዋሉ ችግሮች በመሆናቸው የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲሰጣቸው ተማሪዎቹ ጠይቀዋል።

የተቋሙን ከፍተኛ ችግር ለመቅረፍ የወላጅ መምህራን ህብረት፣ከፍተኛ አመራሮችና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ በመጎብኘት ለወደፊት ጊዜያዊ መፍትሄ ለማበጀት ውይይት አካሂደዋል።

የመተከል ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ጸሃይ ጉዮ ፤በተቋሙ ላይ የተጋረጠው ችግር በዘላቂነት ምላሽ እስኪያገኝ አስቸኳይ ጊዜያዊ መፍትሄ በመስጠት ተማሪዎች መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት መረባረብ እንዳለበት አሳስበዋል።

ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ተቋማትን፣ ባለሃብቶችን እና ግለሰቦችን በማስተባበርና ከፍተቶችን በመሙላት ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል።

ችግሮችን ለመቅረፍ በአጎራባች ትምህርት ቤቶች የመጽሃፍ ድጋፍ ማፈላለግ፣ጊዜያዊ የመቀመጫ ወንበሮችን ማሟላትና የፈረሱ መማሪያ ክፍሎችን ለመጠገን የህብረተሰብ ንቅናቄ በመፍጠር ለመስራት በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Gelgelbeles-11-14

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA : በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ህጻናት የወደፊት ህልማቸውን ያጋራሉ።

በጥቅምት 24 ቀን 2013 በትግራይ ግጭት ተቀስቅሶ ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች ከተስፋፋ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች ተጎድተዋል / ወድመዋል፤ ሌሎች በርካታ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ተፈናቃዮችን አስጠልለዋል።

በአጠቃላይ በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልል ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ወንድ እና ሴት ልጆች የመማር እድል እንዳመለጣቸው ይገመታል።

አስያ አህመድ (እድሜ 11 አመት - ከአፋር ክልል) ፦


በግጭት ሳቢያ ተፈናቅላ አሁን በአፋር ክልል ጭፍራ ከተማ ነው የምትገኘው።

አስያ ፥ "ሰላም ለኔ ትምህርት ቤት መሄድ፣ ከጓደኞች ጋር መሆን እና መጫወት ነው” ትላለች።

“የተኩስ ድምጽ ስሰማ በጣም ፈርቼ ነበር” የምትለው አስያ ፥ “በአካባቢው ያሉ ሰዎችም እየሸሹ ነበር…አስኩማ ወደሚባል ቦታ ሄድን። ከዚያም አንድ ቀን እዚያ አሳልፈን በማግስቱ ጭፍራ ደረስን" ስትል በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ታስታውሳለች።

አስያ እና ቤተሰቧ በጭፍራ ከተማ ትንሽ ቦታ ተከራይተው ነው የሚገኙት።

አስያ አህመድ መቼ ወደ ቤቷ እንደምትመለስ እርግጠኛ አይደለችም።

አስያ ወደፊት ህመም ያለባቸውን ሰዎች ለማከም ዶክተር ለመሆን ተስፋ አድርጋለች።

ተመስገን ኃይለ (እድሜ 11 ዓመት - ከትግራይ ክልል) ፦

ተመስገን ኃይለ የትግራይ ክልል ነዋሪ ሲሆን እድሜው 11 ዓመቱ ነው። ተመስገን እጅግ በጣም ባለብሩህ እእምሮ ያለውና ጎበዝ ልጅ ነው።

ሳይንቲስት መሆን የሚፈልገው ተመስገን "የትምህርት ቆይታዬን ሳስብ እንደ ህልም ነው" ይላል። ጦርነት ባመጣው መዘዝ ተፈናቅሎ አሁን የሚኖረው በመቐለ ሀወልቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ባለች አንድ ክፍል ነው።

መሰረት ተኳር (እድሜ 16 ዓመት - ከአማራ ክልል) ፦

በአካባቢዋ (ቆቦ) ጦርነቱ ሲጀምር ከ2 ወንድሞቿ ጋር ሆና ከእናታቸው ተነጥላ ነው ጦርነት ሽሽት ደሴ የገባችው።

“ግጭቱ ሲጀመር እኛ ቤት ላይ ጥይት ሲዘንብ ነበር። በአካባቢው አንድ ሰውም ተገድሏል። ከአያቶቻችን ጋር ነበርን በኃላም ለደህንነታችን ስንል ሸሸን" ትላለች መሰረት።

"ስለ እናቴ አስባለሁ" የምትለው መሰረት ፥ " እዚያ (ቆቦ) ሰዎች ተገድለዋል የሚሉ ብዙ ወሬዎችን እንሰማለን። ያ በጣም ያሳስበኛል” ስትል ተናግራለች።

መሰረት ትምህርቷን ስትከታተል የነበረው 7ኛ ክፍል ቢሆንም ደሴም ሆነ ሌላ ቦታ ትምህርቷን መቀጠል ትችል እንደሆነ እርግጠኛ አይደለችም። 

የ16 ዓመቷ መሰረት ፥ “ሰላም ለእኔ ከቤተሰብ፣ ከጓደኞችና ከማውቃቸው ሰዎች ጋር መሆን ነው። ሰላም ማለት ትምህርት ቤት ገብቶ ከአስተማሪዎችና ከጓደኞቼ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ማለት ነው” ብላለች።

ሙሉውን ያንብቡ 👉https://telegra.ph/UNICEF-11-05
#SUDAN

ትላንት ሱዳን ውስጥ በነበረ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስትኑን በሚቃወም ከፍተኛ የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የፀጥታ ኃይሎች 4 ሰልፈኞችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል።

የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ (CCSD) ባወጣው ሪፖርት ትላንት በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ 4 ሰዎች በቀጥታ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን ገልጿል።

ሟቾችን በተመለከተ ፦ አንድ በሮያል ኬር ሆስፒታል ውስጥ የነበረ ወንድ ህይወቱ አልፏል፤ የ18 ዓመት ወንድ በምስራቅ ናይል ሆስፒታል ህይወቱ አልፏል ፤ የ35 ወንድ በፊውቸር ሆስፒታል፣ እና የ19 ወንድ ወንድ በአልአርባኢን ሆስፒታል ህይወታቸው አልፏል።

በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ካውንስል ፀጥታ ሃይሎች የተገደሉት የንፁሀን ዜጎች ቁጥር ወደ 5 ከፍ ማለቱንም የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ አሳውቋል።

ሱዳን ውስጥ በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ እየደረሰ ያለው አሰቃቂ ጥቃት በቀጠለበት ወቅት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳቶች ደርሰዋል።

በተጨማሪም የወታደራዊ ጁንታው ሃይሎች የቆሰሉ ንፁሀንን ወደ ሆስፒታሎች ለማጓጓዝ እንቅፋት እየፈጠሩ እንደነበረም ኮሚቴው ሪፖርት አድርጓል።

የወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ካውንስል ፀጥታ ኃይሎች አል አርባን ሆስፒታልን ወረው በስራ ላይ ያሉ ዶክተሮች ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ፣ ሲቪሎችን፣ ቤተሰቦቻቸውን ማቁሰላቸው እና አንዳንዶቹንም እንዳሰሩ ተመላክቷል።

CCSD ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በጁንታው እና ታጣቂዎቹ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ በሚተገብሩ ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየፈፀሙት ላለው ወንጀል ትኩረት እንዲሰጡ ተማጽኗል።

@tikvahethiopia
አሜሪካ የተሳተፈችባቸው ጦርነቶች ...

#Repost

በ21ኛው ክፍለ ዘመን አሜሪካ በበርካታ ሀገራት ውስጥ በተደረጉ ጦርነቶች እጇን አስገብታለች።

በጥቂቱ...

#አፍጋኒስታን

አል-ቃይዳ መስከረም 11 ቀን 2001 በአሜሪካን ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ አሜሪካ ታሊባንን ከስልጣን ለማስወገድ አሜሪካ የአፍጋኒስታንን ወረራ መርታለች። 20 ዓመታት የዘለቀ እጅግ ዋጋ ያስከፈለ ጦርነት ነበር። በመጨረሻ ግን ታሊባን ወደቦታው ተመለሰ። አሜሪካም ጓዟን ጠቅልላ ወጣች።

#ኢራቅ

በፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ዘመን አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ 2003 ኢራቅን በመውረር ሳዳም ሁሴን ከሥልጣን አስነስታለች። በኢራቅ ጦርነት በርካቶች አልቀዋል፣ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ኢራቅ ዛሬም አስተማማኝ ሙሉ ሰላም የላትም። ለዳግም ግንባታም ደፋ ቀና እያለች ነው።

#ሊቢያ

የአሜሪካና የአውሮፓ አጋሮች እኤአ በ 2011 በሊቢያ የአየር ዘመቻ ከፍተው ነበር ፤ ጥቃቱ ሙአመር ጋዳፊ በአረብ አብዮት ለመቃወም በተነሳሱ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ግፍ ለመከላከል በሚል ነው ፤ የእነ አሜሪካ መዘቻ ጋዳፊን አወረደ ፣ ሊቢያ ግን ወደ ትርምስና ቀውስ ገባች፤ ዛሬም እዛው ናት።

#ሶሪያ

አሜሪካ ከሌሎች አጋሮቿ ጋር ሆና በሶሪያ ጦርነት ውስጥም እጇ ያለበት ሲሆን በሶሪያ የሚንቀሳቀሱ የበሽር አል አሳድ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት በምትወስደው እርምጃ የሶሪያ ከተሞች ክፉኛ አውድማለች።

#የድሮን_ጥቃቶች

አሜሪካ ሽብርን ለመዋጋት በሚል በፓኪስታን፣ የመን፣ ሱማሊያ፣ ሊቢያ የድሮን ጥቃቶችን ፈፅማለች (አሜሪካ ከፍተኛ የሰራዊት ቁጥር አላሰፈረችም)።

እነሊቢያ፣የመን፣ ሱማሊያ ጦርነት ምስቅልቅላቸውን አውጥቶት ዛሬም ማገገም ያልቻሉ ለደህንነት አስጊ ሀገራት ሆነው ቀርተዋል።

@tikvahethiopia
" ሁለቱም ወገኖች ሰላም፣ ጸጥታና የኢትዮጵያ መረጋጋት ምኞታቸው መሆኑን ገልፀውልኛል " - ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ

በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የመንግስትን እና የህወሃትን አመራሮችን ማነጋገራቸውን ካስታወቁ በኋላ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ኦባሳንጆ ሁሉም ወገኖች ወታደራዊ ፍልሚያውን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል፡፡

ከመንግስትም ሆነ ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀው ህወሃት በኩል የሰላም ፍላጎቶች መኖራቸውን የገለጹት ከፍተኛ ተወካዩ ‘የሰላም መንገዱ ምን ይሁን’ የሚለው ግን ልዩነታቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የአፍሪካ መሪዎችና ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ሕብረቱ የጀመረውን የማሸማገል ጥረት እንዲደፉ እና ግጭቱን ሊያባብሱ ከሚችሉ ነገሮች እንዲቆጠብም ኦባሳንጆ ጥሪ አቅርበዋል።

ኦባሳንጆ፥ "ሆን ተብሎም ይሁን ባለማወቅ ግጭቱን የሚባብሱና ወደከፋ ደረጃ ከሚያደርሱ ንግግሮች መቆጠብ ያስፈልጋል" ብለዋል ።

ኦባሳንጆ፤ ውጊያው ከቆመ የንግግር ዕድል እንደሚኖር የገለጹ ሲሆን አሁን ባለው ሁኔታ ውጊያ እየተደረገ ግን ለመነጋጋር የሚመች እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ኦባሳንጆ ፥ የኦሮሚያ እና አማራ ክልል አመራሮችን ማግኘታቸውን በመግለጫቸው ላይ የገለፁ ሲሆን በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የአፋር ክልል አመራሮችን እንደሚያገኙ አሳውቀዋል።

ኦባሳንጂ ይህ የማሸማገል ስራ እንዲሳካ ቁርጠኛ እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን ፦
- #የኬንያ
- #ኡጋንዳ
- #ጅቡቲ
- #ደቡብ_ሱዳን
- #ሶማሊያ እና ሱዳን መሪዎችን ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አስማሚ ሁኔታ ይፈጠራል ብዬ አስባለሁ ያሉት ኦባሳንጆ ሁለቱም ወገኖች ሰላም፣ ጸጥታና የኢትዮጵያ መረጋጋት ምኞታቸው መሆኑን እንደገለጹላቸው አሳውቀዋል።

Credit : #Al_AIN
Pic : AU

@tikvahethiopia
ኡሁሩ ኬንያታ አዲስ አበባ ገቡ።

የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ " ውድ ወንድሜ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ወደ ሁለተኛው ቤትዎ እንኳን ደህና መጡ " ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia
አንቶኒ ብሊንከን ዛሬ ናይሮቢ ይገባሉ።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከዛሬ ጀምሮ ሦስት የአፍሪካ አገራትን ይጎበኛሉ።

ሚኒስትሩ ኬንያ፣ ናይጄሪያና ሴኔጋልን ነው በይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው የሚጎበኙት።

ብሊንከን ጉብኝታቸው የ6 ቀናት ሲሆን ጉብኝታቸው ከናይሮቢ የሚጀምሩ ሲሆን ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመገናኘት በኢትዮጵያ፣ በሶማሊያ እና በሱዳን ያሉ ጉዳዮችን ጨምሮ በሌሎች ርዕሶች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኬንያው ፕሬዜዳንት ትላንት ኢትዮጵያ ነበሩ።

የኬንያ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ጉብኝቱን በማስመልከት ኡሁሩ ኬንያታ ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር መወያየታቸውን ገልጿል።

ኬንያታ እሁድ ከሰዓት በኋላ በአዲስ አበባ ለሰዓታት ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው ማምሻውን ወደ ናይሮቢ መመለሳቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን መዘገባቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia