TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

ትላንትና የፍትህ ሚኒስትር ዶክተር ጌዴዎን ጢሞቲዮስ እና የጠ/ሚ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ለአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ለሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በኦን ላይን ማብራርያ ሰጥተው ነበር።

የትላንቱ ማብራሪያ አላማ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ውስብስብ ሁኔታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማስረዳት ነው።

የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዴዎን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መናሻውን እና ሂደቱን በዝርዝር ያብራሩ ሲሆን በፍቃደኝነት ህወሓት ጦርነቱን ሙሉ በሙሉ አቁሞ ከወረራቸው የአማራ እና አፋር ክልሎች ካልወጣ ምንም አይነት ድርድር እንደማይኖር አስረግጠው ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ህወሓት በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ጥቃት ለማድረስ እያሴረ መሆኑን መንግስት የተረጋገጠ መረጃ እንዳለው አሳውቀዋል።

" ህወሓት በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች ጥቃት የማድረስ ሙኩራ እንደሚያደርግ የተረጋገጠ የደህንነት መረጃ ደርሶናል " ሲሉ ነው የተናገሩት ሚኒስትሩ።

ቢልለኔ ስዩም ፥ የፌዴራሉን መንግስት እና ህወሓትን እኩል ደረጃ ታይተው ለድርድር እንዲቀርቡ መጠየቁ ስህተት ነው ብለዋል።

የሀገሪቱ መንግስት በሽብርተኝነት የፈረጀውን ታጣቂ ቡድን የሚያደርሰው ጥቃት በዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ በበቂ ሁኔታ ባለመወገዙ ወቅሰዋል።

ቢልለኔ የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የተመረጠ እና ሰፊ ድጋፍ ያለው መሆኑን ገልፀው የተጠና በሚመስል መልኩ የሚቀርበው ክስ አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ካደረገ በኃላ የእርዳታ እቃዎች ወደትግራይ እንዲገቡ ቢያደርግም ህወሓት ለውጊያ ተግባር እንዳዋላቸው ገልፀዋል።

ሁለቱም የኢትዮጵያ ተወካዮች ህገመንግስቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ጦር ማደራጀት ስልጣን የሰጠው ለፌዴራል መንግሥት ብቻ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ከህወሓት ጋር ድርድር እንዲደረግ ህወሓት የያዘውን ትጥቅ መፍታቱ የማያደራድር ቅድመ ሆኔታ መሆኑን አበክረው ተናግረዋል።

ያንብቡ 👉https://telegra.ph/ETHIOPIA-11-06
#AddisAbabPolice

የአዲስ አበባ ፖሊስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሰረት በማድረግ ለከተማው ፀጥታ ስጋት ናቸው
ያላቸውን የግለሰቦች መኖሪያ ቤቶች፣ ንግድ ቤቶች እና ድርጅቶች ብርበራ ማድረጉን አሳውቋል።

ፖሊስ አደረኩት ባለው ብርበራ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎችና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በኤግዚቢትነት መያዙን ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ከህዝብ የደረሰኝን መረጃ በመቀበልና በመተንተን በ11ዱ ክ/ከተሞች የህወሃት ደጋፊና ናፋቂ በሆኑ እና በተጠረጠሩ ግለሰቦች እንዲሁም በመኖሪያ ቤቶች ፣ ንግድ ቤቶችና ድርጅች ላይ ከጥቅምት 23 - 25 ቀን 2014 ዓ/ም ባሉት 3 ቀናት ውስጥ ብርበራ ና ፍተሻ አድርጊያለሁኝ ብሏል።

በዚህም፦
- የተለዩ የጦር መሳሪያዎች
- ክላሽ- ኮቭ ጠብመንጃ
- በተሽከርካሪ በድብቅ ተጭነው የገቡ መትረየስ ጠብመንጃዎች
- የብሬን ጥይቶች
- ቦንብ
- SKS ጠብ-መንጃ
- በርካታ የተለያዩ የጦር መሳሪያ ጥይቶች
- የጦር ሜዳ መነፅሮችን
- የተለያዩ የፀጥታ አካላት መገልገያ ቁሳቁሶች
- የመገናኛ ሬዲዮ ቻርጀር
- ወታደራዊ አርማዎችና ወታደራዊ ኮምፓስ ይዣለሁኝ ብሏል።

ከእነዚህ የጦር መሳሪያዎችና የፀጥታ አካላት የደንብ አልባሳት በተጨማሪ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከህወሃት ደጋፊዎችና ናፋቂዎች እጅ በህግ ከሚፈቀደው መጠን በላይ የተከማቸ የአሜሪካ ዶላር ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችና የዝሆን ጥርስም በብርበራ ወቅት ይዣለሁ ሲል ገልጿል።

በተለያዩ ተቋማት ስም የተዘጋጁ ሀሰተኛ ሰነዶች ከእነ ማዘጋጃ መሳሪያዎቹ መያዙን የገለፀው ፖሊስ በግለሰቦች እጅ መገኘት የማይገባቸው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሰነዶችን ጨምሮ በርካታ ፓስፖርቶች እንዲሁም የተለያዩ ሃሰተኛ ሰነዶች በቁጥጥር ስር አውያለሁ ብሏል።

More : telegra.ph/AA-11-06-7

@tikvahethiopia
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ህወሓትን የሚያወግዝ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ ይደረጋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ፥ "የሀገርን ህልውናን እየተፈታተነ ያለውን ሽብርተኛውን የህወሃት ቡድን ለማውገዝ እና የሀገርን አንድነት ለማስከበር የሚፋለመው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ያለውን እርምጃ ለመደገፍ ነገ ጥቅምት 28 ቀን 2014 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል" ሲል አሳውቋል።

ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረሰ በመስቀል አደባባይ እና በዙሪያው የሚገኙ መንገዶች ለተወሰነ ሰዓት ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፦

• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ

• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይና ታች

• ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት

• በቸርችልር ጎዳና ወደ መ/አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ ሆቴል

• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደመ/አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር መብራት

• ከሜክሲኮ አደባባይ፣ በሰንጋ ተራ በድሉ ህንፃ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት

• ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መ/ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ ለቀላል ተሽከርካሪዎች ደግሞ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ ዝግ ይሆናሉ።

መንገዶቹ የሚዘጉት ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ነው። ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ በመስቀል አደባባይና በዙሪያው ባሉ መንገዶች ተሽከርካሪ ለእረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ነገ የሚዘጉ መንገዶች ! ነገ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ህወሓትን የሚያወግዝ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ ይደረጋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ፥ "የሀገርን ህልውናን እየተፈታተነ ያለውን ሽብርተኛውን የህወሃት ቡድን ለማውገዝ እና የሀገርን አንድነት ለማስከበር የሚፋለመው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ያለውን እርምጃ ለመደገፍ ነገ ጥቅምት 28 ቀን 2014 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ…
#HappeningNow

በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ህወሓትን እና ሸኔን የሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ነው።

በሰልፉ ላይ የውጭ ሀገር ጣልቃ ገብነትንና የውጭ ሀገር መገነኛ ብዙሃንን አጥብቀው የሚተቹ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የተፃፉ የተለያዩ መፈክሮች በሰልፈኞች ተይዘዋል።

ሰልፈኞች ካያዟቸው መፈክሮች መካከል ፦

- የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ኤምባሲዎች ከኢትዮጵያ ይውጡና ቦታው ለልማት ይዋል።

- CNN ፣ BBC በኢትዮጵያ ጉዳይ ሀሰተኛ ዜናዎቻችሁን አቁሙ።

- የአውሮፓ መንግስታት መሰሪነታችሁን አቁሙ ፤ በግልፅ ግቡኑና ህወሓትን በጦር ሜዳ አግዙት።

- ኢትዮጵያ በውክልና ጦርነት አትንበረከክም።

- SHAME ON YOU USA !

- You are liar you can't repeat #Libya in Ethiopia again.

- Americans don't come back we are better off without you.

- #No_More የሚሉት ይገኙበታል።

በተጨማሪም ሰልፈኞቹ ከያዟቸው ሌሎች መፈክሮች መካከል ፦

- ይህ ትውልድ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ያስከብራል።

- የቀኝ ገዢዎች ሀሳብ ይመክናል ፤ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።

- ክብር ለመከላከያ ሰራዊት

- ኢትዮጵያን ማሸነፍ አይቻልም።

- እኔ የሀገሬ ጠባቂ ነኝ።

- ከኢትዮጵያዬ 🇪🇹 የሚበልጥብኝ የለም።

- እኛ እያለን ኢትዮጵያ ሀገራችን በፍፁም አትፈርስም፤ የሚሉት ይጠቀሳሉ።

ፎቶ ፦ ከአ/አ ፕሬስ ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ህወሓትን እና ሸኔን የሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ነው። በሰልፉ ላይ የውጭ ሀገር ጣልቃ ገብነትንና የውጭ ሀገር መገነኛ ብዙሃንን አጥብቀው የሚተቹ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የተፃፉ የተለያዩ መፈክሮች በሰልፈኞች ተይዘዋል። ሰልፈኞች ካያዟቸው መፈክሮች መካከል ፦ - የአሜሪካ…
#Update

" ሰልፉ በሰላም ተጠናቋል " - የአዲስ አበባ ፖሊስ

በመስቀል አደባባይና በዙሪያው የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ #በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፕሮግራሙ በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማው ነዋሪ በተለይ ደግሞ የሰላማዊ ሰልፉ ታዳሚዎች ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር በማድረጋቸው ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።

በተጨማሪ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ላሉ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ሰልፉን ላስተባበሩ እና ለመሩ አካላት በሙሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል።

@tikvahethiopia