TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጨማሪ ሱዳን በአፍሪካ ህብረት ከአባልነት መታገዷን ተከትሎ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ የድርድር ሂደት ላይ እንደማትሳተፍ ተሰምቷል። በየትኞቹም የድርጊት መርሃ ግብሮቹ እንዳትሳተፍ በአፍሪካ ህብረት የታገደችው ሱዳን የአፍሪካ ህብረት መር በሆነው የግድቡ የድርድር ሂደት እንደማትሳተፍ አል ዐይን ኒውስ የአማርኛው አገልግሎት ከህብረቱ ምንጮች መረጃ ማግኘቱን አሳውቋል። ዜና ወኪሉ እገዳው…
#SUDAN

ስለ ሱዳን 5 ጉዳዮች ፦

1ኛ. የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ለሱዳን የተመደበውን 700 ሚሊዮን ዶላር እንደሚቋረጥ አሳውቋል።

2ኛ. የዓለም ባንክ ለሱዳን የሚያደርገውን ድጋፍ አቁሟል።

3ኛ. አውሮፓ ህብረት ሱዳን ወደነበረችበት የሽግግር ሂደት የማትመለስ ከሆነ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያቋርጥ፤ ጠንካራ እርምጃዎችንም እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

4ኛ. አውሮፓ ህብረት ሌ/ጄ አብዱል ፈታ አልቡርሃን በሚመሩት ጦር በተፈፀመ መፈንቅለ መንግስት ከቦታቸው ገለል የተደረጉት ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ አሁንም የሱዳን ህጋዊ መሪ ናቸው ብሏል።

5ኛ. ሱዳን በአፍሪካ ህብረት ከማንኛውም ተሳትፎዋ ታግዳለች ፤ ይህም በህብረቱ መር የሚካሄደውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድርን ይጨምራል።

Source : VOA/AFP/REUTERS/ALAIN

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በትግራይ ክልል ጀምሮ ወደአፋር እና አማራ ክልሎች የሰፋው ጦርነት 1 አመት ሊደፍን ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርቶታል።

ጦርነቱ ከጀመረ አንስቶ ሚሊዮኖችን ችግር ላይ ወድቀዋል፤ አሁን ድረስ የምን ያህል ዜጎች ህይወት እንደረገፈ ለማወቅ አዳጋች ነው።

በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ፣ አማራና አፋር ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ሚሊዮኖች ሜዳ ላይ ወድቀዋል።

ጦርነቱ ከትግራይ ወደ አማራ እና አፋር ከሰፋ በኃላ ቀደም ብሎ በትግራይ ክልል በችግር ላይ የነበሩ ዜጎችን ጨምሮ የተጎጂዎችን ቁጥር በእጅጉ እንዲያሻቅብ አድርጓል።

የኢንተርኔት፣ የስልክ ግንኙነት አለመኖር ስለዜጎች ደህንነት እንኳን ለማወቅ ትልቅ ፈተና ሆኗል።

በተለይ ይህ ጦርነት በወሎ ላይ ከፍተኛ ችግርን ያስከተለ ሲሆን ተፈናቃዮች የችግሩ መጠን ከሚነገረው በላይ ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በወሎ ችግር ላይ የወደቀው ህዝብ ያለበት ሁኔታ በተገቢው ልክ ዓለም ያላወቀው እንደሆነ ገልፀው፤ አካባቢውን ሄዶ ለተመለከተው ሰው የችግሩን ስፋትና አስከፊነት በትክክል መገንዘብ ይችላል ብለዋል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት ደግሞ በተለያዩ ቦታዎች ግጭቶች መባባሳቸውን ተከትሎ የተሻለ ሰላም አለባቸው ወደተባሉ አካባቢዎች እናቶች ልጆቻቸውን አዝለው፣ አቅመ ደካሞች በቻሉት ድጋፍ ሁሉ እየገቡ፤ ለደህንነታቸው ሲሉም እየሸሹ ነው።

በተለያዩ ቦታዎች ምንም ድጋፍ ሊያገኙ በማያስችል ሁኔታ የሰፈሩ ሺዎች አሉ።

ቃላቸውን የሰጡን ተፈናቃዮች ለዚህ ሁሉ ችግር አስቸኳይ መፍትሄ ካልተበጀ ጊዜው በረዘመ ቁጥር በንፁሃን ላይ የሚደርሰው እጅግ የከፋ መከራ ብዙ ጉዳት የሚያድረስ ነው ብለዋል።

NB : አማራ ክልል በተፈተው ጦርነት ከ750 ሺ በላይ ሰዎች፤ በአፋር ከ200 ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

ፎቶ : ሶሻል ሚዲያ (የወሎ ተፈናቃዮች)

@tikvahethiopi
#MoE

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን ለማዘመን መንግስት ትኩረት እንደሚሰጥ ገለፁ።

ሚኒስትሩ በአሁን ሰዓት ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከተወጣጡ አመራሮች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው።

ተቋማቱ የአስተዳደር እና የመሰረተ ልማት ችግሮች እንደሚስተዋልባቸው ያነሱት ፕሮፌሰር ብርሃኑ የላብራቶሪ እና የአይቲ መሰረት ልማት አለመሟላት ከሚገጥሟቸው ፈተናዎች ዋነኞቹ ናቸው ብለዋል።

አብዛኛዎቹ ዩኒቨርስቲዎች ከትምህርት ጥራት ጋር በተያያዘ የሚነሳባቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲችሉ ያሉባቸውን ክፍተቶች በአፋጣኝ ለይተው የመፍትሄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ፕሮፌሰር ብርሃኑ መመሪያ ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል ዩኒቨርስቲዎች የፌዴራል ተቋማት እንጂ የክልል ተቋማት አይደሉም ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ህዝብን እንጂ ማንኛውንም የፖለቲካ አቋም አራማጅ መሆን እንደሌለባቸው አሳስበዋል።

ከመንግስት ተጽዕኖ ነጻ የሆነ አሰራር ለመመስረት እንዲሁም አካባቢያዊነትን፣ ሌብነትንና የሃብት ብክነትን ለማስቀረትም ዩኒቨርስቲዎቹ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

መረጃው የኢብኮ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቦረና ነዋሪዎች ያሉበት ሁኔታ ፦ - 539,679 ዜጎች የውሃ እጥረት ገጥሟቸዋል ፤ ከነዚህ ውስጥ 177,553 ዜጎች ብቻ በቦቴ ውሃ አግኝተዋል። - በምግብ እጥረት 6,398 ህፃናት ፣ 9,078 እናቶች ፣ 2,226 አዛውንቶች ላይ የጤና ችግር ታይቷል። - 188,864 ሰዎች የምግብ እርዳታ አግኝተዋል ፤ 166,136 ዜጎች ተጨማሪ እርዳታ ይፈልጋሉ። - በድርቅ ምክንያት 7,540 ከብቶች ሞተዋል…
#BORENA

በቦረና አካባቢ በተከሰተ ድርቅ የዱር እንስሳት በውሃ እጥረት ለአደጋ ተጋልጠዋል።

የቦረና ብሔራዊ ፓርክ በኢትዮጵያ የትልቁ የሜዳ አህያ (Gravy's Zebra) ሁለተኛው ወሳኝ ቀጣና ሲሆን ገረኑክ፣ የቆላ አጋዘን፣ የሜዳ ፍየሎች፣ ሰጎን እና የበርካታ አእዋፍ መገኛ ነው።

የብሔራዊ ፓርኩን መገኛ ጨምሮ በቀጠናው በተከሰተ ድርቅ ምክንያት የዱር እንስሳቱ የሚመገቡት እና የሚጠጡት ውሃ ከቤት እንስሳት ጋር በመጋራታቸው እጥረት ተከስቷል።

ችግሩ እንዲቀረፍም በአጭር ጊዜ በተወሰደው መፍትሄ ከዞኑና ወረዳዎች ጋር ከአካባቢው ማህበረሰብ በመነጋገር የውሃ አቅርቦት እንዲኖር ማድረግ ተችሏል።

የቤት እንስሳቱ በቀን እንዲጠጡ እና ሌሊቱን ደግሞ የዱር እንስሳቱ ሳይረበሹ ውሃ የሚያገኙበትን አማራጭ እያካሄዱ እንደሆነ ፖርኩ ገልጧል።

የፓርኩ ጽ/ቤት ተጨማሪ ስራዎችን ለማከናዎን የሎጅስቲክ ከፍተኛ ችግር እንደገጠመው አስረድተው የሚመለከታቸው አካላት በአስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል " አረንጓዴ ሀሳቦች " ገፅ አስነብቧል።

በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ በርካታ ዜጎቻችን ችግር ላይ የውደቃቸውን ፤በርካታ እንስሳትም መሞታቸውን ፤ አሁንም አደጋ ላይ ያሉ ለመኖራቸውን ከዚህ ቀደም መረጃ መለዋወጣችን አይዘነጋም።

በድርቅ ምክንያት ችግር ለገጠማቸው ወገኖች ለመድረስ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ዜጎች ርብርብ እያደረጉ መሆኑን ለማውቅ ችለናል።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ! በሰላም እጦትና አለመረጋጋት ሳቢያ በንፁሃንና በሀገር ደህንነት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እንዲያበቃ ህዝበ ምዕመኑ ፀሎትና ተማፅኖውን እንዲያበረታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቅርባለች። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ ምልዓተ ጉባዔን አስጀምረዋል። ምዕመናንና ሀገርን መጠበቅ…
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥቅምት 11 ቀን 2014ዓ.ም. ጀምሮ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ሲያካሂድ ሰንብቶ ለቤተ ክርስቲያኗ እና ለሀገሪቱም ይበጃሉ ያላቸውን ማህበራዊና መንፈሳዊ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በዚሁ መሠረት ፦

- የ2014 ዓ.ም. የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ መልእክት አሁን በአገሪቱ እየታየ ባለው ጦርነት እና የርስበርስ ግጭት ላይ ያተኮረ ሲሆን፡-

• ጦርነቱ በወንድማማቾች መካከል እየተደረገ ያለና ሀዘኑን የከፋ ያደረገው መሆኑ፣ 

• በዚሁ ጦርነትና ግጭት በርካታ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ለሞት ለስደትና ለረሀብ መዳረጋቸው፣ 

- በዚህ ምክንያት በአገሪቱ እየታየ ያለው የኑሮ ውድነት አገራዊ ልማት ላይ እያደረሰ ያለው ተጽእኖ ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ ይህ ጦርነትና ግጭት ተወግዶ በአገሪቱ ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን ከሁሉም በላይ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ይቅርታ ምሕረት መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑን የሚያስገነዝብ በመሆኑ ጉባኤው ይህንኑ መልእክት ተቀብሎ በመላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተግባራዊ እንዲሆን ወስኗል፡፡  

- በኢትዮጵያ አሁን ያለው የሰላም እጦትና ጦርነት ወደፊትም ሊያስከትል የሚችለው ችግር ከፍተኛ መሆኑ ስለታመነበት በተቻለ አቅም ዜጐች ሁሉ ለአገራዊው አንድነትና ሰላም መገኘት ዘብ እንዲቆሙ የየበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አሳልፏል።

- በአገራዊ የሰላም እጦት እየተደረገ ያለውን ጦርነት ምክንያት አድርገው ከአገር ውጭ የሚገኙ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናትና ካህናት አገራዊ ሰላም ላይ ጥላ በሚያጠላ አገራዊና ሕዝባዊ አንድነትን በሚያፈርስ መልኩ ቅስቀሳ ማድረጋቸው ከቤተ ክርስቲያንና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ነን ከሚሉ በፍጹም የማይጠበቅ ሆኖ እንዳገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል።
በመሆኑም ፦
- በአውስትራልያ፣
- በካናዳ፣
- በአውሮፓና በአሜሪካ ሁነው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም እየፈጸሙ ካለው አገራዊና ሕዝባዊ አንድነት ከሚያደፈርስ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ቅዱስ ሲኖዶስ እያሳሰበ አሁንም ወደ ሰላሙና አንድነቱ እንዲመለሱ ጥሪውን አቅርቧል።

ይህንንም የሰላም ተልዕኮ የሚያስፈጽም በውጭው ዓለም የሚገኙ ብፁዓን አባቶች የሚመሩት የጋራ የሰላም ልዑክ እንዲቋቋም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 

- በጦርነት ምክንያት ከቄያቸው ለተፈናቀሉና በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ችግር ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ዕርዳታ እንዲሆን ብር 50,000,000.00 (ሃምሳ ሚሊየን ብር) በቤተ ክርስቲያናችን ስም ችግሩ ለደረሰባቸው ወገኖች እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡  

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/EOTC-10-28
TIKVAH-ETHIOPIA
ከወራት በፊት የጀመረው ምርመራ ተጠናቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) እና ኢሰመኮ ምርመራ ቡድን በትግራይ ያካሄዱትን የመስክ ስራ አጠናቀዋል። ሁለቱ ተቋማት የመስክ ምልከታ አድርገው መረጃዎችን ፤ ቃለመጠይቆችን እና ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን የመሰብሰብ ስራዎችን ማጠናቀቃቸውን ተገልጿጻ። የመስክ ምርመራ ስራው የተካሄደው ፦ - በመቐለ - ውቅሮ፤ - ሳምረ፤ - አላማጣ፤ - ቦራ፤ - ማይጨው፤…
#Update

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ግጭት ዙሪያ በጋራ ያካሄዱት ምርመራ ሪፖርት ጥቅምት 24/2014 ዓ/ም ይፋ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ እንዲሁም የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት የጋራ ሪፖርቱን ግኝቶች፣ መደምደሚያዎች እና ምክረ ሃሳቦችን ለማቅረብ በአዲስ አበባ እና በጄኔቫ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SUDAN ስለ ሱዳን 5 ጉዳዮች ፦ 1ኛ. የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ለሱዳን የተመደበውን 700 ሚሊዮን ዶላር እንደሚቋረጥ አሳውቋል። 2ኛ. የዓለም ባንክ ለሱዳን የሚያደርገውን ድጋፍ አቁሟል። 3ኛ. አውሮፓ ህብረት ሱዳን ወደነበረችበት የሽግግር ሂደት የማትመለስ ከሆነ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያቋርጥ፤ ጠንካራ እርምጃዎችንም እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። 4ኛ. አውሮፓ ህብረት ሌ/ጄ…
የሱዳን ወታደራዊ ጁንታ በዚህ ሳምንት ያደረገውን የመንግስት ግልበጣ በመቃወም የተናገሩ ቢያንስ 6 አምባሳደሮችን ከሥራና ኃላፊነታቸው ማበረሩን የመንግስት ቴሊቪዥን ዛሬ ማሳወቁን የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

ቴሌቪዥን ጣቢያው ጀኔራል አብዱፈልታ አል ቡርሃን በአሜሪካ ፣ አውሮፓ ህብረት፣ ቻይና ፣ ኳታር እና ፈረንሳይ እንዲሁም በጀኔቭ የተባበሩት መንግሥታት የሱዳን ተወካይ መልክተኛን ማባረራቸውን ገልጿል፡፡

በዚህ ሳምንት አንድ ላይ የተሰባሰቡ የሱዳን ዲፕሎማቶች ባወጡት የጋራ መግለጫ ባላፈው ሰኞ ጠ/ሚ ሀምዶክና ባለቤታቸው መታሰራቸውን፣ ጀኔራል አልቡርሃን የልዕልና ምክር ቤቱን በመበተን፣ በአገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸውን አውግዘዋል፡፡

አሁን “የቀደሞ” የተባሉት በተባበሩት መንግሥታት የሱዳን አምባሳደር ኑረዲን ሳቲ፣ የሱዳንን ወታደራዊ ጁንታን የማይቀበሉት መሆኑን ትናንት ረቡዕ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

“በዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ውስጥ ከሚገኙ ጓደኞቼ እዚህ በአሜሪካም ሆነ በተለያዩ የዓለም ክፍል ከሚገኙ የዳያስፖራ አባላት ጋር፣ ይህ መፈንቅለ መንግሥት ተቀባይነት የሌለው በመሆኑን በአስቸኳይ እንዲቀለበስ እሰራለሁ” ብለዋል፡፡

አልቡርሃን ወታደራዊ ኃይሉ እኤአ በሀምሌ 2023 ከሚደረገው ምርጫ በኋላ ሥልጣኑን ለተመረጠው የሲቪል መንግሥት እንደሚያስረክቡ ተናግረዋል፡፡

ወታደራዊ ክፍሉ የሲቪሉን የሽግግር መንግስት የገለበጠው የእርስ በርስ ጦርነትን ለማስወገድ መሆኑንም መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ሱዳን ውስጥ በርካታ የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች እና ግለሰቦች እየታሰሩ መሆኑ ተግሯል ፤ ተቃውሞው አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirForce የኢትዮጵያ አየር ኃይል በትግራይ ክልል የሚወስደውን የአየር ጥቃት የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለት መቐለ ኵሃ አካባቢ የአየር ጥቃት ፈፅሟል። የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳሳወቀው ፥ ዛሬ መቐለ ኲሃ አካባቢ የተፈፀመው የአየር ድብደባ ኢላማው የልዩ ኃይል ፖሊስ ማሠልጠኛ ተቋም ነው። የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ በአየር…
#Mekelle : የኢትዮጵያ አየር ኃይል በትግራይ ክልል TPLF ለሽብር ተግባር ይጠቀምባቸዋል ያላቸውን ቦታዎች በአየር መደብደቡን የቀጠለ ሲሆን ዛሬም በመቐለ የአየር ድብደባ ተፈፅሞ ነበር።

የኢትዮጵያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ በአየር የተደበደበው የመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ሁለተኛ ክፍል መሆኑን አሳውቋል።

ድብደባ የተፈፀመበት የመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ሁለተኛው ክፍል የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ወታደራዊ መሳሪያዎችን የሚጠግንበት መሆኑንም መንግስት አሳውቋል።

የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከዛሬው የአየር ጥቃት ጋር በተገናኘ የሰዎች ህይወት ማለፉንና መጎዳታቸውን ገልጿል።

የሆስፒታሉ የድንገተኛ ህክምና ክፍል ኃላፊ ግርማይ ለገሰ ጥቃቱን በተመለከተ ለጀርመን ድምፅ በሰጡት ቃል ፥ 28 ታካሚዎች ወደ ሆስፒታል እንደመጡ ከ28ቱ 6ቱ እዛው ሞተው የመጡ ናቸው ብለዋል። ከ28ቱ መካከል 14 ሴቶች እና 10 የሚደርሱ ህፃናት እንደሚገኙበት አክለዋል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ በዛሬው ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ ተብሎ የሚነገረው ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በተለያየ የሀሰተኛ መረጃ ለማምታት የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው ብለውታል።

ወ/ሮ ሰላማዊት፥ " ጥቃቱ በዋነኝነት ወታደራዊ አገልግሎትን የሚሰጠው እንዲሁም የህወሓት ወታደራዊ መሳሪያዎች የሚጠገንበት እና የሚያከማችበት ቦታ (መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ሁለተኛ ክፍል) ብቻ ኢላማ አድርጎ ነው የተንቀሳቀሰው፤ ያንን ኢላማውን ብቻ ዛሬ ያሳካው። ከዚህ በተጨማሪ የሚወጡት መረጃዎች በሙሉ ዛሬ ከተፈፀመው ተልእኮ ጋር የሚገናኙ አይደሉም" ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

#UPDATE የሟቾች ቁጥር 10 መድረሱን የሆስፒታል ምንጮች አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 16 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,578 የላብራቶሪ ምርመራ 386 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 486 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
Facebook ➡️ Meta

ፌስቡክ ኩባንያ ስሙን ወደ ሜታ (Meta) እንደሚቀይር የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ማርክ ዙከርበርግ ዛሬ አሳውቀዋል።

በኩባንያው ስር የሚገኙት ፦
- ፌስቡክ፣
- ዋትስአፕ፣
- ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር የቀደመ ስማቸውን ይዘው ይቀጥላሉ።

ምንጭ፦ The Verge

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AGOA : ኢትዮጵያ በ "AGOA" በኩል ያላት ተጠቃሚነት ላይ አሜሪካ በቅርቡ ውሳኔ ላይ እንደምትደርስ ካትሪን ታይ (የንግድ ተወካይ) ተናግረዋል። ኃላፊዋ በይፋዊ መንገድ እና በግብረሰናይ ድርጅቶች በኩል የሚደርሱን መረጃዎች አበረታች አይደሉም፤ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያ ቢልለኔ ስዩም፥ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ…
#AGOA : የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አማካሪና ዋና የንግድ ተደራዳሪ ማሞ ምህረቱ ኢትዮጵያ ከAGOA እንድትወጣ ከሚሰሩት መካከል የሕወሃት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም አንዳንድ አሜሪካ መንግስት ውስጥ ያሉ ሰዎችም እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

አቶ ማሞ ይህን ያሉት ከአል ዓይን አማርኛው ክፍል ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ነው።

ኢትዮጵያ ከAGOA እንድትወጣ የሚሰሩት እንነማን እንደሆኑ ? ከዜና ወኪሉ የተጠየቁት የጠ/ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ ፦ አንደኛ የሕወሃት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች እንደሆኑ አመልክተዋል።

እነዚህ ሰዎች የሚከራከሩ ሰዎችን በመቅጠር በአሜሪካ ውስጥ ያሉ የኮንግረንስ ሰዎችን እንዲያሳምኑ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ በይፋ የሚታወቅ ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ ሰዎች (አሜሪካ መንግስት ውስጥ ያሉ ሰዎችም) እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት ትግራይን አስመከልክቶ ባለው ግጭት ውስጥ የተለያዩ የፖለቲካ ሃሳቦችን፤ የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች እንዲሟሉ በማድረግ AGOAን እንደ አንድ የውጭ ፖሊሲ መሳሪያ አድርጎ የማስቀረት ጉዳይ አለ ሲሉ አቶ ማሞ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ፥ " በእኛ እምነት የፖለቲካ ሂደቱን በተመለከተ AGOA ትክክለኛው መሳሪያ ነው ብለን አናምንም፤ ምክንያቱም AGOA ከተነሳ የሚጎዱት በዋነኛነት በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚሰሩ ሰራተኞች ናቸው በተለይ ሴቶች ናቸው የሚጎዱት " ብለዋል።

አክለውም ፥ "አንድ ሀገር የፖለቲካ መሳሪያውን ለማሳካት ሲባል ከጦርነቱ /ከግጭቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ሰዎች መጉዳት ትክክለኛ ነው ብለን አናምንም፡፡ ይህ እንዳይሆንም የበኩላችንን ጥረት እያደረግን ነው" ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ “አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Home Grown Economic Reform) ምሰሶዎች የሆኑትን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ሥራ ዕድል ፈጠራ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። 

በአዲስ አበባ ለ2 ቀናት በተካሄደው 18ኛው የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን መርሃግብር ላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከፍተኛ አመራሮች በዋና ሥራ አስፈጻሚው ሚስተር አንዋር ሱሳ መሪነት በመገኘት የኢትዮጵያን አገራዊ የዲጂታል እድገት ለውጥ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸው “ወደገበያ ለመግባት እየተዘጋጀንበት ባለበት በዚህ ወሳኝ ምዕራፍ የኢትዮጵያ መንግስት ላደረገልን አበረታች ድጋፍ ላመሰግን እወዳለሁ። በኢትይጵያ ድንቅ አቅም እንዳለ ተመልክተናል። ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን ማመቻቸት፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የዲጂታል ክህሎት ስልጠናዎችን መስጠት እንዲሁም የኢትዮጵያን የዲጂታል 2025 ዕቅድ ከግብ ለማድረስ የሚያስችል ስነምህዳር መገንባትን እንቀጥላለን” ብለዋል። 

ያንብቡ : https://telegra.ph/Safaricom-Ethiopia-10-28